አጠቃላይ ጉባኤ
የዘለአለም ታላቅ ስጦታዎች፤ የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ፣ ትንሳኤ፣ ዳግም መመለስ
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


13:57

የዘለአለም ታላቅ ስጦታዎች፤ የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ፣ ትንሳኤ፣ ዳግም መመለስ

እያንዳንዳችን በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ፣ ትንሳኤ፣ እና ዳግም መመለስ---ሰላምን፣ መሆንን እና የዚያ አካል መሆንን-- በዘላቂነት እውነት እና ለዘለዓለም አስደሳች የሆነውን እናገኝ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ስም እጸልያለሁ፣ አሜን።

ከአመታት በፊት፣ በጠዋት የሚካሄደው የወንጌል ትምህርት ክፍላችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በቃል ይሸመድድ ነበር። እኔ በተፈጥሮ አጫጭር ምንባቦች ይስቡኛል። ይህም ዮሐንስ 11፥35ን—የሚያካትት ሲሆን በቅዱስ መጽሐፍ በጣም አጭሩ ጥቅስ፣ በእንግሊዘኛ ሁለት ቃላት ብቻ ያሉት ነው--ይህም “ኢየሱስ እንባውን አፈሰሰ” የሚለው ነው።

አሁን ለእኔ፣ ኢየሱስ በሀዘን እና በደስታ የሚያነባ መሆኑ እኚህን ተአምራዊ እውነታን የሚመሰክርልኝ ነው፦ መለኮታዊው የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ምድራዊው አለም መምጣቱ እና እንዴት ዘወትር ከእኛ ጋር ለመሆን እና እኛን ለመባርክ በስጋም መሰረት የተማረ መሆኑ ነው።

በሀዘንም ሆነ በደስታ ስናነባ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም በሆነ መንገድ ይረዳናል። የዘለአለም ታላቅ ስጦታዎች የሆኑት የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ፣ ትንሳኤ፣ ዳግም መመለስ፣ እጅግ በሚያስፈልጉን ጊዜ እርሱ ሊገኝልን ይችላል።

ኢየሱስ አለቀሰ።

ማርያም እና ማርታ ለሞተው ለወንድማቸው ለአልአዛር አልቅሰዋል። በርህራሄ ተሞልቶ፣ ኢየሱስ እንባውን አፈሰሰ። አልዓዛርንም ከሞት አስነሳ።

ኢየሱስ በፋሲካ ዋዜማ ኢየሩሳሌምን ተመለከተ። ዶሮ ጫጩቶቿን እንደምትሰበስብ፣ ህዝቡን ሊሰበስብ ባለመቻሉ፣ አለቀሰ። ሊሆን ይችል ስለነበረ ነገር በምናዝንበት ጊዜ ዛሬ ላይ የእርሱ የሃጢያት ክፍያ ተስፋን ይሰጠናል።

የአትክልት ስፍራው ባለቤት አገልጋዮቹን፣ “ለአትክልት ስፍራዬ ከዚህ የበለጠ ምን ላደርግለት እችላለሁ?” በማለት በጠየቃቸው ጊዜ አልቅሷል፣ ይህም ዛሬ የአገልግሎት ወንድሞች እና እህቶች እንደመሆናችን እኛንም ሊያካትት ይችላል።

ማርያም በተስፋ እጦት በመቃብሩ ስፍራ ቆመች። ኢየሱስም፣ ‘’አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሻለሽ?’’ በማለት በርጋታ ጠየቃት። “ለቅሶ ለሊቱን ሙሉ ሊቆይ እንደሚችል፥ ጥዋት ግን ደስታ እንደሚሆን” ያውቃል። ትንሳኤ ለሁሉም የንጋት ጸሃይን ያመጣል።

በመጽሐፈ ሞርሞን ምድሮች፣ ታማኝ ህዝቡ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ የኢየሱስ ደስታ ሙሉ ነበር። እርሱ ያነባል።

“አንድ በአንድም ህፃናቶቻቸውን ወሰዳቸውና፣ ባረካቸው፣ ስለእነርሱም ወደ አብ ፀለየ።

እናም ይህንንም ሲያደርግ በድጋሚ አለቀሰ።’’

ይህ ትንሳኤ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እርሱ የልባችንን ናፍቆት ይሞላል እንዲሁም የነፍሳችንን ጥያቄዎች ይመልሳል። እርሱ ከደስታ እንባችን በስተቀር፣ እንባችንን ያብሳል።

እንባዎቻችን ሲወርዱ፣ አንዳንድ ጊዜ ሀፍረት ይሰማንና ይቅርታ እንጠይቃለን። ነገር ግን በመራራ እና በጣፋጭ ሁኔታዎች ባለፍን ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወትን ህመሞች እና ደስታዎች የሚረዳ መሆኑን ማወቃችን እኛ ካለን በላይ ብርታትን ይሰጠናል።

በደቡብ አሜሪካ፣ አንድ አባት በሃዘን ይንሰቀሰቅ ነበር። በህይወቱ ውስጥ የደስታው ነጸብራቅ የነበረችው ወጣት ሴት ልጁ በሞት ሰለተለየችሁ “እርሷን ዳግም ለማየት የትኛውንም ነገር እሰጣለሁ፣” እያለ በክንዶቼ ላይ አነባ። እኔም እንዲሁ አነባሁ።

ኤልደር ጎንግ በሜክሲኮ ፑኤብላ ቤተመቅደስ ምርቃት ስነስረአት ላይ።

በሜክሲኮ፣ ፑኤብላ የቤተመቅደስ ምርቃት ላይ፣ የደስታ እንባ የአንዲትን ውድ እህት ፊት አራሰ። ገጽታዎቿ እምነትን እና መስዋእትነትን የሚያፈነጥቅ ነበር። እርሷም አለች፣ “ቶዶስ ሚስ ኢሆስ ኤስታን አኪ ኤን ኤል ቴምፕሎ ኦይ”—”ዛሬ ሁሉም ልጆቼ እዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ አሉ።” በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የአንድ ቤተሰብ ትውልዶች መሰባሰብ የደስታ እና ምስጋና እንባን ያመጣል።

በአስከፊው የእርስ በርስ ጦርነት፣ ቤተሰቦች እና ጎረቤቶች አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ለመነገር የማይችሉ ድርጊቶችን አጸሙ። መራር እንባዎች ቀስ በቀስ ለተስፋ መንገዶችንን እየለቀቁ ነው። ድምጿ እየተንቀጠቀጠ፣ የትንሽ መንደር ሴት እንዲህ አለች፣ “ጎረቤቶች፣ ወደ መቃብሬ ከመግባቴ በፊት፣ የጠፉትን የቤተሰባችሁን የት ልትፈልግጛቸው እንድአምትችሉ እንድታውቁ እፈልጋለሁ።”

መልከ መልካም የሆነ ሙሽራ እና እንደ ጸዳል ያማረች ሙሽሪት በጌታ ቤት ውስጥ እየታተሙ ነው። እንደ እርሱ፣ እርሷም 70 ዓመቷ ነው። ቆንጆዋ ሙሽሪት፣ ይህንን ቀን ብቁ በመሆን ስትጠባባቅ ነበር። በእፍረት ቬሎዋን ወዲህ እና ወዲያ ታወዘውዛለች። የደስታ እንባን አነባን። የእግዚአብሔር ቃልኪዳኖች ተፈጽመዋል። የእርሱ ቃልኪዳኖች በረከቶችን ያመጣሉ።

አንዲት ባሏ የሞተባትን ሴት በቤት ለቤት ጉብኝት እያስተማረ እያለ፣ ወጣቱ ቦይድ ኬ. ፓከር አዲስ ትምህርት ተማረ። ከባለቤቷ ጋር የነበራትን አለመስማማት አስከትሎ፣ ይቺህ እህት የመጨረሻ የሚያሳዝን ንግግር አደረገች። በዚያ ቀን ያልተጠበቀ ድንገተኛ አደጋ የባለቤቷን ህይወት ነጠቀ። መበለቲቱ በሀዘን ስሜት፣ “ለሃምሳ ዓመታት ያህል፣ እርሱ ከከንፈሮቼ የሰማቸው የመጨረሻ ቃላት እነዚያ ተናዳፊ፣ መርዛማ ንግግሮች መሆናቸውን በማወቅ በገሃነም ውስጥ ስኖር ቆይቻለሁ እያለች አነባች።’’

የኢየሱስ ክርስቶስ ፋሲካ በመጋረጃው በሁለቱም በኩል የሚገኙ ግንኙነቶቻችንን እንድንጠግን፣ እርቅ እንድናወርድ፣ እንድናስተካክል ይረዳናል። ኢየሱስ ሃዘንን ይፈውሳል፤ እርሱ ይቅርታን እንድናገኝ ያስችላል። እኛም ሆንን ሌሎች ከተናገርናቸው ወይም ካደረግናቸው ነገሮች ምርኮኛ አድርገው ከያዙ ነገሮች እርሱ ነጻ ሊያወጣን ይችላል።

በኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ፋሲካ የእግዚአብሄር ድጋፍ እንዲሰማን ያደርጋል። ይህ ዓለም በጣም ረጅም፣ በጣም አጭር፣ በጣም ሰፊ፣ በጣም ጠባብ፣ ጎበዝ፣ ቆንጆ ወይም በበቂ ሁኔታ መንፈሳዊ አለመሆናችንን ይነግረናል። በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በመንፈስ በመቀየር አድካሚ የሆነውን ፍጹማዊነት ማምለጥ እንችላለን።

በፋሲካ ደስታ፣ “ሞት ተሸነፈ፤ ሰውም ነጻ ሆነ። ክርስቶስ ድል ነስቷል።” የክርስቶስ ትንሳኤ ከሞት፣ በጊዜ ከሚመጣ ደካማነት እና በአካል ፍጹም ከአለመሆን ነጻ ያደርገናል። በተጨማሪም የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ መንፈሳዊነታችንን ይመልስልናል። ለሃጢያት እና መለያየት ማምለጫን ያስገኝልን ዘንድ፣ የደም እንባ በሚመስል መልኩ፣ ከእያንዳንዱ የሰውነቱ ቀዳዳ የደም ነጠብጣብ ይፈስ ነበር። እርስ በርሳችን እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር በሙላት እና በቅድስና ያዋህደናል። በሁሉም መልካም ነገሮች፣ በነበረው ብቻ ሳይሆን ሊሆን በሚችለው—ኢየሱስ ክርስቶስ በብዙ ይመልሳል።

የኢየሱስ ህይወት እና ብርሃን እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለውን ፍቅር ይመሰክራል። እግዚአብሔር አባታችን በሁሉም እድሜና ምድር ያሉትን ልጆቹን ሁሉ በመውደዱ ምክንያት፣ በብዙ ባህሎች እና ልምዶች ያለን እኛ ወደ እርሱ በመምጣት ሰላምን እና ሃሴትን ለማግኘት የእርሱን የፍቅር ግብዣ እናገኛለን። የትም እንሁን፣ ማንም እንሁን፣ እንደ አንድ ፈጣሪ ልጆች መለኮታዊ ማንነትን እንካፈላለን። በተመሳሳይ መንፈስ፣ የእስልምና፣ የአይሁድ እና ክርስትና እምነት ተከታዮች በአባታችን አብርሃም እና ግብጽ ውስጥ በነበሩ ክስተቶች የቃልኪዳን ግንኙነት አማካይነት ሃይማኖታዊ ቅርስን በጋራ ይካፈላሉ።

አባታችን አብርሃም ወደ ግብጽ መጥቷል እና ተባርኳል።

በግብፅ ለባርነት የተሸጠው ዮሴፍ፣ የፈርዖን ሕልም ትርጋሜው፣ ለሰባት ዓመታት ጥጋብ እና ለሰባት ዓመታት ረሃብ የሚመጣ እንደሆነ ያውቅ ነበር። ዮሴፍ ቤተሰቡን እና ህዝቡን ታደገ። ቃል ኪዳኖቻቸውን ለሚጠብቁ ለእነዚያ ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሚደረግላቸው ዮሴፍ የእግዚአብሔርን ታላቁን እቅድ እንዳየ አነባ።

በፈርኦን ቤት ውስጥ በግብጽ ያደገው ሙሴ ለእግዚአብሔር ልጆች መሰባሰብ ቁልፍን ተቀበለ በኋላም ዳግም መልሶ አመጣ።

ዮሴፍ፣ ማርያም፣ እና ኢየሱስ ወደግብጽ ሸሹ

ትንቢቱን በመፈጸም፣ ዮሴፍ፣ ማርያም፣ እና ህጻኑ ክርስቶስ በግብጽ መጠለያን ፈለጉ። በካይሮ፣ አንድ ለእምነቱ የተሰጠ ሙስሊም አማኝ‘ከበሬታ በተሞላው መንገድ “ቁርአን ዮሴፍ፣ ማርያም፣ እና ህጻኑ ኢየሱስ በእኔ ሃገር ደህንነትን እና ጥገኝነትን አግኝተው እነበር ያሳተምራል። በእኔ ሃገር፣ ኢየሱስ ጨቅላ ሆኖ እያለ ምግባችንን በልቷል፣ የመጀመሪያ እርምጃዎቹን አድርጓል፣ የመጀመሪያ ቃላቶቹን ተናግሯል። እዚህ በሃገሬ ውስጥ፣ ዛፎች ለእርሱ እና ለቤተሰቡ ፍሬያቸውን ለመስጠት ወደታች ዝቅ ብለውለት እንደነበር እናምናለን። የእርሱ በእኔ ሃገር መሆን ህዝባችንን እና ምድራችንን ባርኳል’’ በማለት ተናግሯል።

የእግዚአብሔር የሞራል እና ምድራዊ ምርጫዎች ከራሳችን ልምዶች እንድንማር ይፈቅዱልናል። አንዳንዶቹ ታላላቅ የህይወት ትምህርቶች ጭራሽ ከማንመርጣቸው ነገሮች ይመጣሉ። በፍቅር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ታች ወርዷል እንዲሁም ከሁሉም ነገሮች በላይ ወደ ላይ ወጥቷል። እርሱ ለፈጠራ እና ለደስታ፣ የምላሽን ተስፋ በማይጠይቅ ደግነት፣ ለንሰሃ እና ይቅርታ እምነት ባለን መለኮታዊ ችሎታዎቻችን ሃሴትን ያደርጋል። ብዙውን ጊዜ በሰዎች ምርጫ በሚመጡ—ሰማያት እና የሰማይ አምላክ እንደሚያደርገው ሁሉ-—እርሱ ለአብዛኛዎቹ ሰብአዊ ስቃዮቻችን፣ ጭካኔ፣ ሚዛናዊ ያለመሆን በሃዘን ያነባል።

እያንዳንዱ የፋሲካ የጸደይ ወቅት የሚመሰክሩት መንፈሳዊ ተከታታይነት እና ግንኙነትን ነው ይህም ሁለቱም የሃጢያት ክፍያው፣ የትንሳኤው፣ እና በኢየሱስ ክርስቶስ የዳግም መመለሱን መለኮታዊ ንድፍ አካል መሆናቸውን ነው። ይህ የተቀደሰ እና ምሳሌያዊ ግንኙነት በድንገት ወይም በአጋጣሚ የሚመጣ አይደለም። የሆሳዕና እሁድ፣ ቅዱስ ሳምንት፣ እና ፋሲካ የክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤን ያከብራሉ። እንደዛሬው፣ በእያንዳንዱ ሚያዝያ 6፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን መመስረት እናስባለን። ይህ ዳግም መመለሱ በየአጠቃላይ ጉባኤው በእያንዳንዱ ሚያዝያ የመጀመሪያ እሁድ የመሰብሰባችን ዋነኛው ምክንያት ነው።

ዳግም መመለሱ በተጨማሪ የመጣው ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሙሴ፣ እና ኤልያስ አዲስ በተመረቀው የከርትላንድ ቤተመቅደስ በፋሲካ እሁድ፣ 1836 (እ.አ.አ) የክህነት ቁልፍን እና ስልጣንን በመለሱ ጊዜ ነው። በዚያ አይነት በዚያ ቀን ለኋለኛው ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ልጆቹን ለመሰብሰብ፣ የእርሱን ልጆች ወደ እርሱ ለመመለስ፣ እና ቤተሰቦችን ለዘለአለም ለማገናኘት የእግዚአብሔር ስልጣን እና በረከት መጣ። ዳግም መመለሱ በዚያ ቀን በፋሲካ በመከናወን ትንቢት እንዲፈጸም አድርጓል።

ኤልደር ጎንግበከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ።

የከርትላንድ ቤተመቅደስን ጨምሮ፣ በቅርቡ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች በራእይ እግዚአብሔር አብን እና ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ያዩበትን ቅዱሳን ስፍራዎች ጎብኝቻለሁ። ነቢዩ ጆሴፍ መንግስተ ሰማይ ምን እንደሚመስል አይቷል። በሰማይ፣ የሰማይ አባት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት፣ ‘’የእጆቹን ስራዎች ሁሉ በአንድነት በክብር መንግስት ውስጥ ’’ አስቀምጧል። በብቸኝነት የዚህ አካል ያልሆኑት በፈቃዳቸው ‘’አብ ከገለጠላቸው በኋላ ወልድን የካዱት ናቸው።’’

የምድራዊ አገልግሎቱ እንደጀመረ፣ በየትኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ምድር፣ በየትኛውም ሁኔታ—ኢየሱስ ሁላችችንም፣ ልንቀበለው በፈቀድነው ሁሉ ሊባርከን ተልእኮውን ይፋ አደረገ። ለአርባ ቀናት ከጾመ በኋላ፣ ኢየሱስ ወደ ምኩራብ ገባና “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበሩትን እፈውስ ዘንድ፣ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል’’ በማለት አነበበ።

ድሆች፣ ልባቸው የተሰበረ፣ የታሰሩ፣ ማየት የተሳናቸው፣ በደዌ የተያዙ--ያ እያንዳንዳችን ነን።

የኢሳያስ መጽሐፍ የተስፋ፣ ነጻ የመውጣት፣ የእርግጠኝነት መሲሀዊ ተስፋን ይቀጥላል፤ “በጽዮን አዝነው ላሉት፣…ልባቸው የተሰበረውን ይጠግን ዘንድ … የሚያለቅሱትንም ሁሉ ያጽናና ዘንድ … በአመድ ፋንታ አክሊልን፣ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፣ በሃዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጎናጸፍያ ይሰጣቸው ዘንድ ይህን ያደርጋል።”

በመሆኑም፣ ‘’በእጅጉ በጌታ ሃሴት አደርጋለሁ፣ ነፍሴም በአምላኬ ሃሴትን ታደርጋለች፤ የደህንነትን ልብስ አልብሶኛልና፣ በጽድቅም መጎናጸፊያ ሸፍኖኛልና’’ በማለት እንጮሃለን።

በፋሲካ እያንዳንዱ ወቅት፣ በምሳሌያዊነት፣ በኢየሱስ ዘለዓለማዊ ታላቅ ስጦታ ውስጥ---የእርሱን የሃጢያት ክፍያ፣ የእርሱን (እና የእኛን የራሳችንን የተስፋ) ቀጥተኛ ትንሳኤ፣ የእግዚአብሄርን ልጆች ሁሉ በሚባርክ የክህነት ቁልፎች እና ስልጣን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዳግም መመለስ እናከብራለን። በደህንነት ልብስ እና በጽድቅ መጎናጸፊያ ሃሴትን እናደርጋለን። “ሆሳእና ለእግዚያብሄር እና ለበጉ !“ በማለት እንጮሃለን።

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና።

እያንዳንዳችን በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ፣ ትንሳኤ፣ እና ዳግም መመለስ—ሰላምን፣ ሆኖ መገኘትን እና የዚያ አካል መሆንን—በዘላቂነት እውነት እና ለዘለዓለም አስደሳች የሆነውን እናገኝ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ስም እጸልያለሁ፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. አልማ 7፥11–12 ይመልከቱ። በቅዱስ ቁርባን የቃልኪዳን ተስፋ ውስጥም እንዲሁ፤ በተቀደሰው የቁርባን ስርአት፣ አብን በመጥራት የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ፣ ሁል ጊዜ ‘’እርሱን ለማስታወስ እና ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ መንፈሱ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር እንዲሆን ቃል እንገባለን’’ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77)።

  2. ዮሐንስ 11፥33-35፣ 39-44 ተመልከቱ።

  3. ሉቃስ 19፥41–44 ተመልከቱ፤ እንዲሁም ማቴዎስ 23፥37 ተመልከቱ፤ ሉቃስ 13፥34

  4. ያዕቆብ 5፥41

  5. ዮሐንስ 20፥15 ይመልከቱ።

  6. መዝሙር 30፥5

  7. 3 ኔፊ 17፥21–22

  8. መዝሙር 107፥9ያዕቆብ 33፥3 ተመልከቱ።

  9. ኢሳይያስ 25፥8 ተመልከቱ።

  10. አልማ 26፥12 ተመልከቱ።

  11. ቦይድ ኬ. ፓከር፣ “ቅዱሳን በጥንቃቄ ያድራሉ፣” ኤንዛይን፣ ጥር 1973 (እ.አ.አ)።

  12. ‘’እርሱ ተነስቷል!፣’’ መዝሙሮች ቁ. 199፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የምስራቹን ዜና ያስተጋባል 2 ኔፊ 9፥10’’አቤቱ፣ ከዚህ ከሚያስቀይመው አስፈሪ እቅፉ፣ አዎን፣ እኔ የስጋ ሞት፣ እናም ደግሞ የመንፈስ ሞት ብዬ የምጠራው ያ አስፈሪ ሞትና ሲኦልን ሊያስመልጠን መንገዱን ያዘጋጀልን የአምላካችን ጥሩነት እንዴት ታላቅ ነው።’’

  13. ዘፍጥረት 37-47 ይመልከቱ። ዮሴፍ አባቱን፣ ያእቆብን፣ እና ቤተሰቡን ወደ ግብጽ ማምጣቱ ከረዥም ጊዜ በኋላ የተገናኙትን አባት እና ልጅ የሚወክል ነው። ሌሂ እና ቤተሰቡን ጨምሮ የያእቆብ ቤተሰብ እና የቃልኪዳኑ ዘር የሚጠበቁበትን መንገድ ነው። (1 ኔፊ 5፥14–156፥2 ተመልከቱ።)

  14. ዘፍጥረት 45፥1-8 ይመልከቱ።

  15. ሮሜ 8፥28ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥2498፥3ይመልከቱ።

  16. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥11፤ ደግሞም ዘጸዓት 9፥ 2-10ሉቃስ 9፥ 28-36 ይመልከቱ።

  17. ማቴዎስ 19፥13–15ይመልከቱ።

  18. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6122፥8 ይመልከቱ።

  19. ሙሴ 7፥28 ይመልከቱ።

  20. ፋሲካ በመጋቢት ወይም በሚያዝያ ሊመጣ እንደሚችል እና ጸደይ በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ በመጋቢት ወይም በሚያዝያ እንደሚሆን ስለ ፋሲካ የጸደይ ወቅት እንናገራለን። በየትኛውም የጸደይ የፋሲካ ቀን ይሁን፣ የፋሲካ ወቅት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የመጣውን ዘለዓለማዊ ታላቅ ስጦታ ያስታውሰናል።

  21. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥3115፥4 ይመልከቱ።

  22. በእያንዳንዱ የፋሲካ ወቅት የሚመጣው የተቀደሰ አከባበር አንዳንድ ጊዜ በትክክል ይገጥማል። ለምሳሌ፣ በ2026 እና በ2029 (እ.አ.አ) ፋሲካ እና አጠቃላይ ጉባኤ በአንድ እሁድ ይውላሉ። የሆሳዕና እሁድ እና የአጣቃላይ ጉባኤ በ2031 እና በ2034 (እ.አ.አ) በአንድ የእሁድ ቀን ይውላሉ። በ2026 እና በ2029 (እ.አ.አ) የቂጣ በአል በፋሲካ አካባቢ ይውላል። እነዚህ በዓላት በትክክል ይግጠሙም አይግጠሙ፣ በአንድነት የመግጠማቸው እድል በአጋጣሚ ወይም በድንገት እንዳልሆነ እንገነዘባለን፤ ይህ የተቀደሰ እና ምሳሌያዊ ነው።

  23. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110 ይመልከቱ።

  24. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥43፤ ደግሞም ቁጥር 42 ይመልከቱ።

  25. ፕሬዚዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ ሲያስተምሩ፤ ‘’የዚህች በዳግም የተመለሰች ቤተክርስቲያን የትምህርት እና የፖሊሲዎች አላማ የእግዚአብሔርን ልጆች በሰለስቲያል ክብር ለደህንነት፣ በተለይም በትልቁ ክብር ውስጥ ለዘለዓለማዊነት ማዘጋጀት ነው’’(“Kingdoms of Glory [የግርማ መንግስት],” ሊያሆና, ህዳር 2023 (እ.አ.አ))።

  26. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፣43

  27. ሉቃስ 4፥18ደግሞም ኢሳያስ 61፥1 ተመልከቱ።

  28. ኢሳይያስ 61፥3

  29. ኢሳይያስ 61፥10

  30. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥79

  31. ዮሐንስ 3፥16