ዮሐንስ 10፥1–18
ኢየሱስ መልካሙ እረኛ ነው።
“የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል”
ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ላሉት ህዝብ እርሱ እንደ መልካም እረኛ እንደሆነ ነገራቸው። ደቀ መዛሙርቱ፣ ወይም ተከታዮቹ፣ እንደ በጎቹ ናቸው። መልካሙ እረኛ በጎቹን ያፈቅራል። የእያንዳንዱን ስም ያውቃል።
ዮሐንስ 10፥3፣ 14፤ ደግሞም ሔላማን 15፥13 ተመልከቱ
በጎች የመልካሙን እረኛ ድምጽ ያውቃሉ። ሲጠራቸው፣ እነርሱ ያዳምጣሉ እናም ይታዘዛሉ።
ዮሐንስ 10፥4፣ 27
መልካሙ እረኛ በጎቹን ይንከባከባል። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዘለአለም ህይወት እንደሚመራን ሁሉ፣ እርሱም ወደ ለምለም መስክ ይመራቸዋል።
ዮሐንስ 10፥9–10፣ 28
ሌላ ሰው በጎቹን እንዲንከባከብ ሲቀጠር፣ ድምጹን ስለማያውቁት እርሱን አይከተሉትም። አደጋ ሲመጣም፣ የተቀጠረው ሰው ይሸሻል። እንደ መልካሙ እረኛ ስለበጎቹ ግድ የለውም።
ዮሐንስ 10፥5፣ 12–13
መልካሙ እረኛ በአደጋ ጊዜ አይሸሽም። በጎቹን ለመጠበቅ ይቆያል። ዘለአለማዊ ህይወት ይኖረን ዘንድ ኢየሱስ ለእኛ ህይወቱን አሳልፎ እንደሰጠ፣ ለእነርሱም ህይወቱን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ነው።
ዮሐንስ 10፥11፣ 17–18
ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ላሉ ሰዎች በሌላ ቦታዎች የሚገኙ ሌሎች በጎች እንዳሉት ነገራቸው። ኢየሱስ እነርሱንም ይገባኛል፣ እንዲሁም የእርሱን ትምህርቶች ይሰማሉ። መፅሐፈ ሞርሞን ኢየሱስ በአሜሪካ የሚገኙትን ሌሎች በጎቹን ስለመጎብኘቱ ይነግረናል።
ዮሐንስ 10፥16፤ 3 ኔፊ 15፥11–24