ማቴዎስ 20፥1–16
የወይኑ ስፍራ ሰራተኞች ምሳሌ
የተስፋ መልእክት
ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ መንግስተ ሰማያት ምን እንደምትመስል እንዲገባቸው ለመርዳት አንድን ምሳሌ ወይም ታሪክ ነገራቸው። በምሳሌውም ውስጥ አንድ ሰው በወይን አትክልቱ ውስጥ እንዲሰሩለት ሰራተኞችን ፈለገ። በመሆኑም፣ በአንድ ማለዳ፣ በአንድ ዲናር ቀኑን በሙሉ ለመስራት የተስማሙለትን ጥቂት ሰራተኞች አገኘ። መስራትም ጀመሩ።
ማቴዎስ 20፥1–2
ከሶስት ሰዓታትም በኋላ፣ ሰውየው ተጨማሪ ሰራተኞችን ቀጠረ። እርሱም በአትክልት ስፍራው በቀኑ ቀሪውን ጊዜ እንዲሰሩ ጠየቃቸው። የሚገባቸውንም ሊከፍላቸው ቃል ገባላቸው።
ማቴዎስ 20፥3-4
ከዚያም ሶስት ሰዓታት በኋላ ሰውየውም መስራት የሚፈልጉ ሌሎች ሰራተኞችን አገኘ። እነርሱንም በአትክልት ስፍራው እንዲሰሩ ጠየቃቸው።
ማቴዎስ 20፥5
በመጨረሻም፣ ቀኑም በመሸ ጊዜ፣ ሰውየውም ምንም ስራ የማይሰሩ ሰዎችን አየ። እነርሱም ቀኑን በሙሉ ምንም የሚሰሩት ስራ እንዳልተሰጣቸው ነገሩት። ሰውየውም በቀኑ የመጨረሻ ሰዓት ላይ በአትክልት ስፍራው ውስጥ መስራት ይችሉ እንደነበር ነገራቸው።
ማቴዎስ 20፥6-7
በቀኑ መጨረሻ፣ ሰውየው ለሰራተኞቹ ከፈላቸው። ለአንድ ሰዓት ለሰሩት ሰዎች አንድ ዲናር ሰጣቸው። ለቀሩትም ሰራተኞች እንዲሁ እንድ ዲናር ሰጣቸው። ቀኑን ሙሉ ሲሰሩ የነበሩት ሰራተኞች ተቆጡ። እነርሱ ከሌሎቹ ሰዎች በላይ ሊከፈላቸው እንደሚገባ ያስቡ ነበር።
ማቴዎስ 20፥8-12
በአንድ ዲናር ቀኑን በሙሉ ለመስራት የተስማሙ መሆኑን ለሰራተኞቹ አስታወሳቸው። እርሱም በአትክልት ስፍራው ለሰሩት ሌሎች ሰራተኞች ደግ ለመሆን በመምረጡ ሊቆጡ እንደማይገባ ተናገረ።
ማቴዎስ 20፥13–16