አምልኮ
ለእኔ እና ለአንተ እግዚአብሔርን ማምለክ ምን ማለት ነው?
“ኢየሱስም በይሁዳ ቤተልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
“ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በማለት ተናገሩ።.”
ሰብአ ሰገልም፣ አንዳንድ ጊዜ እንደዛ በመባል የሚታወቁት፣ መሲሑን ለማግኘት እና ለማምለክ በመፈለግ ጥበበኞች ነበሩ። ለእነርሱ፣ አምልኮ ማለት በእርሱ ፊት መውደቅ እና የወርቅ እና የከበሩ ሽቶዎችን ከርቤና እጣን ስጦታ መስጠት ማለት ነበር።
ለእኔ እና ለአንተ እግዚአብሔርን ማምለክ ምን ማለት ነው?
ስለ አምልኮ ስናስብ፣ ሀሳቦቻችን በግል እና በቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ውስጥ ለሃይማኖታዊ መሰጠት ወደ ምናሳይባቸው መንገዶች ይመሩናል። የሰማይ አባታችንን እና የተወደደውን ልጁን፣ አዳኛችንን፣ የማምለክን ጉዳይ በጥንቃቄ ሳጤነው፣ አራት ጽንሰ-ሐሳቦች ወደ አእምሮዬ መጡልኝ፡ በመጀመሪያ፣ የእኛ የአምልኮ አካል የሆኑ ተግባሮች፤ ሁለተኛ፣ በአምልኳችን ውስጥ ያሉ ጠባዮችና ስሜቶች፤ ሦስተኛውየአምልኮታችን ገለልተኝነት፤ እና አራተኛ፣ የምናመልካቸውን ቅዱስ መለኮቶችን መምሰል አስፈላጊነት ነው።
መጀመሪያ፣ የእኛ የአምልኮ አካል የሆኑ ተግባሮች
በጣም ከተለመዱት እና አስፈላጊ ከሆኑት የአምልኮ ዓይነቶች አንዱ በተቀደሰ ቦታ ላይ መሰብሰብ እና የአምልኮ ተግባራትን ማከናወን ነው። እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- “ከአለም ነገሮች ራስህን ንጹህ እና ነውር የሌለበት ለማድረግ ወደ ጸሎት ቤት ሂድ፣ እናም በቅዱስ ቀኔም ቅዱስ ስርዓቶችህን አቅርብ።” ይህ፣ በእርግጥ፣ የጸሎት ቤቶችን ለመገንባት ቀዳሚ ተነሳሽነታችን ነው። ነገር ግን አስፈላጊ ከሆነ፣ ቡራኬ ባልተደረገበትም ስፍራ ላይ እንኳ በተወሰነ ደረጃ ቅድስናን ስራ ላይ ብናውል ያም ቦታ የአምልኮ ስፍራ ይሆናል።
በጣም አስፈላጊው ነገር በጌታ ቀን ስንሰበሰብ የምናደርገው ነገር ነው። እርግጥ ነው፣ አቅማችን በቻልነው ልክ፣ አግባብ ባለው መልኩ ነው እንለብሳለን—ከልክ ያለፈም ሳይሆን፣ ስርዓት ያለው ለአምላክ ያለንን አክብሮትና ከበሬታን ለማሳየት ነው። ምግባራችንም በተመሳሳይ በአክብሮትና በከበሬታ የተሞላ ነው። በጸሎት በመተባበር እናመልካለን፤ መዝሙር በመዘመር እናመልካለን (ዝማሬውን ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን አብረን በመዘመርም ጭምር)፤ እርስ በርሳችን በመምራት በመማር እናመልካለን። ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “በዚህ በጌታ ቀን ቁርባንህን [ማለትም፣ ‘መስዋዕትህን… የጊዜ፣ መክሊት ወይም ገንዘብ፣ ለእግዚአብሔርና ለሰው ልጆች አገልግሎት አውለው’]እናም መስዋዕትህን እና ቅዱስ ቁርባንህን ለወንድሞችህና በጌታ ፊት ኃጢአትህን በመናዘዝ ለልዑልህ ለማቅርብ አስታውስ።” በአንድ ላይ የምንሰበስበው ለመዝናናት ወይም ለማዝናናት አይደለም—ለምሳሌ፣ እንደ መዝሙር ኦርኬስታራ — ነገር ግን እርሱን ለማስታወስ እና በወንጌሉ “ይበልጥ ፍጹም በሆነ መንገድ ለመማር ነው።
በቅርቡ በተደረገው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ፣ ሽማግሌው ፓትሪክ ኪሮን እንዳስታወሰን ከሆነ፣ “በሰንበት ቀን የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ የምንሰበሰበው እንዲሁ ለመታደም እና እንደ እለታዊ ዝርዝር ተግባር እያጣራን እንድናልፍ አይደለም። በአንድ ላይ የምንሰበሰበው ለአምልኮ ነው። በሁለቱ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። መታደም ማለት በቦታው መገኘት ማለት ነው። ነገር ግን አምልኮ ማለት ደግሞ ታስቦበት የሚደረግ የሙገሳ እና እኛን በሚለውጥ መንገድ አምላካችንን መውደድ ማለት ነው!”
ሰንበቶቻችንን ለጌታ እና ለእርሱ ዓላማው ማድረግ በራሱ አምልኮ ነው። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት፣ የወቅቱ ሽማግሌ ራስል ኤም. ኔልሰን እንደተረዱት፦ “ሰንበትን እንዴት ቅዱስ እናደርጋለን? ገና በለጋ ዕድሜዬ፣ በሰንበት ቀን መደረግ ያለባቸውንና የሌለባቸውን ነገሮች ዝርዝር ያዘጋጁትን የሌሎችን ሰዎች ሥራ አጠናሁ። በሰንበት ምግባሬ እና አመለካከቴ በእኔ እና በሰማይ አባቴ መካከል ምልክት መሆኑን ከቅዱሳት መጻህፍት የተማርኩት በኋላ ነበር [ ዘጸአት 31፥13፤ ተመልከቱ። ሕዝቅኤል 20፥12፣ 20] በዚህ ግንዛቤ፣ ከአሁን በኋላ የሚሰሩ እና የማይሰሩ ዝርዝሮች አያስፈልጉኝም። አንድ ተግባር በሰንበት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ውሳኔ ለማድረግ ስፈልግ፣ ‘ለእግዚአብሔር ምን ዓይነት ምልክትን ልሰጠው እፈልጋለሁ?’ ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ።”
በጌታ ቀን ላይ አምልኮ በኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ የኃጢያት ክፍያ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት በተለየ ምልክት ተደርጓል። ትንሳኤውን በተገቢው እና በልዩ ሁኔታ በፋሲካ እናከብራለን፣ ግን ደግሞም ሁልጊዜ ትንሳኤውን ጨምሮ፣ በየሳምንቱ የኃጢያት ክፍያው አርማ ቅዱስ ቁርባኑም፣ ስንካፈልም ጭምር። ንስሃን ለሚገቡት፣ ቅዱስ ቁርባንን መካፈል የሰንበት አንዱ የአምልኮ ድምቀት ነው።
እንደ “የክርስቶስ አካል” በጋራ ማምለክ እና እርስ በርሳችን ስንማማር፣ ስናገለግል እና ስንደጋገፍ ልዩ የሆነ ሃይል እና ጥቅሞች አሉት። የሚገርመው፣ አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደሚያመለክተው መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ሙሉ በሙሉ ግላዊ አድርገው የሚመለከቱ ሰዎች ለመንፈሳዊ እድገት ቅድሚያ የመስጠት ዕድላቸው አነስተኛ ነው፣ ወይም እምነታችን በጣም አስፈላጊ ነው ለማለት ወይም ከእግዚአብሔር ጋር አዘውትረው የማምለክ ጊዜን የማግኘት ዕድላቸው አነስተኛ ነው። እንደ አንድ ማሀብረ ቅዱሳን በአምልኮ እና በእምነት እርስ በርሳችን እንበረታታለን።
ይህም ሆኖ በግልም ሆነ በቤታችን የምናደርገውን የዕለት ተዕለት የአምልኮ ሥርዓት መርሳት የለብንም። አዳኝ እንደሚያስታውሰን፣ “ነገር ግን፣ በሁሉም ቀናት እና በሁሉም ጊዜያት ስእለትህም በፅድቅ ይቅረብ።” አንዲት እህት በጥበብ እንዲህ ብላለች፣ “ትንንሽ ልጆቹን ወደ ህይወታችን ከመቀበል እና እነሱን መንከባከብ እና ለእነርሱ ያለውን እቅድ ከማስተማር የበለጠ ጥልቅ የሆነ እግዚአብሔርን የማምለክ መንገድ ማሰብ አልችልም።
አልማ እና አሙሌቅ ከምኩራቦቻቸው የተከለከሉትን ዞራማውያንን በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁል ጊዜም እናም በየትኛውም ቦታ ቢሆኑ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አስተምሯቸዋል።” ጸሎት እንደ አምልኮ እንደሆነ ተናገሩ፦
“ነፍሳችሁን በእልፍኞቻችሁ፤ እናም በሚስጥር ቦታዎቻችሁ እንዲሁም በምድረበዳው አፍስሱ።
አዎን፣ እናም ወደ ጌታ በማትጮኹበት ጊዜ፣ ልባችሁ ለደህንነታችሁና፣ ደግሞ በዙሪያችሁ ላሉት ደህንነት ባለማቋረጥ በፀሎት ወደ እርሱ በመትጋት ሙሉ ይሁን።”
ቅዱሳት መጻሕፍትን ስለመመርመር፣ ስለ ክርስቶስ መመስከር፣ ስለ በጎ አድራጎት ተግባራት እና አገልግሎት፣ መንፈስ ቅዱስን ስለ መቀበል እና በየቀኑ በምስጋና ስለ መኖር ተናግረዋል። “በየቀኑ በምስጋና መኖር” የሚለውን ሃሳብ አስቡበት። ይህም ሁለተኛውን ሀሳቤን ያቀርባል፦
በእኛ አምልኮ ውስጥ የምንወርሳቸው ጠባዮች እና ስሜቶች
ለእግዚአብሔር ምስጋናን መግለጽ እና መስጠት፣ በእውነቱ፣ አምልኮን እንደ አንድ ተጨማሪ ግዴታ ከመመልከት በተቃራኒ በሃሴት የመታደስን ስሜት የሚያመጣ ነው።
እውነተኛው አምልኮ እግዚአብሔርን መውደድ እና ልናቀርበው ከምንችለው በላይ ውድ ስጦታ የሆነውን ፈቃዳችንን ለእርሱ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው። ኢየሱስ ከህግ ሁሉ የመጀመሪያው ትእዛዝ የትኛው እንደሆነ ሲጠየቅ፣ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም እና በፍጹም አሳብህም ውደድ” ነው ብሎ መልሷል። ታላቁ ትእዛዝ ብሎ ጠራው።
ይህ ኢየሱስ እራሱ አብን የሚያመልክበት ምሳሌ ነበር። ሕይወቱና የኃጢያት ክፍያው ለአብ ክብር የተሰጥ ነበር። በማይታሰብ መከራና ሀዘን መካከል የኢየሱስን የሚያሳዝን ልመና እናስታውሳለን፡- “አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።”
አምልኮ ማለት ይህንን ፍጹም ምሳሌ ለመከተል መጣር ማለት ነው። በዚህ አካሄድ በአንድ ጀምበር ፍጽምና አናገኝም፤ ነገር ግን በእያንዳንዱ ቀን “የተሰበረ ልብና የተዋረደ መንፈስን ለእርሱ መሥዋዕት ካቀረብንለት” እንደገና በመንፈሱ ያጠምቀናል እና በጸጋው ይሞላናል።
ሶስተኛ፣ የአምልኮታችን ግለኛነት
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የመጀመሪያ ክፍል፣ ጌታ ይህንን የአለምን ክስ እንዲህ ብሎ ተናግሯል፡-
“ከስርዓቴ እርቀዋል፣ እናም ዘለአለማዊ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና፤
“ጽድቁን ለመመስረት ጌታን አይፈልጉም፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው በገዛ መንገዱ፣ እናም ቁሳቁሱ የጣኦት በሆነው፣ አምሳያውም የአለም በሆነው፣ አርጅቶም በባቢሎን በሚጠፋው፣ እንደ አምላኩ ምስል ይጓዛል።”
ሌሂ እና ቤተሰቡ ኢየሩሳሌምን ለቀው ከወጡ ብዙም ሳይቆይ ወደ ባቢሎን በምርኮ የተወሰዱትን የሦስቱን አይሁዳውያን ወጣቶች ማለትም የሃናንያ፣ ሚሳኤል እና አዛርያን ምሳሌ ማስታወስ ለእኛ መልካም ነው። ንጉሥ ናቡከደነፆር ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ብሎ ጠራቸው። በኋላ፣ እነዚህ ሦስቱ ናቡከደነፆር ያቆመውን ምስል ለማምለክ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ ወደሚነድድ እቶን እንዲጣሉ አዘዘ፣ “ከእጄ የሚያድናችሁስ አምላክ ማን ነው?” አላቸው።”
ደፋር መልሳቸውን ታስታውሱ ይሆናል፦
“በድፍረት የሰጡትን መልስ ታስታውሳላችሁ:- “የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ!
“ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።”
የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፥ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው። ናቡከደነፆርም መልሶ እናም እዲህ አለ፣ “ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን … የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ።” በያህዌ ነፃ አውጪነት ታምነው ነበር፤ “ካልሆነ ግን” ማለትም፣ እግዚአብሄር በጥበቡ ሞታቸውን ባይከለክለውም እንኳ ለእርሱ ታማኝ ሆነው ይቀጥላሉ።
ከአብና ከወልድ አምልኮ ቅድሚያ የሚሰጠው ማንኛውም ነገር ጣዖት ይሆናል። እነዚያ እግዚአብሔር የእውነት ምንጭ መሆኑን የሚቃረኑ ወይም ከእርሱ ጋር ምንም ዓይነት ተጠያቂነትን የሚክዱ፣ በተጨባጭም ራሳቸውን አምላካቸው አድርገው ይለውጣሉ። ከሚቀድመው ከመለኮታዊ መመሪያ ይልቅ ቅድሚያ ለፖለቲካዊ ፓርቲ ወይም ዓላማ ታማኝነትን የሚሰጥ ሰው ጣኦትን ያመልካል። እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚጥሩ ነገር ግን በማስመሰል ትእዛዛቱን የማይጥብቁ እንኳን በራሳቸው መንገድ እየሄዱ ነው፡- “በከንፈራቸው ወደ እኔ ይቀርባሉ፣ ልባቸው ግን ከእኔ የራቀ ነው።” የምናመልከው “ብቻውን እውነተኛ አምላክና [እርሱም] የላከው ኢየሱስ ክርስቶስን” ብቻ ነው።”
በመጨረሻም፣ እንደ አብና ወልድ የመምሰል አስፈላጊነት
በመጨረሻም፣ የህይወታችን አኗኗራችን ምናልባት የተሻላ፣ እውነተኛው የአምልኮ መንገድም ይሆናል። ታማኝነታችንን ማሳየት ማለት የአብ እና ወልድ ባህሪያዎችን እና ማንነታቸውን በራሳችን ውስጥ ማዳበር ማለት ነው። ምናልባትም፣ እንደ አባባሉ ከሄድን፣ አንድ ነገርን ለመምሰል መጣር ማለት ለዛ ነገር ያለን አድናቆት ከበሬታ መግለጫ ነው፣ ስለዚህ ስለ እግዚአብሄር አምላክነት ስንገልጽ፣ እርሱን ለመምሰል መጣር የከበረ እውነተኛ አምልኮ ነው። ይህ የሚያሳየው፣ በግላችን በንቃት ቅድስናን ለማግኘት የምናደርገውን ጥረት ነው። ነገር ግን ይበልጥ ክርስቶስን መምሰል የአምልኮታችን ተፈጥሯዊ ውጤትም ነው። ቀደም ሲል ስለ ማምለክ የተጠቀሰው የሽማግሌ ኪሮን ንግግር ሃሳብ “በሚለውጥ መንገድ” የሚለው ጠቃሚ ነገር ነው። እውነተኛ አምልኮ ለውጥ ያመጣል።
ይህ የቃል ኪዳኑ አንዱ ውብ መንገድ ነው—የአምልኮ፣ የፍቅር እና ለእግዚአብሔር ታማኝ የመሆን መንገድ። ወደዚያ መንገድ የምንገባው በጥምቀት፣ የክርስቶስን ስም በእኛ ላይ ለመውሰድ እና ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ቃል በመግባት ነው። የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ እንቀበላለን ያም፣ የአዳኙን የጸጋው መልእክተኛ ንስሐ ስንገባ የሚቤዠን እና ከኃጢአት የሚያነጻን ነው። በመወከል እርሱን እያመለክን ነን ማለት እንችላለን።
በጌታ ቤት እኛን የበለጠ የሚቀድሱን ተጨማሪ የክህነት ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ይከተላሉ። የቤተመቅደስ ተግባሮች እና ስነ ስርዓቶች ከፍ ያለ የአምልኮ ይዘትን ይመሰርታሉ።
ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን በዚያ ላይ አጽንዖት ሰጥተዋል “በክህነት ስነስርዓቶች ውስጥ የሚሳተፉ ወንድ እና ሴት ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖችን የገቡ እና የሚጠብቁ የእግዚአብሔርን ኃይል በቀጥታ ማግኘት ይችላሉ።” ይህ ለማገልገል እና ለመባረክ የምንቀበለው ሀይል ብቻ አይደለም። ያም እኛን ለማጥራት እና ለማንፃት በውስጣችን የሚሰራው መለኮታዊ ሃይልም ጭምር ነው። በቃል ኪዳኑ መንገድ ስንጓዝ፣ የሚቀድሰው “እግዚአብሔርን የመምሰል ኃይል” በእኛ ውስጥ ይገለጣል።
እንደ ጥንቶቹ ኔፋውያን እና ላማናውያን፣ “በኢየሱስ እግር ስር ወድቀን … እናመልከው።” ኢየሱስ ባዘዘን መሠረት “ወድቀን ለአብ በወልድ ስም አመለክን።”29 መንፈስ ቅዱስን እንቀበል እና ልባችንን ለእግዚአብሔር እናስረክብ፣ ከእርሱ በቀር ሌሎች አማልክቶች የሉንም፣ እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት፣ በራሳችን ህይወት የሱን ባህሪ እንከተል። ይህን ስናደርግ የአምልኮን ደስታ እንደምናጣጥም እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።