አጠቃላይ ጉባኤ
“እፈውሳችሁ ዘንድ … ወደ እኔ ተመለሱ“
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:3

“እፈውሳችሁ ዘንድ … ወደ እኔ ተመለሱ“

በሚመለሱት በእነዚያ በሰማይ ሃሴት እንዳለ። ለመመለስ አልረፈደባችሁም።

በአንድ ወቅት አስደናቂ በሆኑ ዛፎች በተከበበ ቤት ውስጥ እንኖር ነበር። ከመግቢያው ቀጥሎ ያማረ ዊሎው የተባለ የዛፍ አይነት ነበር። በአንድ አሳዛኝ ሌሊት ሃያል አውሎነፋስ ነፈሰ፣ እናም ይህ ዊሎው የተባለው ዛፍ ተደረመሰ። ስሮቹ ተነቅለው ወደ ውጪ ሆኖ በመሬት ላይ ወድቆ ነበር እናም ያ አሳዛኝ እይታ ነበር።

እኔም በፍጥነት የመቁረጫ መጋዝ ማሽኑን ለማስነሳት እና ዛፉን ለማገዶነት ልቆራርጠው ተዘጋጅቼ በነበርኩበት ጊዜ ጎረቤቴ ሊያስቆመኝ ፈጥኖ መጣ። እርሱም በዛፉ ተስፋ በመቁረጤ ገሰጸኝ እንዲሁም እንዳናስወግደውም አጥብቆ አሳሰበን። ከዚያም መሬት ላይ ወደ ወደቀው አንድ ቅርንጫፍ በመጠቆም ይህን ዛፍ ብናቀናው፣ ቅርንጫፎቹን ብንቆርጣቸው፣ እና ብንንከባከበው፣ ስሮቹ እንደገና ተመልሰው ያቆጠቁጣሉ በማለት ተናገረ።

የወደቀ የዊሎው ዛፍ
አንድ የዛፍ ሥር በመሬቱ ውስጥ ይቀር ነበር።

እኔም በግልጽ የወደቀ እና ችግር ውስጥ ያለ ዛፍ እንዴት ተመልሶ ሊለመልም እና ነፍስ ሊዘራ ይችላል በሚል አመነታሁ እንዲሁም ተጠራጠርኩ። እንደገና ተመልሶ የሚያድግ ቢሆን እንኳን ቀጣዩን አውሎነፋስ ሊቋቋም አይችልም በማለት ምክንያቴን አቀረብኩ። ነገር ግን ጎረቤቴ ዛፉ አሁንም ወደፊት ተስፋ እንዳለው በማወቁ፣ በእቅዱ ተስማማን።

ቅርንጫፎቹ የተመለመሉ የዛፍ ግንድ
በዛፉ ላይ የሚታዩ የማደግ ምልክቶች።

እና ውጤቱም? ከተወሰነ ጊዜ በኋላ፣ ዛፉ ስሩ መያዝ እንደጀመረ የህይወት ምልክቶችን አየን። አሁን፣ ከ12 ዓመታት በኋላ፣ ዛፉ ከጠንካራ ሥሮች ጋር ንቁ እና ህይወት የተሞላበት ሆኗል እንዲሁም ለመልክዓ ምድሩ ውበት ዳግመኛ አስተዋጸኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ንቁ እና ጤናማ ዛፍ

በዓለም ላይ ያሉትን ቅዱሳን ሳገኝ፣ ስለዚህ ዊሎው ዛፍ እና ሁሉም የጠፋ በሚመስልበት ጊዜም እንኳን ተስፋ እንዳለ አስታውሳለሁ። አንዳንዶች እንደ ዊሎው ዛፍ ሁሉ በአንድ ወቅት ጠንካራ የወንጌል ምስክርነት የነበራቸው እና ንቁዎች ነበሩ። ከዚያም፣ ለተለየ የግል ምክንያቶች፣ እነዚህ ምስክርነቶች እየደከሙ ሄደው እምነት ወደማጣት ያመራሉ። ሌሎች ከወንጌሉ አፈር አፈንግጠው በቀጫጭን ስሮቻቸው ተንጠልጥለዋል።

ይህም ሆኖ ደግሞ ደጋግሞ፣ ደቀመዝሙርነታቸውን ለማደስ እና ወደ ቤት ቤተክርስቲያናቸው ለመመለስ በመረጡ በብዙዎች ታሪክ እነሳሳለሁ። ልክ ፋይዳ እንደሌለው የማገዶ እንጨት እምነታቸውን ከማቋረጥ ይልቅ፣ ይልቁኑም ለመመለስ ለመንፈሳዊ መነቃቃት እና የፍቅር ግብዣ ምላሽ ሰጥተዋል።

በኮሪያ አንድ ከሚስዮን የተመለሰ የቤተክርስቲያን አባል የሚከተለውን ያካፈለበትን የካስማ ጉባኤ ስብሰባ ተገኝቼበት ነበር፤ ‘’እምነተቢስነቴን እና ድክመቴን ተቀብለው ወደ እኔ ለመምጣት ፈቃደኛ የሆኑ ወንድሞችን እና ለእኔ ዘወትር ደግ የሆኑ አባላትን አመሰግናለሁ። አሁንም በዙሪያዬ ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑ አያሌ ጓደኞች አሉኝ። አስገራሚ ነው፣ ነገር ግን እምነታቸው ዳግም እንዲመለስ አንዳቸው ለአንዳቸው ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ እንዳለባቸው ይናገራሉ። እኔ እንደማስበው ምናልባት ሁሉም እምነታቸውን እየናፈቁ ናቸው።”

እምነታችሁን እየናፈቃችሁ ላላችሁ ሁሉ፣ እንድትመለሱ እንጋብዛችኋለን። በድጋሚ ከቅዱሳን ጋር ብታመልኩ እምነታችሁ እንደሚጠነክር ቃል እገባላችኋለሁ።

አንድ በአፍሪካ የቀድሞ ሚስዮናዊ የነበረ ሰው፣ አንድ አረጋዊ የቤተክርስቲያን መሪ፣ በዚያን ጊዜ ቤተክርስቲያኗን ትቶ እንዲሄድ ያደረገውን ባህላዊ ወግን የተመለከተ ትምህርት በማስተማራቸው ቅር ተሠኝቶ የነበረ በመሆኑ ይቅርታን እና ምህረትን ለመጠየቅ ደብዳቤ ጻፈላቸው። እርሱም በትህትና እንዲህ ገለጸ፦ ‘’በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ከ15 ዓመታት በፊት ቅር የተሰኘሁበት ጉዳይ እጅግ ከባድ ዋጋን እንድከፍል አድርጎኛል። ብዙ ነገር አጥቻለሁ—ከምገምተው በላይ እጅግ ብዙ ነገር። በመንገዴ ላይ ፈጥሬ ሊሆን ስለሚችለው ጉዳት በጥልቀት ሐፍረት ተሰምቶኛል፣ ነገር ግን ከሁሉም ነገር በላይ ለመመለስ መንገዱን በማግኘቴ ተደስቻለሁ።’’

ያጣችሁትን ለተገነዘባችሁ ሁሉ፣ የወንጌልን አስደሳች ፍሬ አንድ ጊዜ ዳግም መቅመስ ትችሉ ዘንድ እንድትመለሱ እንጋብዛችኋለን።

በዩናይትድ ስቴትስ አንዲት እህት ለብዙ ዓመታት ከቤተክርስቲያን ርቃ ነበር። የእርሷ የመመለስ ታሪክ ከመንገዱ በሳቱ ውዶቻቸው ለሚጨነቁ ወላጆች እና ቤተሰቦች ታላቅ ትምህርት ሊሆን የሚችል ታሪክን ያካተተ ነው። እርሷም እንዲህ ጻፈች፦

‘’ከቤተክርስቲያን፣ ወንጌልን፣ እና በሂደትም ቤተሰቦቼን፣ ትቼ የሄድኩባቸውን ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ምክንያቶች ልዘረዝር እችላለሁ። ነገር ግን እነዚያ በእውነቱ ትርጉም የላቸውም። ቤተክርስቲያኗን ትቶ ለመሄድ አንድ ትልቅ ውሳኔን ብቻ አላደረግሁም — ምናልባትም ሺህ ምርጫዎችን አድርጌአለሁ። ነገር ግን ዘወትር ያወቅሁት አንድ ነገር ወላጆቼ አንድ ትልቅ ውሳኔን አድርገዋል፣ እና በዛም ጸንተዋል። እኔን ለመውደድ ወስነዋል።

“ለእኔ ሲባል ስንት እንባዎች እንደፈሰሱ፣ ስንት እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች እንዳለፉ ወይም ስንት ከልብ የሆኑ የጸሎት ምልጃዎች እንደተነገሩ ላውቅ አልችልም። እነርሱ በሰራሁት ሐጥያት አልኮነኑኝም፤ ይልቁኑም፣ እኔን ከኃጥያት እንድወጣ ለማገዝ ደረሱልኝ። እነርሱም በቤታቸው እና በቤተሰብ ስብስብ ውስጥ ጥሩ ያልሆነ አቀባበል አላደረጉልኝም፤ የትኞቹም እነዚህ ስሜቶች የራሴው ስራ ውጤቶች ናቸው። ይልቁኑም፣ እኔን መቀበላቸውን ቀጠሉ። ብርሃኔ በጊዜ ሂደት ሲደበዝዝ አስተውለው መሆን አለበት። ነገር ግን ከዚህ ቀደም የነበረው ማንነቴ ወደ ፊት ልሆን ያልኩት ማንነት ጥላ እንደነበር አውቀዋል።

‘’ከቤተክርስቲያን የራቅኩበት መንገድ ውስብስብ እንደነበረው ሁሉ፣ መመለሻ መንገዴም እንዲሁ ነበር። ነገር ግን አንድ ለመመለስ ከባድ ያልነበረው ነገር ወደ የምካተትበት ቦታ የመመለሱ ስሜት ነበር።’’

የዛሬው መልዕክቴ በተለይ በአንድ ወቅት መንፈስ ተሰምቷቸው ለነበረ ነገር ግን ዳግም በተመለሰችው በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሡስ ክኢርስቶስ ቤተክርስቲያን መመለሻ መንገድ ወይም ለእነርሡ ቦታ መኖሩን ለሚጠይቁ ነው። የወንጌል ምሥክርነት ለሌላቸው ወይም ከቤተክርስቲያኗ ለመራቅ ለተፈተኑትም ጭምር ነው።

ይህ መልእክት ፈተና አይደለም፣ እንዲሁም ኩነኔም አይደለም። ወደ መንፈሳዊ ቤታችሁ ስትመለሱ አቀባበል ለማድረግ በፍቅር እና በልባዊ ፍላጎት የቀረበ ግብዣ ነው።

ከአዳኛችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የቀረበውን ይህንን የፍቅር ግብዣ እና አስደናቂ የተስፋ ቃል አሁን በምትሰሙበት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት እንዲሰማችሁ ጸልያለሁ።

እፈውሳችሁ ዘንድ ለኃጥያታችሁ ንስሃ ገብታችሁ እናም ተለውጣችሁ አሁን ወደ እኔ አትመለሱምን?”

በጸጥታ እና በትህትና ኢየሱስ ቃል የገባላቸውን ፈውስ በመፈለግ፣ ብዙዎች በየሳምንቱ ወደ ደቀመዝሙርነት እና ወደ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ እየተመለሱ ለአዳኙ ግብዣ መልስ በመስጠት ላይ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ከሚዘዋወረው ትርክት በተቃራኒም፣ ወጣቶቻችን እስከዛሬ ታይቶ በማያውቅ ቁጥር ጠንካራ ሆኖ መቆየትን እየመረጡ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው እምነት እያደጉ እንደሆነ ነው።

በቅፍርናሆም የነበሩ የኢየሱስ ተከታዮች ትምህርቱ ከባድ እንደሆነ አግኝተውት እና ለመሄድ በመረጡ ጊዜ፣ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘወር በማለት እንዲህ ሲል ጠየቀ፣ ‘’“እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?”’’

የራሣችንን የግል የፈተና ጊዜዎች በተጋፈጥን ጊዜ እያንዳንዳችን ልንጠይቀው የሚገባው ጥያቄ ይህ ነው። ለጌታ የመለሰው የጴጥሮስ መልስ ጊዜ የማይሽረው እና የሚያስተጋባ ነው፤ “ጌታ ሆይ፣ ወደ ማንስ እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ህይወት ቃል አለህ።’’

ስለዚህ ወደ እርሱ እንድትመለሱ አዳኙ ያቀረበውን ግብዣ ባሰባችሁ ጊዜ፣ ከዊሎው ዛፉ ታሪክ ምን መማር ትችላላችሁ?

  1. የመመለሱ መንገድ አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ወይም የሚመች አይደለም፣ ነገር ግን ዋጋ ያለው ነው። የእኛ ዊሎው ዛፍ ዳግም ተመልሶ በቆመ ጊዜ፣ ሁሉም ቅርንጫፎቹ ተቆርጠው ነበር። የሚያምር አልነበረም። አሮጌውን መንገድ ባቋረጥን ጊዜ እና ከትእቢት በተላቀቅን ጊዜ እኛም እንዲሁ በቀላሉ የመጠቃት ስሜት ሊሰማን ይችላል። እምነታችሁን በኢየሱስ እና በወንጌሉ ባደረጋችሁ ጊዜ—ግንዱ እና ስሮቹ—ለመመለስ የመጀመሪያውን እርምጃ ለመውሰድ ተስፋ እና ብርታትን ይሰጧችኋል።

  2. የእኛ ዊሎው ዛፍ የቀድሞ ብርታቱን እና ውበቱን ዳግም እንዲያገኝ አያሌ ዓመታት ወስደውበት ነበር። አሁን ከቀድሞው ይልቅ ብርቱ እና ይበልጥ ያማረ ነው። እምነታችሁ እና ምስክርነታችሁ እንዲሁ ባደጉ ጊዜ ትእግስተኞች ሁኑ። ይህ የሚያጠቃልለው ‘’በእነዚህ ዓመታት ሁሉ የት ነበርክ ወይም የት ነበርሽ?’’ በመሳሰሉት በድንገት በሚሰነዘሩ አስተያየቶች ያለመከፋትን ነው።

  3. ያለ ተከታታይ ጥንቃቄ እና እንክብካቤ የዊሎው ዛፉ በጭራሽ ሊሰነብት ባልቻለ ነበር። በየሳምንቱ ከቅዱስ ቁርባኑ ጠረቤዛ በተመገባችሁ እና በጌታ ቤት ባመለካችሁ ጊዜ እምነታችሁን እና ምስክርነታችሁን ታፋፋላችሁ።

  4. የዊሎው ዛፍ ቅርንጫፎቹ እና ቅጠሎቻቸው እንደገና እንዲበቅሉ የፀሐይ ብርሃን እንደሚያስፈልገው ሁሉ፣ ለመንፈስ ስሜት እና ምስክር ስሜት የሚሰማችሁ ስትሆኑ ምስክርነታችሁ ያድጋል። የራሱን ተሳታፊ ያልሆነ አባል ስለመሆን እንዲህ ከገለጸው አሙሌቅ እንማን፣ “ብዙ ጊዜ ተጠርቼ [አልሰማሱም]።”

  5. ጎረቤቴ የዊሎው ዛፉ ዳግም እንደገና ምን እንደሚሆን አውቆ ነበር። ስለዚህም ጌታ መለኮታዊ ብቃታችሁን እንዲሁም እምነታችሁ እና ምስክርነታችሁ ምን እንደሚሆን ያውቃል። እርሱ ፈጽሞ በእናንተ ተስፋ አይቆርጥም። በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካይነት፣ የተሰበረው ሁሉ ሊፈውስ ይችላል።

በሚመለሱት በእነዚያ በሰማይ ሃሴት እንዳለ እመሰክራለሁ። እናንተ ትፈለጋላችሁ፣ እና እናንተ ተወዳችኋል። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እንደሆነ እንዲሁም ወደ እርሱ የተመለሱትን ሁሉ እንደሚባርከን እመሰክራለሁ። የእርሱ የምህረት ክንዶች አልታጠፉም ነገር ግን ለእናንተ የተከፈቱ እና የተዘረጉ ናቸው። ለመመለስ የረፈደ አይደለም። በፍቅር በሞላው ልባችን ፣ ወደ ቤት እንጋብዛችኋለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ይህ ለዋሽንግተን ስፖካን ሚስዮን የሚስዮን ቤት የነበረ እና አሁንም ሆኖ ያለ ነው። የዊሎው ዛፍ ፎቶዎች በባለቤቴ፣ ጃኪ የተወሰዱ ናቸው።

  2. 3 ኔፊ 9፥13። ንሰሃ ለመግባት የተደረገው ግብዣ ሁላችንንም የሚመለከት መሆኑን አስተውሉ። “1ኛ ዮሐንስ 1፥8 (”ሃጢያት የለብንም ብንል፣ እራሳችንን እናታልላለን፣) እንዲሁም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ በየቀኑ ንሰሃ ስለመግባት የየስጡትን ግብዣ፣ ‘’የመንፈሳዊ ፍጥነት ሃይል፣’’ ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 98ን ይመልከቱ።

  3. See Quentin L. Cook, “Facing Life and Faith Challenges” (worldwide devotional for young adults, Nov. 14, 2023), Gospel Library: “’ለመረጃ ያህል፣ በስፋት ሲሰራጭ እንደነበረው ካለፈው ይልቅ ታዳጊዎች እና ወጣት ጎልማሶች በንቃት የማይሳተፉ ወይም ቤተክርስቲያንን በከፍተኛ ቁጥር እየተዉ አይደለም። ሊያገለግሉ የተጠሩ ሚስዮናውያን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። እየተነሳ ላለው ትውልድ የቤተክርስቲያን ተሳትፎ በፐርሰንት በከፍታ እያመራ እንደሆነ ያሳያል። በተጨማሪም፣ ኢንስቲቲዩት እየተካፈሉ ያሉ የወጣት ጎልማሶች ቁጥርም እንዲሁ ጨምሯል።

    በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን እና ክላርክ ጂ. ጊልበርት፣ ‘’ቪድዮ፦ ሽማግሌ ክሪስቶፈርሰን ትርክትን ተጠራጠሩ፣ መንፈስ በወጣቱ እየሰራ ነው አሉ፣” Church News [የቤተክርስቲያን ዜናዎች]፣ ታህሳስ 13 2024 (እ.አ.አ)።

  4. ዮሀንስ 6፥67

  5. ዮሀንስ 6፥68

  6. አልማ 5፥28 ተመልከቱ።

  7. ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “ስሮቹን ተንከባከቡ፣ እና ቅርንጫፎቹ ያድጋሉ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2024 (እ.አ.አ)፣ 102፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ እና የእርሱ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት የምስክርነታችን ስር ናቸው። ሌሎች ነገሮች ሁሉ ቅርንጫፎች ናቸው። … ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን ምስክርነት ስናሳድግ፣ አንዳንድ ጊዜ ቅርንጫፎቹ ስሮች ይመስሉን ይሆን ብዬ አስባለው። … ሥሮቹን ተንከባከቡ ከዚያም፤ ቅርንጫፎቹ ያድጋሉ።”

  8. አልማ 32፥41 ይመልከቱ።

  9. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ)፣ 118–20። እናም በቤተመቅደስ ውስጥ ያላችሁ አገልግሎት እና አምልኮ ስለ ሰለስቲያል እንድታስቡ ይረዳችኋል።

    ደግሞም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “በክህነት ቁልፎች ስጦታ ደስ ይበላችሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ)፤ 3 ኔፊ 27፥9–11 ይመልከቱ፦ “ቃል ይእምገባላችሁ እነሆ። በቤተመቅደሥ አዘወትራችሁ የማምለክን ያህል በበለጠ ሁኔታ የብረቱን በትር አጥብቃችሁ ለመያዝ የሚረዳችሁ ምንም ነገር የለም። የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን እና የእርሱን የኃጢያት ክፍያ ምሥክርነት የበለጠ የሚያጠናክርላችሁ ወይም የእግዚአብሔርን ድንቅ ዕቅድ የበለጠ እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁ ምንም ነገር የለም።

  10. አልማ 32፥28 ይመልከቱ።

  11. አልማ 10፥6

  12. ፓትሪክ ኪረን፣ ‘’የእግዚአብሔር ሀሳብ እናንተን ወደ ቤቱ ማምጣት ነው፣’’ ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ) 87 ይመልከቱ።

  13. ጄፍሪ አር. ሆላንድ፣ “የተሰበሩ ነገሮችን መጠገን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2006 (እ.አ.አ)።

  14. ሉቃስ 15፥11-32ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥13ን ይመልከቱ።

  15. ዮሐንስ 15፥9 ይመልከቱ።

  16. አልማ 5፥33 ይመልከቱ።

  17. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2024 (እ.አ.አ) ይመልከቱ፦ ’አምልኮአዊ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ትሆኑ ዘንድ በጣም የዘገየ አይደለም፣ እንዲሁም በጣም አልረፈደም። ከዚያም የኃጢያት ክፍያውን በረከቶች ሙሉ በሙሉ ታገኛላችሁ።’’

    ደግሞም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የመንፈሳዊ ፍጥነት ሃይል፣” (99)፦ ‘’ከቃል ኪዳኑ መንገድ በጣም እንደራቃችሁ ወይም የመመለሻ መንገድ እንደሌላችሁ ከተሰማችሁ፣ በቀላሉ ያ እውነት አይደለም።’’