አጠቃላይ ጉባኤ
የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ዋናውን ማዳን ያመጣል
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


14:16

የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ዋናውን ማዳን ያመጣል

የአለም አዳኝ ወደሆነው፣ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንዞር፣ በሃጥያት ክፍያው ከህይወት ማእበሎች ያድነናል።

የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በዚህ ህይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙን ፈተናዎች ዋናውን ማዳን ያመጣል። ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን የካስፐር ዋዮሚንግ ቤተመቅደስን ባርኬ እንድከፍት መድበውኝ ነበር። ያም ጥልቅ፣ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ተሞክሮ ነበረ። በአዳኙ የሀጥያት ክፍያ አማካኝነት የእግዚአብሔርን ልጆች በማዳን ውስጥ ቤተመቅደስ ያለውን ሚና በግልጽ ያሳየ ነበር።

በካስፐር ዋዮሚንግ ቤተመቅደስ አውራጃ ውስጥ ያሉት ካስማዎች በ1847 እና 1868 (እ.አ.አ) መካከል በመስራች የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጥቅም ላይ የነበሩ የእግር መንገዶችን ያካትታሉ። ለቤተመቅደስ ምረቃ በምዘጋጅበት ጊዜ፣ በካስፐር አቅራቢያ በፕላት ወንዝ በኩል ሰላለው እና እስከ ሶልት ሌክ ሲቲ ድረስ ስለሚቀጥለው የእግር መንገድ ታሪክ ዳግም አነበብኩ። ያ የእግር መንገድ በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ምዕራባዊ ስደተኞች ማለፊያ ነበር። ዋናው ትኩረቴ የነበረው ከ60 ሺህ በሚበልጡት በመንገዱ ላይ የተጓዙ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መስራቾች ላይ ነበር።

አብዛኞቹ የእኛ መስራቾች በሰረገላ የመጡ ሲሆን ወደ 3 ሺህ የሚሆኑት ግን የተሻገሩት በአስር የእጅ ጋሪ ቡድኖች ነበር። ከእጅ ጋሪ ቡድኖች ውስጥ ስምንት የሚሆኑት አስደናቂውን ጉዞ ያከናወኑት በታላቅ ስኬት እና በጥቂቶች ሞት ነበር። የ1856 (እ.አ.አ) የዊሊ እና ማርቲን ቡድኖችን ግን ከዚህ የተለዩ ነበሩ።

መጥፎ የአየር ሁኔታ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያለውን የዊሊ እና ማርቲን የእጅ ጋሪ ቡድን መዛግብትን ከለስኩ። ስዊትዋተር ሪቨር፣ ማርቲንስ ኮቭ፣ ሮኪ ሪጅ፣ እና ሮክ ክሪክ ሃሎውን በሚሻገሩበት ወቅት ስላጋጥሟቸው ችግሮች በጥልቀት አወኩ።

የእጅ ጋሪ መስራቾች በበረዶ ውስጥ።

በማዕበል መካከል፣ በአልቢን ቬሴልካ

ከመመረቁ አስቀድሞ በካስፐር ቤተመቅደስ ውስጥ ገብቼ አላቅም ነበር። ወደ መቆያው ስገባ፣ በማእበል መሃል [Between Storms]፣ በሚል የተሰየመ ቀዳሚ የእጅ ጋሪ ስዕል ወዲያውኑ ቀልቤን ሳበው። ምስሉ ተከስቶ የነበረውን ሃዘን እንዲያሳይ የታቀደ እንዳልነበር ግልጽ ነው። በጥሞና እየተመለከትኩት፣ እንዲህ አሰብኩ፣ “ይህ ስዕል ትክክል ነው፣ አብዛኛዎቹ በእጅ ጋሪ የተጓዙ መስራቾች አሰቃቂ ሆኔታዎች አላጋጠማቸውም ነበር።” ይሄ በአጠቃላይ ህይወትን እንደሚመስል ተሰማኝ። እኛ አንዳንዴ በማእበሎች፣ አንዳንዴ ደግሞ በዳመናዎች እና በጸሃይ መካከል እንሆናለን።

ስዊትዋተር ወንዝ።

የሰማይ ፖርታል[መግቢያ]፣ በጂም ዊልኮክስ

የሰማይ አምሳያ [Heaven’s Portal] ተብሎ ወደተሰየመው ቀዳሚ ስዕል ስዞር፣ “የዲያብሎስ በር [Devil’s Gate]” ተብሎ ይጠራ የነበረው፣ ረጋ ያለ እና ንጹህ የስዊትዋተር ወንዝ በውስጡ እያለፈ፣ መስራቾች በዚያ አስፈሪ የክረምት ወቅት ያጋጠማቸውን ችግሮች ብቻ ሳይሆን፣ ውብ የሆነውን የጌታ ፍጥረት ያሳይ ነበር።

ከዚያም ወደ ፊት ለፊት ተመለከትኩ፣ ከመግቢያ ፈቃድ ጠረጴዛ ጀርባ፣ እንዲሁም የአዳኙን ውብ ምስል ተመለከትኩ። ያም ወዲያው ጥልቅ የሆነ የምስጋና ስሜትን ፈጠረ። እጅግ ውብ በሆነችው አለም ውስጥ፣ ግዙፍ ችግሮችም አሉ። የአለም አዳኝ ወደሆነው፣ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንዞር፣ በአብ እቅድ መሰረት በሃጥያት ክፍያው ከህይወት ማእበሎች ያድነናል።

ለእኔ የዘለአለማዊ ደህንነትን ስረዓቶች ለመቀበል፣ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለመግባት፣ እና የአዳኙን የሃጥያት ክፍያ ለመቀበል እና የበረከቶቹ ተቋዳሽ ለመሆን የሚያስችሉንን ወደ ቤተመቅደስ ስርአት ክፍሎች መግቢያው ፍጹም ማዘጋጃ ነበር። የአብ የደስታ እቅድ በአዳኙ የሃጥያት ክፍያ ማዳን ላይ የተመሰረተ ነው።

የመስራቾች ተሞክሮ ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የታሪክ ባህል እና በደምብ የተዋቀረ መንፈሳዊ ቅርስን የሚሰጥ ነው። ለአንዳንዶች፣ ከሚዙሪ እና ናቩ ከሁለቱም በሃይል ከተባረሩ በኋላ የመጣው ስደት ለአመታት የዘለቀ ነበር። ለሌሎች ደግሞ የጀመረው፣ ፍልሰትን ይበልጥ የሚቻል እንዲሆን ከታቀደው የፕሬዚዳንት ብሪገም ያንግ የእጅ ጋሪ እቅድ በኋላ ነበር። የእጅ ጋሪዎቹ ዋጋ ከሰረገላዎች እና በሬዎች ይቀንስ ነበር።

ሚለን አትዉድ የሚባል አንድ የእንግሊዝ አገር ሚስዮናዊ የእጅ ጋሪን እቅድ ሲተዋወቅ እንዳለው፣ “በደረቅ ገለባ ላይ እንዳለ እሳት ነበር የሄደው፣ የቅዱሳን ልብ በደስታና ሃሴት ተሞልቶ ነበር”። አብዛኛዎቹ፣ “በተራራዎች ውስጥ ከወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ጋር ለመገናኘት ቀን ከሌት ጸልየዋል እንዲሁም ጾመዋል።”

አብዛኞቹ የእጅ ጋሪ ቅዱሳን ከባድ ጊዜን አሳልፈዋል ነገር ግን ከዚያ የባሱ ትልቅ ክስተቶችን አስወግደዋል። ነገር ግን ሁለት የእጅ ጋሪ ቡድኖች፣ የዊሊ ቡድን እና የማርቲን ቡድን፣ እረሃብን በረዶአማ የአየር ሁኔታ መጋፈጥን፣ እና የብዙዎችን ሞት አይተዋል።

እነዚህ አብዛኛዎቹ ተጓዦች በግንቦት 1856 (እ.አ.አ) በሁልት መርከቦች ተሳፍረው ከሊቨርፑል፣ እንግሊዝ የተጓዙ ናቸው። በአይዋ ከተማ ያለው የእጅ ጋሪ መሸጫ የደረሱት በሰኔ እና ሐምሌ ነበር። ማስጠንቀቂያዎች ቢሰጣቸውም፣ ሁለቱም ቡድኖች ወቅቱ በጣም ከረፈደ በኋላ ነበር ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ ያቀኑት።

የእነዚህ ቡድኖችን አስከፊ ሁኔታ ፕሬዚዳንት ብሪጌም ያንግ መጀመሪያ የሰሙት በጥቅምት 4፣ 1856 (እ.አ.አ) ነበር። በቀጣዩ ቀን በሶልት ሌክ ሲቲ በቅዱሳን ፊት በመቆም እንዲህ አሉ፣ “አብዛኛዎቹ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የእጅ ጋሪዎችን ይዘው በመንገድ ላይ ናቸው፣ … እነርሱን ወደዚህ ማምጣት አለበን፣ ክረምት ከመግባቱ በፊት … እርዳታ ልንልክላቸው ይገባል።”

60 የበቅሎ ጥማዶችን፣ 12 ወይም ከዚያ የሚበልጥ ሰረገላዎች፣ እና 12 ቶን(10,886 kg) ዱቄት እንዲያዘጋጁ ኤጲስ ቆጶሶችን ጠየቁ፣ “ሂዱ እና እነዚያ ሰዎች ከመንገድ አምጧቸው”፣ በማለት አወጁ።

በዊሊ እና ማርቲን የእጅ ጋሪ ቡድኖች ውስጥ ያሉ መስራቾች አጠቃላይ ቁጥር 1 ሺህ 100 ገደማ ነበር። ከእነዚያ ውድ አባላት ውስጥ 200 የሚሆኑት በመንገድ ላይ ሞቱ። በጊዜው የደረሰ እርዳታ ባይኖር ኖሮ፣ ከዚያም የበለጠ ብዙ ሰዎች ይጠፉ ነበር።

የመጀመሪያዎቹ ረጂዎች ከሶልት ሌክ ሲቲ ከሄዱ ሁለት ሳምንታት በኋላ የክረምት ማእበል ጀመረ። ማዕበሉን ተከትሎ ከጀመረው መጥፎ የአየር ሁኔታ በኋላ የነበሩትን አሰቃቂ ችግሮች የዊሊ እና ማርቲን የእጅ ጋሪ ቡድን የአባላት መዛግብት ያብራራሉ። እነዚህ ዘገባዎች እርዳታ ሰጪዎች በደረሱበት ወቅት የተሰማውን ታላቅ ደስታ ያመለክታሉ።

የደረሱበትን ወቅት ስታብራራ ሜሪ ሀረን እንዲህ አለች፣ “በወንዶቹ ጉንጮች እንባዎች ወረዱ፣ ልጆቹም በሃሴት ፈነጠዙ። ሰዎቹ ስሜታቸውን መቆጣጠር እንደቻሉ፣ በበረዶው ላይ ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ምስጋናን ሰጡ።”

ከሁለት ቀናት በኋላ፣ የዊሊ ቡድን በሮኪ ሪጅ ላይ፣ በበረዷማ ማእበል ውስጥ በጣም አስቸጋሪውን የመንገድ ክፍል መጓዝ ነበረባቸው። የመጨረሻዎቹ ሰዎች እስከ ቀጣዩ ማለዳ 11 ሰአት ወደ መጠለያ አልደረሱም ነበር። አስራ ሶስት ሰዎች ሞተው በአንድ መቃብር ስፍራም ተቀበሩ።

በህዳር 7 ቀን፣ የዊሊ ቡድን ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ እየተቃረቡ ነበር፣ ነገር ግን በዚያ ጠዋት፣ አሁንም ሌላ ሶስት ሞተው ነበር። ከሁለት ቀናት በኋላ፣ የዊሊ ቡድን በመጨረሻ ወደ ሶልት ሌክ ደረሰ፣ እዚያም በአስደናቂ ሰላምታ ወደ ቅዱሳን ቤቶች አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር።

በዚያው ቀን፣ የማርቲን ቡድን አሁንም 325 ማይል (523 km) ርቀት ላይ ነበሩ፣ በብርድ እና በቂ ያልሆነ ምግብ መሰቃየተቻውን ቀጥለዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት፣ የስዊትዋተርን ወንዝ ተሻግረው አሁን ማርቲንስ ኮቭ እየተባለ የሚጠራው ቦታ ላይ ደርሰው ነበር፣ እዚያም ከከባቢ አየር ጥበቃ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገው ነበር። ከመስራቾች ውስጥ አንዱ እንዲህ አለ፣ “የጉዞው በጣም መጥፎው ክፍል ወንዝ መሻገር ነበር።” 17 አመቱ የነበረው የኔ ታላቅ ቅድመ አያት፣ ዴቪድ ፓተን ኪምቦል አይነት አንዳንድ ረጂዎች፣ ከወጣት ጓደኞቹ “ጆርጅ ደብሊው. ግራንት፣ አለን ሀንቲንተን፣ ስቴፈን ቴይለር፣ እና አይራ ነበረክ በባም ብርድ በነበረ ውሃ ውስጥ ሰአታትን አሳለፉ፣” በጋር በመሆን በጀግንነት ቡድኑ በስዊትዋተር እንዲሻገሩ ረዱ።

ይህ ክስተት ብዙ ትኩረት ቢያገኝም፣ ስለ ረጂዎቹ የበለጠ ስማር፣ ሁሉም ነቢዩን እየተከተሉ መሆናቸውን እና መንቀሳቀስ ያልቻሉትን ቅዱሳንን በማዳን ወሳኝ ሚና እንደተጫወቱ ተረዳሁ። ልክ እንደ ስደተኞቹ፣ ሁሉም ረጂዎች ጀግኖች ነበሩ።

ታሪካቸውን በማጥናቴ፣ በስደተኞች መካከል ያለውን ውድ ግንኙነት እና የረጅም ጊዜ ዘለአለማዊ እይታ አደነቅኩ። ጆን እና ማሪያ እንዲሁም ሶስቱ ወንድ ልጆቻቸው የዊሊ ቡድን አባላት ነበሩ። ጆን የሞተው የመጀመሪያ ረጂዎች ከመድረሳቸው ሰአታት በፊት ነበር ። ጉዞውን በማድረጋቸው ደስተኛ ሰለመሆኑ ለማሪያ ነግሯት ነበር። “በህይወት እያለሁ በሶልት ሌክ ከተማ ለመድረስ አልችልም፣ ነገር ግን አንቺ እና ወንድ ልጆቹ ትደርሳላችሁ፣ እንዲሁም ወንዶች ልጆቻችን ማደግ ከቻሉና ቤተሰቦቻቸውን በፅዮን ውስጥ ማሳደግ ከቻሉ፣ እኛ ላይ ስለተከሰቱት ነገሮች ሁሉ ምንም አልቆጭም” አለ።

ፕሬዘደንት ጄምስ ኢ ፎስት ይህን አስደናቂ ማጠቃለያ አቅርበዋል፡- “የእጅ ጋሪ መስራቾች ባደረጉት የጀግንነት ጥረት፣ ታላቅ እውነትን እንማራለን። ሁሉም በማጣሪያው እሳት ውስጥ ማለፍ ነበረባቸው፣ እና በህይወታችን ውስጥ ትርጉም የሌላቸው እና አስፈላጊ ያልሆኑት እንደ ዝገት ይቀልጣሉ እንዲሁም እምነታችንን ብሩህ፣ ያልተነካ እና ጠንካራ ያደርጉታል። ትክክል የሆነውን ለማድረግ እና ታማኝ ለመሆን ከልባቸው የሚሹትን ጨምሮ ለሁሉም ሰው የሚሆን ሙሉ ጭንቀት፣ ሀዘን፣ እና ብዙ ጊዜ የልብ ሰቆቃ ያለ ይመስላል። ሆኖም ይህ ከእግዚአብሔር ጋር ለመተዋወቅ የመንጻቱ አካል ነው።”

ዘለአለማዊነትን በሚቀርጸው የሃጥያት ክፍያው እና ትንሳኤው፣ አዳኙ “ሞትን ድል በማድረግ፣ የሞትን ቀንበሮች” ለሁሉም ሰብሯል። ለኃጢያታቸው ንስሐ ለገቡ፣ “በራሱም ላይ ክፋታቸውንና መተላለፋቸውን በማድረግ፣ እነርሱን በማዳን፣ እናም የፍትህን ፍላጎት አሟልቷል።”

ያለ ኃጥያት ክፍያ፣ እራሳችንን ከኃጥያት እና ሞት ማዳን አንችልም ነበር። በፈተናዎቻችን ውስጥ ኃጢአት ትልቅ ሚና ሊጫወት ቢችልም፣ የህይወት ችግሮች በስህተቶች፣ በመጥፎ ውሳኔዎች፣ በሌሎች ክፉ ድርጊቶች እና ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ብዙ ነገሮች የተደመሩ ናቸው።

ወንጌሌን ስበኩ እንደሚያስተምረው፦ “በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ላይ ስንመካ፣ በፈተናዎቻችን፣ በበሽታዎቻችን እና በህመሞቻችን እንድንታገስ ሊረዳን ይችላል። በደስታ፣ በሰላም፣ እና በመፅናናት ለመሞላት እንችላለን። በህይወት ሚዛናዊ ያልሆኑ ነገሮች በሙሉ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ትክክል መሆን ይችላሉ።”

በፋሲካ ወቅት፣ ትኩረታችን በአዳኙእና የእርሱ የሃጥያት ክፍያ መሰዋትነት ላይ ነው። የኃጢያት ክፍያ ለብዙዎች ጨለማ እና አስፈሪ በሚመስልበት ጊዜ ተስፋ እና ብርሀን ይሰጣል። ፕሬዚዳንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ እንዲህ ብለዋል፣ “ሁሉም ታሪክ ሲፈተሽ፣ … እንደዚህ የጸጋው ተግባር የምደንቅ፣ ግርማ ሞገስ ያለው፣ እጅግ ታላቅ የሆነ ነረግ የለም።”

በተለይ ለዘመናችን ጠቃሚ ናቸው ብዬ የማስበውን ሶስት ምክሮችን አካፍላለሁ።

በመጀመሪያ፣ ሌሎችን ከሥጋዊና በተለይም ከመንፈሳዊ ተግዳሮቶች ለማዳን የምንችለውን ማድረግ ያለውን አስፈላጊነት አቅልላችሁ አትመልከቱ።

ሁለተኛ፣ የአዳኙን የሃጥያት ክፍያ በአምስጋኝነት ተቀበሉ። የህይወትን ችግሮች ስናስተናግድም እንኳ ቢሆን ደስታን እና ሃሴት ማድረግን መለማመድ አለብን። ግባችን በፀሃይ ጎዳና ላይ በብሩህ ተስፋ መኖር መሆን አለበት።። ውድ አጋሬ፣ ሜሪ ይህን በሕይወቷ በሙሉ ስትፈጽም ተመልክቻለሁ። ለዓመታት ችግሮች ቢያጋጥሙንም አንጸባራቂ እና አነቃቂ በሆነው አቀራረቧን እደንቃለሁ።

ሦስተኛው ምክሬ የአዳኙን የኃጢያት ክፍያ በታማኝነት ለማሰላሰል ቀጣይነት ያለው ጊዜ እንዲመደብ ነው። በግላዊ የሃይማኖት ተግባር ውስጥ ይህን ለማድረግ ብዙ መንገዶች አሉ። ሆኖም፣ ቅዱስ ቁርባ ስብሰባ ላይ መገኘት እና ቅዱስ ቁርባንን መካፈል በተለየ ሁኔታ አስፈላጊ ነው።

የሚቻል ከሆነ በየጊዜው ቤተመቅደስን መካፈል በተመሳሳይ ሁኔታ አስፈላጊ ነው። ቤተመቅደስ የአዳኙን የሃጥያት ክፍያ እና ምን እንዳሸነፈ በቀጣይነት ለማስታወስ ይረዳል። ከዚያም በበለጠ የሚያስፈልገው፣ ላለፉት ወዳጆቻችን እና ለአያቶቻችን መንፈሳዊ መዳንን ለማምጣት የሚያስችለው የቤተመቅደስ ተሳትፎ ነው።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ ባለፈው ጉባኤያችን ላይ ይህንን መርህ በጽኑ አመላክተዋል፣ እንዲህም በማለት ጨምረዋል፣ “[የቤተመቅደስ] በረከቶች … ዓለምን ለጌታ ዳግም ምጽዓት ለማዘጋጀት ሊረዱ የሚችሉ ሰዎችን ለማዘጋጀት ይረዳሉ!”

የቀደምት ትውልዶችን መስዋዕቶች እና ምሳሌዎችን በፍፁም መርሳት የለብንም ነገር ግን የእኛ ደስታ፣ አድናቆት እና አምልኮ በአለም አዳኝ እና በስርየት መስዋዕቱ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት። ለአብ የደስታ እቅድ ቁልፉ በአዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የመጣው የሃጥያት ክፍያ እንደሆነ እመሰክራለሁ። እርሱ ህያው ነው፣ ቤተክርስቲያኑንም ይመራል። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በዚህ ህይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙን ፈተናዎች ዋናውን ማዳን ያመጣል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. የካስፐር ዋዮሚንግ ቤተመቅደስ በህዳር 24 ቀን 2024 (እ.አ.አ) ተመረቀ።

  2. የዊሊ እና ማርቲን ቡድኖች እና ያጋጠሟቸውን አሳዛኝ ሁኔታዎች ያወኩት በጣም ወጣት እያለሁ ነበር። ቅድመ አያቴ ዴቪድ ፓተን ኪምባል ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ እነዚህን ቅዱሳን ለማዳን የላኩት የሶልት ሌክ ሸለቆ የቡድኑ አካል ነበር። The Story of the Church of Jesus Christ in the Latter Days [ቅዱሳን፦ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ]፣ ቅጽ 2፣ No Unhallowed Hand [ምንም ያልጸዳ እጅ]፣ 1846–1893 [2020 (እ.አ.አ)]፣ 237 ይመልከቱ።

  3. Albin Veselka, Between Storms, original painting in the Casper Wyoming Temple (see “Casper Wyoming Temple Open House Commences,” Newsroom, Aug. 26, 2024, newsroom.ChurchofJesusChrist.org).

  4. “በደመና ይሁን በጸሃይ ብረሃን፣ ጌታ ሆይ፣ ከእኔ ጋር ሁን!” (“Abide with Me; ” Hymns፣ no. 166።)

  5. Jim Wilcox, Heaven’s Portal, original painting in the Casper Wyoming Temple (see “Casper Wyoming Temple Open House Commences,” newsroom.ChurchofJesusChrist.org).

  6. Joseph Brickey, Risen Hope, giclée of original painting (see “Casper Wyoming Temple Open House Commences,” newsroom.ChurchofJesusChrist.org).

  7. ዊሊያም ጂ. ሃርትሊ፣ “The Place of Mormon Handcart Companies in America’s Westward Migration Story [የሞርሞን የእጅ ጋሪ ኩባንያዎች ቦታ በአሜሪካ ምዕራባዊ የስደት ታሪክ ውስጥ]፣” The Annals of Iowa፣ vol. 65, nos. 2, 3 (ጸደይ/በጋ 2006 (እ.አ.አ))፣ 107–9።

  8. ሚለን አትዉድ፣ “Account of His Mission,” Deseret News፣ ህዳር 26፣ 1856፣ 300; በአንድሪው ዲ. ኦልሰን እና ጆሊን ኤስ. አልፊን ውስጥ የተጠቀሱ፣ Follow Me to Zion: Stories from the Willie Handcart Pioneers [ተከተለኝ ወደ ጽዮን፦ ታሪኮች ከዊሊ የእጅ ጋሪ] [2013 (እ.አ.አ)]፣ xi።

  9. የሆዴትስ እና የሃንት ሰረገላ ቡድኖች በማርቲን የእጅ ጋሪ ቡድን አቅራቢያ ተጉዘዋል እናም መታደግም አስፈልጓቸው ነበር።

  10. አብዛኛው የዊሊ ቡድን በግንቦት 4፣ 1856 (እ.አ.አ) በ ቶሮንቶን መርከብ ከሊቨርፑል፣ እንግሊዝ ለቆ ወጥቷል። አብዛኛው የማርቲን ቡድን በግንቦት 25፣ 1856 (እ.አ.አ) በ ሆራይዘን መርከብ ከሊቨርፑል፣ እንግሊዝ ለቆ ወጥቷል።

  11. “Handcart Camp Dedicated in Iowa as Historic Site [ለየእጅ ጋሪ ካምፕ በአዮዋ እንደ ታሪካዊ ቦታ የተመረቀ]”፣ Church News፣ ነሃሴ 9፣ 1980 (እ.አ.አ)፣ 3፣ 5 ይመልከቱ።

  12. Brigham Young, “Remarks,” Deseret News, Oct. 15, 1856, 252. punctuation modernized.

  13. ብሬገም ያንግ፣ “Remarks [ንግግሮች]፣” 252።

  14. ኦልሰን እና አልፊን፣ Follow Me to Zion፣ 217 ይመልከቱ።

  15. Mary Hurren, in Olsen and Allphin, Follow Me to Zion, 131.

  16. በሃምሌ 23፣ 1994 (እ.አ.አ)፣ ፕሬዚዳንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ የሮክ ክሪክ ሀሎው ሀውልትን ባርከው ከፈቱ እና በሮኪ ሪጅ ላይ በተደረጉት ጉዞ ለሞቱት ታማኝ ቅዱሳን ማስታውሻ ጊዜን አድርገዋል (“see Julie Dockstader Heaps Trail of Handcart Pioneers Sanctified by Sacrifice [በመስዋዕት የተቀደሱ የእጅ ጋሪ አቅኚዎች ዱካ]፣” Church News፣ ሃምሌ 30፣ 1994 (እ.አ.አ)፣ 8–9፣ 11 ይመልከቱ። ፕሬዚዳንት ሮበርት ስኮት ሎሪመር ከፕሬዚዳንት ሂንክሊ ጋር በምርቃው ላይ አብረው ነበሩ። የሪቨርተን ዋዮሚንግ የካስማ ፕሬዚዳንት፣ አደጋው ለደረሰባቸው ሰዎች ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ድርጊቶችን በመለየት እና በመቆጣጠር ማዕከላዊ ሚና ተጫውቷል።

  17. የጄምስ ጂ ዊሊ የስደት ኩባንያ መዝገብ ይመልከቱ፣ ህዳር 7፣ 1856 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ ሶልት ሌክ ከተማ።

  18. ጆን ጃክስ፣ “Some Reminiscences [አንዳንድ ትዝታዎች]፣” Salt Lake Daily Herald፣ Dec. 15፣ 1878 (እ.አ.አ)፣ 1።

  19. ቅዱሳን፣ 2፥237። የዴቪድ ፓተን ልጅ፣ አያቴ ክሮዚየር ጠቃሚ ትምህርቶችን አስተምሮኛል። ዴቪድ ነቢዩን እየተከተለ መሆኑን አበክሮ ገልጿል፣ እና እኛም በዘመናችን የነቢዩን ምክር መከተል አለብን።

  20. John Linford, in Golden C. Linford, Linford Family Heritage (1995), 214; see also Val Parrish, “President’s Message,” Pioneer, vol. 71, no. 3 (Fall 2024), 1.

  21. James E. Faust, in “Faith in Every Footstep: The Epic Pioneer Journey” (video presentation in general conference, Apr. 6, 1997), Ensign, May 1997, 63.

  22. ሞዛያ 15፥8

  23. ሞዛያ 15፥9፤ በተጨማሪም ኢሣይያስ 34፥16ንተመልከቱ።

  24. አልማ 22፥12–15ን ይመልከቱ።

  25. ወንጌሌን ስበኩ፦ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የማካፈል መመሪያ [2023 (እ.አ.አ)]፣ 56።

  26. Gordon B. Hinckley, “The Wondrous and True Story of Christmas,” Liahona, Dec. 2000, 4.

  27. President Thomas S. Monson both taught and lived the rescue principle (see Teachings of Presidents of the Church: Thomas S. Monson [2020], 67–76).

  28. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2024 (እ.አ.አ)፣ 121