አጠቃላይ ጉባኤ
ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ለመዘጋጀት ተሳተፉ
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:24

ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ለመዘጋጀት ተሳተፉ

በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ የምንገባባቸው ጥሪዎች እና ሌሎች መንገዶች አዳኝን ለመገናኘት በልዩ ሁኔታ ያዘጋጁናል።

ከጥቂት ወራት በፊት፣ አዳራሽ ውስጥ ቆሜ ሳለሁ ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን በዚያ ያልፉ ነበር። በጊዜው እንደ አዲስ አጠቃላይ ባለስልጣን ጥሪን ተቀብዬ ነበር። ብቃት እንደሌለኝ ዓይነት የሚመስል ስሜት ሲሰማኝ አይተው ፈገግ አሉና “እሺ፣ የሚያደርገውን የማያውቅ የሚመስል ሰው በዚያ አለ” በማለት ተናገሩ ።

እኔም “እውነተኛ ነቢይ እና ባለ ራእይ አለ” በማለት አሰብኩ።

ከዚያም ሽማግሌ አንደርሰን በሹክሹክታ፣ “አትጨነቅ፣ ሽማግሌ ሸምዌይ። ከአምስት ወይም በከስድስት ዓመታት በኋላ ትለምደዋለህ” በማለት ተናገሩ።

በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከአቅማችን በላይ የሚመስሉ ነገሮችን እንድናደርግ ለምን እንደተጠየቅን አስባችሁ ታውቃላችሁን? ከህይወት ፍላጎቶች ጋር፣ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ ጥሪዎች እንደሚያስፈልገንስ ጠይቃችኋል? ደህና፣ እኔ ጠይቄ አውቃለሁ።

እናም በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ባሉት ንግግራቸው ላይ መልሱን አግኝቻለሁ፣ “አሁን እናንተ እና እኔ ለጌታችን እና ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የምንዘጋጅበት ጊዜ ነው።” ፕሬዚዳንት ኔልሰን ይህንን ሲናገሩ፣ በእግዚአብሔር ስራ ላይ ስንሳተፍ፣ ለክርስቶስ ዳግም መምጣት እራሳችንን እና ሌሎችን እያዘጋጀን እንደሆንን መንፈስ አስተምሮኛል። ጥሪዎች፣ አገልግሎቶች፣ የቤተመቅደስ ማምለክ፣ የመንፈስ መነሳሳቶችን መከተል እና ሌሎች በእግዚአብሔር ስራ የምንጀምራቸው መንገዶች ከአዳኙ ጋር ለመገናኘት እንድንዘጋጅ የጌታ ቃል ኪዳን ያስገድዳል።.

እግዚአብሔር በሥራው ላይ ስንሰማራ ይደሰታል።

በዚህ ‘’ታላቅ ጊዜ ውስጥ፣’’ የእግዚአብሔር መንግሥት በሚሰፋበት እና ቤተመቅደሶች በምድር በሚበዙበት ጊዜ፣ በእግዚአብሔር ሥራ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ነፍሳት ፍላጎት እያደገ ነው። ያለ ራስወዳድነት ማገልገል የክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ዋናው ጉዳይ ነው። ነገር ግን ማገልገል ብዙውን ጊዜ አመቺ አይደለም። ልጆቹን በማገልገል ከራስ ወዳጅነት ነፃ በሆነ መንገድ እግዚአብሔርን ለማገልገል ምኞቶቻችሁን እና ተግዳሮቶቻችሁን ወደ ጎን ያደረጋችሁትን እናንተን የቃል ኪዳን ጠባቂ ደቀመዛሙርትን፣ ውድ ሚስዮናችንንም ጨምሮ፣ አደንቃችኋለሁ። እግዚአብሔር “በፅድቅ … [የምታገለግሉትን እናንተን ያከብራል]።” “ዋጋ[ችሁ]ም ታላቅ እና ክብራ[ችሁ]ም ዘለአለማዊ ይሆናል” በማለት ቃል ገብቷል። ለማገልገል እሺ ስንል፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ እሺ እያልን ነው። ክርስቶስን እሺ ስንል፣ ይበልጥ የተትረፈረፈ ሕይወትን እሺ እያልን ነው።

ይህንን ትምህርት የተማርኩት ኮሌጅ ውስጥ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ሆኜ በምሰራበት እና በምማርበት ጊዜ ነው። በአንድ አጥቢያ ውስጥ ላሉ ላላገቡ ወጣቶች የመሳተፊያ እቅድ እንዳወጣ ተጠይቄ ነበር። ይህ ለእኔ እንደ ቅዠት ሆኖብኝ ነበር። ቢሆንም፣ ተቀበልኩኝ፣ እናም በመጀመሪያ የማያስደስት ስራ ነበር። ከዚያም አንዲት ቆንጆ ልጅ የአይስ ክሬም መስተንግዶዬን አይታ በፍቅር ተነክታ ነበር። ቀልቤን ለመውሰድ ስትል ሶስት ጊዜ ትመላለስ ነበር። በፍቅር ወደቅን፣ እናም ከሁለት ሳምንት በኋላም የጋብቻ ጥያቄን አቀረበች። እንግዲህ፣ ምናልባት ያን ያህል የፈጠነ ላይሆን ይችላል፣ እና እኔ ነበርኩ ጥያቄውን ያቀረብኩት፣ ነገር ግን እውነታው ወዲህ ነው፣ ያን የተሰጠኝን ጥሪ እምቢ ብል ኖሮ ከሀይዲ ጋር የመገናኘት እድል አለማግኘቴ የሚሰቅቅ ሀሳብ ነበር።

የእኛ ተሳትፎ ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ዝግጅት ነው።

በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ የተሰማራነው እግዚአብሔር ስለሚፈልገን ሳይሆን እግዚአብሔርን እና በረከቶቹን ስለምንፈልግ ነው። እንዲህም ቃል ገብቷል፣ “ስለሆነም፣ እነሆ፣ በወይኑ ስፍራዬ የሚሰሩትን በታላቅ በረከት እባርካቸዋለሁ።” በእግዚአብሔር ስራ መሳተፋችን አዳኝን ለመገናኘት እንዴት እንደሚባርክ እና እንድንዘጋጅ በመርዳት የሚያስተምሩንን ሶስት መርሆችን ላካፍላችሁ።

በመጀመሪያ፣ ስንሳተፍ ወደ “[ራሳችን] ተፈጥሮአዊ አቅም” እናድጋለን።

ይህንን ሂደት የምንማረው በፍጥረት ታሪክ ውስጥ ነው። ከእያንዳንዱ የሥራ ቀን ክንውን በኋላ፣ እግዚአብሔር የተገኘውን እመርታ “መልካም ነበር” በማለት ገልጿል።” ሥራው አልቋል ወይም ፍጹም ነው አልነበረም ያለው። ነገር ግን በእያንዳንዱ ቀን እድገት ነበር፣ እና በእግዚአብሔርም ዓይን፣ ያ መልካም ነበር!

ጥሪ የግል ብቃትን ለመወሰን ወይም ለማረጋገጥ አይደለም። ይልቁኑም፣ ከእግዚአብሔር ጋር በሚፈልገው ማንኛውም መንገድ ስንሰራ፣ ወደ ራሳችን ተፈጥሮአዊ ልክ እናድጋለን።

እግዚአብሔር በለውጣችን ይደሰታል፣ የምንሰራው ስራ እያለብንም እንኳ ቢሆን፣ እኛም እንዲሁ መሆን ይገባናል። አንዳንድ ጊዜ፣ በጥሪ ውስጥ ለማገልገል ጥንካሬን ወይም ዘዴ ይጎድለን ይሆናል። አሁንም፣ እንደ ጸሎት እና የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ባሉ ትርጉም በሚሰጡ መንገዶች በስራው መሳተፍ እና ምስክርነታችንን መጠበቅ እንችላለን። ፈቃደኞች ስንሆን ነገር ግን ለማገልገል ሳንችል ስንቀር አፍቃሪ የሰማይ አባታችን አይኮንነንም።

ሁለተኛ፣ ማገልገል ቤቶቻችንን እና ቤተክርስቲያናችንን የቃል ኪዳን ኑሮን የምንለማመድባቸው ቅዱሳን ቦታዎች እስከሚሆኑ ከፍ ያደርጋቸዋል።

ለምሳሌ፣ ክርስቶስን ሁል ጊዜ የምናስታውስበት ቃል ኪዳናችን በግለሰብ ደረጃ የሚፈፀም ነው፣ ነገር ግን ይህ ቃል ኪዳን ሌሎችን ስናገለግል ተግባራዊ ይሆናል። ጥሪዎች አንዳችን የአንዳችንን ሸክም በምንሸከምባቸው እድሎች ይከቡናል፣ በዚህም የክርስቶስን ህግ እንፈጽማለን። እግዚአብሔርን በመውደድ እና ቃል ኪዳኖቻችንን መኖር በመፈልግ ስናገለግል፣ አሰልቺ እና አድካሚ ይመስል የነበረው አገልግሎት አስደሳች እና አስደናቂ ለውጥን የሚያመጣ ይሆናል።

ስርዓቶች የሚያድኑን የሰማይን መቆጣጠሪያ ስለሚያሟሉ ብቻ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ ከእነዚህ ስርዓቶች ጋር በተያያዙት ቃል ኪዳኖች ስንኖር፣ በእግዚአብሔር ፊት መሆን የምንፈልገውን አይነት ሰው እንሆናለን። ይህ ግንዛቤ ለማገልገል ማመንታትን ወይም ላለማገልገል ምርጫዎችን ያስወግዳል። እግዚአብሔር የሚፈቅደውን መጠየቅ አቁመን እግዚአብሔር የሚመርጠውን መጠየቅ ስንጀምር ኢየሱስ ክርስቶስን የመገናኘት ዝግጅታችን ይፋጠናል።

ሦስተኛ፣ በእግዚአብሔር ሥራ መሳተፍ የእግዚአብሔርን የጸጋ ስጦታ እንድንቀበል ይረዳናል።

ስናገልግል የገንዘብ ማካካሻን አንቀበልም። ይልቁንም፣ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት፣ “በመንፈስ እንድንበረታ፣ የእግዚአብሔርንም እውቀት እንዲኖረን [እና] … ከእግዚአብሔር በተገኘ ኃይልና ሥልጣን እናስተምር ዘንድ ለአገልግሎታችን [እኛ] የእግዚአብሔርን ጸጋ እንቀበላለን።” ያ በጣም መልካም ልውውጥ ነው!

በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት፣ መቻል ወይም አለመቻላችን ጥሪን እንድንቀበል መሰረታዊ ነገሮች አይደሉም ወይም ክህሎት ላይ መሰረት ያደረጉ አይደሉም። እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ ተግባርን ወይም በስራው ላይ በልዩ ችሎታ እንዲሰራለት አይጠብቅም። እንደዚያ ከሆነ፣ ንግሥት አስቴር ሕዝቧን አታድንም ነበር፣ ጴጥሮስም ቀደምት ቤተክርስቲያንን አይመራም ነበር፣ እናም ጆሴፍ ስሚዝ በዳግም መመለስ ጊዜ ነቢይ ባልሆነ ነበር።

ከአቅማችን በላይ የሆነ ነገር ለማድረግ በእምነት ስንሰራ፣ ድካማችን ይገለጣል። ይህ መቼም ምቾት አይሰጥም፣ ነገር ግን “[በእግዚአብሔር] ጸጋ፣ … እነዚህን ነገሮች የማድረግ ኃይል እንዳለን እናውቅ” ዘንድ ለእኛ አስፈላጊ ነው።

በእግዚአብሔር ሥራ ስንሳተፍ አብዛኛውን ጊዜ እንወድቃለን። ነገር ግን በጥረታችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይይዘናል። ቀስ በቀስ ከውድቀታችን እና ከፍርሃታችን እና መቼም በቂ የማንሆን መስሎ ሲሰማን መዳንን እንድንለማመድ ያደርገናል። ለእኛ ከሁሉም በላይ ጥሩ የሆነችውን ትንሿን ጥረት በቅድስና ስናደርግ፣ እግዚአብሔር ይህን ያጎላዋል። ለኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት ስናደርግ፣ እርሱ ይቀድሰናል። ይህ የመለወጥ የእግዚአብሔር የጸጋው ኃይል ነው። ስናገለግል፣ “በአብ አማካኝነት [በመነሳት]፣ … [በኢየሱስ ክርስቶስ] ፊት ለመቆም [ለመቻል]” እስክንዘጋጅ ድረስ በጸጋ እናድጋለን።

ሌሎች የጥሪዎችን ስጦታ እንዲቀበሉ እና በዚያም እንዲደሰቱ እርዷቸው።23

በፊቱ ስቆም አዳኙ የሚጠይቀኝን ሁሉ አላውቅም፣ ነገር ግን ምናልባት አንድ ጥያቄ ሊጠይቅ ይችላል፣ “ማንን ይዘህ መጣህ? ጥሪዎች፣ ሌሎችን ከእኛ ጋር ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ የሚረዳቸው ከአፍቃሪው የሰማይ አባት የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው። ስለዚህ፣ መሪዎችን እና እያንዳንዳችንን ጥሪ የሌላቸውን ሆን ብለን እንድንፈልግ እጋብዛለሁ። አበረታቷቸው እንዲሁም በእግዚአብሔር ሥራም እንዲሳተፉ እርዷቸው።

ኤጲስ ቆጶሱ ጆንን ሲጎበኘው እና ጌታ የሚሠራው ሥራ እንዳለው ሲነግረው፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ አልነበረም። ጆንን ሲጃራ ማጨስን እንዲያቆም ጋበዘው። ጆን ለማቆም ብዙ ጊዜ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም፣ በዚህ ጊዜ አንድ የማይታይ ኃይል እንደረዳው ተሰማው።

ከሶስት ሳምንታት በኋላ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ጆንን ጎበኘው። በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ እንዲያገለግል ጠራው። ጆን ደንግጦ ነበር። ማጨስ እንዳቆመ ለካስማ ፕሬዚዳንቱ ነገረው። ይህም ማለት እሁድ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን የመከታተል ባህሉን መተውም ነበረበት፣ እንግዲህ ያ ብዙ ሊያስቸግረው ይችላል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ የመነሳሳት ምላሽ ቀላል ነበር፦ “ጆን፣ እኔ አይደለሁም የምጠይቅህ፣ እግዚአብሄር ነው እንጂ።”

ጆንም፣ “እንዲያማ ከሆነ እኔ አገለግላለሁ” ሲል መለሰ።

ጆን ለማገልገል እነዚህ መሥዋዕቶች ለእርሱ እና ለቤተሰቡ መንፈሳዊ የለውጥ መንገድ እንደሆኑለት ነገረኝ።

እንደ ሰዋዊ አመለካከታችን፣ የማይመጥኑ ወይም የማይገባቸው ለሚመስሉ ግለሰቦች ጥሪዎችን ለመስጠት ስንሞክር አሻግረን እንዳናይ የሚይዘን ነገር አለ ብዬ አስባለሁ። ወይም ደግሞ ከእድገት ትምህርት ይልቅ የአፈጻጸም ባህል ላይ በማተኮር፣ በማይመስሉ እና ባልተፈተኑ ሰዎች ውስጥ አዳኙ እንዴት አቅምን እንደሚጨምርላቸው ማየትን ቸል እንል ይሆናል።

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “እያንዳንዱ [ሴት እና ወንድ] ግዴታቸውን እንዲማሩ እና እንዲተገብሩ ማስቻል፣” የሚለውን የቅዱስት መጻህፍት ትእዛዝ አስፈላጊነት ያስተምራሉ። ይህን እናደርጋለንን? መሪዎች እና ወላጆች ሌሎች እንዲማሩ እና ለራሳቸው እንዲሰሩ ሲፈቅዱ፣ ያብባሉ እናም ይለመልማሉ። ቀላሉ መንገድ ታማኝ አባላትን ሁለተኛ ጥሪ መስጠት ቢሆንም፣ ከሁሉ የተሻለው መንገድ ለማገልገል አይችሉም ብሎ የሚታሰብባቸውን መጋበዝ እና እንዲማሩ እና እንዲያድጉ ማድረግ ነው።

ክርስቶስ በአካል እዚህ ቢኖር ኖሮ፣ ሕሙማንን ይጎበኛል፣ የሰንበት ትምህርት ቤቱን ያስተምራል፣ ልቧ ከተሰበረች ወጣት ልጃገረድ ጋር ይቀመጣል እንዲሁምም ህጻናትን ይባርካል። እርሱ የራሱን ስራ መስራት ይችላል። ነገር ግን እርሱ እኛ እንድንተገብረው እና እንድንማረው የሚያደርገውን መርሕ ስለሚኖር እንድንሰራበት በእርሱ ቦታ እኛን ይልካል።

በእግዚአብሔር ሥራ መሳተፍ “እግዚአብሄርን የመወከል መብት፣ እድል እና ኃላፊነትን” ያመጣል። ራሳችንን ሳይሆን ክርስቶስን ለማጉላት ስናገለግል፣ አገልግሎታችን ደስታን የሚያመጣ ይሆናል። ሌሎች ከክፍላችን፣ ከስብሰባ፣ የአገልግሎት ጉብኝታችን ወይም ከእንቅስቃሴዎች ሲወጡ፣ እኛን ከማስታወስ በላይ ክርስቶስን ሲያስታውሱ ለስራው ሀይል የሚሰጥ ነው።

አዳኙን ለመወከል ከልብ በመሻት፣ እርሱን እየመሰልን እንመጣለን። አዳኙን ለመወከል ከልባችን በመፈለግ፣ ይበልጥ እርሱን እንመስላለን። ያን ጊዜ እያንዳንዳችን ተንበርክከን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ብለን በምንመሰክርበት ጊዜ፣ በእርግጥም እንደሆነ አምናለሁ፣ ለተቀደሰው ወቅት ጥሩ መዘጋጃ ነው፣ እናም ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ጌታ ቅርብ ስለሆነ፣ ለዓለም ድርቻ በሙሉ” ለሚመጣው ነገር ይበልጥ “እንድንዘጋጅ” ዘንድ የእርሱ “… ድምጽ ናቸው።’’ ቅዱስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2024 (እ.ኤ.አ)፣ 121።

  2. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4፥2-4ን ይመልከቱ።

  3. ረስል ኤም ኔልሰን “The Lord Jesus Christ Will Come Again [ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል”፣ 121።

  4. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥5–6

  5. ዮሐንስ 10፥10 ተመልከቱ።

  6. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥9

  7. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥19

  8. ዘፍጥረት 1 ተመልከቱ።

  9. በአዳኙ የመክሊት ምሳሌ ላይ (ማቴዎስ 25፥14–28 ተመልከቱ)፣ መምህሩ ለእያንዳንዱ አገልጋይ “ጥቂት ነገሮችን” በሀላፊነት ይሰጣል። መምህሩ እያንዳንዱ አገልጋይ “በብዙ ነገሮች ላይ” ስልጡን እንዲሆኑለት በሚያደርገው እድገት ላይ የበለጠ ያተኮረ ነበር እናም ለንብረቶቹ መመለስ ብዙም አያሳስበውም። አንድ የፈራና ማገልገል የማይፈልግ አገልጋይ ተወገዘ እናም ያለ እድገት ባከነ። (ማቴዎስ 25፥14-28 ይመልከቱ።)

  10. ሉቃስ 21፥19 ይመልከቱ። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “የጽድቅ ሥራ የመንፈሳዊ እድገት አስፈላጊ ነው” በማለት አስተምረዋል” (“Things as They Really Are 2.0፣” [worldwide devotional for young adults፣ Nov. 3፣ 2024]፣ Gospel Library).

  11. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥4 ይመልከቱ።

  12. ሞዛያ 4፥24 ተመልከቱ።

  13. ራስል ኤም. ኔልሰንን “እየተማርን ያለነው እና መቼም የማንረሳው” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 79) ይመልከቱ። በቤተስብ ውስጥ አድርጎ ወደ ምድር የላከን እንዲሁም በአጥቢያዎች እና በካስማዎች ያደራጀን በዚህ ምክንያት ነው። ለዚህም ነው እርስ በርሳችን እንድናገለግል የጠየቀን። … ብቻችንን ለማድረግ ከምንችለው በላይ በጋራ ብዙ ለማከናወን እንችላለን። ልጆቹ አንዳቸው ከሌላው ተለይተው ቢቀሩ እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው የደስታ እቅድ ይሰናከላል።

  14. ገላትያ 6፤2፤ ደግሞም ሞዛያ 18፥8–9 ተመልከቱ።

  15. ፕሬዘደንት ሄንሪ .ቢ .አይሪንግ እንዳስተማሩት፣ “ለአገልግሎት ለመጠራት እኛ የምናገለግለውን ጌታ እንድንወድ የሚያደርግ ነው። ተፈጥሮአችን ለውጥ እንዲያመጣ የሚያደርግ ጥሪ ነው” (“እንደ ልጅሊያሆና፣ ግንቦት 2006 (እ.አ.አ))።

  16. ሄንሪ ቢ. አይሪንግን ፣ “የኋለኛው ቀን ቅዱስ አንድን ምርት አጠቃቀሙ የጥበብን ቃል ሲጥስ መሸጥ አለበት?ኢንዛይን፣ ሚያዝያ 1977 (እ.አ.አ)፣ 30። ይመልከቱ

  17. ሞዛያ 18፥26ሞዛያ 27፥5ን ይመልከቱ።

  18. 2 ኔፊ 3፥13፣ 24 ይመልከቱ።

  19. ያዕቆብ 4፥7

  20. ኢሳይያስ 40፥29–312 ቆሮንቶስ 12፥9 ይመልከቱ።

  21. ማቴዎስ 14፥15–21ን ይመልከቱ። ምንም እንኳን ብዙሃኑን ህዝቦች ለመመገብ ትቂት አምስት ዳቦዎች እና ሁለት አሳዎች ቢቀርቡም፣ አዳኙ በአመስጋኝነት ያንን መስዋዕት ወስዶ ከሚፈለገው በላይ እንዲበዛ አድርጎታል። የዚህ ታላቅ ተአምራዊ ትምህርት አንዱ አዳኝ የሚሰጠን ጥቂት ነገር ሁል ጊዜም ከበቂ በላይ መሆኑን ነው!

  22. መስዋዕት የሚለው የላቲን ሥርወ-ቃሉ ሳከር ማለት ቅዱስ ወይም የተቀደሰ ማለት ሲሆን ፋሰሬ ማለት ደግሞ ማድረግ ማለት ነው። ለእግዚአብሔር ስንሰዋ እርሱ ቅዱስ ያደርገናል። (ሄለማን 3፥35ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 132፥50) ተመልከቱ።

  23. 3 ኔፊ 27፥14

  24. ትምህርት እና ቅል ኪዳኖች 15፥616፥618፥10-16 ተመልከቱ።

  25. ሞሮኒ 7፥2በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል4.1፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  26. “ሁላችንም ወደ ፊት እንግፋ” የሚለውን መዝሙር፣ ቁ. 243 ይመልከቱ

  27. የግል አጋጣሚ እና ደብዳቤ፣ ጥር 4 ቀን 2025 (እ.ኤ.አ)፤ ስም ተቀይሯል።

  28. ማቴዎስ 10፥5–8ሉቃስ 10፥1–9አጠቃላይ የእጅ መጽሀፍ4.2.6 ይመልከቱ።

  29. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥99 ትኩረቶች ተጨምረዋል፤ ደግሞም ሙሴ 6፥582024 ተመልከቱ

  30. የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥20 ይመልከቱ። ወጣቶቻችን በቤተክርስቲያን ወስጥ የወደፊት መሪዎች ብቻ አይደሉም። አሁን ላይ ተጨባጭ በሆነ መንገድ ሊመሩ ይችላሉ። ይህ እውነት ከ2019–2022 (እ.ኤ.አ) በኢለኖይ ቺካጎ ተልዕኮ ውስጥ ከ744 እጅግ አስደናቂ ከሆኑት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጋር በማገለግልበት ጊዜ አይቻለሁ። በኮቪድ ወቅት፣ እነዚህ ወጣቶች ግን ኃያላን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በሚያስደንቅ እና አዳዲስ መንገዶች የእግዚአብሔርን ስራ ታይቶ ወደማይታወቅ ከፍታዎች መርተዋል።

  31. 2 ኔፊ 27፥20–21 ይመልከቱ።

  32. ወንጌሌን ስበኩ፦ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የማካፈል መመሪያ [2023 (እ.ኤ.አ)]፣ 3።

  33. ያዕቆብ 1፥17፣ 19 ውስጥ፣ የያዕቆብ ስራ የጌታ ስራ ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያስተምር እና በመጨረሻው ቀንም ነውር የሌለበት ሆኖ እንዲገኝ ለጌታ እንጂ ጥሪውን ለራሱ አላጎላም።

  34. See 3ኛ ኔፊ 27፥27ን ይመልከቱ።

  35. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 1፥11–12