ለህይወት ዋጋ መስጠት
ሕይወት፣ የአባታችን ፍጹም ዕቅድ በጣም ውድ የሆነ ክፍል ነው፣ ስለዚህም በእርሱ አዋጅ ህይወትን እናከብራለን እናም ሕይወትን እንጠብቃለን።
አዳኙ፣ “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ” በማለት አስተምሮናል።
በዩታ የሚኖር አንድ ኤጲስ ቆጶስ በእርሡ አጥቢያ ውስጥ ለአንዲት ወጣት ሴት እና ለቤተሰቧ እየተሰጠ ስላለው በርካታ ፍቅር በቅርቡ አካፍለውኛል። በተደረጉላቸው ተከታታይ የሆኑ አስደሳች ዝግጅቶች ወላጆቹ ወደ አዳኙ እና ወደ ቤተክርስቲያኗ ለመመለስ ወሰኑ። ከቤተክርስቲያኗ ርቀው በነበሩበት ወቅት፣ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የምትገኘው ልጃቸው ከአንድ ወጣት ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምራ ነበር። ይህች ውድ ሴት ልጅ ሙሉ ለሙሉ መሣትፍ ስትጀምር በወጣት ሴቶች የምሥክርነት ስብሰባ ላይ የሠማይ አባቷ ከፍተኛ ፍቅር ተሰማት። ስለዚህም የበለጠ በትእዛዛቱ ለመኖር ወሰነች። እንዲህ ስትል ጽፋለች፣ “ከኤጲስ ቆጶሴ ጋር የንስሐ ሂደቱን ጀመርኩኝ።”
ብዙም ሳይቆይ ታመመች። በፃፈችው ደብዳቤ፣ ያደረኩት ምርመራ ነፍሰ ጡር እንደነበርኩ አሳየ… ። ማልቀስ ጀመርኩ።… አባቴ በክንዶቹ እቅፍ አደረገኝና ሁሉም ነገር እንደሚስተካከል አረጋገጠልኝ። የወንድ ጓደኛዬ… ህፃኑን እንዳስወርድ ጠየቀኝ። እኔም እምቢ አልኩኝ።”
እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መንከባከብ
እንዲህ ስትል ትቀጥላለች፦ “ከአጥቢያው ቤተሰባችን ብዙ ፍቅር እና ድጋፍ አግኝቻለሁ። እጅግ በጣም ብዙ ነበር። [የእኔ] ኤጲስ ቆጶስ እና የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንት ፍቅራቸውን እና ድጋፋቸውን ለማሳየት ከዚህ በላይ ሄደዋል። … የጌታ እጅ እኔን እና ቤተሰቤን ሲመራ አይቻለሁ። … እኔ እንዳለኝ ዓይነት አጥቢያ ሁሉም ሰው የሚያስፈልገው ቤተሰብ ነው፣ በተለይ እንደእኔ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ላለች ወጣት ሴት።”
እርሷና ቤተሰቧ እና የአጥቢያው ቤተሰቧ ባለፈው የካቲት ወር ልጇን በፍቅር ተቀብለዋል።
ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፥ “የጌታ እውነተኛ እና ህያው ቤተክርስቲያን ምልክት ቢኖር፣ ሁልጊዜም ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጆች እና ለቤተሰቦቻቸው፣ እርሱ [በፍቅራዊ ደግነት እንዳገለገለው] የሚደረግ የተደራጀ፣ የተመራ የአገልግሎት ጥረት ነው።
ጻድቃዊ ምርጫዎችን ለማድረግ መርዳት
አንዲት ነጠላ ሴት ያላሰበችበትን ልጅ ልትወልድ እንደሆነ ስታውቅ፣ የጤና ጉዳዮች፣ የመንፈስ ጭንቀት፣ እፍረት፣ ስለገንዘብ ማሠብ፣ ስለትምህርት ማሠብ፣ ትዳር የማግኘት ሥጋቶች እንዲሁም በህመም እና ግራ በመጋባት ጊዜ ያልተሣኩ ህልሞች የሚያስከትሉት ሀዘን አሳቢ የሆነች ሴት ጥልቅ ህመምን እና ጸጸትን የሚያስከትል እርምጃ እንድትወስድ ይገፋፋታል።
ፅንስ ከማስወረድ ወይም በዛ ከመሳተፍ ከባድ ህመም እና ጸጸት ላጋጠማችሁ ይህን ለምታዳምጡ ሁሉ እባካችሁ አስታውሱ፣ “ያለፈውን መለወጥ የማንችል ቢሆንም እግዚአብሔር ያለፈውን መፈወስ ይችላል።” በትሑት ልብ እና በንስሐ ወደ እርሱ ስትመለሱ በእርሡ የሃጢያት ክፍያ ፀጋ ተአምር ይቅርታ ሊገኝ ይችላል።
ሁለት ቃላት ብዙውን ጊዜ ከሥጋዊ ውልደት ቅድስና ጋር የተያያዙ ናቸው፦ ሕይወት እና ምርጫ። ሕይወት፣ የአባታችን ፍጹም ዕቅድ በጣም ውድ የሆነ ክፍል ነው፤ ስለዚህም በእርሱ አዋጅ ህይወትን እናከብራለን እናም እንጠብቃለን፤ እንዲሁም የተፀነሠ ህይወት እንዲቀጥል ማድረግን እንመርጣለን። የስነምግባር ምርጫ ሥጦታን ከፍ አድርገን እንመለከታለን፣ እንዲሁም ዘለአለማዊ ደስታን የሚያመጡ ምርጫዎችን፣ በእግዚአብሔር የተፈቀዱ የጽድቅ ምርጫዎችን እናጠናክራለን።
አንዲት ሴት እና አንድ ወንድ እንዲህ ያለ አስቸጋሪ ጊዜ ሲገጥማቸው፣ በቃላቶቻችን፣ በእጆቻችን፣ እና በልቦቻችን የአዳኙ ፍቅር እንዲሰማቸው ለመርዳትእና፣ ፕሬዚዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ እንደተናገሩት፣ “እያዩ እንደሆነ ከሚያስቡት” ወደ “እስካሁን ማየት ወዳልቻሉት” መንፈሳዊ ዓይኖቻቸውን እንዲከፍቱ በመርዳት—በመንፈሳዊ፣ በስሜት እና በገንዘብ በመደገፍ—በአንድነት እናገለግል።
የሟች ህይወት ትምህርት
ፕሬዚዳንት ዳልን ኤች. ኦክስ እንዲህ ብለዋል፦ “ፅንስ ስለማስወረድ ያለን አመለካከት ሥጋዊ ህይወት መቼ እንደሚጀምር በተገለጠው እውቀት ላይ የተመሰረተ አይደለም። ሁሉም የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች ለታላቅ ዓላማ ወደዚህ ምድር መምጣት አለባቸው፣ እንዲሁም ያ ግለሠባዊ ማንነት የጀመረው ከመፀነሱ ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሆነና በዘለዓለምም ሁሉ እንደሚቀጥል ባለን ዕውቀት ላይ የተመሠረተ ነው።”
በቀዳሚ አመራር እና በአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን በኩል ስለፅንስ የተነገረው የጌታ ቃል የተላያየ ሆኖ አያውቅም፣ እንዲም በየዘመናቱ የነበሩትን የነቢያትን ቃል ያስተጋባል፣ ይህም ጌታ ስለጠየቀን መግለጫ ይሰጣል።
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሠው ልጅ ሕይወት የተቀደሠ መሆኑን ታምናለች። ስለዚህ ቤተክርስቲያኗ ለግል ወይም ለማህበራዊ ምቾት ሲባል የተመረጠ ጽንስ ማስወረድን ትቃወማለች፤ እንዲሁም አባሎቿ እንዳይቀበሉት፣ እንዳይፈፅሙት፣ እንዳያበረታቱት፣ ያንን ለማድረግ ክፍያ እንዳይፈፅሙ ወይንም እንደዚህ አይነት ጽንስ ማስወረድን እንዳያመቻቹ ትመክራለች።
“[ጌታ] ለሚከተሉት ለየት ያሉ ሁኔታዎች ይፈቅዳል፦
-
በአስገድዶ መድፈር ወይም የሥጋ ዝምድና ባላቸው መካከል በተከሠተ የጾታ ግንኙነት ምክንያት የተከሠተ እርግዝና፣ ወይም
-
በሙያው ብቃት ያለው ሐኪም የእናትየው ህይወት ወይም ጤና ከባድ አደጋ ላይ እንደሆነ ከወሰነ፣ ወይም
-
በሙያው ብቃት ያለው ሐኪም ፅንሱ ከተወለደ በኋላ በሕይወት እንዲተርፍ የማይፈቅዱ ከባድ ጉድለቶች እንዳሉት ከወሰነ።”
ቀዳሚ አመራር እንዲህ ይቀጥላሉ፦ “ጽንስ ማስወረድ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው። [በእነዚህ ለየት ያሉ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን] ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች በጸሎት አማካኝነት ማረጋገጫ ካገኙ” እንዲሁም ከሌሎች ጋር ከተመካከሩ በኋላ ነው።
ከሠላሳ ዓመታት በፊት የጌታ ነቢያት ለዓለም የተላለፈ አዋጅ አውጥተው ነበር።። እነዚህን ቃላት ያካትታል፦
“የተቀደሱት የመዋለድ ሀይሎች እንደ ባልና ሚስት በህግ በተጋቡት ወንዶች እና ሴቶች መካከል ብቻ መፈጸም እንዳለበትም እግዚአብሔር እንዳዘዘ ጨምረንም እናውጃለን።
“ሟች ህይወትን የሚፈጠሩበት መንገድም በመለኮታዊ የተወሰኑ እንደሆኑም እንገልጻለን። የህይወትን ቅድስና እና በእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ ውስጥ ያለውን አስፈላጊነትንም እናረጋግጣለን።”
ያልተወለደ ፅንስን ሕይወት መንከባከብ እና መጠበቅ ፖለቲካዊ አቋም አይደለም። ጌታ በነቢያቱ ያረጋገጠው የስነምግባር ህግ ነው።
በግልጽ በመናገር
በቀዳሚ አመአር ድሮ ያገለገሉት ፕሬዚዳንት ጄ. ሩብን ክላርክ የዛሬን ወጣቶች ወብታማ በሆነ ሁኔታ ገልጸዋል፦ ““የቤተክርስቲያኗ ወጣቶች የመንፈስን ነገር ይራባሉ፤ ወንጌልን ለመማር ጉጉት አላቸው፣ እናም ይህን የሚፈልጉት በቀጥታ፣ ሳይበረዝ ነው። ስለእኛ እምነት … ማወቅ ይፈልጋሉ፤ ስለእውነት ምስክርነት ለማግኘት ይፈልጋሉ። እነርሱ… ጠያቂዎች፣ እውነትን ፈላጊዎች ናቸው።” በወጣቶቻችን፣ በቤታችን፣ እናም እርስ በርስ እንዲሁም በመረዳጃ ማህበር እና በክህነት ቡድን ስብሰባዎቻችን ላይ ስለ ጌታ የንፅህና ህግ፣ ስለህይወት ቅድስና እና ስላልተወለደ ፅንስ እና ስለእናቶቻቸው እንክብካቤ ደጋግመን በእምነት እና በርህራሄ እንነጋገር።”
አንዲት ውድ እህት ከዓሥርተ ዓመታት በፊት ስለነበራት ተሞክሮ ጻፈችልኝ፦ “በ17 አመቴ ከወንድ ጓደኛዬ ያገኘሁት ድጋፍ በጣም ጥቂት ወይም ምንም ያልሆነ በሆነበት እርጉዝ ነበርኩኝ። ሃፍረት እና ብቸኝነት ተሰማኝ [ሆኖም] [ጽንስን ማስወረድ] በፍፁም ግምት ውስጥ አላስገባሁም። እኔ መመሪያ ለመቀበል አዘወትሬ የማገኛቸው አፍቃሪ ቤተሰብ እና ኤጲስ ቆጶስ [ነበሩኝ]። … ወደ እግዚአብሔር ቀረብኩኝ። ቅዱሳት መጻህፍትን አጠናሁ … እንዲሁም ጸለይኩ [ከዚያም] በአዳኙ እና በንስሃ ሂደት ጥንካሬን አገኘሁ። [ለጸሎቴ] ልክደው የማልችለውን መልስ አገኘሁ። በጣም ልብ የሚሠብር ነበር ሆኖም ልጄን ለጉዲፈቻ እንደምሠጠው አውቅሁ። … ብርቱነት ለማግኘት ጸለይኩ [ከዚያም] በንስሃ በኩል የአዳኙ ፍቅር በጣም ግልፅ በሆነ መልኩ ተሰማኝ፣ እግዚአብሔር … ለጸሎቶች መልስ እንደሚሠጥ እና እንደሚያጠነክረን አውቃለሁ።”
አስደሳች ጥንዶች ይህችን ልጅ በጉዲፈቻ ተቀበሉት፣ እናም ወንጌልን አስተማሯት። አሁን ባለትዳር እና የራሷ የሆነ ቆንጆ ቤተሰብ ያላት ነች።
እንዳንዴም፣ ጥልቅ የሆነ እና ከልክ ያለፈ ጭንቀት የህይወት ጥበቃን ሊያስከትል ይችላል።
በቅርብ ጊዜ እኔ እና ካቲ የምንወዳቸው አንድ ወጣት ጥንዶች ለመውለድ ስለሚጠብቁት ውድ ህጻን ጽፈው ነገሩን።
አባትየው እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “[ባለቤቴ] የ10 ሣምንት ነፍሰ ጡር እያለች ተዓምራዊዋ ልጃችን በተለምዶ ዳውን ሲንድሮም በመባል የሚታወቀው ትራይሶሚ 21 በዘር የሚተላለፍ በሽታ እንዳለባት አወቅን። ፅንስ ማቋረጥን እንድናስብበት ከህክምናው ዘርፍ ጫና እየተደረገብን እንደሆነ ተሰማን። ከጥቂት ሣምንታት በኋላ … ያልተወለደችው ልጃችን … በህይወቷ የመጀመሪያው ዓመት ላይ ብዙ የልብ ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልጋት አወቅን። በዚህ ሂደት ውስጥ በሙሉ መለኮታዊ እርዳታ ለማግኘት ጠብቀን ስንጸልይ፣ … መንፈስ መፅናናትን ሲሰጠን ተሰምቶናል። ሴት ልጃችን የሰማይ አባት ምርጥ ልጅ እንደሆነች እና የቤተሰባችን አካል የመሆን እና ወደ ምድር የመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት መገለጥን እና ግንዛቤን ተቀብለናል።”
የሕፃኗ እናት እንዲህ በማለት ጽፋለች፦ “[እኛ] በሠማነው ዜና ደነገጥን፣ ግራ ተጋባን እንዲሁም ጥልቅ ሃዘን ተሠማን። … የ14 ሳምንታት ነፍሰ ጡር ሳለሁ ልጃችን ህይወትን ሊያሣጣ በሚችል ሁኔታ ልቧ ከሁለት በላይ በሆኑ ቦታዎች እንዳይሰራ የሚያደርግ በሽታ እንዳሉባት አወቅን። እርግዝናው ከ10–18 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በነበረ ጊዜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ዶክተሮች እና ስፔሻሊስቶች ጋር ቀርበናል። … በእያንዳንዱ ቀጠሯችን ላይ እርግዝናውን መቀጠል ወይንስ ማቋረጥ እንደምንፈልግ እንጠየቅ ነበር። … አዳኙ ልቤን ፈውሷል እንዲሁም ስለሴት ልጃችን የሰላም እና የደስታ ስሜት ሰጥቶኛል። … [የሰማይ አባት] ለእኔ ፍጹም ዕቅድ እንዳለው ደግሞ ደጋግሞ አሳይቶኛል [ስለዚህም] በእርሱ እታመናለሁ።”
እነርሱም በደስታ ህጻን ልጅቱእን ከዛሬ አንድ ሳምን በፊት ተቀበሏት። እርሷ የእነርሱ ናት እናም እነርሱም ለእርሷ ለዘለአለም ናቸው።
የማይደክም እምነት እና አስደናቂ ብርቱነት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ልዩ ገፅታዎች ናቸው።
አስደናቂ የእምነት ምሳሌ
ባለፉት አመታት ከአባልነት ከተሠረዙ ከብዙ አመታት በኋላ ወደ ቃል ኪዳኑ መንገድ እንዲሁም ወደ ክህነት እና ወደቤተመቅደስ በረከቶች ለመመለስ በትህትና ከፈለጉት ወንዶች እና ሴቶች ጋር የመገናኘት ዕድል አግኝቻለሁ።
በአንድ ወቅት ቀዳሚ አመራርን ወክዬ የክህነት እና የቤተመቅደስ በረከቶች ይመለሡለት ዘንድ ለአንድ ሰው ቃለ መጠይቅ ላደርግ ነበር።
በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ከተጋቡ እና ሶስት አስደናቂ ልጆችን ከወለዱ በኋላ ሰውየው ለሚስቱ እና ለቅዱስ ኪዳኖቹ ታማኝ አልነበረም። አንዲት ያላገባች ሴት አረገዘች ከዚያም ፅንሱን ማስወረድ ፈለገች።
የባልየው የተቀደሰች ሚስት ሴትየዋ ልጁን እንድትወልድ ተማጸነቻት እንዲሁም ከተወለደ በኋላ ልጅዋን ከልጆቿ ጋር እንደምታሳድግ ቃል ገባችላት።
ያላገባችው ሴት እርግዝናውን ላለማቋረጥ ተስማማች።
አሁን አሥር ዓመታት አልፈውታል። ከፊት ለፊቴ የተቀመጠችው ትሁት እህት ልጁን እንደ ራሷ ልጅ ትወደው ነበር እንዲሁም ባሏ ለመካስ እና እሷን እና ቤተሰቡን ለመውደድ እና ለመንከባከብ የሚያደርገውን ጥረት ነገረችኝ። እሷ ስትናገር አባትየው አለቀሰ።
ይህች የተከበረች የእግዚአብሔር ሴት የባሏን ታማኝ አለመሆን በየቀኑ የሚያስታውሳትን ልጅ እንዴት የራሷ አድርጋ ልትወስድ ቻለች? እንዴት? ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ጥንካሬን አግኝታለች እንዲሁም ህይወት ቅዱስ መሆኑን ታምናለች። ያልተወለደው ሕፃን የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዲሁም ምንም የማያውቅና ንጹሕ መሆኑን ታውቃለች።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ላልተወለዱ ህጻናት ያለው ፍቅር እየቀነሰ መምጣቱ በጣም አሳሳቢ ነው። እግዚአብሔር ለሕይወት ዋጋ ይሠጣል። የልጆቹን ህያውነት እና ዘለዓለማዊ ህይወት ማምጣት ስራው እና ክብሩ ነው። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለህይወት ዋጋ እንሠጣለን። “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።” በጣም ለሚፈልጉን ፍቅራችንን አብዝተን እናካፍል። ለእናንተ ያለኝን ፍቅር እና የሰማይ አባታችን ወደ ምድር ለሚመጡት ልጆቹ ያለውን ፍቅር እገልጻለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።