ሉቃስ 15
የጠፋው በግ፣ የጠፋው ገንዘብ፣ እና የጠፋው ልጅ
ስለ እግዚአብሄር ፍቅር ሶስት ምሳሌዎች
አንዳንድ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን እነርሱ ሃጢያተኛ ናቸው ብለው ከሚሏቸው ሰዎች ጋር ኢየሱስን ሲነጋገር እና ሲበላ አዩት። መሪዎቹም ኢየሱስ ከሃጢያተኞቹ ጋር መብላቱ ትክክል እንዳልነበር አስበዋል። ኢየሱስም እያንዳንዱን ሰው ንሰሃ እናዲገባ እና ይህንንም ሲያደርጉ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነ ለመርዳት መሪዎቹም እንዲገባቸው ለማስረዳት ሶስት ታሪኮችን ወይም ምሳሊዎችን ነገራቸው።
ሉቃስ 15፥1-3
የመጀመሪያው ምሳሌ 100 በጎች ስለጠፉበት ሰው ነው። ከበጎቹ አንዷ ጠፍታ ነበር።
ሉቃስ 15፥4
ሰውየውም ሌሎቹን 99ኙን ትቶ የጠፋችውን በግ ፍለጋ ሄደ። እስከሚያገኛትም ድረስ ፍለጋውን ቀጠለ።
ሉቃስ 15፥4
በመጨረሻም የጠፋውን በግ ባገኘ ጊዜ፣ እጅግ ተደሰተ! በጉንም በትከሻው ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሄደ እናም ለባልንጀሮቹ እና ለጎረቤቶቹ አብረውት ይደሰቱ ዘንድ ነገራቸው። ኢየሱስም የሰማይ አባት አንድ ሰው ከሃጢያቱ ንሰሃ ሲገባ እና ወደ እርሱ ሲመለስ እንዲሁ እንደሚደሰት ተናገረ።
ሉቃስ 15፥5-7
ሁለተኛው ምሳሌ 10 የብር ሳንቲሞች ስለጠፉባት አንዲት ሴት ነበር። አንዱ ሳንቲም በጠፋባት ጊዜ፣ የጠፋውን ፍለጋ መብራትን አብርታ ቤቱን ጠረገች። እስከምታገኘውም ድረስ ፍለጋዋን ቀጠለች።
ሉቃስ 15፥8
በመጨረሻም የጠፋውን ሳንቲም ባገኘች ጊዜ፣ እጅግ ተደሰተች! ከእርሷም ጋር አብረው ይደሰቱ ዘንድ ለባልንጀሮቿ እና ለጎረቤቶቿ ነገረቻቸው። ኢየሱስም የሰማይ መላእክት አንድ ሰው ከሃጢያቱ ንሰሃ በገባ ጊዜ እንዲሁ እንደሚደሰቱ ተናገረ።
ሉቃስ 15፥9-10
ሶስተኛው ምሳሌ ሁለት ልጆች ስለነበሩት አንድ ሰው ነበር። ታናሹ ልጅ ከዚህ በኋላ ከአባቱ ጋር አብሮ መኖርን አልወደደም ነበር። ከቤተሰቡ ገንዘብ ላይ ድርሻውን እንዲሰጠው አባቱን ጠየቀ። ከዚያም ታናሹ ልጅ ቤቱን ትቶ ወደ ሩቅ ሃገር ሄደ።
ሉቃስ 15፥11-13
ልጁም አንዳንድ መጥፎ ውሳኔዎችን አደረገ። አባቱ ሰጥቶት የነበረውን ገንዘብ አባከነ።
ሉቃስ 15፥13
ሁሉም ገንዘቡ ከጠፋ በኋላ፣ በጣም ተራበ። ማንም የሚበላውን የሚሰጠው አልነበረም። በመጨረሻም እሪያዎችን ለመመገብ ስራ አገኘ። ልጁ እጅግ ተራበ፣ የእሪያዎቹንም ምግብ ለመብላት ተመኘ። ወደ አባቱ መመለስ እንዳለበት አወቀ።
ሉቃስ 15፥14-18
ነገር ግን አባቱ ዳግም ተቀብሎ እንደሚያስተናግደው እርግጠኛ አልነበረም። ከአባቱ ቤት አገልጋዮች እንደ አንዱ ሆኖ ማገልገል እንደሚፈልግ አባቱን ለመጠየቅ ወሰነ።
ሉቃስ 15፥17-19
ልጁም ወደ ቤቱ እየመጣ በነበረ ጊዜ፣ አባቱም ከሩቅ ሲመጣ አየው። አባቱ በጣም ተደሰተ፣ ወደ ልጁም እየሮጠ ሄደ!
ሉቃስ 15፥20
አባትየውም ልጁ ላይ እጆቹን አድርጎ ሳመው። ለአገልጋዮቹም የተመረጠውን ልብስ ለልጁ እንዲያመጡለት እናም ድግስ እንዲያደርጉለት ነገራቸው። ልጁ ወደ ቤቱ ስለተመለሰ እያንዳንዱ ሰው እንዲደሰት ፈለገ።
ሉቃስ 15፥20-24
በዚህ ጊዜ፣ ትልቁ ልጅ በመስክ እየሰራ ነበር። ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ፣ የሙዚቃ እና የዳንስ ድምጽ ሰማ። ሲካሄድ የነበረው ምን እንደነበር አገልጋዩን ጠየቀ። አገልጋዩም ታናሽ ወንድሙ ወደ ቤቱ ተመልሶ እንደመጣ ነገረው፣ በደስታ እያከበሩ እንደሆነም ነገረው።
ሉቃስ 15፥25-27
ታላቅ ወንድሙም ተበሳጭቶ ነበር። አባቱ ወደ ግብዣው እንዲመጣ ጠየቀው፣ ነገር ግን ይሄድ ዘንድ አልወደደም። ለአባቱም ለብዙ ዓመታት ሲያገለግለው እንደነበር፣ ነገር ግን ማንም ግብዣ አድርጎለት እንደማያውቅ ነገረው። አባቱም፣ ‘’እኔ ያለኝ ሁሉ ያንተ ነው፣’’ ነገር ግን አንድ ሰው ንሰሃ ሲገባ እና ተመልሶ ሲመጣ መደሰት ጥሩ ነው! በማለት ተናገረ።
ሉቃስ 15፥28–32