ማቴዎስ 16-17
ኢየሱስ ለሃዋርያቱ የክህነትን ቁልፍ ሰጣቸው
’’በዚህ ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እመሰርታለሁ’’
አንድ ቀን፣ ሰዎች ማን እንደሚሉት ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው። ደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ ሰዎች ዮሐንስ መጥምቁ ነው ይላሉ በማለት መለሱለት። ሌሎች ዳግም ተመልሶ የመጣ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
ማቴዎስ 16፥13-14
ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ማን እንደሚሉት ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፣ ‘’አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለው።’’
ማቴዎስ 16፥15-16
ኢየሱስም ጴጥሮስ ይህን ሲናገር በመስማቱ ተደሰተ። ለጴጥሮስም ኢየሱስ ማን እንደሆነ ከሌሎች ሰዎች እንዳልተማረ ነገረው። የሰማይ አባት ነው የገለጠለት።
ማቴዎስ 16፥17
ኢየሱስም ጴጥሮስን፣ ’’በዚህ ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እመሰርታለሁ’’ አለው። ከዚያም እርሱ እና ሌሎች ሐዋርያት በምድር ላይ ቤተክርስቲያኑን መምራት ይችሉ ዘንድ ለጴጥሮስ የክህነት ስልጣን ቁልፎችን፣ ወይም ከእግዚአብሄር ስልጣንን እንደሚሰጠው ቃል ገባለት።
ማቴዎስ 16፥18–19
ከጥቂት ቀናት በኋላም፣ ኢየሱስ ሊጸልይ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብን፣ እና ዮሐንስን ወደ ተራራ ይዟቸው ወጣ።
ማቴዎስ 17፥1፤ ሉቃስ 9፥28
ኢየሱስ ሲፀልይ፣ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ። ልብሱ እንኳን ያበራ ነበር።
ማቴዎስ 17፥2፤ ሉቃስ 9፥29
ሁለት የብሉይ ኪዳን ነቢያት፣ ሙሴ እና ኤሊያስ፣ ተገለጡ። በቅርቡ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው፣ ስለ ሞቱ እና ስለትንሳኤው ከኢየሱስ ጋር ተነጋገሩ። ጴጥሮስም ኢየሱስን፣ ‘’ጌታ ሆይ፣ ለእኛ በዚህ መሆን ይሻለናል’’ አለው።
ማቴዎስ 17፥3-4፤ ሉቃስ 9፥30–33 (በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ 31ሀ) ተመልከቱ።)
ጴጥሮስ እየተናገረ እያለ፣ ብሩህ ደመና ሸፈናቸው። የእግዚአብሔርንም ድምጽ፣ ‘’በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት’’ ሲል ሰሙ። ጴጥሮስ፣ ያእቆብ እና ዮሐንስ ፈሩ እናም በመሬት ላይ ወደቁ።
ማቴዎስ 17፥5-6
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን በመንካት እንዲህ አላቸው፣ ‘’ተነሱ፣ አትፍሩ።’’ ወደ ላይ ተመለከቱ። ሙሴ እና ኤሊያስም ተለዩ። በዚህም ተራራ ጴጥሮስ፣ ያእቆብ፣ እና ዮሐንስ ኢየሱስ ቃል የገባላቸውን የክህነት ቁልፎችን ተቀበሉ።
ማቴዎስ 17፥7–9; እንዲሁም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 27፥12–13ተመልከቱ።