በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ተነስቷል—ኢየሱስ ሞትን ለሁሉም አሸነፈ


ሉቃስ 24፥1–12፣ 36–49ዮሀንስ 20

ተነስቷል

ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ለሁሉም አሸነፈ

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከመቃብሩ ሲወጡ።

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሰውነቱን በመቃብር ውስጥ አስቀመጡ። ሰውነቱን ለመንከባከብ ተጨማሪ ነገሮች ለማድረግ ፈለጉ፣ ነገር ግን ሰንበት ደርሶ ነበር። ከሰበት በኋላ ለመጨረሽ ለመመለስ አቅደው ነበር።

ሉቃስ 23፥52–56

መግደላዊት ማርያም እና ሌሎች ወደ መቃብሩ ተመለሱ።

ከኢየሱስ ሞት በሶስተኛው ቀን ጠዋት ላይ፣ መግደላዊት ማርያም እና ሌሎች ወደ መቃብሩ ተመለሱ።

ሉቃስ 24፥1ዮሀንስ 20፥1

ሰውነቱ በመቃብሩ ውስጥ አልነበረም።

በዚያ ሲደርሱም፣ መቃብሩን ሸፍኖ የነበረው ድንጋይ ተፈንቅሎ እንደነበር ተመለከቱ። በመቃብሩ ውስጥ ገቡ፣ እና የኢየሱስ ሰውነት በዚያ አልነበረም።

ሉቃስ 24፥2–3ዮሀንስ 20፥1

ማርያም ለጴጥሮስ እና ዮሀንስ አንድ ሰው የኢየሱስን ሰውነት ወስደዋል ብላ ነገረቻቸው።

ማርያም ለጴጥሮስ እና ዮሀንስ አንድ ሰው የኢየሱስን ሰውነት ወስደዋል ብላ ለመንገር ሮጣ ሄደች። ጴጥሮስ እና ዮሀንስ ወደ መቃብሩ ሮጠው ሲሄዱ።

ዮሀንስ 20፥2–4

ጴጥሮስ እና ዮሀንስ የኢየሱስ ሰውነት በመቃብሩ ውስጥ እንደሌለ አዩ።

ወደ መቃብሩ ሲደርሱ፣ ጴጥሮስ እና ዮሀንስ ወደውስጥ ገቡ። የኢየሱስ ሰውነት እንደሌለ ተመልከቱ። ሰውነቱ ተሸፍኖበት የነበረው ልብስ ኝ በዚያ ነበረ።

ዮሀንስ 20፥5–7

ማርያም ሁለት መላእክት በመቃብሩ ውስጥ አየች።

ጴጥሮስ እና ዮሀንስ ወደ ቤት ተመለሱ፣ ግን ማርያም እያለቀሰች በመቃብሩ አጠገብ ቆየች። በመቃብሩ ውስጥ ተመለከተች እና ሁለት መላእክት አየች። እነርሱም ለምን እንደምታለቅስ ጠየቋት። እርሷም አንድ ሰው የኢየሱስን ሰውነት ወስደዋል፣ እናም የት እንዳለ አለውቅም አለች።

ዮሐንስ 20፥11–13

ኢየሱስ ማርያምን ለምን እንደምታለቅስ ጠየቃት።

ከዚያም ኢየሱስ መጣ፣ ግን ማርያም እርሱ እንደሆነ አላወቀችም ነበር። ኢየሱስም እንዲህ ብሎ ጠየቃት፣ “አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ?” ማርያም እርሱ የአትክልት ጠባቂ መስሏት ነበር። የኢየሱስ ሰውነት የት እንዳለ እንደሚያውቅ ጠየቀችው።

ዮሀንስ 20፥14–15

ማርያም ዞር አለች እና ኢየሱስን አየችው።

ኢየሱስ “ማርያም” አለ። እርሷም ዞር አለች። አሁን እርሱ ኢየሱስ እንደሆነ አወቀች! እርሷም “መምህር ሆይ” አለችው። ኢየሱስ ለሌሎች ደቀ መዛሙርት ወደ ሰማይ አባቱ መፌድ እንደሚያስፈልገው እንድትነግራቸው ጠየቃት። ማርያም ሌሎች ደቀ መዛሙርትን አገኘች እናም ኢየሱስን እንዳየትና እርሱም ዳግም ህያው እንደሆነ ነገረቻቸው።

ዮሀንስ 20፥16–18

ኢየሱስ ከHእዋሪያቱ ጋር ለመነጋገር መጣ።

በዚያ ምሽት፣ ብዙዎቹ ሐዋሪያት አብረው ተሰብስበው ነበር። የአይሁዶች መሪዎች እነርሱን ለማግኘት እንደሚፈልጉ በመፍራት በሮቹን ዘጉ። በድንገት፣ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆሞ አዩት። በመጀመሪያ ፈርተው ነበር። እርሱ መንፈስ መስሏቸው ነበር። ኢየሱስም፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።

ሉቃስ 24፥33–38ዮሀንስ 20፥19

ከሐዋሪያት አንዱ የኢየሱስን እጅ ነካ።

ኢየሱስ ሐዋሪያት እጆቹን እና እግሮቹን እንዲነኩ ጋበዛቸው። እርሱ መንፈስ ቻ ሳይሆን፣ ሰውነት እንዳለው እንዲያውቆ ፈለገ። ከእነርሱም ጋር አሳ እና የማር ወለላ በላ። ሐዋሪያት እርሱን በማየታቸው በጣም ተደሰቱ!

ሉቃስ 24:39–44ዮሀንስ 20፥20

ኢየሱስ ስለሞቱ እና ትንሳኤው አስተማረ።

ከዚያም ኢየሱስ ሐዋሪያቱ ስለሞቱ እና ትንሳኤው ያስተማሩትን ቅዱሳት መጻህፍት እንዲገነዘቡ ረዳቸው። በእርሱ ምክንያት ንስሀ መግባት እና ይቅርታ ማግኘት እንደሚችሉ ለሁሉም እንዲያስተምሩ ፈልጓቸው ነበር። ሐዋሪያት የእርሱ ምስክሮች ይሆናሉ።

ሉቃስ 24፥44–48

ቶማስ ከሁለት ሌሎች ሐዋሪያት ጋር ሲነጋገር።

ሐዋርያው ቶማስ ኢየሱስ ሲመጣ እዚያ አለነበረም። በእጆቹ ላይ የምስማሩን ምልክት ካላየሁ፣ ኢየሱስ በህይወት መኖሩን አላምንም አለ።

ዮሀንስ 20፥24–25

ኢየሱስ እንደገና መጣ።

ከስምንት ቀናት በኋላ፣ ደቀመዛሙርት እንደገና ተሰብስበው ነበር። ኢየሱስ እንደገና መጣ። በዚህ ጊዜ ቶማስ እዚያ ነበር።

ዮሀንስ 20፥26

ቶማስ በኢየሱስ ፊት ተንበርክኮ።

ኢየሱስ ቶማስ በእጆቹ እና በጎኑ ያሉትን ቁስሎች እንዲነካ ጋበዘው። ቶማስን “ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን” አለው። ቶማስም “ጌታዬ አምላኬም” ብሎ መለሰለት። ቶማስ ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ አሁን አመነ። ኢየሱስም እርሱን ባያዩም የሚያምኑ ሰዎች የተባረኩ ናቸው አለ።

ዮሀንስ 20፥27–29