መለኮታዊ ሥልጣን፣ ማራኪዎቹ ወጣት ወንዶች
የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች፣ በእርሱ ሀይል፣ ስርዓቶች፣ እና ሀላፊነቶች ሁላችንንም እንደሚባርኩ እመሰክራለሁ።
ሽማግሌ አንደርሰን፣ የክህነት ስልጣንን እና የአዳኙን የሀጢያት ክፍያ ሀይል በተመለከተ ለሠጡን አስደናቂ መግለጫ አመሰግናለሁ።
በዚህ ጥር ወር በአንድ ዕሁድ ጠዋት፣ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ተቀምጬ ሳለሁ፣ ከደርዘን የሚበልጡ ወጣት ወንዶች ወደ አሮናዊ ክህነት ተሹመው ነበር። ከእግራችን ስር አለም ሲለወጥ ተሰማኝ።
በዓለም ዙሪያ፣ በእያንዳንዱ የጊዜ ሰቅ(ታይም ዞን)፣ እንደዚህ ባሉ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዲያቆናት፣ አስተማሪዎች እና ካህናት የእስራኤልን ማሰባሰብ በቤተክርስቲያኗ በሁሉም ቦታ ለህይወት ዘመን የክህነት አገልግሎት እንዲሾሙ መደረጉ ብልጭ አለልኝ።
በእያንዳንዱ ጥር ወር ወደ 100,000 የሚጠጉ ወጣቶች በክህነት ክፍል ይሾማሉ፣ ይህም በሥርዓት በኩል ከጆሴፍ እና ከኦሊቨር የዳግም መመለሥ ዘመን ወደ ኋላ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ብሩህ የሥልጣን መስመር ያገናኛቸዋል።
የእኛ ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜም በጣም ራሷን የምትገልፅ ቤተክርስቲያን አይደለችም። በዚህ፣ እኛም በእርግጥ ከሆነው በታች ነው የምንለው።
ነገር ግን አሁንም የእነዚህ አዲስ የተሾሙ የክህነት ስልጣን ተሸካሚዎች የነጎድጓድ ድምፅ በምድር ላይ ሲያስተጋባ ሣይ “የደስታ ቤተክርስቲያን” በምታደርገው ዓይነት መንገድ—ከጣራ ላይ በመሆን ድምፅን ከፍ አድርጎ መነገር አይገባውም ወይ ስል አሰብኩኝ። “ዛሬ፣ ነጋሪት መጎሠም፣ የሚንሿሿ ጸናጽል እና የሚተኮስ መድፍ መኖር አለበት። ሰልፍ መኖር አለበት!” ብዬ አሰብኩ።
የእግዚአብሄር ኃይል በእውነት ምን እንደሆነ በማወቃችን፣ በአምላካዊ ሥልጣን ምድርን በማጥለቅለቅ የዚህ ዓለም ምሳሌዎች መታወክ ምሥክር ነበርን።
እነዚህ ሹመቶች እነዚህ ወጣቶች በተከታታይ ጊዜያት እና ቦታዎች እራሳቸውን ወደሚያገኙበት የእነርሱ መኖር እና ጸሎቶች እና የያዙት የእግዚአብሔር ክህነት ሀይሎች በጥልቅ አስፈላጊ ወደሚሆኑበት ወደ የህይወት ዘመን አገልግሎት ያስጀምራቸዋል።
ይህ ቁጥጥር የሚደረግበት ድርጊት የተጀመረው ከእግዚአብሔር በተላከ አገልጋይ መልአክ ነው። ከሞት ት የተንሳው መጥምቁ ዮሐንስ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ተገለጠላቸው፣ እጆቹንም በራሳቸው ላይ ጭኖ እንዲህ አለ፦ “አገልጋይ ባልንጀሮቼ፣ የመላእክትን፣ እና የንስሀን ወንጌል፣ እና ለኃጢአት ስርየት በማጥለቅ የማጥመቅ አገልግሎት ቁልፎች የያዘውን የአሮንን ክህነት በመሲሁ ስም ለእናንተ እሰጣችኋለሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1)።
ዮሐንስ ይህንን ስልጣን በሙሴ ወንድም እና በክህነት አጋሩ ሥም “አሮናዊ ክህነት” ብሎ ሠየመው። በጥንት ጊዜ፣ የዚህ የአሮን ክህነት ተሸካሚዎች ማስተማር እና በስርዓቶች መርዳት ነበረባቸው—በወደፊቱ መሲህ፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ደቀመዝሙርነትን ያተኮሩ ስነስርዓቶችን መርዳት ነበረባቸው (ዘዳግም 33፥10 ተመልከቱ)።
የኦሪት ዘኍልቍ መጽሐፍ የሥርዓቱን ዕቃዎች የማደራጀት ሥራዎችን የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች ለሆኑት በግልጽ ይመድባል። “አሮንንና ልጆቹን አቁማቸው … መሠዊያዎቹንም፥ የሚያገለግሉበትንም የመቅደሱን ዕቃ … ሁሉ ይጠብቃሉ” (ዘኁልቁ 4:10፣ 31 ይመልከቱ)።
የብሉይ ኪዳኑ የእንስሳት መስዋዕትነት በአዳኝ ህይወት እና በኃጢያት ክፍያ ተፈጸመ እና ተተካ። ያ ጥንታዊ ሥርዓት አሁን የጌታ እራት ቅዱስ ቁርባን በምንለው ሥርአት ተተካ።
ጌታ ዛሬ፣ የዘመኑ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች በጥንት ጊዜ ያደርጉት የነበረውን ተመሳሳይ ነገር ያደርጉ ዘንድ ጌታ ይጠብቃቸዋል፦ ለማስተማር እና ሥርዓቶችን ለማስተዳደር—ሁሉም የኃጢያት ክፍያውን እንድናስታውስ ነው።
ዲያቆናት፣ አስተማሪዎች እና ካህናት በቅዱስ ቁርባን ሥርአት ላይ ሲያገለግሉ፣ ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ በረከቱን ይቀበላሉ፦ በግለሰብ ደረጃ ከዳቦውና ከውሃው በሚካፈሉበት ጊዜ የሚገቡትን ቃል ኪዳን ይጠብቃሉ ሆኖም እነዚህን ቅዱስ ተግባራት በማከናወን፣ ስለክህነት ሚናቸው እና ሀላፊነታቸው የበለጠ ይማራሉ።
የአሮናዎ ክህነት መዘጋጃ ክህነት ተብሎ ይጠራል ምክንያቱም ስርአቶቹ እነርሱ የማገልገልን ሃላፊነት እና በጌታ ስራ ላይ መሆንን እንዲያገኙ ያደርጋልና፣ እንዲሁም ሊተነበዩ በማይችሉ መንገዶች እንዲያገለግሉ ለሚጠሩበት ጊዜ ለወደፊት የክህነት አገልግሎት ይዘጋጃሉ—ይህም ተስፋ እና ህልም እንዲሁም ህይወት እና ሞት እንኳን በፍጥነት ሊለወጡበት በሚችሉበት ጊዜ ውስጥ በመንፈሥ የተነሣሱ በረከቶችን መስጠትን ይጨምራል።
እንዲህ ያሉ ከባድ ነገሮች ከባድ ዝግጅት ያስፈልጋቸዋል።
ትምሕርት እና ቃል ኪዳኖች፣ ዲያቆናት እና አስተማሪዎች፣ “ማስጠንቀቅ፣ ማብራራት፣ ማበረታታት፣ እናም ማስተማር፣ እናም ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ አለባቸው” በማለት ያብራራል”( (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥59)። ከእነዚህ ዕድሎች በተጨማሪ ካህናት “መስበክ፣ … እናም ማጥመቅ” አለባቸው (ትምሕርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥50)።
ሁሉም ነገር ብዙ ይመስላል፣ ነገር ግን በተግባር ሲታዩ እነዚህ ነገሮች በተፈጥሮ በመላው ዓለም የሚከናወኑ ናቸው።
አንድ ኤጲስ ቆጶስ አዲሱን የዲያቆን ቡድን አመራርን እነዚህን ህግጋት አስተማሯቸው። ስለዚህ፣ ወጣት አመራሩ በእነርሱ ቡድን እና አጥቢያ ውስጥ እንዴት ሊሠሩ እንደሚችሉ መነጋገር ጀመሩ። የሚያስፈልጋቸውን ለማወቅ እና ሄደውም ያንኑ ለማከናወን እንዲችሉ እድሜያቸው የገፉ የአጥቢያ አባላትን ለመጎብኘት መጀመር ወሠኑ።
ካገለገሏቸው መካከል የሌሎችን ምቾት የሚነሣው፣ ለሠው ክብር የማይሠጠው እና አንዳንዴም ጠበኛ ጎረቤት የሆነው አላን ይገኝበታል። የአላን ሚስት ዋንዳ የቤተክርስቲያኗ አባል ሆነች፤ ነገር ግን አላን፣ በእኛ አባባል ሊሠራበት የሚገባው ሠው ነበር።
ያም ሆኖ ዲያቆናቱ ከመንገዱ ላይ በረዶውን ሲጠርጉና የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎቹን በሚያወጡበት ጊዜ የሚናገረውን ስድብ በቀልድ መልክ ቸል በማለት ወደ ሥራ ገቡ። ዲያቆናትን መጥላት ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህም አላን በመጨረሻ ከእነሡ ጋር የነበረውን ጓደኝነት መውደድ ጀመረ። በአንድ ወቅት ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመጣ ጋበዙት።
“ቤተክርስቲያንን አልወድም” ሲል መለሰላቸው።
“ጥሩ፣ እኛን ትወደናለህ፣” “ስለዚህ ከእኛ ጋር ሂድ አሉት። ወደ ዲያቆናት ቡድን ሥብሠባችን መምጣት ትችላለህ።”
ከዚያም በኤጲስ ቆጶሡ ፈቃድ መጣ—ከዚያም መምጣቱን ቀጠለ።
ዲያቆናቱም አስተማሪዎች ሆኑ፣ እርሡን ማገልገላቸውን ሲቀጥሉም መኪኖችን እንዴት መጠገን እንደሚቻል እና ነገሮች እንዴት እንደሚሠሩ አስተማራቸው። ወደ አስተማሪነት የተለወጡት ዲያቆና ካህናት ሲሆኑ አለን “ልጆቼ” እያለ ይጠራቸው ነበር።
ለሚስዮን በትጋት እየተዘጋጁ ነበር ስለዚህም ከእርሱ ጋር የሚስዮናዊ ትምህርቶችን መለማመድ ይችሉ እንደሆነ ጠየቁት። በምንም እንደማያዳምጥ ወይም እንደማያምን መሀላ ገብቶ ነበር፣ ግን፣ አዎን በቤቱ ውስጥ መለማመድ ይችሉ ነበር።
ከዚያም አለን ታመመ። ተለሣለሠ።
አንድ ቀን፣ በቡድን ስብሠባ ላይ ማጨስ ያቆም ዘንድ እንዲፀልዩለት በትህትና ጠየቃቸው፣ እነርሡም ፀለዩለት። ነገር ግን ወደ ቤቱ ተከትለው የደበቀውን ትምባሆ ወሰዱበት።
የጤንነቱ መዛባት አለንን በሆስፒታሎች እና በማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ ቢያቆየውም፣ “ልጆቹ” በጸጥታ የክህነት ሥልጣንን በሥራ ላይ በማዋል እና ፍቅርን ያለ ግብዝነት በማሳየት አገለገሉት(see Doctrine and Covenants 121:41).።
አለን መጠመቅ እንደሚፈልግ ሲጠይቅ ተዓምሩ ቀጠለ— ነገር ግን ያ ከመሆኑ በፊት ከዚህ አለም በሞት ተለየ። እርሡ በጠየቀው መሠረት፣ ወደ ክህነት የተቀየሩት ዲያቆናቱ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ አስከሬኑን የሚሸከሙና ተናጋሪዎቹ ሆኑ፤ እነርሱም—በተገቢው ሁኔታ—አስጠነቀቁ፣ አብራሩ፣ አበረታታቱ፣ እናም አስተማሩ፣ እናም ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ጋበዙ።
በኋላም፣ የቀድሞ የዲያቆናት ቡድን ፕሬዚዳንት የነበረውን ለአለን በቤተመቅደስ ውስጥ በውክልና ያጠመቁት “ከአለን ልጆች” አንዱ ነበር።
መጥምቁ ዮሐንስ እንዲደረግ የተናገረውን ሁሉ አደረጉ። በመላው ቤተክርስቲያኗ እና በአለም ዙሪያ ሁሉ ዲያቆናት፣ አስተማሪዎች እና ካህናት የሚያደርጉትን አደረጉ።
የአሮን ክህነት ተሸካሚዎች እንዲያደርጉ ከተያዙት ነገሮች አንዱ፣ የቅዱስ ቁርባንን ስርዓት ያካትታል።
ባለፈው አመት አንድን በመንፈሥ የተነሳሳ ኤጲስ ቆጶስ እና አስደናቂ ባለቤቱን አገኘኋቸው። በቅርቡ በአንድ ቅዳሜ ጠዋት፣ ለልጃቸው ጥምቀት በመኪና እየሄዱ ሳሉ በደረሰው አደጋ ምክንያት ውዷ የሁለት አመት ሴት ልጃቸው የቴስ አሳዛኝ እና ድንገተኛ ሞት ደረሠባቸው።
በማግስቱ ጠዋት፣ የአጥቢያቸው አባላት የቅዱስ ቁርባን ስብሰባን ለማካሄድ በዚህች ፍጹም የሆነች ትንሽ ልጅ ሞት ምክንያት በስቃይ ውስጥ በመሆን በርኅራኄ ተሞልተው ተሰበሰቡ። በዚያ ጠዋት የኤጲስ ቆጶሱ ቤተሰብ በቤተክርስቲያን እንደሚገኙ ማንም የጠበቀ አልነበረም፣ ነገር ግን ስብሰባው ከመጀመሩ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት በጸጥታ ገቡና ቦታቸውን ያዙ።
ኤጲስ ቆጶሱ ወደ መድረኩ ሄዶ የተለመደውን በአማካሪዎቹ መካከል የሚቀመጥበትን መቀመጫውን አልፎ በቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛው በካህናቱ መካከል ተቀመጠ።
ማስተዋል እና ሠላም በሚፈለግበት በዚያ አስጨናቂ እና እንቅልፍ አልባ ምሽት፣ ቤተሰቡ በጣም የሚፈልገው—እንዲሁም አጥቢያው በጣም የሚፈልገውየቅዱስ ቁርባን ተስፋዎች ንግግር እንደሆነ ጠንካራ ግንዛቤ አግኝቷል። የአጥቢያ የአሮናዊ ክህነት ፕሬዚዳንታቸው፣ በሐዘን ላይ የነበረውን አባታቸው፣ ኤጲስ ቆጶሳቸው፣ የቅዱስ ቁርባን ቃል ኪዳን የሚሠጣቸውን ተሥፋ ሲናገር ለመስማት ነበር።
ስለዚህ ከጊዜ በኋላ ከካህናቱ ጋር ተንበርክኮ አባቱን አነጋገረ። በዚያ ወቅት በተከሰቱት ችግሮች፣ ማንኛውም ሰው በዚህ የህይወት ዘመን ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲናገር ከተፈቀደለት በጣም ኃይለኛ ቃላት የተወሰኑትን ተናገረ።
ዘለዓለማዊ ውጤት የሚያስከትሉ ቃላት።
የሥርዓት ቃላት።
የቃል ኪዳን ቃላት።
ከዚህ ህይወት ዓላማዎች —እንዲሁም የሰማይ አባት ለእኛ ካለው ዕቅድ እጅግ አስደናቂ ውጤቶች ጋር የሚያገናኘን መመሪያ።
በዚያ ዕለት ምዕመናኑ በዚያ ጸሎት ቤት ምን እንደሰሙ መገመት ትችላላችሁ?—በየእሁዱ በጸሎት ቤታችን ውስጥ በምንሰማቸው ቃላቶች ውስጥ ምን ሠምተው ሊሆን እንደሚችል መገመት ትችላላችሁ?
“አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ዳቦ ለሚቋደሱት ነፍሳት ሁሉ የልጅህን አካል በማስታወስ እንዲበሉት እና፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ እነርሱ የልጅህን ስም በላያቸው ላይ ለመውሰድ ፈቃደኞች መሆናቸውን፣ እና ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱና እርሱ የሰጣቸውን ትእዛዛት እንደሚጠብቁ ለአንተም ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜ እንዲኖራቸው ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን። አሜን። ”(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20:77). ተመልከቱ።
ከዚያም፦ “አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ውሀ የሚጠጡት ነፍሳት ሁሉ ለእነርሱ የፈሰሰውን የልጅህን ደም በማስታወስ ያደርጉት ዘንድ፣ ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱ ለአንተም፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ እንዲኖራቸው፣ ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን። አሜን።” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥79 ተመልከቱ።
እነዚህ መልካም አባት እና እናት ተሥፋው እንደተፈፀመ መሠከሩ። እነርሱ በእርግጥ ለዘለዓለማዊ መጽናናታቸው ሲሉ “የእርሱ መንፈስ አላቸው።”
የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች ከሃይሉ፣ ከሥርአቶቹ እና ከሃላፊነቶቹ ጋር “የመላእክትን እና የንስሃን ወንጌል፣ እና ለኃጢአት ስርየት በማጥለቅ የማጥመቅ አገልግሎት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1) ቁልፎች አማካኝነት ሁላችንንም ስለሚባርኩ ዘለአለማዊ ምስጋና አለኝ ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።