ማቴዎስ 5–7
ኢየሱስ የተራራ ስብከቱን አስተማረ
ይበልጥ እንደሰማይ አባታችን እንድንሆን እየረዳን
ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ በገሊላ ባህር አጠገብ ወዳለ አንድ ተራራ ሄዱ። በዚያም ኢየሱስ እንዴት ደስተኞች እና ይበልጥ እንደሰማይ አባታችን መሆን እንደምንችል አስተማረ።
ማቴዎስ 5፥1–2
ኢየሱስ ሰዎች ትሁት፣ ልበ ንጹሃን፣ እና ትክክል የሆነውን ለማድረግ የሚጥሩ ሲሆኑ የተባረኩ እና ደስተኞች እንደሚሆኑ አስተማረ። ለሌሎች ምህረትን የሚሰጡ ምህረትን ሊያገኙ ይችላሉ። የሚያስተራርቁ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉ።
ማቴዎስ 5፥3–9
ኢየሱስ የእርሱ ደቀመዛሙርት ለዓለም ብርሃን ናቸው አለ—ሁሉም ሰው ሊያያት እንደሚችል በተራራ ላይ እንዳለች ከተማ። ብርሃናችንን ልንሰውር አይገባንም።
ማቴዎስ 5፥14
ኢየሱስን ስንከተል እኛ በክፍሉ ውስጥ ለሁሉም ሰው ብርሃንን እንደሚሰጥ ሻማ ነን። መልካም ስራችን ሰዎችን በሰማይ አባት እንዲያምኑ ሊረዳ ይችላል።
ማቴዎስ 5፥15–16
ኢየሱስ ሁሉንም ሰው፣ እንዲሁም የማይወዱንን ሰዎች ቢሆን እንኳን፣ መውደድ አለብን አለ። ለእነርሱ መጸለይ አለብን። ኢየሱስ ልክ እንደ ሰማይ አባታችን ለመሆን መጣር እንዳለብን አስተማረ። ሰዎችን ስንረዳ፣ ያደረግነውን ለሁሉም ሰው መናገር እንደሌለብን አስተማረ። እግዚአብሔር ያደረግነውን መልካም ስራ ይመለከታል፣ እናም ይባርከናል።
ማቴዎስ 5፥38–48፤ ማቴዎስ 6፥1–4
ስንጸልይ፣ ሌሎች ሰዎች ስለእኛ ስለሚያስቡት ነገር መጨነቅ አይገባንም። የምንናገረውን ከልባችን ካልሆነ፣ ቃላቶቹን በየጊዜው መድገም ተገቢ አይደለም። ከልባችን ልንናገር ይገባል። የሰማይ አባት ጸሎታችንን ይሰማል እንዲሁም የሚያስፈልገንን ያውቃል። ሌላ ማንም ሊሰማን ባይችል እንኳን እርሱ ይሰማናል።
ማቴዎስ 6፥5–8
ከሌሎች ሰዎች የተሻልን ነው ብለን ራሳችንን መቁጠር እንደሌለብን ኢየሱስ አስተማረ። ሁላችንም ተግዳሮቶች እንዳሉብን ልናስታውስ ይገባል። በሌሎች ከመፍረድ ይልቅ፣ እንዴት የተሻለ ማድረግ እንዳለብን ማሰብ ይገባል። እኛ ሊደረግልን እንደምንፈልገው ለሌሎች እንዲሁ ልናደርግ ይገባል።
ማቴዎስ 7፥1–5፣ 12
ኢየሱስ ቤቱን በአሸዋ ላይ ስለሰራው ሰነፍ ሰው እና ቤቱን በአለት ላይ ስለሰራው ብልህ ሰው ታሪክን ተናገረ። ሃይለኛ ዝናብ በመጣ ጊዜ በአሸዋ ላይ የነበረው ቤት ወደቀ፣ እና በአለት ላይ የነበረው ቤት መቀም ቻለ። ኢየሱስም የእርሱን ትምህርቶች ብንሰማ እና ብንከተላቸው እንደብልሁ ሰው እንደሆንን ተናገረ።
ማቴዎስ 7፥24–28