የሐዋርያት ስራ 10
ቆርኔሌዎስና ጓደኞቹ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ
ወንጌል ለሁሉም ነው
ቆርኔሌዎስ የሮማ ወታደሮች መሪ ነበር። እሱና ቤተሰቡ በእግዚአብሔር ያምኑ ነበር፤ ነገር ግን አይሁዶች አልነበሩም፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አያውቁም ነበር። ቆርኔሌዎስ የነበረውን ለድሆች አካፍሏል እናም ብዙ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር።
የሐዋርያት ስራ 10፥1–2
አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ፣ ቆርኔሌዎስ እየጾመና እየጸለየ ሳለ አንድ መልአክ ወደእርሱ መጣ። መልአኩም “ቆርኔሌዎስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶአል” አለው። እግዚአብሔር ቸርነቱን አይቶታል። መልአኩ ቆርኔሌዎስ ኢዮጴ በምትባል ከተማ ይኖር የነበረውን ሐዋርያው ጴጥሮስን እንዲያገኝ ነገረው። ጴጥሮስ ምን ማድረግ እንዳለበት ለቆርኔሌዎስ ይነግረዋል።
የሐዋርያት ስራ 10፥3–6፣ 30–32
ቆርኔሌዎስ መልአኩ የተናገረውን ለአገልጋዮቹ ነገራቸው። ጴጥሮስ እንዲጎበኝው እንዲመጣ እንዲጠይቁም ወደ ኢዮጴ ላካቸው።
የሐዋርያት ስራ 10፥7–8
በኢዮጴ ጴጥሮስ በቤቱ ሰገነት ላይ እየጸለየ ነበር። ተርቦ ነበር እና ሊበላ ሲል ድንገት ራእይ አየ።
የሐዋርያት ስራ 10፥9–10
ጴጥሮስም ከሰማይ በሁሉም ዓይነት አራዊትና ወፎች የተሞላ አልጋ ሲወርድ አየ። ጴጥሮስም እነዚያን እንስሳት መብላት አለብህ የሚል ድምፅ ሰማ። እነዚህ ግን አይሁዶች እንዲበሉት ያልተፈቀደላቸው እንስሳት ነበሩ። የሙሴ ህግ እነዚህ ርኩስ ናቸው ብሏል። ጴጥሮስም ሊበላቸው አልፈለገም።
የሐዋርያት ስራ 10፥11–14
ድምፁም እግዚአብሔር አንድን ነገር ንጹህ ካደረገው፣ ይህም ርኩስ ተብሎ ሊጠራ አይገባም አለው። ራዕዩ ሦስት ጊዜ ተደጋገመ። ጴጥሮስም ይህ ምን ማለት እንደሆነ ጠየቀ።
የሐዋርያት ስራ 10፥15–17
በዚያን ጊዜ መንፈስ ጴጥሮስን ሦስት ሰዎች እየፈለጉት እንደሆነ ነገረው። መንፈስ ቅድስም፣ “እኔ ልኬአቸዋለሁና ከእነርሱ ጋር ሂድ” አለው።
የሐዋርያት ስራ 10፥16–21
ሦስቱም ሰዎች የቆርኔሌዎስ አገልጋዮች ነበሩ። ቆርኔሌዎስ ስላየው መልአክ ለጴጥሮስ ነገሩት፤ ጴጥሮስም መጥቶ ያስተምረው እንደሆነ ጠየቁት። አይሁዶች ብዙውን ጊዜ አይሁድ ባልሆኑ ሰዎች ቤት አይገቡም ነበር፣ ሐዋርያትም ወንጌልን አላስተማሩአቸውም። ነገር ግን ጴጥሮስ ራእዩን በማስታወስ ለመሄድ ወሰነ።
የሐዋርያት ስራ 10፥22፣ 28
ጴጥሮስ በደረሰ ጊዜ፣ ቆርኔሌዎስ ከብዙ ጓደኞችና ከቤተሰቦቹ ጋር ይጠብቀው ነበር። እግዚአብሔር እንዲነግራቸው ያዘዘውን ሁሉ ለመስማት ዝግጁ መሆናቸውን ለጴጥሮስ ነገረው።
የሐዋርያት ስራ 10፥26፣ 33
ጴጥሮስም እግዚአብሔር በራእዩ ምን እያስተማረው እንዳለ ተረዳ። ጴጥሮስ እግዚአብሔር አንዱን ብሔር ወይም ህዝብ ከሌላው በላይ እንደማይወድ ለሁሉም ነገረ። እግዚአብሔር ትሱም የሚከተልን እና መልካም የሚያደርግን ሁሉ ይቀበላል። ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስንና ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተማረ።
የሐዋርያት ስራ 10፥34–43
ሲያስተምር መንፈስ ቅዱስ ለሚሰሙት ሁሉ ተሰጠ። ጴጥሮስ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ጋበዛቸው። ጴጥሮስ ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት እንዳላቸው ተረዳ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለሁሉም ተሰበከ።
የሐዋርያት ስራ 10፥44–48