ማቴዎስ 14፥22–33
በውሀ ላይ መራመድ
እምነት ፍርሃትን ያሸንፋል
ኢየሱስ ለብቻው በመሆን ይጸልይ ዘንድ የተወሰነ ጊዜ አስፈለገው። ደቀመዛሙርቱን በጀልባ ወደ ሌላኛው የገሊላ ባህር ክፍል እንዲሄዱ ላካቸው። ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ሄደ።
ማቴዎስ 14፥22–23
በዚያም ሌሊት፣ ነፋሱ ከባድ እና ማዕበሉም ትልቅ ነበር። የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ጀልባውን ወደ ባሕሩ ማዶ ለማሻገር ሌሊቱን ሙሉ ይታገሉ ነበር።
ማቴዎስ 14፥24–25
ሌሊቱም በተገባደደ ጊዜ፣ ደቀመዛሙርቱ የሆነ ሰው በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ ሲመጣ ተመለከቱ። መናፍስትም ስለመሰላቸው ፈሩ። መናፍስት አልነበረም፤ ኢየሱስ ነበር! ጠራቸውናም፦ “አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።
ማቴዎስ 14፥25–27
ጴጥሮስም በውሃ ላይ ወደ እርሱ እንዲመጣ እንዲጋብዘው ኢየሱስን ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “ና!” አለው። ጴጥሮስም ከጀልባው ወርዶ ልክ እንደ ኢየሱስ በውኃው ላይ መራመድ ጀመረ።
ማቴዎስ 14፥28–29
ነገር ግን ጴጥሮስ ሃያሉን ነፋስ እና ታላላቅ ማዕበሎችን ባየ ጊዜ ፈራ። ወደ ውሃው ውስጥ መስጠም ጀመረ። ወደ ኢየሱስም ጮኸና፣ “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ” አለ።
ማቴዎስ 14፥30
ኢየሱስ እጁንም ዘርግቶ ጴጥሮስን ያዘው። ይበልጥ እርሱን ከማመን ይልቅ ለምን እንደተጠራጠረ ጴጥሮስን ጠየቀው።
ማቴዎስ 14፥31
ኢየሱስ እና ጴጥሮስ ወደ ጀልባው ሲመለሱ ነፋሱ ቆመ። በሆነው ነገር ደቀመዛሙርቱ ተገርመው ነበር። ኢየሱስ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አወቁ እናም አመለኩት።
ማቴዎስ 14፥32–33