አጠቃላይ ጉባኤ
በአይናችን ፊት
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


14:1

በአይናችን ፊት

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአባላት እና በቤተሰቦች፣ በሚስዮን እና በሚስዮናውያን፣ በመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ እና ቤተመቅደሶች፣ እንዲሁም በሴሚናሪ፣ ኢንስቲትዩት፣ እና በአለም ዙሪያ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የምዝገባ ቁጥር እያደገ ነው።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ከእናንተ ጋር በመሆኔ በጣም አመስጋኝ ነኝ። እንወዳችኋለን፤ ስለእናንተ አመስጋኞች ነን፤ እንዲሁም በጸሎታችሁ እንደተባረክን ይሰማናል።

ባለፈው ጉባኤያችን ላይ ፕሬዚዳንት ራሰል ኤም. ኔልሰን እንዲህ አሉ፣ “በአይናችን ፊት እየተከናወነ ያለውን ታያላችሁን? የዚህን ወቅት ታላቅነት የምናስተውልበት ዕድል እንዳያመልጠን እጸልያለሁ! በእርግጥ ጌታ ስራውን እያፋጠነ ነው።

ስራውን ማፋጠን። ዋጋ ያለው ቃል ‘’ማፋጠን’’ የሚለው ነው። የሚያመላክተውም በፍጥነት መሄድን፣ ፍጥነት መጨመርን፣ እንዲሁም አስቸኳይነትን ነው። በቤተክርስቲያን እድገት እና በክርስቶስ እቅድ ውስጥ፣ መፋጠን እየተከናወነ ነው። እና ሁላችንም የዚህ አካል ነን።

በሚያዝያ 1834 (እ.አ.አ)፣ በከርትላንድ፣ ኦሃዮ፣ በግምት ወደ 4.3 ሜትር በምትሆን ትንሽ መማሪያ ቤት ውስጥ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ክህነት ያላቸውን በሙሉ በዚያ ሰበሰባቸው። ትርፍ ክፍልን በማስቀረት፣ እነዚያን ደርዘን የሚሆኑ መማሪያ ቤቶች በዚህ የጉባኤ አዳራሽ ውስጥ በአንድነት ልናደርጋቸው እንችላለን። ጆሴፍ ስሚዝም እንዲህ አለ፣ ‘’ዛሬ ምሽት በዚህ የምታዩአቸው በጣት የሚቆጠሩትን ክህነቶች ነው፣ ነገር ግን ይህ ቤተክርስቲያን ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካን ይሞላል- አለምን ይሞላል።’’

ያ ትንቢት ‘’በአይናችን ፊት’’ እየተፈጸመ ነው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአባላት እና በቤተሰቦች፣ በሚስዮን እና በሚስዮናውያን፣ በመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ እና ቤተመቅደሶች፣ እንዲሁም በሴሚናሪ፣ ኢንስቲትዩት፣ እና በአለም ዙሪያ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የምዝገባ ቁጥር እያደገ ነው።

ቤተክርስቲያን በቁጥር እና በተጽእኖ እያደገች ባለችበት ወቅት በምድር ላይ በመሆናችን አመስጋኞች ነን፣ ነገር ግን ይበልጥ አስፈላጊ በሆነው በአባላቶቿ ልብ እና ህይወት። እኛ እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቶች እንታወቃለን። ስለ እርሱ፣ ስለ ቤተክርስቲያኑ፣ ስለ መንገዱ፣ እና ስለ ቃል ኪዳን መንገዱ ያለንን ምስክርነት እናካፍላለን። እኛም የእርሱ ህዝብ ነን፣ እርሱም አዳኛችን ነው።

ፕሬዚዳንት ኔልሰን ‘’የዚህን ጊዜ ታላቅነት’’ በተናገሩት እና ለጌታ ስለስራው በገለጹት ድንቅ ምስጋና እኔ እገረማለሁ። በጥንትም ሆነ በዘመኑ ትንቢቶች መፈጸም የአይን ምስክሮች በመሆን እንደ እርሱ ደቀመዛሙርት ከፍ ብለን እንድንቆም ራሳችንን አበረታታለሁ።

‘’እነሆ በዚህ እና እነሆ በዚያ፣’’ እያሉ ልክ እንደ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ጊዜ የሚጮሁ አይደለም ባዮች አሉ። ይሁን እንጂ፣ አሉ እና ይኖራሉ ነገር ግን በዚህ የከበረ ስራ ውስጥ ከንቱ የግርጌ ማስታወሻዎች ናቸው። የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን ቃላት አስታውሱ፤ ‘’ያልተቀደሰ ማንም እጅ የስራውን እድገት ማቆም አይችልም፤ … ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነት በድፍረት፣ በግርማ፣ በገለልተኝነት፣ በሁሉም አህጉራት ዘልቆ እስኪገባ፣ ሁሉንም ድንበር እስኪጎበኝ፣ ሁሉንም አገራት እስኪጠርግ፣ እናም እያንዳንዷ ጆሮ እስክትሰማ፣ የእግዚአብሔርም ዓላማ እስኪሳካ እናም ታላቁ ያህዌ ሥራው ተጠናቋል እስኪል ድረስ ይጓዛል።”

በዚህ ዓመት በተሰጠኝ የስራ ድርሻ ውስጥ፣ ‘’የእርሱን ስራ በማፋጠን’’ ለጌታ የፊት ተርታ መቀመጫ አግኝቼ ነበር። ለተጨማሪ አባላት በጌታ ቤት ውስጥ የማምለክን እድል በመስጠት፣ ቤተክርስቲያኗ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ቤተመቅደሶችን እየገነባች ነው። ሁለተኛ፣ ሚስዮናዊ ስራ ወደ መልካሙ እረኛ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በረት ውስጥ ሬከርድ ያላቸው ቁጥሮችን እየሰበሰበ ነው። እና ሶስተኛ፣ የቤተክርስቲያን ትምህርት በአያሌ አደረጃጀቶች ውስጥ ‘’ይህን ኢየሱስን በመሻት’’ ላይ ያሉትን በማስተማር በአዲስ ከፍታ ላይ ነው።

ዛሬ ቤተክርስቲያኗ በተለያዩ የንድፍ ደረጃዎች፣ ግንባታዎች፣ ወይም አፈጻጸም 367 ቤተመቅደሶች አሏት። እና ለምን ዓላማ? መልሱ በእያንዳንዱ ቤተመቅደስ ላይ የታወጀ ነው፤ ‘’ቅድስና ለእግዚአብሔር።’’ ቤተመቅደስ የሰማዩ አባታችን ለእኛ ለእያንዳንዳችን ላለውን ከፍተኛ በረከቶች መንገዱን የሚከፍት ነው። ወንድሞች እና እህቶች፣ እኛ ለቤተመቅደስ ብቁ ሆነን ስንኖር፣ በጌታ ቤት ውስጥ ስናመልክ፣ እና ለራሳችን እና ከመጋረጃው በሌላኛው በኩል ላሉት ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳንን ስናደርግ ‘’ቅድስናችንን’’ እያፋጠንን ነው።

ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ አሉ፤ ‘’የጠላት ጥቃቶች በእጥፍ፣ በጥልቀት እና በአይነት እየጨመሩ ይገኛሉ። በቤተመቅደስ ውስጥ በየጊዜው ለመገኘት ያለው አስፈላጊነት ከዚህ በፊት ከነበረው በላይ ታላቅ ነው። ጊዜአችሁን እንዴት እንድምታሳልፉ በጸሎት እንድትመለከቱ እለምናችኋለሁ።’’ በእርሱ ቤት ውስጥ፣ የጌታ የተቀደሰ መገኘት እና የላቀ ሰላም ሊሰማን ይችላል።

ሽማግሌ እና እህት ራስባንድ በታይላንድ።

ባለፈው ዓመት፣ በሜንዶዛ አርጀንቲና ቤተመቅደስ ምርቃት ላይ በበላይነት መሪ የመሆን እድል አግኝቼ ነበር። በመልእክቴ፣ ‘’ልክ የኦክ ዛፍ ከአኮሪኒ በአንድ ቀን ተመዝዞ እንደማይሄድ’’ የጌታም ስራ በአንድ ወቅት ከደቡብ አሜሪካ ተነስቶ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ እንደሚቀላቀሉት፣ እና የደቡብ አሜሪካ ሃገሮች ‘’ለቤተክርስቲያን ሃይል’’ እንደሚሆኑ የሽማግሌ ሜልቪን ጄ. ባላርድን የ1926ቱ ትንቢት ጠቅሼ ነበር። ያ ትንቢት ‘’በአይኖቼ ፊት’’ ሲፈጸም አይቻለሁ።

ሜንዶዛ፣ በአንድ ወቅት ትንሽ አኮርኒ የነበረች ቢሆንም፣ ሃያል የኦክ ዛፍ ለመሆን በቃች። ያ እድገት ከአህጉራት ተሻግሮ እስከ ባህር ደሴቶች እየተደገመ ነው።

ጌታ በሚስዮኖች ስራውን ሲያፋጥን እናያለን። በ2024 (እ.አ.አ) 80,000 የሚያህሉ ሚስዮናውያን በ450 የሚያህሉ ሚስዮኖች እያገለገሉ ነበር። ከእነዚያ ሰላሳ ስድስቱ አዲስ ሚስዮኖች ናቸው። ባለፈው ዓመት፣ ሚስዮናዊ ስራ ከ300 ሺህ በላይ አዲስ አባላትን ወደ ቤተክርስቲያኗ አምጥቷል። ከቁጥርም በላይ፣ የመሰባሰብ መንፈስ ነፍሳትን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወደ ወንጌሉ እያመጣ ነው።

ሀዋርያት ብሪግሀም ያንግ እና ሂበር ሲ. ኪምቦል በ1839 (እ.አ.አ) ወደ እንግሊዝ ደሴቶች እንደሚስዮናዊ የተጓዙበትን አስባለሁ። ታመው ነበር፤ ሲሄዱ ቤተሰቦቻቸውን በህመም እና በእጦት ነበር የተለዩአቸው። ይሁን እንጂ፣ በሚወዷቸው ሰዎች እይታ ውስጥ እያለ፣ ሁለቱ ወደ ጋሪው ወጡ፣ ሂበርም እንዲህ አለ፣ ‘’እንነሳ እና የደስታ ሰላምታን እንስጣቸው።’’ ሁለቱ በእግራቸው ለመቆም በመታገል፣ ‘’ሁራ፣ ሁራ ለእስራኤል’’ በማለት ጮኹ።

በአካባቢያችሁ ካሉ ሚስዮናውያን ጋር ተገናኙ።

ከሚስዮናዊ ማሰልጠኛ ማእከል እና ሊማ ከሚገኘው ሚስዮን ሚስዮናውያንን ባገኘሁ ጊዜ በሊማ፣ ፔሩ፣ ለጌታ ስራ ያንኑ ታላቅ ፍላጎት አይቻለሁ። እንዴት ያለ እይታ ነው! ‘’ፍጥነቱን’’ በአይኔ ፊት አይቻለሁ። አሁን በሊማ ከተማ ብቻ ሰባት ሚስዮኖች አሉ።

በውይይታችን መጨረሻ፣ ሚስዮናውያን ለእኔ የተለየ አስገራሚ ነገር ነበራቸው። ተነስተው፣ ‘’ሁራ ለእስራኤል’’ በማለት ተደሰቱ። ያንን ጊዜ በጭራሽ ልረሳው አልችልም፤ ሁላችሁም እዚያ መሆን ብትችሉ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ። ‘’በአይኖቻችን ፊት’’ ጌታን ለማገልገል እና የእርሱን መምጣት ለማፋጠን ሚስዮናውያን ‘’የዚህን ዓለም ነገሮች ወደ ጎን ትተዋል።’’

ጌታ ለአባላቶቻችን፣ እና በአለም ዙሪያ ላሉ አባል ላልሆኑትም ጭምር የትምህርት እድሎችን ሲያፋጥን እናያለን። እንደቤተክርስቲያን ከሚለዩን ነገሮች አንዱ ለትምህርት የምንሰጠው ትኩረት ነው። ጌታ “ትምህርትን፣ እንዲሁም በጥናት እና ደግሞም በእምነት” በመሻት እምነታችንን እንዴት ለማጠናከር እንደምንችል በጥንቱ የዳግም መመለስ ወቅት ትእዛዝን ሰጥቷል። ያም ዛሬ እየተከናወነ ነው እናም ‘’ሁራ’’ ማስተጋባቱ የሚገባ ነው።

በዚህ ወቅት 800,000 ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሴሚናሪ እና ኢንስቲትዩት ተመዝግበዋል፣ ይህም በቤተክርስቲያን ታሪክ በጣም ከፍተኛው ምዝገባ ነው። ታዳጊዎቻችን ከጠዋት ማለዳ ጀምሮ፣ በቀን፣ እንዲሁም እስከምሽት የተልእኮ ክፍሎች ድረስ በተለያየ መንገድ እየተሰባሰቡ ነው። እነርሱ ስለ አንዳቸው ከአንዳቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ሲማሩ ብርታትን በማግኘት፣ እርሱን የሚከተሉ፣ እና የእግዚአብሔር ልጅነቱንም የመመስክሩ ሃያል እና ጽድቅ ሻለቃዎች ናቸው።

ለሰሚናሪ እና ኢኒስቲቲወት ተማሪዎች መልእክቴን ሳደርስ።

ባለፈው በልግ ወቅት ለሴሚናሪ እና ኢንስቲትዩት ተማሪዎች እና በዩታ ለሚገኙ ወላጆቻቸው በአንድ ዙሪያውን በታጠረ የመወዳደሪያ ስፍራ በነበረ መንፈሳዊ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርጌአለሁ። በዚያ መገኘታቸው ኢየሱስ ክርስቶስን ስለማወቅ እና ስለመከተል ብዙ ይናገራል። ለእነዚያ ተማሪዎች የነበረኝ ግልጽ መልክት፤ ለጌታ እኩል ጊዜን ስጡ የሚል ነበር። ትምህርታቸውን በእውነተኛ፣ በከፍተኛ ጥናት በተለይም ስለ ‘’ህያው እግዚአብሔር ልጅ’’ በማጥናት ሚዛናዊ እንዲያደርጉ መክሬአቸዋለሁ።

ዛሬም ተመሳሳይ ነገርን እጠይቃለሁ፤ በ’’ምታደርጓቸው’’ ነገሮች ዝርዝር ላይ ምንም ይሁን ምን፣ የግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት፣ እንደቤተሰብም የ ኑ፣ ተከተሉኝ፣ ጥናት፣ የቤተክርስቲያን ጥሪዎች ላይ፣ ቅዱስ ቁርባንን ስትካፈሉ፣ በቤተመቅደስ ስታመልኩ፣ እና የእግዚአብሔርን ነገሮች ስታሰላስሉ ትርፍ ጊዜን ሳይሆን እኩል ጊዜን ስጡ። ጌታችን እና አዳኛችን ሲናገር፣ “ከእኔም ተማሩ፥ … ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።” ብሏል። በቃሉ ተገኙለት። እና እኩል ጊዜን ስጡት።

ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፣ “እግዚአብሔር በህይወታችሁ እንዲያሸንፍ እንድትፈቅዱለት እማጸናችኋለሁ። ካላችሁ ጊዜ ውስጥ ተገቢውን ድርሻ ስጡት። ይህንን ስታደርጉ፣ በአዎንታዊ መንፈሳዊ ፍጥነታችሁ ላይ ምን እንደሚከሰት ልብ በሉ።”

ያንን ፍጥነት በሴሚናሪ፣ ኢንስቲትዩት፣ እና በቤተክርስቲያን ዩኒቨርሲቲዎች እየተገነባ እናያለን። በእነዚህ አካባቢዎች፣ ጌታ ቅድሚያ ያገኛል። ስለዚህ እርሱ በእያንዳንዳችን ህይወት ውስጥ ሊሆን ይገባዋል።

ሌላኛው በቤተክርስቲያን የትምህርት እድገት ማማ ላይ የምናየው የBYU–Pathway ነው። በዓለም ዙሪያ፣ ምዝገባ እስከ 75000 ደርሷል እና በፍጥነትም እያደገ ነው። አብዛኞቹ አባላት ናቸው፣ እና ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሆኑት በአፍሪካ ናቸው። Pathway በአጠቃላይ የትምህርት እድልን ስለማግኘት ነው። ኮርሶቹን ማጠቃለል ማለት የስራ እድል ማግኘት ማለት ነው፣ እና የስራ እድል ማግኘት ማለት ደግሞ ለቤተሰቦች የተሻለ ህይወት እና ጌታን ለማገልገል ተጨማሪ እድሎች ማግኘት ማለት ነው።

በአካባቢያችሁ ካሉ ሚስዮናውያን ጋር ተገናኙ።

በዩጋንዳ የካስማ መሪዎችን ባገኘሁ ጊዜ፣ አጠቃላይ የካስማ አመራሩ በBYU–Pathway እንደተመዘገቡ አውቄያለሁ። በጊዜያዊነት እና በመንፈሳዊነት ራሳችንን የምናዘጋጅ ከሆነ፣ የሰይጣንን የማያቆም ጥቃት ለመቋቋም በተጨማሪ የተዘጋጀን እንሆናለን። ሐዋርያው ጴጥሮስ እንዲህ ሲል አስጠነቀቀን፥ “በመጠን ኑሩ ንቁም፣ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና።”

በወንጌል የምስራች ዜናዎች መካከል፣ የእምነት፣ የጥርጣሬ፣ እና መልስ ያላቸው ከማይመስሉ ጥያቂዎች ጋር እየታገሉ ያሉ እንዳሉ አውቃለሁ። ወንድሞች እና እህቶች፣ መልሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከእርሱ ጋር ጀምሩ። በሕይወታችሁ ውስጥ የእርሱን እጅ ፈልጉ። እርሱን ስሙ። ‘’ልባችሁ አይታወክ፣’’ በጌቴሴማኒ ፊትመስቀሉን በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ከመሸከሙ በፊት፣እርሱ ብቻ፣ አንድያ የእግዚአብሔር ልጅ ሊያደርገው የሚችለው የሃጢያት ክፍያውን ካጠናቀቀበት በጌቴሴማኒ የመጨረሻዋ ሰዓቱ ላይ ለደቀመዛሙርቱ ይህን አለ።

እርሱ እንደሚረዳ እወቁ። እርሱ ሃጥያታችንን በሙሉ፣ ለዘለዓለም ከሰማዩ አባታችን ጋር እንኖር ዘንድ ስህተቶቻችንን፣ ስቃዮቻችንን፣ እና ክፉ የሆኑ ቀናቶቻችንን በላዩ ላይ ወስዷል። “ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ እኔ ተመልከቱ፣ አትጠራጠሩ፣ አትፍሩ፡” በማለት ተናግሯል። እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ‘’ሊያነሳችሁ’’ እና የቆሰለ ነፍሳችሁን ሊፈውስ ይችላል። እመኑት እናም ‘’ወደ ፍቅሩ ክንዶች’’ መመለሻችሁን ታፋጥናላችሁ።

የህያው ነቢያችንን ቃላት ’’በአይናችን ፊት እየተከናወነ ያለውን ታያላችሁን?? የዚህን ወቅት ታላቅነት የምናስተውልበት ዕድል እንዳያመልጠን እጸልያለሁ! በእርግጥ ጌታ ስራውን እያፋጠነ ነው። ጌታ ስራውን እያፋጠነ ነው’’ ያሉትን ማሳሰብ እፈልጋለሁ። 37 እንደ ጊዜአችን ደቀመዛሙርት ለአዳኛችን መመለስ በተዘጋጀን ጊዜ ‘’ሁራ ለእስራኤል፣’’ በማለት እንጮህ ዘንድ ይሁን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2024 (እ.አ.አ)፣ 121፤ እንዲሁም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥73; “እነሆ፣ በጊዜው ስራዬን አፋጥናለሁ።”

  2. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (እ.አ.አ)(2007), 137.

  3. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል፣” 121፤ እንዲሁም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥73፤ “እነሆ፣ በጊዜው ስራዬን አፋጥናለሁ።” ይመልከቱ።

  4. የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥5

  5. ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1838፥-1856፣ ቅጂ C-1, 1285, josephsmithpapers.org

  6. ኤተር 12፥41

  7. ‘’ቅድስና ለጌታ’’ የሚለው የተቀረጸ ጽሁፍ በእያንዳንዱ የቤተመቅደስ የውጪ ክፍል ላይ ያለ ነው። አብዛኛው ‘’የጌታ ቤት’’ የሚል ሃረግ ያለበት ነው።

  8. ራስል ኤም. ኔልሰን ፣ “ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን አርአያ መሆን፣” ኢንዛይን ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ) ፣ 114 ይመልከቱ፡፡

  9. ሜልቪል ጄ. ባላርድ፣ በሜልቪል አር.ባላርድ ፣ ሜልቪል ጄ. ባላርድ: Crusader for Righteousness (1966) (እ.አ.አ), 21284.

  10. ሜሪ ሪቻርድን፣ አስተናጋጅ፣ Church News podcast፣ ክፍል 217፣ “ሽማግሌ ደብሊው. ማርክ ባሴት እና ዴቪድ ኤን. ዌይድማን የቤተክርስቲያኗ የሚስዮናውያን ክፍል በሚስዮናዊነት ሥራ ማስፋት ሚና ላይ፣” Church News፣ ዲሴምበር 3፣ 2024 (እ.አ.አ)፣ thechurchnews.com ን ይመልከቱ።

  11. ‘’የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 36 አዲስ ሚስዮኖችን በ2024 ይፈጥራል፣’’ Newsroom.ChurchofJesusChrist.org, ህዳር 1፣ 2023 (እ.አ.አ) ይመልከቱ።

  12. መረጃው የተዘጋጀው በቤተክርስቲያን የሚሲዮን ክፍል። በ2022 (እ.አ.አ)፣ የቃል ኪዳን ጥምቀት ቁጥር ከ212፣ 172 በላይ ነበር። በ2023 (እ.አ.አ)፣ ከ251፣ 763 በላይ ጨምሯል። በ2024 (እ.አ.አ)፣ 308፣ 682 ግለሰቦች ተጠምቀዋል።

  13. ጎርደን ቢ. ሂንክሊ ሲናገሩ፤ ‘’ይህ እኛ እየተሳተፍንበት ያለው ስራ ተራ ስራ እንዳልሆነ ላስታውሳችሁ አይገባኝም። የኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ነው። የዘለዓለም አምላካችን መንግስት ነው። ይህ በምድር እየተገነባች ያለች ጽዮን ነች’’ (ለሃገራት ምልክት፣’’ ኤንዛይን፣ ህዳር 1989፣ 53)።

  14. ኦርሰን ኤፍ. ዊትኒ Life of Heber C. Kimball: ሃዋርያ፤ የብሪቲሽ ሚስዮን አባት እና መስራች (1888)፣ 276።

  15. መረጃው የተዘጋጀው በቤተክርስቲያን የሚሲዮን ክፍል።

  16. የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 6፥38 (በ ማቴዎስ 7፥23 ውስጥ፣ የግርጌ ማስታወሻ )።

  17. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፣118

  18. ታድ ዋልች፣ ‘’ወጣት ጎልማሶች እምነታቸው እየደከመ ነው ለሚለው የሃሰት ትርክት ምላሽ የሆነ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ዩኒቨርሲቲዎች የምዝገባ እድገት Deseret News፣ ህዳር 23፣ 2024 (እ.አ.አ) ይመልከቱ።

  19. ሪቻርድ ስተርዘር ጊብሰን፣ ‘’እኩል ጊዜን ስጡ፣’ ሽማግሌ ራዝባንድ ለ10,000 የሚሆኑ ታዳጊዎች እና ወጣት ጎልማሶች በተዘጋጀ መንፈሳዊ ስብሰባ ላይ አበረታትተዋል፣’’ Church News ጥቅምት 14 2024 (እ.አ.አ)።

  20. ማቴዎስ 16፥16

  21. ማቴዎስ 11፥29

  22. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “የመንፈሳዊ ፍጥነት ሃይል፣፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ) 99።

  23. ዋልችን፣ “በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ዩኒቨርስቲዎች የምዝገባ እድገት፣ ” Deseret News፣ ህዳር 23፣ 2024፣ deseret.com ን ይመልከቱ።

  24. 1 ጴጥሮስ 5፥8

  25. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “መልሱ ሁል ጊዜም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ) 127–28።

  26. ዮሐንስ 14፥27

  27. ማቴዎስ 26፥36-38 ።ይመልከቱ።

  28. ሉቃስ 6:14; ዮሐንስ 1:42።ይመልከቱ

  29. ዮሐንስ 19፥171 ኔፊ11፥333 ኔፊ 27፥14–15 ይመልከቱ።

  30. አልማ 7፥14ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥41-42 ይመልከቱ።

  31. ሙሴ 1፥39 ይመልከቱ።

  32. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥36

  33. ሞሮኒ 9፥25ን ይመልከቱ።

  34. መዝሙር 147፥3ያዕቆብ 2፥8 ተመልከቱ።

  35. ምሣሌ 3፥5ን ተመልከቱ።

  36. 2 ኔፊ 1፥15

  37. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል፣” 121፤ እንዲሁም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥73፤ “እነሆ፣ በጊዜው ስራዬን አፋጥናለሁ።” ይመልከቱ።