በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
መግቢያ፦ ስለ አዲስ ኪዳን—የኢየሱስ ክርስቶስ እና የተከታዮቹ ታሪክ


መግቢያ

ስለ አዲስ ኪዳን

የኢየሱስ ክርስቶስ እና የተከታዮቹ ታሪክ

በብራና ላይ እየጻፈ ያለ አንድ የጥንት ነቢይ።

መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን። ብሉይ ኪዳን ከረዥም ጊዜ በፊት በነበሩ ነቢያት የተጽፉትን ጽሁፎች የያዘ ነው። አንዳንዶቹ እነዚህ ነቢያት እግዚአብሔር አዳኝን ለመላክ ቃል እንደገባ ጽፈዋል። እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እና ዳግም ከእግዚአብሔር ጋር መኖር እንችል ዘንድ ከሃጢያት እና ከሞት የሚያድነን ይሆናል።

ኢሳይያስ 53፥3–5ያእቆብ 7፥11ሙሴ 4

ማርያም ህፃኑን ኢየሱስ ታቅፋ።

አዲስ ኪዳን ይህ ቃል ኪዳን እንዴት እንደተፈጸመ ይናገራል። ስለ እግዚአብሔር ልጅ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ይናገራል።

ሉቃስ 2፥4–7

ኢየሱስ የተሰበሰቡ ሰዎችን ሲያስተምር።

አዲስ ኪዳን በተጨማሪ ስለ ኢየሱስ ህይወት ይናገራል። በአይሁድ መካከል ኖረ እና አንድ ቀን ወደ ሰማይ አባት እንዴት መመለስ እንደምንችል አስተማረን።

ማቴዎስ 5፥1–2

ኢየሱስ ክርስቶስ አንድን ልጅ ሲንከባከብ።

ኢየሱስ ህዝቡን ባረከ እና አገለገለ። ለእነርሱም የታመሙትን እንደመፈወስ እና የሞቱትን ዳግም ወደ ህይወት የመመለስ የመሳሰሉትን አያሌ ተዓምራትን አደረገላቸው።

ማቴዎስ 4፥23

ኢየሱስ ከሐዋሪያት አንዱን ሲሾም።

ኢየሱስ አስራ ሁለት ተከታዮቹን ሐዋሪያት እንዲሆኑ መረጣቸው። ቤተክርስቲያኑንም እንዲመሩ ስልጣን ሰጣቸው።

ሉቃስ 9፥1–2

ኢየሱስ ከመቃብር ሲወጣ።

ስለሚወደን፣ ኢየሱስ ህመማችንን፣ ሃዘናችንን፣ እና ሃጢያታችንን በራሱ ላይ ወስዷል። እርሱ ስለእኛም ሞተ። ከዚያም፣ ከሶስት ቀናት በኋላ ሞትን አሸንፎ ተነስቷል! ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ነው በዚህም ምክንያት፣ ለሃጢያቶቻችን ንስሀ መግባት እና ከሞትን በኋላ ዳግም መኖር እንችላለን።

አልማ 7፥11–13

ሁለት የዚህ ዘመን ልጆች አዲስ ኪዳንን እያነበቡ።

ኢየሱስን ያውቁት እና ይወዱት የነበሩ ሰዎች ስለእነዚህ ነገሮች በሙሉ ጽፈዋል። የእርሱ ሐዋሪያት የቤተክርስቲያኗ አባላት በኢየሱስ ክርስቶስ እምነታቸውን እንዲያዳብሩ ለመርዳት ደብዳቤዎችን ጽፈዋል። እነርሱ የጻፏቸው ነገሮች ለብዙ፣ ብዙ ዓመታት ተጠብቀው ቆይተዋል። አሁን የአዲስ ኪዳንን ማንበብ እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደምትከተሉ መማር ትችላላችሁ።

ሉቃስ 1፥1–4