የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ የቅዳሜ ጠዋት ክፍለ ጊዜ የቅዳሜ ጠዋት ክፍለ ጊዜከሚያዝያ 5–6፣ 2025 (እ.አ.አ) የሚካሄደው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የ194ኛ አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤ የቅዳሜ ጠዋት ክፍለ ጊዜ። ዳልን ኤች. ኦክስየአጠቃላይ ባለስልጣናትን፣ የአከባቢ ሰባዎችን እና አጠቃላይ መሪዎችን መደገፍፕሬዚዳንት ኦክስ, የኋለኛው ቀን ቅዱሳ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ባለስልጣናትን፣ የክልል ሰባዎችን እና አጠቃላይ መሪዎችን ለድጋፍ ያቀርባሉ። ጄርድ ቢ. ላርሰንየቤተክርስቲያኗ ኦዲት ክፍል ሪፖርት፣ 2024 (እ.አ.አ)ጄርድ ቢ. ላርሰን የቤተክርስቲያኗን ኦዲት ሪፖርት ያነባሉ፡፡ ጀፍሪ አር. ሆላንድእንደ ትንሽ ልጅፕሬዚዳንት ሖላንድ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለመግባት እንደ ትንሽ ልጅ የመሆን አስፈላጊነትን አስተማሩ። ካሚል ኤን. ጆንሰንበመንፈሳዊነት በእርሱ ሙሉ መሆንፕሬዚዳንት ጆንሰን ስጋዊ እና ስሜታዊ ፈውስ በምንጠብቅበት ጊዜ በመንፈስ ሙሉ ለመሆን እንደምንችል አስተማሩ። ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድበአይናችን ፊትጌታ ስራውን እያፋጠነ መሆኑን በመጥቀስ፣ ሽማግሌ ራስባንድ ቤተክርስቲያኗ በአባላት፣ በምስዮኖች፣ በቤተመቅደሶች እና በትምህርት ጥረቶች ያሳየችውን እድገት እንደገና ይዘረዝራሉ። ክዉንተን ኤል. ኩክየኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ዋናውን ማዳን ያመጣልሽማግሌ ኩክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕይወት ማዕበል እንደሚያድነን ለማስተማር የእጅ ጋሪ መስራቾች ምሳሌን ይጠቀማሉ። ሪካርዶ ፒ. ሂሜኔዝለአዳኙ ያለኝ ፍቅር የእኔ “ምክንያት” ነው።ሽማግሌ ሒሜኔዝ ድርጎቶቻችንን ለኢየሱስ ክርስቶስ ካለን ፍቅር ጋር የማገናኘት አስፈላጊነትን አስተማሩ። ሔንሪ ቢ. አይሪንግ“ወደ እኔ ቅረቡ”ፕሬዚዳንት አይሪንግ በጸሎት፣ መመሪያን በማዳመጥ፣ እና ሌሎችን በማገልገል ወደ አዳኙ ለመቅረብ እንደምንችል አስተማሩ። የቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ክፍለ ጊዜ የቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ክፍለ ጊዜከሚያዝያ 5–6፣ 2025 (እ.አ.አ) የሚካሄደው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የ195ኛ አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤ የቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ክፍለ ጊዜ። ኒል ኤል. አንደርሰንለህይወት ዋጋ መስጠትሽማግሌ አንደርሰን ስለ ህይወት ቅድስና እና ስለመንከባከብ እና ስለመጠበቅ አስፈላጊነት ያስተምራሉ። ስቲቨን ጄ. ለንድመለኮታዊ ሥልጣን፣ ማራኪዎቹ ወጣት ወንዶችፕሬዚዳንት ለንድ ስለአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች ሀላፊነቶች እና በአገልጎታቸው በኩል ስለሚመጡ በረከቶች ያስተምራሉ። ኤስ. ማርክ ፓልመር“እፈውሳችሁ ዘንድ … ወደ እኔ ተመለሱ“ሽማግሌ ፓልመር ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌሉ ለመመለስ የረፈደ እንዳልሆነ ያስተምራሉ። ሳንዲኖ ሮማንእምነት፦ የመተማመን እና ታማኝ የመሆን ትስስርሽማግሌ ሮማን እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መተማመን እና ለእርሱ ታማኝ መሆን እንደሆነ ይገልጻሉ፣ እንዲሁም እምነታችንን እንዴት መንከባከብ እና ማሳደግ እንደምንችል ያስተምራሉ። ዴል ጂ. ረንለንድአዳኙን ለመገናኘት ግላዊ ዝግጅትሽማግሌ ረንለንድ ለዳግም ምጽአት እንዴት መዘጋጀት እንደምንችል ለማስተማር ከሦስቱ የአዳኝ ምሳሌዎች ትምህርቶችን ይጠቀማሉ። ሀንስ ቲ. ቡምወላጆቻችን ላጸኑት እምነት እውነተኛ እንሁንሽማግሌ ቡም በወላጆቻችን እና በአያቶቻችን እምነት እና ምስክርነት ጥንካሬን እንድናገኝ ያስተምሩናል። ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ‘’በዚህም ደቀመዛሙርቴ መሆናችሁን ሁሉም ያውቃሉ’’ሽማግሌ ኡክዶርፍ ለሌሎች ያለን ፍቅር ደቀመዛሙርትነታችንን እንደሚያሳይ እና በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባልነትን እና አንድነትን እንደምናገኝ ያስተምራሉ። የቅዳሜ ምሽት ክፍለ ጊዜ የቅዳሜ ምሽት ክፍለ ጊዜከሚያዝያ 5–6፣ 2025 (እ.አ.አ) የሚካሄደው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የ195ኛ አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤ የቅዳሜ ምሽት ክፍለ ጊዜ። ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰንስለ ክርስቶስ እንናገራለንሽማግሌ ስቲቨንሰን ትንሣኤን ሆን ብለን ለማክበር የቤተክርስቲያን መሪዎች የሚቀርቡልንን ግብዣ ስንቀበል፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለን ግንኙነት እየጠነከረ እንደሚሄድ እንደምናገኘው ያስተምራሉ። ኤሚ ኤ. ራይትአንተ ክርስቶስ ነህእህት ራይት ልጆቻችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ እና እርሱን እንዲመስሉ የመርዳት አስፈላጊነትን አስተምረዋል። ጄምስ አር. ራዝባንድየምህረት እቅድሽማግሌ ራዝባንድ እግዚአብሔር መሀሪ እንደሆነ እና የደህንነት እቅድ የመህረት እቅድ እንደሆነ ያስተምራሉ። ሰርጂዮ አር ቫርጋስየእኛ ሰማያዊ የምሪት ስርዓትሽማግሌ ቫርጋስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ማተኮር የህይወታውሎ ንፋስን ለመቋቋም እና ወደ ሰማይ ቤታችን አንድ ቀን ለመመለስ እንድንዘጋጅ እንደሚረዳን ያስተምራሉ። ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰንአምልኮሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን አምልኮን ስለሚያካትቱ ድርጊቶች፤ ከአምልኮ ጋር ስለተያያዙ አመለካከቶች፤ የአምልኳችን ብቸኛነት፤ እና እኛ የምናመልከውን ፍጡራን መምሰል እንደሚያስፈልግ አስተምረዋል። የእሁድ ጠዋት ክፍለ ጊዜ የእሁድ ጠዋት ክፍለ ጊዜከሚያዚያ 5–6፣ 2025 (እ.አ.አ) የሚካሄደው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የ194ኛ አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤ የእሁድ ጠዋት ክፍለ ጊዜ። ዴቪድ ኤ. ቤድናርየሁሉም ነገሮች መመለሻ ጊዜሽማግሌ ቤድናር የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እና ቤተክርስትያን ዳግም መመለስ ክፍሎችን፣ የመጀመሪያውን ራዕይ፣ መፅሐፈ ሞርሞን እና ክህነትን ጨምሮ፣ አጠቃልለዋል። ። ስቲቨን ዲ. ሻምዌይለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ለመዘጋጀት ተሳተፉሽማግሌ ሻምዌይ ጥሪዎች እና ሌሎች በቤተክርስቲያን ውስጥ የማገልገል መንገዶች እንድናድግ እና በአዳኝ ፊት ለመቆም እንድንዘጋጅ እንደሚረዱን ያስተምራሉ። ታማራ ደብሊው. ሩኒያንስሐችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሸክም አይሆንም፤ ደስታውን ብሩህ ያደርግለታል።እህት ሩኒያ ስህተት ስንሰራ ዋጋችን እንደማይለወጥ እና አዳኙ እንደሚረዳን እንዲሁም እንድንመርጠው እንደሚፈልግ ታስተምራለች። ጄራልድ ኮሴየማካካሻ በረከቶችኤጲስ ቆጶስ ኮሴ እንደሚያስተምሩት ውስንነቶች እና ተግዳሮቶች የእግዚአብሔር ልጆች ጌታ የገባላቸውን በረከቶች እንዳይቀበሉ አያግዷቸውም። ጌሪት ደብሊው. ጎንግየዘለአለም ታላቅ ስጦታዎች፤ የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ፣ ትንሳኤ፣ ዳግም መመለስሽማግሌ ጎንግ ኢየሱስ ክርስቶስ በሀዘናችን እና በደስታችን ወቅት ፍጹም በሆነ ሁኔታ እንደሚረዳን እንዲሁም የኃጢያት ክፍያ፣ የትንሳኤ፣ እና የዳግም መመለስ ስጦታን እንደሚሰጠን ያስተምራሉ። ጆን ኤ. ማክኪዩንበቃልኪዳን ደቀመዝሙርነት የሚገኝ ደሥታሽማግሌ መኪውን ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ጋር ቃል ኪዳኖችን በመግባት እናም በማክበር ለማግኘት ስለምንችለው ደስታ ያስተምራሉ። ዳለን ኤች. ኦክስ“መለኮታዊ እገዛ ለምድራዊ ህይወት ይጠቅማል”ፕሬዚዳንት ኦክስ የሰማይ አባት ለዘለአለም እድገታችን ባለው እቅዱ በኩል በስጋዊ ጉዞዎቻችን ወቅት እኛን የሚረዳበትን የተለያዩ መንገዶችን ገልጸዋል። የእሁድ ከሰዓት በኋላ ክፍለ ጊዜ የእሁድ ከሰዓት በኋላ ክፍለ ጊዜከሚያዝያ 5–6፣ 2025 (እ.አ.አ) የሚካሄደው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የ195ኛ አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤ የእሁድ ከሰዓት በኋላ ክፍለ ጊዜ። ዩሊሲስ ሶሬስቅዱሥ ለሆኑ ነገሮች የሚሠጥ ጥልቅ አክብሮትሽማግሌ ሶሬስ ለቅዱስ ነገሮች ጥልቅ አክብሮት ማሣየት ምስጋናን፣ መገለጥን እና ደስታን እንደሚያመጣ ያስተምራሉ። ማይክል ቢ. ስትሮንግልግስና— የእውነተኛ ደቀ መዝሙርነት ምልክትሽማግሌ ስትሮንግ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርነታችንን ጥልቅ ለማድረግ እና እንደ እርሱ ለመሆን የሚረዱንን መርሆዎች ያስተምራሉ። ስካት ዲ. ዋይቲንግሁለተኛውን ፈተና ተጠንቀቁሽማግሌ ዋይቲንግ ኃጢአታችንን የመደበቅ ፈተናን መቃወም እንዳለብን እና በምትኩ መለኮታዊ እርዳታን መፈለግ እንዳለብን ያስተምራሉ። ክሪስቶፈር ኤች. ኪምልባችሁን አታጠጥሩሽማግሌ ኪም ንስሀ በመግባት፣ በትህትና፣ እና ጌታን በማመን ልባችንን ለማለሳለስ እንደምንችል ያስተምራሉ። ፓትሪክ ኪረንየእርሱን ስጦታ ተቀበሉሽማግሌ ኪረን የሰማይ አባት ለእና ያለውንን ስጦታዎች፣ በልዩም የልጁ እና እኛ የእግዚአብHኤር ልጆን እንደሆንን የሚያመለክቱ እውነቶች ስጦታን እንድንቀበል ጋበዙን፡፡ ቤንጃሚን ኤም. ዜድ. ታይእግዚአብሄር ለእኛ ያለው ፍቅርሽማግሌ ታይ የእግዚአብሔርን እና የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እንዴት እንደሚሰማን ያስተምራሉ። ራስል ኤም. ኔልሰንበእግዚአብሔር ፊት ልበ ሙሉ መሆንፕሬዚዳንት ኔልሰን ህይወታችንን በበጎ ድርገት እና በምግባረ ጥሩነት ስንሞላ በእግዚአብሔር ፊት ልበ ሙሉ መሆን እንደምንችል ያስተምራሉ።