ማቴዎስ 14፥13–21፤ ዮሐንስ 6
ኢየሱስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን መገበ
እርሱ የህይወት እንጀራ ነው
መጥምቁ ዮሐንስ እንደተገደለ ኢየሱስ አወቀ። ለብቻው ጊዜ ይኖረው ዘንድ ከከተማ ራቅ ወዳለ ስፍራ ሄደ።
ማቴዎስ 14፥13
ህዝቡም ኢየሱስ ወዴት እንደሄደ ሲያውቁ ይከተሉት ጀመር። ኢየሱስም አያቸው እና ስለእነርሱም ፍቅር አደረበት። ሲባርካቸው እና ሲፈውሳቸው ሙሉ ቀን ፈጀበት።
ማቴዎስ 14፥13–14
ቀኑም በመሸ ጊዜ፣ ህዝቡ ተራቡ። ደቀመዛሙርቱም ምግብ ያገኙ ዘንድ ህዝቡን ወደከተማ ኢየሱስ መላክ ያለበት መሰላቸው። ነገር ግን ኢየሱስ ባሉበት እንዲሆኑ ፈልጎ ነበር። ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ለህዝቡ የሚበላ ነገር እንዲሰጧቸው ጠየቃቸው።
ማቴዎስ 14፥15–16
ሐዋርያው እንድርያስ ለህዝብ የሚሆን አምስት እንጀራ እና ሁለት ትንሽ ዓሣ ያለው ልጅ አገኘ። ነገር ግን፣ ሴቶችን እና ልጆችን ጨምሮ፣ ለመብላት የሚያስፈልጋቸው 5000 ያህል ወንዶች ነበሩ። በዚህች አነስተኛ ምግብ እንዴት የዚህን ያህል ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ሊመግቡ ይችላሉ?
ማቴዎስ 14፥17፣ 21፤ ዮሐንስ 6፥8–10
ኢየሱስ ምግቡን ያመጡለት ዘንድ ሐዋርያቱን ጠየቀ። ህዝቡንም እንዲቀመጡ ነገራቸው። ከዚያም ኢየሱስ የሰማይ አባትን ለእንጀራው እና ለዓሳው ለማመስገን እና ለመባረክ ጸሎትን አቀረበ። ከዚያም እንጀራውን እና ዓሳውን ቆራረሰ።
ማቴዎስ 14፥18–19፤ ዮሐንስ 6፥10–11
ኢየሱስም እንጀራውን እና ዓሳውን ለህዝቡ እንዲሰጡ ጠየቀ። ሁሉም በሉ እናም ጠገቡ። ከበሉም በኋላ፣ የተረፈው ምግብ 12 መሶብ ሙሉ ነበር።
ማቴዎስ 14፥20፤ ዮሐንስ 6፥11–13
በሚቀጥለው ቀን፣ ህዝቡም ተመልሰው መጡና ኢየሱስን እንደገና አገኙ። ነገር ግን ኢየሱስ ብዙዎቹ የሚከተሉት ምግብ ስለሰጣቸው ብቻ እንደሆነ አወቀ። ኢየሱስ ምግብ ለጥቂት ጊዜ ብቻ የሚቆይ መሆኑን አስታወሳቸው። እርሱ የሚሰጣቸው የተሻለ ነገር አለው።
ዮሐንስ 6፥14፣ 24–27
ኢየሱስም፣ “እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ” አለ። እንጀራ በምድር ህይወትን ይሰጠናል። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ አባት ጋር የዘለዓለምን ህይወት ይሰጠናል።
ዮሐንስ 6፥35–58
አያሌ ሰዎች ኢየሱስ ሊያስተምር እየሞከረ ያለውን ነገር አልወደዱም። ትተውት ሄዱ እናም ኢየሱስን ላለመከተል ወሰኑ።
ዮሀንስ 6፥60፣ 66
ከዚያም ኢየሱስ ለሐዋርያቱ፣ “እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?” አላቸው። ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ ወደ ማንስ እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ህይወት ቃል አለህ” በማለት መለሰለት። ሐዋርያቱ ትተዉት አልሄዱም። እነርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እና የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አውቀዋል።
ዮሐንስ 6፥67–69