በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ሐዋሪያቱን መረጠ— “ሰዎችን አጥማጆች” ለመሆን የቀረበ ግብዣ


ማቴዎስ 10ሉቃስ 5፥1–116፥12–16

ኢየሱስ ሐዋሪያቱን መረጠ

“ሰዎችን አጥማጆች” ለመሆን የቀረበ ግብዣ

ኢየሱስ ሰዎችን በገሊላ ባህር ሲያስተምር።

አንድ ቀን፣ ሰዎች ኢየሱስ ሲያስተምር ለመስማት ወደ ገሊላ ባህር መጡ። በባህሩ ዳርቻ ሆነው ኢየሱስ በታንኳ ሆኖ አስተማራቸው። ታንኳውም ስምኦን የተባለ ሰው ንብረት ነበር።

ሉቃስ 5፥1–3

ኢየሱስ ከስምኦን ጋር ሲነጋገር።

ኢየሱስ ማስተማር በጨረሰ ጊዜ፣ ስምኦንን ታንኳውን ወደ ባህሩ ጥልቅ እንዲወስደው ጠየቀው። እርሱም ዓሣ ለማጥመድ መረቡን ውሃ ውስጥ እንዲጥል ስምኦንን ነገረው። ስምኦንም ሌሊቱን በሙሉ ሲያጠምድ እንደነበር እና ምንም አሳ እንዳልያዘ ነገረው። ነገር ግን ኢየሱስ ስለጠየቀው፣ እንደገና ይሞክራል።

ሉቃስ 5፥4–5

ስምኦን እና ጓደኞቹ ብዙ አሶችን ሲያጠምዱ።

ስምኦን ብዙ አሶችን በማጥመዱ መረቡ ተቀደደ! በሌላ ታንኳ ውስጥ የነበሩትን ጓደኞቹን እንዲረዱት ጠራቸው። ወዲያውኑም ታንኳዎቹ አሳ በመሞላታቸው መስጠም ጀመሩ። ስምኦን እና ጓደኞቹ ተገረሙ!

ሉቃስ 5፥6–7፣ 9

ስምኦን በኢየሱስ ፊት ተንበርክኮ።

ስምኦን በኢየሱስ ፊት ተንበረከከ። እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ” አለ። እርሱም ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ መሆኑን አወቀ። ኢየሱስ እንዳይፈራ ነገረው።

ሉቃስ 5፥8

ኢየሱስ ስምኦን፣ እንድርያስ፣ ያእቆብ፣ እና ዮሐንስ እንዲከተሉት ሲጋብዛቸው።

ኢየሱስ ስምኦን፣ እንድርያስ፣ ያእቆብ፣ እና ዮሐንስ እንዲከተሉት ጋበዛቸው። አሳን ከማጥመድ ይልቅ፣ ሰዎች ወደ ኢየሱስ እንዲመጡ ይረዳሉ።

ማርቆስ 1፥16–17ሉቃስ 5፥10–11

ኢየሱስ አስራ ሁለት ሐዋርያትን ቤተክርስቲያኑን እንዲመሩ የክህነት ስልጣንን ሲሰጣቸው።

ስምኦን፣ ያእቆብ፣ እና ዮሐንስ አሳ የሚያጠምዱበትን ታንኳ ትተው የኢየሱስ ሐዋሪያት ሆኑ። በኋላም ኢየሱስ ለስምኦን ጴጥሮስ የሚልን ስም ሰጠው። ሐዋርያ የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክር ነው። ኢየሱስ 12 ሰዎች የእርሱ ሐዋሪያት እንዲሆኑ ጠራ። ማንን መጥራት እንዳለበት ለማወቅ ጸለየ። ኢየሱስ እነርሱ ቤተክርስቲያኑን እንዲመሩ ለሐዋሪያቱ የክህነትን ስልጣን ሰጣቸው።

ማቴዎስ 10ሉቃስ 6፥12–169፥1–2

ሐዋርያው አንድን ልጅ ሲፈውስ።

ሐዋሪያቱ የእግዚአብሔር ሃይል ስለነበራቸው፣ የታመሙትን ሰዎች መፈወስ፣ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ከሞት ማስነሳት፣ እና ሌሎች ተዓምራትን ማድረግ ይችሉ ነበር።

ማቴዎስ 10፥8

ኢየሱስ የተሰበሰቡ ሰዎችን ሲያስተምር። አንዳንድ ሰዎች በትምህርቱ ይበሳጩ ነበር።

ኢየሱስ ሐዋርያቱ የእርሱን ወንጌል ያስተምሩ ዘንድ ወደ ብዙ ከተሞች ላካቸው። እርሱም መንፈስ ቅዱስ ምን መናገር እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ እንደሚረዳቸው ነገራቸው። አንዳንድ ሰዎች የሚያስተምሩትን ሊወዱ እንደማይችሉ ነገር ግን በታማኝነት ባገለገሉ ጊዜ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ኢየሱስ ነገራቸው።

ማቴዎስ 10፥5–7፣ 19–22