አጠቃላይ ጉባኤ
አንተ ክርስቶስ ነህ
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:12

አንተ ክርስቶስ ነህ

(ማቴዎስ 16፥16)

ልጆቻችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ፣ በቃል ኪዳን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የቤተክርስቲያኑ አባል እንዲሆኑ እና ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምሰል እንዲጥሩ እንፈልጋለን።

ልጃችን ኢላይ አራተኛ ክፍል በነበረበት ጊዜ፣ እኩዮቹ ክፍላቸው ውስጥ ምሳሌያዊ መንግስት አዋቀሩና ዳኛ እንዲሆን መረጡት። አንድ ቀን፣ ከዩታ ሁለተኛ አውራጃ ፍርድቤት የሆነ በዳኝነት ስራ ላይ ያለ አንድ ሰው ጎበኛቸው፣ ኢላይን የዳኝነት ካባ አለበሰውና፣ በክፍላቸው ውስጥ ላለው ሃላፊነት ቃለ መሃላ እንዲገባ አደረገ። ይህም ታዳጊ በሆነው ነፍሱ ውስጥ ህግን እና ህግ ሰጪ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የማጥናት ፍቅርን ጫረበት።

ከብዙ ዓመታት ጥረቶች በኋላ፣ ኢላይ ከሚፈልጋቸው ከፍተኛ የህግ ትምህርት ተቋማት ከአንዱ የቃለመጠይቅ ግብዣ ደረሰው። እሱም “እማ፣ 10 ጥያቄዎችን ተጠየቅኩ። የመጨረሻው ጥያቄ ‘የህሊና ውሳኔዎችህን የምታገኛቸው ከየት ነው?’ የሚል ነበር። በታሪክ ውስጥ የሰው ልጅ የህይወቱን የግብረ ገብነት ስርዓትን ከጥንታዊ ልምዶች ሲያገኝ እንደነበር ገለጽኩ። የሕይወቴን የግብረ ገብ ልምዶች ለማመሳሰል የምተጋው ግን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። የሰው ዘር ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከቱ ላይ ያስተማረውን ትምህርት ቢታዘዝ አለም የተሻለችና ይበልጥ ሰላማዊ ቦታ እንምትሆን ገለጽኩ።” ከዚያም ቃለ መጠይቁ ተጠናቀቀ፣ ለራሱም “የልጅነት ህልሜ አበቃለት። ሃይማኖታዊ ባልሆኑ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መስማት የሚፈልግ ሰው የለም” ሲል አሰበ።

ከሁለት ሳምንት በኋላ፣ ኢላይን ነጻ የትምህርት እድል በመስጠት ተቀበሉት። ከመወሰኑ በፊት፣ ትምህርት ቤቱን ሄደን ጎበኘን። የህግ ትምህርት ቤቱ ቤተመንግስት ይመስል ነበር እንዲሁም በሚያምር ሀይቅ ትይዩ ኮረብታ ላይ ነበር። በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ በሚያማምሩ ቤተመፃህፍት እና መተላለፊያዎች ውስጥ ስንዘዋወር፣ ከተራራው ስብከቶች ውስጥ የተወሰዱ ጽሁፎች በድንጋይ ሰሌዳ ላይ ተቀረጸው አገኘን።

የተራራው ስብከት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረትን የሚስብ ንግግር ነው፣፣ በትምህርቶቹ ውስጥ ፈር ቀዳጅ በመሆን። የኢየሱስ ክርስቶስን ባህሪ፣ መለኮታዊነቱን እና እርሱን ለመምሰል ያለንን ትንልቁን አላማ በተሻለ ለመረዳት ሌላ ስብከት ሊረዳን አይችልም።

የእድሜ ልክ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርነት የሚጀምረው በቤታችን—እና ከ18 ወራት እድሜ ጀምሮ በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ነው። ልጆቻችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ፣ በቃል ኪዳን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የቤተክርስቲያኑ አባል እንዲሆኑ እና ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምሰል እንዲጥሩ እንፈልጋለን።

በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ

በመጀመሪያ ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ።

ከሕይወት እንጀራ ስብከት በኋላ፣ “ብዙዎቹ [የጌታ] ደቀ መዛሙርት” ትምህርቶቹንና ትዕዛዞቹን መቀበል ከብዷቸው ስለነበር “ወደ ኋላ አሉ፣ ከዚያም ወዲህ ከእርሱ ጋር አልሄዱም። ኢየሱስም ወደ አስራ ሁለቱ ዞሮ “እናንተ ደግሞ ትሄዳላችሁን?” በማለት ልብ የሚነካ ጥያቄ ጠየቃቸው።

ጴጥሮስም፦

“ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን?? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ።

“… እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ አምነናል፣ አውቀናልም” በማለት መለሰ።

ጴጥሮስ እንዳሳየው፣ እምነት ማለት “በአንድ ሰው ማመን ወይም የሆነን ነገር እውነት አድርጎ መቀበል” ነው። እምነታችን ወደ ደህንነት እንዲመራን፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት። በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን የምንለማመደው እርሱ እንዳለ ማረጋገጫ ሲኖረን፣ እውነተኛ ባህሪውን እና ተፈጥሮውን ስንረዳ እና እንደ ፈቃዱ ለመኖር የምንጥር መሆናችንን ስናውቅ ነው።

የተወደዱት ነቢያችን ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን የሁሉም እምነት መሰረት እና የመለኮታዊ ሃይል ማስተላለፊያ ነው” ብለዋል።

ልጆች በኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን እምነት እንዲያጠናክሩ እና መለኮታዊ ኃይሉን እንዲያገኙ እንዴት መርዳት እንችላለን? ወደ አዳኛችን ከመመልከት የበለጠ ወደ ሌላ መሄድ የለብንም።

“[ጌታ] ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ተናገረ፦

“እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ። …

ተነሱ እናም ኑ ቅረቡ። …

እናም እንዲህ ሆነ ህዝቡም ሄዱና እጃቸውን በጎኑ አስገቡ፣ እናም ምስማር የተቸነከሩባቸውን እጆቹንና እግሮቹን ዳሰሷቸው፤ ሁሉም እስከሚደርሳቸው አንድ በአንድ እየሄዱ ይህን አደረጉ፣ እናም በዐይኖቻቸው ተመለከቱና፣ በእጆቻቸው ዳሰሱ፣ እናም በነቢያቱ ስለመምጣቱም የተነገረለት እርሱ መሆኑን በእርግጥም አወቁና መሰከሩ

ይህ በታዳጊ ልጆች ህይወት ውስጥ ምን ሊመስል እንደሚችል እንድታሰላስሉ እጋብዛችኋለሁ። የኢየሱስ ክርስቶስን እና የወንጌሉን ምስክርነት ይሰማሉን? የክብር፣ አምልኮታዊ የአገልግሎቱን እና የእግዚአብሔርነቱን ምስሎች ያያሉን? መንፈስ ቅዱስ የእርሱን እውን መሆን እና አምላክነት ሲመሰክር ይሰማቸዋልን እንዲሁም ያስተውላሉን? የእርሱን መልእክት እና ተልዕኮ ያውቃሉን?

በኢየሱስ ክርስቶስ እና በቤተክርስቲያኑ አባል ሁኑ

ሁለተኛ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በቤተክርስቲያኑ አባል ሁኑ።

የንጉሥ ቢንያም ህዝቦች ታላቅ የልብ መለወጥ አጋጥሟቸዋል፣ በሕይወታቸውንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ በቃል ኪዳን ቁርጠኞች ነበሩ። ከእግዚአብሔርና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በገቡት ቃል ኪዳን ምክንያት “የክርስቶስ ወንዶች እና ሴቶች ልጆቹ ተብለዋል።” የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እንደመሆናችን፣ መንግስቱን ለመገንባት እና ለምጽዓቱ ለመዘጋጀት የቃል ኪዳን ሀላፊነት አለብን።

በእግዚአብሔር የቃልኪዳን መንገድ ላይ ልጆችን ለእድሜ ልክ ለማዘጋጀት የሚረዱ ቁሶች

ልጆች ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን እንዲገቡ እና እንዲጠብቁ እንዴት መርዳት እንችላለን? በኑ፣ ተከተሉኝ መመሪያ መጽሐፍ አባሪ ሀ እና ለ ላይ፣ ቤተሰቦችን የሚያበረታቱ እና መምህራንን እና መሪዎችን በቅዱስ ሃላፊነት የሚደግፉ፣ ልጆችን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ለእድሜ ልክ የሚያዘጋጁ የውይይት መነሻዎችን እና ትምህርቶችን እናገኛለን።

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁኑ

ሦስተኛ፣ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁኑ።

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ አዳኙ አዲስ የተጠሩ ደቀመዛሙርቱን በተቻለ መጠን በቅርበት እንዲመስሉት፦ “ምን አይነት ሰዎች መሆን አለባችሁ? እውነት እላችኋለሁ፣ እኔን ምሰሉ።” በማለት መክሯቸዋል።

የተጠመቁ እና ማረጋገጫ ያገኙ ልጆች እራሳቸውን እና ሌሎችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰብሰብ ግዴታቸውን እንዲወጡ እንዴት መርዳት እንችላለን? የዕድሜ ልክ ደቀመዝሙርነት “… ቃሉን አድራጊዎች እንጂ ሰሚዎች ብቻ” አለመሆንን ይጠይቃል።

ለጌታ ታናናሾቹ የጌታ ደቀ መዛሙርት ግብዣ በምታቀርቡበት ጊዜ፣ እባካችሁ በመምራት፣ በአጠገባቸው በመሄድ እና መንገዱን እንዲያገኙ እርዷቸው። ለማስተማር፣ ለመመስከር፣ ለመጸለይ፣ ወይም ለማገልገል ሲዘጋጁ እንዲተማመኑ እና ኃላፊነታቸውን በመወጣት ደስታን እንዲለማመዱ እነዚህን ውድ ትንንሾችን ምከሩ። ይህች ቤተክርስቲያናቸው እንደሆነች እንዲያውቁ እና ለአዳኙ መመለስ በመዘጋጀት ረገድ ወሳኝ ሚና እንሚጫወቱ ለመርዳት የሚያነሳሱ መንገዶችን ፈልጉላቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወታችን ትኩረት በሚሆንበት ጊዜ፣ የምንመኘው እና ያንን የምንፈልግበት መንገድ ለዘለአለም ይቀየራል። መለወጥ ሁሉንም ነገሮች ይቀይራል! ተፈጥሮአችንን ይለውጣል “በቀጣይነት ሁልጊዜም መልካም ለማድረግ እንጂ፣ ክፉ ለማድረግ ዝንባሌ እንዳይኖረን ያደርጋል።” የምናነበው፣ የምናየው፣ የምናዳምጠው እና የምናካፍለው ሁሉ ጊዜያችንን፣ ያለንን የምንጠቀምበትን መንገድ ይቀየራል። ልዩ በሆኑ፣ በሙያዊ ህይወታችን ላይ ወሳኝነት ባላቸው የትምህርት ተቋማት በሚኖረን ቃለ መጠይቅ እንዴት እንደምንመልስ እንኳን ልዩነትን ያመጣል።

በሕይወታችን በሁሉም ማዕዘኖች ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃን ማስረጽ አለብን። በቤታችን እና በዚህች ቤተክርስትያን በእያንዳንዱ ስብሰባ ላይ ስለ እርሱ ቅድመ–ምድራዊ አምላክነት ፣ መለኮታዊ ተልእኮው፣ እና በትንሳኤውም የወህኒ ቤትን ደጆች ሰብሮ የመውጣቱን እውነተኛነት ካልመሰከርን፣ የእኛ የፍቅር፣ የአገልግሎት፣ የታማኝነት፣ የትህትና፣ የምስጋና እና የርህራሄ መልእክቶች በተስፋ የመኖር አነቃቂ ንግግር ከመሆን ያለፈ ምንም ሊሆኑ አይችሉም። ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ የመለወጥ ኃይል አይኖርም፣ ለመነሳሳት ምንም ዓላማ አይኖረንም እንዲሁም የሕይወትን ውጣ ወረድ የሚያስታርቅ ምንም ነገር የለም። በኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ላይ ቸል ካልን፣ ለልጆቻችን ታልቅ የሆነ ጥፋት ሊሆንባቸው ይችላል።

ለልጆቻችንን እንደምንወዳቸው ስንነግራቸው የሰማይ አባታቸውና አዳኛቸው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወዳቸውም ጭምር እየነገርናቸው ነውን? ፍቅራችን ሊያጽናና እና ሊያነሳሳ ይችላል፣ ነገር ግን የእነርሱ ፍቅር መቀደስ ፣ ከፍ ከፍ ማድረግ እና መፈወስ ይችላል።

ይህ ኢየሱስ የልብወለድ ኢየሱስ፣ ወይም ቀለል ያለ ኢየሱስ፣ ወይም አካል የሌለው ኢየሱስ፣ ወይም ተራ የሆነ ኢየሱስ፣ ወይም የማይታወቅ ኢየሱስ፣ መሆነ የለበትም፣ ነገር ግን የከበረ፣ ሁሉን ቻይ፣ ከሞት የተነሣ፣ ከፍ ያለ፣ በአምልኮ የተሞላ፣ ኃያል፣ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ፣ የሆነለማዳን ብርቱ መሆን አለበት። አንድ ቀን በፊሊፒንስ ውስጥ ሳለሁ አንድ ትንሽ ልጅ በሚያሳምን መልኩ እንደመሰከረልን፣ “ለመዳን ብቁ የሆንን ነን!” በተቀደሰው እና በቅዱስ ስሙ “እግዚአብሔር [ታላቅ] ማስተስረያ አድርጎ [ባቆመው]” በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።