አጠቃላይ ጉባኤ
ወላጆቻችን ላጸኑት እምነት እውነተኛ እንሁን
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:0

ወላጆቻችን ላጸኑት እምነት እውነተኛ እንሁን

እባካችሁ ከናንተ ቀድመው ከመጡት፣ ተማሩ እንዲሁም ከእምነታቸው እና ከምስክርነታቸው ጥንካሬን አድኙ።

የቤተመቅደስ ምልከታ ለማድረግ የናሽቪል ቴነሲ ቤተመቅደስን እየጎበኘሁ ሳለ፣ ይህንን ውብ የጌታ ቤት በመመልከት በዚህ ምደባ ውስጥ የእግር ጉዞ የማድረግ እድልን አገኘሁ። በተለይ በቅርንጫፍ ቢሮው ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የሜሪ ዋንላስ ቀጥል የተሰኘውን ሥዕል ስመለከት በጣም ተገረምኩ ።

ከሥዕሉ ጀርባ ያለው ታሪክ ይህ ነው፡

“በሚዙሪ ውስጥ በ1862 (እ.አ.አ) የ14 ዓመቷ ሜሪ ዋንላስ የአካል ጉዳተኛ አባቷ እና አራት ታናናሽ ወንድሞቿ ወደ ታላቁ ሶልት ሌክ ሸለቆ እንደሚደርሱ ለሞት ለተቃረበች የእንጀራ እናቷ ቃል ገባች።… ሜሪ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ አባቷ የነበሩበትን ሠረገላ የሚጎትቱትን በሬዎችና የወተት ላሞች እየነዳች ትሄድ ነበር፤ እንዲሁም ወንድሞቿንና እህቶቿን ትንከባከባቸው ነበር። ከእያንዳንዱ ቀን ጉዞ በኋላ ለምግብነት የሚበቅሉ ተክሎችን፣ አበቦችንና እንጆሪ በመሰብሰብ ቤተሰቡን ትመግባለች። የእሷ ብቸኛ አቅጣጫ ጠቋሚ የነበረው ደመናው ተራሮች እስኪሆኑ ድረስ ወደ ምዕራብ መጓዟን እንድትቀጥል የተሰጣት መመሪያ ነበር ።

“ፀደይ እና በጋን ሙሉ በመጓዝ መስከረም ላይ ዩታ ቫሊ ደረሱ። አባቷ የሞተው ቤተሰቡ በዩታ ግዛት ከሰፈረ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሲሆን ሜሪ ከጊዜ በኋላ እዚያው አግብታ የራሷን ቤተሰብ መሰረተች።”

ይህ የ14 አመት ወጣት ሴት እምነት እና ጥንካሬ አስደናቂ ታሪክ ነው፣ ይህም ዛሬ እያንዳንዳችንን “እንድንቀጥል” ሊረዳን ይችላል።

“ብቻ ቀጥሉ” ወይም በትውልድ አገሬ በደች ቋንቋ ፣ ግዎን ዶርጋን በመባል የሚተረጎመው፣ የእናቴና የአባቴ የዕድሜ ልክ መፈክር ነዉ።

ወላጆቼ እና አማቶቼ በቤተሰባችን ውስጥ ቀደምት መስራቾች ናቸው። በየቀኑ ወደ ቤተክርስቲያን በጌታ ማህደር እየመጡ እንዳሉ ሁሉ እነርሱም የራሳቸውን “ሜዳ” ተሻግረዋል። ታሪካቸው ከበሬዎችና ከሠረገሎች ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ቢሆንም ወደፊት በሚመጣው ትውልድ ላይም ተመሳሳይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።

በወጣትነት እድሜያቸው ወንጌሉን ተቀብለው ተጠመቁ። የሁለቱም ወላጆቼ የልጅነት ሕይወት አስቸጋሪ ነበር። አባቴ ያደገው ጃቫ ኢንዶኔዥያ በምትባል ደሴት ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከቤተሰቡ በግዳጅ ተለይቶ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ገባ፤ በዚያም ገና በለጋ ዕድሜው በቃላት ሊነገር የማይችል ችግር አጋጥሞት ነበር።

እናቴ ያደገችው በፈራረሰ ቤት ውስጥ ሲሆን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በረሃብና በመከራ ተሰቃይታ ነበር። እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ቱሊፕ ስሮችን መመገብ ነበረባት። በአባቷ ድርጊት ምክንያት፣ እንዲሁም ተከትሎ እናቷን መፍታቱ፣ አንዳንድ ጊዜ የሰማይ አባትን እንደ አፍቃሪ አባት ማየት አስቸጋሪ አድርጎባት ነበር።

ወላጆቼ በቤተክርስቲያን ፕሮግራም ላይ ተገናኙና ብዙም ሳይቆይ በበርን ስዊዘርላንድ ቤተመቅደስ ለማግባት እና ለመታተም ወሰኑ። በባቡር ጣቢያው እየጠበቁ ወደ ቤተ መቅደስ ለመሄድ ያጠራቀሙትን ጥቂት ገንዘብ ለመጨረሻ ጊዜ ከተጠቀሙ በኋላ እንዴት መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንደሚያሟሉ ግራ ቢገባቸውም ሁሉም ነገር እንደሚሳካላቸው እርግጠኞች ነበሩ። እንዲህም ሆነላቸው!

ቤተሰባቸውን በአምስተርዳም እምብርት ላይ ከሚገኝ በጣም ትንሽ ባለ አንድ ክፍልአፓርታማ ውስጥ ማሳደግ ጀመሩ። ለበርካታ ዓመታት ልብሳቸውን በእጃቸው ካጠቡ በኋላ የማጠቢያ ማሽን ለመግዛት የሚያስችል በቂ ገንዘብ አጠራቀሙ። ዕቃውን ከመግዛታቸው ትንሽ ቀደም ብሎ ጳጳሱ ጎበኛቸው እና በአምስተርዳም የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለመገንባት መዋጮ እንዲደረግላቸው ጠየቁ። ለማጠቢያ ማሽኑ ያጠራቀሙትን ሁሉ ለመስጠት ወሰኑና ልብሳቸውን በእጅ ማጠብ ቀጠሉ።

በቤተሰብ ውስጥ እንደ ማንኛውም ቤተሰብ ሁሉ እኛም አንዳንድ ችግሮች ያጋጥሙን ነበር። በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት ስለነበርው በሁሉም ዓይነት ፈተናዎችና ችግሮች ድጋፍ እንደተደረገለት ልክ አልማ ታሪኩን ለልጁ ለሄላማን ሲያካፍል እንደነበረው፣እነዚህም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት ጠንካራ እና ጥልቅ እንዲሆን አድርገዋል።

በወጣትነት ዕድሜያቸው ብዙ ፈተናዎች ያጋጠሟቸው ሁለት ሰዎች ልመኘው ከምችላቸው ወላጆች ሁሉ የተሻሉ ሊሆኑ የቻሉት እንዴት ነው? መልሱ ቀላል ነው:- ወንጌልን ሙሉ በሙሉ ተቀብለው እስከዚህ ቀን ድረስ በቃል ኪዳናቸው በመኖራቸው ነው!

ከ65 ዓመታት በላይ በትዳር ከቆየች በኋላ በአልዛይመር በሽታ ትሠቃይ የነበረችው እናቴ በየካቲት ወር አረፈች። በ92 ዓመቱ አሁንም ቤት ውስጥ ይኖር የነበረው አባቴ እሷ እስከምትሞትበት ጊዜ ድረስ በተቻለው መጠን ደጋግሞ ይጠይቃት ነበር። ከጥቂት ጊዜ በፊት ለታናናሽ ወንድሞቼና እህቶቼ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በኢንዶኔዥያ ካምፕ ውስጥ ያሳለፈውን አሰቃቂ ገጠመኞች በመጥቀስ ሚስቱ በዚህ አሰቃቂ በሽታ ስትታመምና ሲብስባት እንዲሁም ዋነኛ እንክብካቤዋን ለሌሎች በአደራ መስጠት የነበረበትና ለብዙ ዓመታት ከጎኗ ሊሆን የማይችልበትን አስከፊ ሁኔታ ገለጸላቸው። የእነርሱ መርህ የነበረው እና አሁንም “ቀጥል” የሚለው ነው፣ በክርስቶስ ፍጹም ተስፋ በመጨረሻው ቀን ለመነሳት እና ከእርሱ ጋር ለዘላለም በክብር ለመኖር ነው።

እምነታቸው እና ምስክርነታቸው ከእነርሱ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶች የሚያነሳሳ ጥንካሬ ነው።

ባለቤቴ ባደገችበት መንደር ውስጥ፣ ጥሩ የቤተ ክርስቲያን ሂያጅ ሰዎች የሆኑት ወላጆቿ፣ እንደ ወጣት ባልና ሚስት ጥንዶች እና የሁለት አመት እድሜ የነበራት እና ብቸኛ ልጃቸው ባለቤቴ ሆነው የተመለሰውን ወንጌል ተቀበሉ። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ለመሆን በመወሰናቸው በመንደሩ ሰዎች እና በቤተሰባቸው ሲገለሉ በህይወታቸው ውስጥ ታላቅ ተፅዕኖ ነበረው። ለቤተሰብ አባላት የፍቅር ማስታወሻዎችን መስጠትና በማኅበረሰቡ ውስጥ በማገልገል በመጨረሻም ተቀባይነት ለማግኘት ብዙ ዓመታት ፈጅቶባቸው ነበር፣።

በአንድ ወቅት የባለቤቴ አባት ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ሲያገለግል በሐሰት ተከሶ ከጥሪው ተነስቶ ነበር። አማቴ በጣም ከመጎዳቷ የተነሳ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ይኖርባቸው እንደሆነ ባሏን ጠየቀችው። ይህ የሰዎች ቤተ ክርስቲያን ሳይሆን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ስለሆነ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄዳቸውን እንደሚቀጥሉ ምላሽ ሰጣት።

እውነት ወደ ብርሃን እስኪመጣና ይቅርታ ከመጠየቁ በፊት የተወሰነ ጊዜ ወስዶበታል ። ሊሰብራቸው ይችል የነበረ ሁኔታ ጠንካራና ጽኑ እምነትን ጨመረላቸው።

አንዳንዶቻችን በመከራቸው ሁሉ በታማኝነት የጸኑትን የወላጆቻችንን እምነትና ምስክርነት አቅልለን የምንመለከተው ለምንድን ነው? ስለ ነገሮች ግልጽ የሆነ ግንዛቤ የላቸውም ብለን እናስባለን? አይደለም፤ ደግሞም አልተታለሉም! ከመንፈስ ጋር ብዙ ተሞክሮዎችን አግኝተዋል፣ ከነብዩ ጆሴፍ ጋር “እኔ አውቄዋለሁ፣ … እና ልክደው አልችልም።” ማለት ይችላሉ።

የህፃናት መዝሙር መፅሀፍ ውስጥ ስለሚገኘው የሄለማን ሰራዊት መዝሙር አትወዱም?

ተወልደናል እንደ ጥንቱ ኔፊ

ጌታን ከሚወዱ ከመልካም ወላጆች።

ተምረናል እንዲሁም እንረዳለን

ጌታ እንዳዘዘው ማድረግ እንዳለብን።

እናቴ በልጅነት ጊዜ እንዳጋጠማት ባይሆንም፣ እናንተ “ጌታን ከሚወዱ መልካም ወላጆች” እና ለሌሎች የጽድቅ ምሳሌ ከሚሆኑ ወላጆች አንዱ መሆን ትችላላችሁ።

ስንዘምር ይህ እውነት እንደሆነ ይሰማናልን? “የሄለማን ሠራዊት” እንደሆናችሁ እና “ለዓለም የእርሱን እውነት የምታመጡ የጌታ ሚስዮናውያን” እንደሆናችሁ ይሰማችኋልን? ይህን መዝሙር በብዙ የFSY ዝግጅቶች እና ሌሎች የወጣቶች ስብሰባዎች ላይ ስዘምር በብዙ አጋጣሚዎች ተሰምቶኛል።

ወይስ “ለእምነት እውነተኛ” የሚለውን መዝሙር ስንዘምር ምን ይሰማናል?

የጽዮን ወጣቶች መድከም አለባቸው

ለእውነት እና ትክክለኛ ጥብቅና ለመቆም?

ጠላት ክፉኛ ሲያጠቃ

“ውጊያውን መሸሽ ወይም መተው አለብን?” የለብንም!

ወላጆቻችን ላጸኑት እምነት እውነተኛ እንሁን።

መጪው ትውልዶች የትም ብትሆኑ እና እራሳችሁን በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ራሳችሁን ብታገኙ እባካችሁ ከናንተ ቀድመው ከመጡት፣ ተማሩ እንዲሁም ከእምነታቸው እና ከምስክርነታቸው ጥንካሬን አድኙ። ምስክርነትን ለማግኘት ወይም ለማሳደግ፣ መስዋዕትነት መከፈል እንዳለበት እንድትገነዘቡ እና “መስዋዕት የሰማይ በረከቶችን እንደሚያመጣ” እንድትረዱ ይረዳችኋል።

ውድ ነቢያችን ፕሬዚዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን፣ ለወጣቶች የሚያስደስት እና የሚያነሳሳ ግብዣ ያደረጉት እንዲህ ነበር፦ “ እያንዳንዱ ብቁ የሆነ “ሁሉ፣ የሚችል ወጣት ወንድ ልጅ በሚስዮን ለማገልገል እንዲዘጋጅ እና እንዲያገለግል ጌታ እንደጠየቀ አበክሬ አረጋግጣለሁ። ለኋለኛው ቀን ቅዱሣን ወጣት ወንዶች፣ ሚስዮናዊ አገልግሎት የክህነት ሃላፊነት ነው። …

እናንተ ወጣት እና የምትችሉ እህቶች፣ ሚስዮን ሃያል የሆነ፣ ነገር ግን በአማራጭነት የቀረበ፣ እድል ነው።”

እንደ አገልግሎት ወይም እንደ አስተማሪ ሚስዮናዊ ልትጠሩ ትችላላችሁ። ሁለቱም አይነት ሚስዮኖች፣ እያንዳንዳቸው በራሳቸው ልዩ እና ሀይለኛ መንገድ ነፍስን ወደ ክርስቶስ በማምጣት ተመሳሳይ አላማ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

በሁለቱም የአገልግሎት ዓይነቶች፣ ጌታን እንደምትወዱት እና እርሱን በደንብ ማወቅ እንደምትፈልጉ ታሳያላችሁ። አስታውሱ “ጌታውን ያላገለገለውን፥ ለእርሱም እንግዳ የሆነን፥ ከልቡም አሳብየራቀውን እንዴት ያውቀዋል?”

ሁላችንም፣ በወንጌል ውስጥ የመጀመሪያው ትውልድም ሆንን አምስተኛው፣ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላልፈው የእምነት፣ የጥንካሬ፣ እና የሰማያዊ ቁርጠኝነት ታሪኮች የትኞቹ እንደሆኑ እራሳችንን መጠየቅ አለብን።

ሁላችንም አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በተሻለ ሁኔታ ለማወቅ እና እርሱን የህይወታችን ማዕከል ለማድረግ በምናደርገው ጥረት እንቀጥል። አስቸጋሪ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ ጸንተን መቆም እንድንችል ልንገነባበት የሚገባን ዓለት እርሱ ነው።

“ወላጆቻችን ላጸኑት እምነት እውነተኛ እንሁን፣ ሰማዕታት ላጸኑት እውነተኛ እውነት፣ ለእግዚአብሔር ትእዛዝ፣ በነፍስ፣ በልብ፣ በእጅ፣ ሁልጊዜ ታማኝና እውነተኛ ሆነን እንቆማለን።” በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “The Story Behind Carry On,” alyoung.com።

  2. አልማ 36፧27

  3. አልማ 36፥28 ይመልከቱ።

  4. የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥25

  5. “We’ll Bring the World His Truth,” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 172–73

  6. (የልጆች መዝሙር መፅሀፍ፣ 172null73።)

  7. “True to the Faith” መዝሙር፣ ቁጥር 254።

  8. “Praise to the Man,” Hymns, no. 27.

  9. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የሰላምን ወንጌል መስበክ፣“ ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 6።

  10. ሞዛያ 5፥13

  11. ሔለማን 5፥12 ተመልከቱ።

  12. Hymns, no. 254.