ማርቆስ 12፥41–44
አንዲት መበለት እና ሁለት ዲናሮች
ኢየሱስ ስለ መስዋእት አስተማረ
ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ሄደ። በዚያም እያለ፣ ሰዎች ለቤተመቅደስ ስራ ገንዘብ ሲሰጡ ተመለከተ። ባለጠጎች ብዙ ገንዘብ ይሰጡ ነበር።
ማርቆስ 12፥41
ከዚያም አንዲት ድሃ መበለት ሁለት ሳንቲሞችን ሰጠች። በጣምም ብዙ አልነበረም፣ ነገር ግን የነበራት ገንዘብ ሁሉ ያ ነበር።
ማርቆስ 12፥42፣ 44
ኢየሱስም ሴቲቱን አይቶ ደቀ መዛሙርቱን ጠራቸው እና ያደረገችውን መጥተው እንዲያዩ ጠየቃቸው።
ማርቆስ 12፥43
ኢየሱስ ሴቲቱ ከሁሉም የበለጠ እንደሰጠች ተናገረ። ባለጠጋ ሰዎች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋል፣ ነገር ግን ከነበራቸው ጥቂቱን ነበር። መበለቷ ትንሽ ገንዘብ ብቻ ነው የሰጠችው፣ ነገር ግን የነበራትን ሁሉ ሰጠች።
ማርቆስ 12፥43-44