በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ አንዲትን ሴት በሰንበት ፈወሰ—በተቀደሰ ቀኑ መልካምን ማድረግ


ማቴዎስ 12፥1–12ሉቃስ 13፥10–17

ኢየሱስ አንዲትን ሴት በሰንበት ፈወሰ

በተቀደሰ ቀኑ መልካምን ማድረግ

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ በእርሻ መካከል አለፉ።

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ በሰንበት ቀን በስንዴ እርሻ መካከል አለፉ። እነርሱም ተርበው ነበር፣ በመሆኑም የተወሰኑ የስንዴ ዘለላዎችን ቀጥፈው በሉ። ፈሪሳውያን የተባሉ አንዳንድ የአይሁድ መሪዎች አዩዋቸው። ፈሪሳውያን ስለሰንበት ቀን አያሌ ህጎችን አውጥተው ነበር። ስንዴን መቀጠፍ የህጋቸው ተቃራኒ ነበር።

ማቴዎስ 12፥1–l2

ፈሪሳውያንም ደቀ መዛሙርቱ ለምን ሰንበትን እንደማያከብሩ ኢየሱስን ጠየቁት።

ፈሪሳውያንም ኢየሱስን ለምን የእርሱ ደቀመዛሙርት ሰንበትን እንደማያከብሩ ጠየቁት። ኢየሱስም ምንም መጥፎ ነገር እንዳላደረጉ መለሰላቸው። እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን የሰጠን ህይወታችንን ሊባርክ እንጂ ሊያከብደው አይደለም።

ማቴዎስ 12፥2–8ማርቆስ 2፥27

ኢየሱስ በምኩራብ እያስተማረ እያለ አንዲትን ሴት አስተዋለ።

በኋላም፣ ኢየሱስ በሰንበት ቀን በምኩራብ እያስተማረ ነበር። ኢየሱስ በዚያም አንዲትን ሴት አስተዋለ። ቀጥ ብላ መቆም አልቻለችም ነበር። ለ18 ዓመታት ይህ ችግር ነበረባት።

ሉቃስ 13፥10–12

ኢየሱስ ሴቲቱን ባረከ።

ኢየሱስ ሴቲቱ ወደ እርሱ እንድትመጣ ጠየቃት። ይባርካትም ዘንድ እጆቹን ጫነባት።

ሉቃስ 13፥12–13

ሴቲቱም ተፈወሰች።

ወዲያውኑም፣ ሴቲቱ ቀጥ ብላ ቆመች። ኢየሱስ በሰንበት ስለፈወሰ የምኩራቡ መሪ ተናደደ።።

ሉቃስ 13፥13–14

ኢየሱስ በሰንበት ለምን እንደሚፈውስ ግልጽ አደረገ።

ኢየሱስ ይህችን ሴት መርዳት ትክክለኛ ነገር እንደሆነ ተናገረ። በሰንበት መልካምን ማድረግ ትክክለኛ ነገር ነው። መሪውም እፍረት ተሰማው፣ እናም ሴቲቱም በመፈወሷ በምኩራቡ የነበሩ ሰዎች ተደሰቱ።

ሉቃስ 13፥15–17፤ በተጨማሪ ሉቃስ 6፥9 ተመልከቱ።