“ወደ እኔ ቅረቡ”
ኢየሱስ ክርስቶስ እያንዳንዳችንን ያፈቅራል። ወደ እርሱ የመቅረብን እድል ያቀርብልናል።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን ጉባኤ ከእናንተ ጋር በመሆኔ ደስታ ይሰማኛል። ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት። በአለም አቀፍ በእርሱ ስም በህንጻዎች እና በቤቶች ውስጥ ተሰብስበናል።
ስሙን በእራሳችን ላይ ስንወስድ ወደ መንግስቱ እንገባለን። የእግዚአብሔር ከሞት የተነሳ እና በግርማ የተጎናጸፈ ልጅ ነው። እኛ ለኃጢያት ለእና ሞት ተገዢ የሆንን ሟቾች ነን። ይሁን እንጂ እርሱ ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሣ ወደ እሱ እንድንቀርብ ጋብዞናል።
ይህም እርሱ ይእሰጠን ግብዣ ነው፦ “ቃላቱም እንዲህ ይላሉ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ ተግታችሁም ፈልጉኝ እናም ታገኙኝማላችሁ፤ ለምኑ፣ ትቀበላላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል።”
የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅርብነት የሚሰማን ጊዜ አለ። ነገር ግን፣ አንዳንድ ጊዜ በሟች ፈተናዎቻችን ወቅት፣ ከእሱ የተወሰነ ርቀት ሊሰማን እና በልባችን ውስጥ ያለውን እንደሚያውቅ እና እንደ ግለሰብ እንደሚወደን ማረጋገጫ እንመኝ ይሆናል።
የአዳኙ ግብዣ ያንን ማረጋገጫ የሚሰማንበትን መንገድ ያካትታል። እርሱን ሁልጊዜ በማስታወስ ወደ እርሱ ቅረቡ። በቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት በትጋት ፈልጉት። ወደ ተወዳጅ ልጁ የመቅረብ ስሜት ለማግኘት የሰማይ አባትን ከልብ በሚመጣ ጸሎት ጠይቁ።
ስለእርሱ ለማሰብ ቀላል መንገድ አለ። ከምትወዷቸው ጓደኞቻችሁ ለተወሰነ ጊዜ ብትለያዩም እንደምታደርጉት ነው። ከእነሱ ጋር የምትነጋገሩበትን መንገድ ታገኛላችሁ፣ ከእነሱ የተቀበላችሁትን ማንኛውንም መልእክት ከፍ አድርጋችሁ ትመለከታላችሁ፣ እንዲሁም እነሱን ለመርዳት የምትችሉትን ሁሉ ታደርጉ ነበር።
በይበልጥ በተከሰተ ቁጥር፣ ጊዜው እየረዘመ በሄደ መጠን የፍቅር ግንኙነቱ እየጠነከረ ይሄዳል፣ እናም እናንተም ይበልጥ እየተቃረባችሁ እንደሆናችሁ ይሰማችኋል። ያለ ተወዳጅ የሐሳብ ልውውጥ እና እርስ በርስ የመረዳዳት እድል ከሌለ ብዙ ጊዜ ካለፈ ግንኙነቱ ይዳከማል።
ኢየሱስ ክርስቶስ እያንዳንዳችንን ያፈቅራል። ወደ እርሱ የመቅረብን እድል ያቀርባል። ልክ እንደ አንድ አፍቃሪ ጓደኛ፣ ከሰማይ አባት ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በጸሎት በመነጋገር፣ የተወደደውን መመሪያ በማዳመጥ እና ሌሎችን ለአዳኙ በደስታ በማገልገል፣ በተመሳሳይ መንገድ ይህን ታደርጉታላችሁ። በቅርቡም ያንን ወደ እሱ የመቅረብ በረከት ይሰማችኋል።
በወጣትነቴ ከአዳኙ ጋር የመቀራረብ ደስታ እናም በቀላል ተግባራት ትእዛዛቱን በመጠበቄ እርሱ ወደ እኔ የቀረበበትን የተሞክሮ ደስታ አግኝቻለሁ። እኔ ወጣት በነበርኩበት ጊዜ ቅዱስ ቍርባን የሚቀርበው በምሽት ስብሰባ ወቅት ነበር። ከ75 ዓመታት በፊት ከቤት ውጭ ጨለማና ቅዝቃዜ የነበረበት አንድ ምሽት አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል። ከቅዱሳን ጋር ተሰብስቤ በቅዱስ ቍርባን ለመካፈል ትእዛዙን እንደጠበቅኩ ስገነዘብ የብርሃን እና የሙቀት ስሜት እንደተሰማኝ አስታውሳለሁ፣ ሁል ጊዜም ልጁን ለማስታወስ እና ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ከሰማይ አባታችን ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ።
በዚያ ምሽት ስብሰባው መጨረሻ ላይ “ከእኔ ጋር ሁን፤ አሁን ምሽት ነው” የሚለውን መዝሙር ዘመርን፣ በዚህም “አቤቱ አዳኝ፣ በምሽት ከእኔ ጋር ቆይ” የሚሉ የሚታወሱ ቃላት ነበሩ።”
እነዚህ ቃላት በልጅነቴም ቢሆን የመንፈስ ቅዱስን ኃይል በሚገባ እንድገነዘብ አድርገውኛል። በዚያ ምሽት የአዳኙ ፍቅርና ቅርበት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ማጽናኛ ተሰማኝ።
ከዓመታት በኋላ፣ በወጣትነቴ በዚያ የቅዱስ ቍርባን ስብሰባ ወቅት የተሰማኝን የአዳኙን ፍቅርና ቅርበት እንደገና ማደስ ፈለግሁ። ስለዚህ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የፈተሽኩትን ሌላ ቀላል ትእዛዝ አከበርኩኝ።
በሉቃስ ወንጌል ላይ ከስቅለቱና ከተቀበረበት ከሦስተኛው ቀን በኋላ ታማኝ አገልጋዮቹ ለአዳኙ ካላቸው ፍቅር የተነሣ አስከሬኑን ለመቀባት እንደመጡ አንብቤያለሁ። ወደ መቃብሩ በደረሱ ጊዜ ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት እናም አካሉም በዚያ አልነበረም።
ሁለት መላእክት መጡ እና ለምን እንደሚፈሩ ጠየቋቸው፦
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ?
“ተነስቶአል እንጂ በዚህ የለም፥ በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ፣
“የሰው ልጅ በሀጦአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ።”
በዚያው ምሽት ሁለት ደቀ መዛሙርት ከኢየሩሳሌም ተነሥተው ወደ ኤማሁስ እየተጓዙ ሳሉ ከሞት የተነሳው ጌታ ተገለጠላቸውና አብሯቸው ተጓዘ።
የሉቃስ ወንጌል በዚያ ምሽት አብረናቸው እንድንጓዝ አስችሎናል።
“ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤
“ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።
“እርሱም። እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው።
“ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ። አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው።”
የእስራኤል አዳኝ እንደሆነ በእርሱ እምነት ስለነበራቸው ኢየሱስ ሞት ስላላቸው ሀዘን ነገሩት።
በሀዘን ላይ ላሉት እነዚህ ሁለት ሀዘነኛ ደቀመዝሙርቶች ሲናገር ከሞት በተነሳው ጌታ ድምጽ ውስጥ የፍቅር ስሜት ይሰማ ይሆንም ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስን ማንበቤን ስቀጥል፣ ከልጅነቴ ጀምሮ የነበሩኝን ስሜት የሚያንፀባርቁ የሚከተሉትን ቃላት ሰማሁ፦
“ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው።
“እነርሱ፣ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።”
አዳኙ በዚያ ምሽት ወደ ደቀመዛሙርቱ ቤት እንዲገባ የቀረበለትን ግብዣ ተቀብሏል። ለመመገብ ከእነርሱ ጋር ተቀመጠ። እንጀራውን አንስቶ ባረከ፣ ቆርሶም ሰጣቸው። ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ፤ እርሱንም አወቁት። ከዚያም እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።
ሉቃስ የእነዚያ የተባረኩ ደቀመዛሙርቶች ስሜት ለእኛ መዝግቦልን ነበር፦ “እርስ በርሳቸውም፣ በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?” ተባባሉ።
ከዚያም ሁለቱ ደቀ መዛሙርት በፍጥነት ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የተከሰተውን ነገር ለአሥራ አንዱ ሐዋርያት ነገሯቸው። ተሞክሮዎቻቸውን ሲያካፍሉ አዳኙ እንደገና ተገለጠ።
እርሱም በመካከላቸው ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።” ከዚያም የአባቱን ልጆች ኃጢአት ለማስተሰረይና የሞትን ማሰሪያ ለማፍረስ የተላከበትን ተልዕኮ አስመልክቶ የተነገሩትን ትንቢቶች ገለጸ።
“እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥
“በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።
ልክ እንደ ተወዳጅ ደቀመዛሙርቱ ሁሉ በጥምቀት በር በኩል ለመግባት የመረጠ የሰማይ አባት ልጅ ሁሉ የአዳኙ ምስክር ለመሆን እና በምድራዊ ሕይወታችን በሙሉ ችግረኞችን በመንከባከብ ቃል ኪዳን ሥር እንኖራለን። ይህ ቁርጠኝነት ከዘመናት በፊት በታላቁ የመጽሐፈ ሞርሞን ነቢይ አልማ በሞርሞን ውኃዎች ላይ ግልጽ ተደርጎልናል።
“እናንተ ወደ እግዚአብሔር በረት ለመምጣትና፣ ህዝቡ ትባሉ ዘንድ፣ እንዲሁም አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም ቀላል እንዲሆኑ ዘንድ ለመሸከም ፈቃደኞች በመሆን እንደፈለጋችሁ፤
“አዎን፣ እናም ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን፤ መፅናናትን ለሚፈልጉም ካፅናናችኋቸው፤ እናም በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገርና፣ በምትኖሩበት ቦታዎች ሁሉ፣ እስከሞት ድረስ፣ የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን ትቆሙ ዘንድና፣ በጌታ ትድኑ ዘንድ፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወትም ይኖራችሁ ዘንድና የመጀመሪያውን ትንሳኤ ከሚያገኙት ጋርም ለመቆጠር ፈቃደኞች ከሆናችሁ”
ለእነዚህ ተስፋዎች ታማኝ ሆናችሁ ስትቀጥሉ ጌታ የገባውን ቃል እንደሚፈፅም ታስተውላላችሁ ሌሎችን በማገልገል አንድነትን በመፍጠር ሸክማችሁን ታቀላችሁ። አዳኙን ማወቅ ትችላላችሁ፤ ከጊዜ በኋላም እሱን መምሰል ትጀምራላችሁ፤ እንዲሁም “በእርሱ ፍጹማን ትሆናላችሁ።” ሌሎችን በመርዳት፣ ወደ አዳኙ ይበልጥ እየቀረባችሁ እንደሆነ ይታወቃችኋል።
ብዙዎቻችሁ ከዘለአለም ህይወት መንገድ በመሰናከል ላይ ያሉ የምታፈቅሯቸው ሰዎች አሉ። እነርሱን ለመመለስ ምን በተጨማሪ ለማድረግ እንደምትችሉ ታስቡበትም ይሆናል። እርሱን በእምነት ስታገለግሉ ጌታ ወደ እነርሱ እንዲቀርብ ልትመኩበት ትችላላችሁ።
ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ ከቤተሰቦቻቸው በተለዩበት ጊዜ ጌታ የገባላቸውን ቃል ኪዳን ታስታውሳላችሁ፥ “በእውነት ባልንጀሮቼ ስድኒ እና ጆሴፍ፣ ጌታ ለእናንተ እንዲህ ይላል፣ ቤተሰቦቻችሁ ደህና ናቸው፤ በእጆቼም ውስጥ ናቸው፣ እና መልካም እንደሚመስለኝም አደርግባቸዋለሁ በእኔ ሁሉም ሀይል አለና።”
እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቁስሎች ስትጠግኑ የጌታ ኃይል ይደግፋቹሃል። ለመርዳት እና የሰማይ አባታችንን ልጆች ለመባረክ ከእናንተ ጋር እጆቹ ተዘርግተዋል።
እያንዳንዱ የኢየሱስ ክርስቶስ የቃል ኪዳን አገልጋዮች ሁሉ ለእርሱ ሲሉ ሌሎችን ሲባርኩና ሲያገለግሉ የእርሱን መመሪያ በመንፈስ ብኩል ይቀበላሉ። ከዚያም የአዳኙን ፍቅር የሚሰማቸው ከመሆኑም በላይ ወደ እሱ በመቅረብ ደስታ ያገኛሉ።
በኤማሁስ መንገድ በነበረ ቤት ውስጥ ከነበሩት ሁለቱ ደቀመዛሙርቶች ጋር አብሬ እንደነበርኩኝ ያህል በትንሳኤ ለተነሳው ጌታ ምስክር ነኝ። እሱ ሕያው እንደሆነ አውቃለሁ።
ይህችም የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት። እኛም በፍርድ ቀን በአዳኙ እይታ፣ ፊት ለፊት እንቆማለን። በዚህ ህይወት ውስጥ፣ በአገልግሎቱ ወደ እርሱ ለቀረቡ እና “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ” የሚሉትን የእርሱን ቃላት ለመስማት በጉጉት ለሚጠባበቁት፣ ለእነዚያ ታላቅ የደስታ ጊዜ ይሆናል።-
እኔም በትንሳኤ ስለተነሳው አዳኝ እና ቤዛችን እንደ ምስክርነቴ፣ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።