በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ የመቶ አለቃውን አገልጋይ ፈወሰ—የሮሜው መሪ ታላቅ እምነት አሳየ


ሉቃስ 7፥1–10

ኢየሱስ የመቶ አለቃውን አገልጋይ ፈወሰ

የሮሜው መሪ ታላቅ እምነት አሳየ

የመቶ አለቃው ከወታደሮቹ ጋር።

የመቶ አለቃው ኢየሱስ በአብዛኛው ሲያስተምር በነበረበት በቅፍርናሆም ይኖር ነበር። እርሱም የታላቅ ወታደሮች ስብስብ መሪ ነበር።

ሉቃስ 7፥1–2

የመቶ አለቃው አገልጋይ በጣም ታምሞ ነበር።

ይህ የመቶ አለቃ ለእርሱ እጅግ ልዩ የነበረ አገልጋይ ነበረው። አገልጋዩም ታመመ እናም ሊሞት ደርሶ ነበር።

ሉቃስ 7፥2

የመቶ አለቃውም አንዳንድ የአይሁድ መሪዎችን ኢየሱስን እንዲያገኙለት ጠየቀ።

ምንም እንኳ የመቶ አለቃው አይሁዳዊ ባይሆንም፣ ስለ ኢየሱስ ሰምቷል። እርሱም ኢየሱስ ታላላቅ ተዓምራትን ያደርግ ዘንድ ሃይል እንዳለው አምኗል። የአይሁድ አንዳንድ መሪዎችን ኢየሱስ እንዲመጣ እና አገልጋዩን እንዲፈውስለት እንዲጠይቁት ላካቸው።

ሉቃስ 7፥3–4

አንዳንድ ሰዎችም ኢየሱስ ወደ መቶ አለቃው ቤት እንዳይሄድ ነገሩት።

መሪዎቹም ስለመቶ አለቃው እና ስለአገልጋዮ ለኢየሱስ ነገሩት። እነርሱም ይህ የመቶ አለቃ ለአይሁድ ደግ እንደነበር ተናገሩ። ኢየሱስ ወደ መቶ አለቃው ቤት መሄድ ጀመረ። ነገር ግን እዚያ ከመድረሱ በፊት፣ የመቶ አለቃው አንዳንድ ጓደኞቹ ኢየሱስን አቆሙት። ወደ እርሱ ቤት እንዳይመጣ ነገሩት።

ሉቃስ 7፥4–6

ሰዎችም ለኢየሱስ የመቶ አለቃው ለዚህ ብቁ ሆኖ እንደማይሰማው ነገሩት።

ጓደኞቹም የመቶ አለቃው ኢየሱስን በቤቱ ለመቀበል ብቁነት የማይሰማው መሆኑን ነገሩት ። እርሱም ኢየሱስ በርቀት ሆኖ አገልጋዩን መፈወስ እንደሚችል አምኗል።

ሉቃስ 7፥6–8

ኢየሱስ የመቶ አለቃው ታላቅ እምነት አለው አለ።

ኢየሱስ በመቶ አለቃው እምነት ተገርሞ ነበር። እርሱም እንደዚህ ያለ ታላቅ እምነት እንዳላየ ተናገረ።

ሉቃስ 7፥9

የመቶ አለቃውም አገልጋይ ተፈወሰ።

የመቶ አለቃው ጓደኞች ወደ ቤቱ ሲመለሱ፣ አገልጋዩ ሙሉ ለሙሉ ተፈውሷል። ልክ የመቶ አለቃው ኢየሱስ ሊያደርገው እንደሚችል እንዳመነው፣ እርሱም ፈወሰው።

ሉቃስ 7፥10