ዮሐንስ 8፥1-11
ሰዎች ሃጢያት የሰራችን ሴት ሊቀጧት ፈለጉ
‘’ሂጂ፣ ደግመሽ ሃጢያት አትስሪ’’
አንድ ቀን በማለዳ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ወዳለች ቤተመቅደስ ሄደ። እርሱም ሲያስተምር ለመስማት አያሌ ሰዎች በዙሪያው ተሰበሰቡ።
ዮሐንስ 8፥1-2
ኢየሱስም ሲያስተምር፣ አንዳንድ የአይሁድ መሪዎች አንዲትን ሴት ወደ ኢየሱስ አመጡ። ከእግዚአብሔር ትእዛዛት አንዱን ስትተላለፍ ተይዛ ነበር። በህጉ መሰረት፣ ሴቲቱን ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይገሏት ዘንድ ይገባ ነበር።
ዮሐንስ 8፥3-5
ሰዎቹም ኢየሱስን ምን መደረግ እንዳለባት ጠየቁት። እነርሱ ኢየሱስን ለመፈተን እየሞከሩ ነበር። ሴቲቱ እንድትጎዳ እንደማይፈቅድ አውቀዋል። ነገር ግን ኢየሱስ ሴቲቱ መቀጣት የለባትም ብሎ ቢናገር፣ እርሱ ህግን አያከብርም በማለት ሊናገሩ ይችላሉ።
ዮሐንስ 8፥6
ነገር ግን ኢየሱስ አልመለሰላቸውም። ወደ መሬት አጎነበሰ እናም አቧራ ላይ መጻፍ ጀመረ። ደግመው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሰዎቹ ጠየቁት።
ዮሐንስ 8፥6-7
በመጨረሻም ኢየሱስ ቀና ብሎ ወደ ሰዎቹ ይመለከት ጀመር። እርሱም ከእናንተ ሃጢያት የሌለበት ማንም ቢኖር በእርስዋ ላይ ድንጋይ ለመወርወር የመጀመሪያ ይሁን አለ።
ዮሐንስ 8፥7
ኢየሱስ ዳግም ወደ መሬት አጎነበሰ እናም በመሬት ላይ መጻፉን ቀጠለ። ሁሉም ሰዎች ሃጢያት እንዳለባቸው አውቀዋል። አንድ በአንድ ትተው ሄዱ።
ዮሐንስ 8፥8-9
ኢየሱስ ዘወር ብሎ ሲመለከት ሴቲቱን ብቻዋን ቆማ አያት። እርሱም ሊወግሯት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ወዴት እንደሄዱ ጠየቃት። ሁሉም እንደሄዱ ነገረችው። ኢየሱስም ለሴቲቱ፣ ’’ሂጂ፣ ደግመሽ ሃጢያት አትስሪ’’ አላት። ከዚያ ጊዜ በኋላ ሴቲቱም በኢየሱስ አመነች።
ዮሐንስ 8፥9–11; የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዮሐንስ 8፥11; በ ዮሀንስ 8፥11፣ የግርጌ ማስታወሻ ሐ)።