“መለኮታዊ እገዛ ለምድራዊ ህይወት ይጠቅማል”
የሰማይ አባታችን እቅድ በሟችነት ጉዞዎቻችን ውስጥ እኛን ለመምራት እርዳታዎችን ይሰጣል።
፩.
በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል፣ እግዚአብሔር ስለ ቅድመ-ምድር ህይወታችን ጥቂት ነገሮችን ገልጧል። በዚያም፣ እንደ እግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች ሆነን ኖረናል። እግዚአብሔር ልጆቹን እንዲያድጉ መርዳት ስለፈለገ፣ አካል የምንቀበልባትን፣ በልምድ የምንማርባት፣ መለኮታዊ ባሕርያትን የምናዳብርባት እና የአምላክንም ትእዛዛት የምንጠብቅ እንደሆነ ለማየት ምድር ለመፍጠር ወሰነ። ብቁ የሆኑት “በራሳቸው ላይ ክብር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ይጨመርላቸዋል” (አብርሃም 3፥26)።
የዚህን መለኮታዊ እቅድ ሁኔታዎች ለመመስረት፣ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አዳኛችን እንዲሆን መረጠ። ሉሲፈር፣ ያቀረበው አማራጭ የሰውን የመምረጥ ነጻነት ያጠፋ ነበር፣ ሰይጣን ሆነ እናም “ወደ ታችም ተጣለ።” ወደ ምድርም የተጣለ እና የሟችነት ሕይወትን መብት የተነፈገው ሰይጣን “[የእግዚአብሔርን ድምጽ] የማያደምጡትን ሁሉ የሚያታልለው እና ሰዎችን እንዳያዩ አድርጎ በፈቃዱም እንደ እስርኞች የሚመራቸው” በመሆን እንዲሞክር ተፈቅዶለታል” (ሙሴ 4፥4)።
ለልጆቹ የሟች ህይወት እድገት የእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ ውስጥ “ለሁሉም ነገሮች ተቃራኒ መኖሩን” (2 Nephi 2:11).እንዲያውቁ አስፈላጊ ነበር። አካላዊ ጡንቻዎቻችን ከመሬት ስበት ህግ ጋር ሳንጣር ማደግ ወይም ማቆየት እንደማይቻል ሁሉ ሟች እድገትም እኛን ከሰይጣን ፈተናዎች እና ከሌሎች ሟች ተቃውሞዎች መቃወምን ይጠይቃል። ለመንፈሳዊ እድገት እጅግ አስፈላጊ የሆነው በመልካም እና በክፉ መካከል የመምረጥ መስፈርት ነው። መልካምን የመረጡ ወደ ዘላለማዊ እጣ ፈንታቸው ሂደት ይቀጥላሉ። ክፋትን የሚመርጡ—በሟችነት ህይወት ውስጥ በሚመጡ ፈተናዎች ሁሉም እንድሚወድቁ ሁሉ—አፍቃሪው አምላክ ሊያቀርበው ያዘጋጀውን፣ የማዳን እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
፪.
እስካሁን ድረስ፣ የእግዚአብሔር ጠንካራው የሟችነት ህይወት እርዳታ መስዋዕትነትን ለመክፈል እና ንስሃ ለገቡ ኃጢያቶች ይቅርታን የሚሰጥ አዳኝ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ አቅርቧል። ያ መሐሪ እና ክቡር የሀጢያት ክፍያ እምነት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል የመጀመሪያ መርሕ እንዲሆን ያስፈለገው ለምን እንደሆነ ያብራራል። የኃጢያት ክፍያው “የሙታንን ትንሳኤ ያመጣል” (አልማ 42፥23) እና “የአለምንም ኃጢያት ያስተሰርያ[ል]” (አልማ 34፥8)፣ ንስሀ የገባንባቸውን ኃጢአቶቻችንን ሁሉ በመደምሰስ እና ለአዳኛችን በሟችነት ህይወት ላይ ድካማችንን እንዲረዳን ሃይልን እንሰጠዋልን።
በመጀመሪያ ደረጃ ከኃጢአት መጠበቅን ጨምሮ ከተሰሩት እና ከተሰረዙት የከበረ የኃጢአት ማስተሰረያ ባሻገር፣ የአፍቃሪ የሰማይ አባት እቅድ እኛን ለመጠበቅ ሌሎች ብዙ ስጦታዎችን ይሰጣሉ። የሟች ህይወታችን ሁል ጊዜ የሚጀምረው ከአባት እና ከእናት ጋር ነው። በሐሳብ ደረጃ፣ ሁለቱም በተለያዩ ስጦታዎች እድገታችንን ለመምራት ይገኛሉ። ካልሆነ ግን፣ የእነርሱ አለመኖር በራሱ እንደ አንድ ተግዳሮት አድረገን በመውሰድ ልናሸንፈው ይገባል።
፫.
የሰማይ አባታችን እቅድ በሟችነት ጉዞዎቻችን ውስጥ እኛን ለመምራት ሌላ እርዳታዎችን ይሰጣል። ከእነዚህ ውስጥ ስለ አራቱ እናገራለሁ። እባካችሁ ከአራተ ነገሮች ብቻ ናቸው ብላችሁ እንዳትገምቱ፣ ምክንያቱም እነዚህ እርዳታዎች በራሳቸው ተያያዥነት ያላቸው ናቸው። ደግሞም፣ ከእነዚህም በተጨማሪ ሌሎች የምህረት ጥበቃዎች አሉ።
የመጀመሪያ፣ ስለ ክርስቶስ ብርሃን ወይም መንፈስ እናገራለሁ። በመጽሐፈ ሞሮኒ ውስጥ ባለው ታላቁ አስተምህሮት፣ ሞሮኒ አባቱን እንዲህ ጠቀሰ “እያንዳንዱ ሰው መልካሙን ከመጥፎው ለይቶ ያውቅ ዘንድ የክርስቶስ መንፈስ ተሰጥቶታል” (ሞሮኒ 7፥16) ሲል ገልጿል። ይህንኑ ትምህርት በዘመናችን በተገለጡ አስተምሮዎች ውስጥ እናነባለን።
“እናም መንፈስም ወደ አለም ለሚመጣው ለእያንዳንዱ ሰው ብርሀን ይሰጣል፤ እናም መንፈስም በአለም ውስጥ ያለውን የመንፈስን ድምፅ ለሚያደምጥ ሰው ሁሉ ያበራለታል።” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥46)።
ትሁቱን እና የተዋረደውን አበራላቸው እና አምላክ የሌላቸውን እኮንን ዘንድ መንፈሴን ልኬአለሁና። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136፥33)።
ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ እነዚህን ጥቅሶች እንደህ ገለጹ፦ “ጌታ ሰዎችን (በዚህ ዓለም ውስጥ ሲወለዱ) ብርሃንን እና እውነተን ለማግኘት በሚጥሩ ጊዜ፣ ረዳት እንደ ሌላቸው ለብቻቸው አልተዋችውም፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው… ምሪትን፣ መመሪያን፣ የክርስቶስን መንፈስ ምክር ወይም የእውነት ብርሃንን የመቀበል መብት ይዞ ነው የተወለደው።”
ሁለተኛው ትክክል የሆነውን እንድንመርጥ በጌታ የተሰጡ ታላቅ እርዳታዎች በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እርስ በርስ የተያያዙ መለኮታዊ አቅጣጫዎች የደህንነት እቅድ (የደስታ እቅድ) አካል ናቸው። እነዚህ መመሪያዎች ትእዛዛት፣ ስነ ስርአቶች እና ቃል ኪዳኖች ናቸው።
ትእዛዛት ወደ ዘለአለማዊው ሂደታዊ የህይወት ጉዞ እንድናደርግ ያዘጋጀልንን የሰማይ አባታችን መንገድ ይገልፃሉ። እግዚአብሔር ትእዛዛትን ማንን ለመቅጣት እንደሚፈልግ የሚወስንበት መንገድ አድርገው የሚወስዱ ሰዎች ይህንን የእግዚአብሔርን የደስታ እቅድ አላማ ከመረዳት የሳቱ ናቸው። በዚያ መንገድ ስንራመድ፣ ከአዳኛችን ጋር ያለንን ግንኙነት በሂደት እናዳብራለን እናም እርሱ ለእያንዳንዳችን ወደ ሚፈልገው መድረሻ እንዲመራን የበለጠ ሀይሉን ለመቀበል ብቁዎች መሆን እችላለን። የሰማይ አባታችን ሁሉም ልጆቹ እግዚአብሔር እና አዳኛችን ወደሚኖሩበት ወደ ሰአልስቲያል የክብር መንግስት እንዲመለሱለት እና በዚያም ሰማያዊ ክብር ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች አይነት ህይወት እንዲኖራቸው ይፈልጋል።
ስነ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ወደ ዘላለማዊ ህይወት የሚወስደውን መንገድ የሚገልጹ የህግ አካላት ናቸው። ስነ ስርዓቶች፣ እና በእነርሱ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባቸው ቅዱስ ቃል ኪዳኖች፣ በመንገዱ ላይ እንድናደርግ የሚያስፈልጉ ደረጃዎች እና አስፈላጊ የጥበቃ መንገዶች ናቸው። የቃልኪዳንን ሚና በእግዚአብሔር እቅድ ስር እንዳለ አድርጌ ለማሳየት እፈልጋለሁ፣ የእርሱ ከፍተኛ በረከቶች የሚሰጡት ወስነው ትእዛዛትን ለመጠበቅ አስቀድመው ቃል ለሚገቡ እና እነዚያን ተስፋዎች ለሚጠብቁ ነው።
ትክክለኛ ምርጫዎችን ለማድረግ ሌሎች ከእግዚአብሔር የተሰጡ እርዳታዎች የመንፈስ ቅዱስ መገለጫዎች ናቸው። መንፈስ ቅዱስ ሶስተኛው የመለኮታዊ አባል ነው። ሥራውም፣ በቅዱሳት መጻሕፍት እደተገለፀው፣ ስለ አብና ወልድ መመስከር፣ እኛን ማስተማር፣ ሁሉንም ነገሮች ወደ ማስተዋል ማምጣት እና ወደ እውነት ሁሉ መምራት ነው። ቅዱሳት መጻህፍት የመንፈስ ቅዱስን መገለጦች ብዙ መግለጫዎችን ያካትታሉ፣ ለምሳሌ ስለ መጽሐፈ ሞርሞን እውነተኛነቱን አስመልክቶ ለሚነሱ ጥያቄዎች መንፈሳዊ ምስክርነትን ምላሽ ማግኘት። መገለጥ ከጥምቀት በኋላ ከሚሰጠው ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ጋር መምታታት የለበትም።
እግዚአብሔር ለታማኝ ልጆቹ ከሚሰጣቸው እርዳታዎች አንዱና ዋነኛው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። የዚህ ስጦታ አስፈላጊነት ከንስሐ እና ከውሃ ጥምቀት በኋላ በመደበኛነት የተሰጠ መሆኑ ግልፅ ነው፣ “ከዚያም [ቅዱሳት መጻህፍት እደሚያብራሩት] የኃጢአታችሁ ስርየት በእሳት እና በመንፈስ ቅዱስ ይመጣል።(2 ኔፊ 31፥17)። ይህን የኃጢያት ስርየት ያገኙ ሰዎች—እናም ደግሞ በየእለቱ ንስሃ በመግባት እና በገቡት በቅዱስ ቁርባን የቃል ኪዳን ስነ ስርአት መሰረት በመኖር መንጻታቸውን አዘውትረው የሚያድሱ ሰዎች—መንፈስ ቅዱስ፣ የጌታ መንፈስ፣ “ሁልጊዜም … ከእነርሱ ጋር ይሆናል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77)።
በዚህም፣ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ እንደሚደርግ አስተምረዋል፦“ሰለ እግዚአብሔር ስለሆኑ ነገር በተመለከተ የሰዎችን አእምሮ ብሩህ ያደርጋል፣ በመለወጣቸው ዘመን የአብን ፈቃድ መፈጽማውን እንዲያሳምናቸው፣ እና በህይወታቸው ዘመን ሁሉ አብሮነት ያለው የማይለወጥ ምስክርነት ይኖር ዘንድ፣ ወደ እውነት ሁሉ እንደ እርግጠኛ እና አስተማማኝ ምሪት በመሆን እና በየቀኑ በሃሴት እና በደስታ ይሞላቸዋል፣ ለሰው ሁሉ መልካም ለማድረግ በማሰብ፣ ክፉን ከመሥራት ይልቅ ክፉን መታገስ፣ ቸርና መሐሪ፣ በመከራ መጽናትና ለጋስ ያደርጋል። ይህ የማይተመን ስጦታ፣ ታላቅ የዕንቁ ዋጋ ያላቸው ሁሉ፣ የማያቋርጥ የጽድቅ ጥማት አለባቸው። ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ” በማለት ፕሬዝዳንት ስሚዝ እንዲህ ደመደሙ “ማንም ሟች የሆነ ሰው በቀጭኑ እና በጠባቡ መንገድ መሄድ አይችልም።”
፬.
ሟች በሆነው ጉዞአችን ውስጥ እኛን ለመምራት ባሉ ብዙ ሃያል እርዳታዎች እያሉ፣ ብዙዎች ከአዳኛችን እና ቤዛቸው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለሚያደርጉት ስብሰባ ዝግጁ ሳይሆኑ መቅረታቸው ያሳዝናል። በዚህ ጉባኤ ላይ በተደጋጋሚ የተነገረው ስለ አስሩ ደናግል ምሳሌ እርሱን እንዲገናኙት ከተጋበዙት መካከል ግማሹ እንደማይዘጋጁ ይጠቁማል።
ያልተዘጋጁትን ምሳሌዎች ሁላችንም እናውቃቸዋለን፥ ከእንቅስቃሴ-እጥረት የተነሳ መንፈሳዊ እድገታቸውን ያቋረጡ ተመላሽ ሚስዮናውያን፣ በቤተክርስቲያን ትምህርት እና ተግባራት ውስጥ እራሳቸውን በማግለል መንፈሳዊ እድገታቸውን አደጋ ላይ የጣሉ ወጣቶች፣ ለመልከጼዴቅ ክህነት የሹመታቸውን ጊዜ ቀጠሮ የሚያራዝሙ ወንዶች፣ ወንዶች እና ሴቶች—አንዳንዶቹ ከቀደሙት አቅኚዎች ወይም ጻድቅ ወላጆች የተወለዱ—በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ሙሉ በሙሉ ሳያደርጉ ወይም ሳይጠብቁ ከቃል ኪዳኑ መንገድ የራቁ።
አብዛኛዎቹ እንደዚህ ያሉ ልዩነቶች የሚከሰቱት አባላት መሰረታዊ የመንፈስ ጥገና እቅድ የሆኑትን የግል ጸሎትን፣ መደበኛ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን እና በቀጣይነት ንስሐን መከተል ሲሳናቸው ነው። በሚነጻጸር ሁኔታ፣ አንዳንዶች በየሳምንቱ የቅዱስ ቁርባንን በመካፈል ቃል ኪዳኖችን ማደስን ቸል ይላሉ። አንዳንዶች ከጌታ የተትረፈረፈውን ትምህርት እና ሌሎችን እንድናገለግል ከሚሰጠን ብዙ እድሎች ይልቅ ለወደፊት ፍላጎታቸው በማስቀደም ቤተክርስቲያን ፍላጎታቸውን እያሟላች አይደለም ይላሉ።
ትህትና እና በጌታ መታመን ለእንደዚህ አይነት ልዩነቶች ፍቱን መዳኒት ናቸው። መፅሐፈ ሞርሞን እንደሚያስተምረው፣ ጌታም እምነታቸውን በእርሱ ላደረጉ … [ይባርካቸውና፣ ያበለፅጋቸዋል]” (ሔላማን 12፥1)። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እና የነቢያቱን ትምህርቶች ከሚለዋወጡት ዘመን አመጣሽ የአለም ግኝቶች እና ጥበብ ጋር በስህተት ለሚመዝኑ ሰዎች ሁሉ በጌታ መታመን በተለይ አስፈላጊ ነው።
በሰማይ ያለው አፍቃሪ አባታችን ልጆቹ ወደ እርሱ እንዲመለሱ ምን ያህል ምድራዊ እርዳታ እደሰጠን ተናግሬአለሁ። በዚህ መለኮታዊ እቅድ ውስጥ የእኛ ድርሻ በእግዚአብሔር መታመን እና እነዚህን መለኮታዊ እርዳታዎች፣ በተለይም የተወደደውን ልጁን፣ አዳኛችን እና ቤዛችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያን መፈለግ እና መጠቀም ነው። እነዚህን መርሆዎች እንድታስተምሩ እና እንድትኖሩባቸው እጸልያለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።