አጠቃላይ ጉባኤ
የቤተክርስቲያኗ ኦዲት ክፍል ሪፖርት፣ 2024 (እ.አ.አ)
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


1:44

የቤተክርስቲያኗ ኦዲት ክፍል ሪፖርት፣ 2024 (እ.አ.አ)

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቀዳሚ አመራር

ውድ ወንድሞች፣ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 120 ላይ እንደተመዘገበው በራዕይ በመመራት፣ የቀዳሚ አመራርን፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድንን፣ እና የኤጲስ ቆጶስ አመራርን ያቀፈው የአስራት አጠቃቀም መወሠኛ ሸንጎ ለቤተክርስቲያኗ ከተመደበ ገንዘብ ላይ የሚወጡ ወጪዎችን ይፈቅዳሉ፡፡ የቤተክርስቲያኗ አካላት የተመደበውን ገንዘብ በፀደቀው በጀት፣ መመሪያ እና የአሰራር ደንብ መሠረት ያከፋፍላሉ፡፡

በቂ የትምህርት መረጃ ባላቸው ሞያተኞች እና ከሌሎች የቤተክርስቲያኗ ክፍሎች እና አካላት ነፃ በሆነ ሁኔታ የተዋቀረው የቤተክርስቲያኗ የኦዲት ክፍል፣ የተሰበሰቡ መዋጮዎችን፣ ወጪ የተደረጉ ገንዘቦችን፣ እና የቤተክርስቲያኗን ሀብት መጠበቅን በሚመለከት አስተማማኝነት ያለው ኦዲት የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡

በተከናወነው ኦዲት መሠረት፣ ሁሉንም ቁሣቁሶች በሚመለከት፣ የተሰበሰቡ መዋጮዎች፣ ወጪ የተደረጉ ገንዘቦች፣ እና ለ2024 (እ.አ.አ) ዓመት የቤተክርስቲያኗ ንብረቶች፣ ቤተክርስቲያኗ ባፀደቀቻቸው በጀቶች፣ የኦዲት ልምድ እና መመሪያዎች መሠረት በአግባቡ የተመዘገቡ ስለመሆኑ የቤተከርስቲያኗ ኦዲት አስተያየት ያሣያል፡፡ ቤተክርስቲያኗ ለአባላቶቿ በበጀት ስለመኖር፣ ዕዳን ስለማስወገድ እና አስፈላጊ ለሆነ ጊዜ ስለመቆጠብ ያስተማረቻቸውን ልምዶች ትከተላለች፡፡

በአክብሮት የቀረበ፣

የቤተክርስትያኗ ኦዲት ክፍል

ጄርድ ቢ. ላርሰን

የአስተዳደር ዳይሬክተር