በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
አዳኝ ተወለደ—የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተፈጸመ


ሉቃስ 2ማቴዎስ 2፥1–15

አዳኝ ተወለደ

የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተፈጸመ

ዮሴፍ እና ማርያም ወደ ቤተልሔም ሲጓዙ።

ዮሴፍ እና ማርያም በናዝሬት ይኖር ነበር። ማርያም በቅርቡ ልጅ ትወልድ ነበር። እያንዳንዱ ሰው ወደየትውልድ ሃገሩ መሄድ እና ግብር መክፈል ነበረበት። ይህም ዮሴፍ እና ማርያም የዮሴፍ የትውልድ ሃገር ወደሆነው ቤተልሄም መሄድ ነበረባቸው ማለት ነው። እዚያም ለመድረስ ረዥም ርቀት መጓዝ ነበረባቸው።

ሉቃስ 2፥1–5

ማርያም እና ዮሴፍ በቤተልሄም።

ጉዞው ለማርያም ቀላል አልነበረም። ብዙ ሰዎች ወደ ቤተልሔም መምጣት ስለነበረባቸው፣ ማርያም እና ዮሴፍ ልጇን የምትወልድበት ስፍራ ሊያገኙ አልቻሉም ነበር።

ሉቃስ 2፥6–7

ማርያም እና ዮሴፍ አዲስ የተወለደውን ህጻን ኢየሱስ አቅፈው።

በአብዛኛው እንሰሳት የሚቀመጡበትን ስፍራ አገኙ። በዚህ ትህትና በተሞላበት ስፍራ፣ ኢየሱስ ተወለደ። ማርያም እና ዮሴፍ ህጻኑን ኢየሱስን ይወዱት እና ይንከባከቡት ነበር። ይሞቀው እና ይመቸው ዘንድ ለመርዳት በጨርቅ ጠቀለሉት። በልምድ እንስሳትን ለመመገብ በሚውል ግርግም ውስጥ አስተኙት።

ሉቃስ 2፥6–7

አንድ መልአክ ለእረኞች ስብስብ ሲገለጥ።

በአቅራቢያውም፣ በሌሊት እረኖች ከብቶቻቸውን እየጠበቁ ነበር። በድንገት፣ በዙሪያቸው ደማቅ ብርሃን አንጸባረቀ፣ እና አንድ መልአክም ተገለጠ። እረኞቹም ፈርተው ነበር።

ኢየሱስ እንደተወለደ መልአኩ ለእረኞቹ ሲነግራቸው።

መልአኩ ድንቅ ዜና የነበረው በመሆኑ ምክንያት እንዳይፈሩ ነገራቸው። አዳኙ በቤተልሄም ተወልዷል፣ እናም በግርግም ተኝቶ ሊያገኙት ይችላሉ። ብዛት ያላቸው መላእክት፣ “ክብር ለእግዚአብሐር በዓርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” በማለት እየዘመሩ መጡ።

ሉቃስ 2፥10–15

እረኞቹ ህፃኑን ኢየሱስን ሰላም ሲሉ።

ልክ መልአኩ እንዳለው፣ እረኞቹ ወደ ቤተልሄም ፈጥነው ሄዱ እና ህጻኑን ኢየሱስን አገኙት። ስላዩት እና ስለሰሙት ነገር ለህዝቡ ተናገሩ። ኢየሱስ የተለየ ልጅ እንደነበር አወቁ።

ሉቃስ 2፥16–17

ስምኦን ህጻኑን ኢየሱስን አቅፎ።

ማርያም እና ዮሴፍ ለእግዚአብሔር ሊያቀርቡት ህጻኑን ኢየሱስን ወደ ቤተመቅደስ ወሰዱት። በዚያም ስምዖን የተባለን ሰው አገኙ። መንፈስ ቅዱስ ስምዖንን ከመሞቱ በፊት አዳኙን እንደሚያገኘው ነግሮት ነበር። ህጽኑን አቀፈው እናም ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ልጆች ሁሉ እንደሚያድናቸው ተናገረ። ዮሴፍ እና ማርያም እርሱ በተናገረው ነገር ተገርመዋል።

ሉቃስ 2፧22–35

ሃና ህጻኑን ኢየሱስን ስታገኝ።

በቤተመቅደስ ሃና የተባለች ሌላ ሴት ነበረች። ባሏም ከአያሌ ዓመታት በፊት ሞቶ ነበር። ሃና በቤተመቅደስ ጊዜዋን በሙሉ እግዜአብሔርን ስታመልክ የነበረች ነበረች። አዳኙን ለማግኘት በመታደሏ እግዚአብሔርን አመሰገነች። አዳኙን የሚጠባበቅ ሰው ባገኘች ጊዜ ሁሉ፣ ስለ ኢየሱስ ትነግራቸው ነበር።

ሉቃስ 2፥36–38

ሰብአ ሰገል አዲስ ኮከብ በሰማይ ሲገለጥ ሲመለከቱ።

ኢየሱስ ሲወለድ፣ በሌላ ምድር ሰብአ ሰገል አዲስን ኮከብ ተመለከቱ። የእግዚአብሔር ልጅ እና የዓለም አዳኝ የሆነ አንድ የተለየ ልጅ የተወለደ መሆኑን አወቁ። ይህንን ልጅ ሊጎበኙት እና ሊሰግዱለት የረዥም ርቀት ጉዞ መጓዝ ጀመሩ። ለእርሱ ያላቸውን ፍቅር ለማሳየት ስጦታን ሊያመጡለት ፈለጉ።

ማቴዎስ 2፥1–7፤ በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ማስታወሻ፣ 2a) ተመልከቱ።

ሰብአ ሰገል በኢየሩሳሌም አዳኙን ሲፈልጉ።

ለረዥም ጊዜ ከተጓዙ በኋላ፣ ሰብአ ሰገል ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። አዳኙ፣ አዲሱ የአይሁድ ንጉስ፣ እንደተወለደ እና ሊሰግዱለት እንደመጡ ተናገሩ። አዲሱን ንጉስ የት ማግኘት እንደሚችሉ ጠየቁ።

ማቴዎስ 2፥1–2

ሄሮድስም ለራሱ ሰዎች አዲሱን ንጉስ እንዲፈልጉት ነገራቸው።

ሰብአ ሰገል አዲሱን ንጉስ እየፈለጉ እንዳለ ሄሮድስ የተባለ ንጉስ ሰማ። እርሱም ተጨነቀ። የእርሱ ካህናት እና ጸሃፍት በቤተልሄም አዲስ ንጉስ እንደሚወለድ ቅዱሳት መጻህፍት እንደተናገሩ ነገሩት። ሄሮድስም ሰብአ ሰገል በቤተልሄም እንዲፈልጉት እና ባገኙትም ጊዜ መጥተው እንዲነግሩት ነገራቸው።

ማቴዎስ 2፥3–8

ሰብአ ሰገል ለህጻኑ ኢየሱስ ሲሰግዱለት።

ሰብአ ሰገል ወደ ቤተልሄም መጡ። ወደ ኢየሱስ የመራቸውን ኮከብ ተከተሉ። እርሱን፣ ማርያምን እና ዮሴፍን ባገኙ ጊዜ፣ ለኢየሱስ ሶስት ልዩ ስጦታዎችን አበረከቱለት እናም ሰገዱለት። እግዚአብሔርም ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ አስጠነቀቃቸው በመሆኑም በሌላ መንገድ ወደ ቤታቸው ሄዱ።

ማቴዎስ 2፥9–12

ቤተሰቡን ወደ ግብጽ ይዞ እንዲሄድ መልአክ ለዮሴፍ ነገረው።

ሰብአ ሰገል ከሄዱ በኋላ ዮሴፍ ህልምን አየ። በህልሙም፣ ሄሮድ እንደተበሳጨ መልአክ ነገረው። በዚያም ደህንነትን ያገኙ ዘንድ ዮሴፍ ማርያምን እና ኢየሱስን ወደ ግብጽ መውሰድ አስፈለገው።

ማቴዎስ 2፥13

ዮሴፍ፣ ማርያም፣ እና ኢየሱስ ወደግብጽ ሲሄዱ።

ዮሴፍ ወዲያው ተነሳ። ሌሊት እያለ ከማርያም እና ከኢየሱስ ጋር ወደ ግብጽ ሄደ።

ማቴዎስ 2፥14

ዮሴፍ፣ ማርያም፣ እና ኢየሱስ በቤታቸው።

ማርያም፣ ዮሴፍ እና ኢየሱስ መልአክ መጥቶ ሄሮድስ እንደሞተ እና ለመመለስ የተመቸ መሆኑን እስኪነግራቸው ድረስ በግብጽ ቆዮ። ከዚያም በናዝሬት ለመኖር ተመለሱ።

ማቴዎስ 2፥15፣ 19–23