አጠቃላይ ጉባኤ
የእርሱን ስጦታ ተቀበሉ
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


14:5

የእርሱን ስጦታ ተቀበሉ

አንቺ የእግዚአብሔር ውድ ሴት ልጅ ነሽ፣ አንተ የእግዚአብሄር ተወዳጅ ወንድ ልጅ ነህ፣ እናም ለእናንተ ፍፁም፣ ቅዱስ ልጁን ስጦታ ሰጥቷችኋል፡፡

ስጦታ መስጠት

ስጦታ መስጠት ሁሉንም ባህሎች፣ ሥልጣኔዎች እና የሺህ ዓመታትን የሚሸፍን ማህበራዊ ባህል ነው። በመላው ጊዜያት፣ ሰዎች ግንኙነቶችን ለማጠናከር፣ ፍቅርን እና ምስጋናን ለመግለጽ እና እንደ ሰርግ፣ የልደት ቀናት እና በዓላትን አስመልክቶ አስፈላጊ ክስተቶችን ለማስታወስ ስጦታዎችን ተሰጣጥተዋል። እናም ከእግዚአብሔር ፍጥረታት መካከል አንዳቸው ለሌላው ስጦታ የሚሰጣጡ ሰዎች ብቻ አይደሉም! ልናመለክተው ከምንችላቸው ብዙ ምሳሌዎች መካከል፣ ፔንግውኖች ወደፊት ጥንዳቸው ለሚሆኑት የሚያብረሸርቅ ድንጋይ እንደሚሰጧቸው ይታወቃል፣ እንዲሁም የቺምፓንዚ ዘመድ የሆኑት ቦኖቦዎችም የጓደኞቻቸውን ቁጥር ለማብዛት ፍራ ፍሬ ይሰጣሉ፡፡

ፔንግውኖች የሚያብረሸርቅ ድንጋይ እየሠጡ
ቦኖቦዎች ፍራ ፍሬ እየሠጡ

ምን ስጦታዎች ሰጥታችኋል? ለምትወዱት ሰው ፍፁም የሆነን ስጦታ ያገኛችሁበት ወይም ያዘጋጃችሁበትን ጊዜ አስቡ። ስጦታው በእርግጠኝነት ይህ የምትወዱት ሰው የሚፈልገው እና የሚያከብረው ነገር እንደሆነ ታወቃችሁ። ስጦታው ምን ነበር? ይህ ለእናታችሁ ነበር? ለጓደኛችሁ? ለልጃችሁ? ለአስተማሪ፣ ለወንድ አያታችሁ? ይህንን ስጦታ ስታገኙ ምን ተሰማችሁ? የምትወዱት ይህ ሰው ስጦታውን ሲከፍት ስታስቡ ምን ተሰማችሁ? በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ፍጹም የሆነውን ስጦታ ለእናንተ መቼ ነው የሰጣችሁ? ስጦታውንስ ስትቀበሉ ምን ተሰማችሁ?

አባቴ ለኔ የሰጠኝ ስጦታ

የሰባት ዓመት ልጅ ሳለሁ ከወላጆቼ ጋር በአረብ አገር ስኖር ቺቲ ቺቲ ባንግ ባንግ የተባለ የልጆች ፊልም ተለቀቀ። ፊልሙ እራሱን ስለሚነዳ፣ ውሃ ላይ የሚንሳፈፍ እና እንዲያውም መብረር ስለሚችል ተአምራዊ መኪና ነው! በአገር ቤት እንግሊዝ ውስጥ ቺቲ ቺቲ ባንግ ባንግን የመሰለ ትንሽ አሻንጉሊት መኪና እንደሠሩ አውቃለሁ፣ እናም ያንን ለማግኘት እንዴት ስጓጓ ነበር! እጀታውን ስትስቡ የአሻንጉሊት መኪናው ክንፎች ይዘረጋሉ! አባቴ ለቢዝነስ ጉዞ ወደ እንግሊዝ ሄደ እናም የሆነ ነገር እንዲያመጣልኝ እፈልግ እንደሆነ ጠየቀኝ እና ከቺቲ ቺቲ ባንግ ባንግ መኪኖች መካከል አንዷን ማግኘት ምን ያህል እንደምፈልግ ነገርኩት።

ከጉዞው ሲመለስ፣ ምንም መኪና አልነበረም። በጣም አዘንኩ እና እርሱ ረስቶ መሆን አለበት ብዬ አሰብኩኝ። ግን፣ ከ10 ቀናት በኋላ ልደቴ ነበር፣ እና ትንሽ ስጦታ፣ በሚያምር ሁኔታ ተጠቅልሎ፣ እየጠበቀኝ ነበር። በታላቅ ጉጉት፣ በጣም ትልቅ ተስፋ ለማድረግ ሳልደፍር፣ ስጦታውን ስከፍት መኪናዬን አገኘሁት። በጣም ደስተኛ ስለነበርኩ አለቀስኩ። እጀታውን ሣብኩ እና ክንፎቹ ተዘረጉ፣ ልክ በፊልሙ ውስጥ እንዳለው መኪና! ለዚህ በጣም ውድ ስጦታ አባቴን በጣም አመሰገንኩት። በዚያ መኪና ለዓመታት ተጫወትኩኝ እናም ለብዙ ተጨማሪ አመታትም አቆየሁት። ስቀበል የወደድኩትን ያህል አባቴ ያንን መኪና ለእኔ መስጠትን የወደደ ይመስለኛል።

መስጠት፣ መቀበል፣ መክፈት እና መውሰድ

ስጦታ መስጠት ሦስት ክፍሎች እንዳሉት ልናስብ እንችላለን።

  1. ስጦታውን መስጠት፣ ሰጪው ስጦታውን ይመርጣል፣ ያበጃል፣ ወይም ያዘጋጅና እና ለሚወደው ሰው ያቀርባል። ይህም በሰጪው በኩል አንድን ትርጉም ያለው ነገር ለመስጠት አሳቢነትን ያካትታል።

  2. ስጦታን መቀበል እና መከፈት ተቀባዩ ስጦታውን ከሰጪው ሲቀበል ብዙውን ጊዜ በመገረም፣ በአመስጋኝነት እና በደስታ መግለጫዎች፣ ከመክፈቱ በፊት፣ ስጦታው ምን እንደሆነ ለማወቅ ማሰሪያውን ፈቶ እና ጥቅሉን ይዘረጋል።

  3. እናም ከዚያ፣ የሚቀጥለው ምናልባት በጣም አስፈላጊው ክፍል፣ ስጦታውን መቀበል ነው። በቅንነት የተሰጠ ስጦታን መውሰድ ከመቀበል እና ከመክፈት የበለጠ ነገር ነው። የስጦታውን ዋጋ ከማወቅ እና ለሰጪው ምስጋናን ከመግለጽ የበለጠ ነገር ነው። ስጦታን በእውነት ለመቀበል፣ ዋጋ በመስጠት ለራሳችን፣ በሙሉነት በህይወታችን በመጠቀም እናም ሰጪውን በአመስጋኝነት እናስታውሳለን።

ስጦታን መቀበል ጥረት የማያስፈልገው አይደለም ግን እና መጠቅለሊያውን ከመፍከት በላይ የሆነ ምክንያት ያለው እና ትርጉም ያለው ድርጊት ነው። መቀበል ማለት ስጦታውን እና የሰጪውን ልብ በሰጪ እና በተቀባዩ መካከል ያለውን ትስስር በሚያጠናክር መልኩ ሁለቱንም ማድነቅ እና ማገናኘት ነው። በጣም ከልብ ስፈልግ የነበረውን የአሻንጉሊት መኪና ሳስብ ብዙ ወርቃማ ትዝታዎችን ያመጣልኛል፣ አሁንም በዚያ ስጦታ እና መቆጠር በማይችሉ ሌሎች ደግ ድርጊቶች የተወከለው የአባቴ ጥልቅ ፍቅር እና እንክብካቤ ይሰማኛል።

የሰማይ አባታችን ስጦታዎች

የሰማይ አባታችን በእያንዳንዳችን፣ ውድ በሆኑት ልጆቹ ላይ ለማውረድ የተዘጋጁ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የብርሀን እና የእውነት ስጦታዎች አሉት። ከቸር ልቡ ልክ እንደ ምድረ በዳ የውሃ ምንጭ፣ ከለጋስ ሰጪው ይጎርፋሉ። “በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው ከብርሃናትም አባት ይወርዳሉ።” ከአብ ጋር ባለን የቃል ኪዳን ትስስር እርሱ ሁልጊዜም ሰጪ ነው እኛም ትሁት ተቀባዮች ነን።

ሁሉም ስጦታዎች የሚፈሱባቸው ከአብ ስጦታዎች ሁሉ ትልቁ ስጦታ

ነገር ግን ከአብ የጸጋ ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ የሆነው፣ የሚወደው በጉ፣ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌለ ምንም ልንቀበል አንችልም። ሁሉም የአባታችን ስጦታዎች አዳኙ በጌቴሴማኒ እና በመስቀል ላይ ባቀረበው የፈቃድ መስዋዕትነት እና በአሸናፊው ትንሳኤው ይፈሳሉ እናም ህያው ናቸው። መሐሪው ቤዛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ከብርሃን አባታችን ከተሰጡን የላቀው ስጦታ ነው። “እግዚአብሔርም በልጁ ስጦታም ይበልጥ የተመረጠውን መንገድ አዘጋጅቷል።”

አንድ ሁሉን አቀፍ የሆነ የዘላለም እውነት ስጦታ

አባታችን ሊሰጠን የሚፈልገውን ሁሉንም የመቀበል ችሎታችንን የሚያጎናጽፍ አንድ ሁሉን አቀፍ ስለሆነ የዘላለም እውነት ስጦታ ለመናገር እፈልጋለሁ —ይህም አስፈላጊ የእውቀት ስጦታ ሙሉ በሙሉ ስንቀበለው እና በነፍሳችን ውስጥ በጥልቅ ስንወስደው፣ የህይወትን ደስታ እና ውጣ ውረድ፣ እና ላልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ትርጉም ይሰጣል፡ ይህም፣ እኛ በእውነት የእግዚአብሔር ልጆች ነን ያህ እውነት በጣም አስደናቂ ነው! የሚገርም ነው! እና ይህ እውነት ምሳሌያዊ አይደለም።

ይህን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማችሁ እንደሆናችሁ አስቡበት! በእውነቱ እናንተ የተወደዳችሁ ሴት ልጆቹ ናችሁ። በእውነቱ እናንተ ውድ ወንድ ልጆቹ ናችሁ። እና ያላችሁበት መንገድ የእሱ እቅድ የደስታ እቅድ ነው። ሁሉን በሚችል ፍቅሩ፣ ወደ ምድር ከመላካችሁ በፊት ማን እንደሆናችሁ፣ በሟች ህይወትዎ እስካሁን ያጋጠማችሁትን ያውቃል፣ እና ለነገዎቻችሁ ሁሉ በምህረቱ አቅዷል። እና ኦህ፣ የሁሉም ውብ ስጦታዎቹ የመጨረሻ አላማ የሆነውን፣ ከእርሱ ጋር የዘላለም ህይወት ለመቀበል አንድ ቀን ወደ እርሱ እንድትመለሱ እንዴት ይጓጓል።.

ጥያቄው ይህ የእውነት ስጦታ እውን መሆን እና አለመሆኑን ሳይሆን፣ ነገር ግን አግኝተን ስለመቀበል እና አለመቀበላችን ነው። ስጦታውን ቀድሞውንም አብ በላያችን ላይ አፍስሧል። የዚህ ስጦታ የመጨረሻ እቅድ ዋጋ አስቀድሞ በአዳኝ ተከፍሏል። ነገር ግን ይህንን እውነት ለዓመታት ከተማራችሁ፣ ይህን ካላችሁ፣ እና ይህን ከዘመራችሁ፣ ምናልባት ግሩሙ ድንቅ ነገር ከረጅም ጊዜ በኋላ ደብዝዞ ኃይሉ እና ሰላሙ ላይሰማችሁ ይችላል።

ይህ በዋጋ የማይተመን የማስተዋል ስጦታ እና ከእርሱ የሚፈሱት መልካምነት፣ ሰላም እና ተስፋ ተቀባይነት ሳይኖራቸው፣ ሳይከፈቱ እና ሳይቀበሉ ቢቀሩ፣ ለእኛ ምንኛ አስከፊ ኪሳራ ነው! ለሰጪው እንዴት ያለ ሀዘን ነው! “ለሰው ስጦታ ቢሰጠው እና ስጦታውን ባይቀበለው ምን ይጠቅመዋል? እነሆ፣ በተሰጠው አይደሰትም፣ ወይም በስጦታ ሰጪውም አይደሰትም።”

አናንተ በእውነት የእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ልጅ እንደሆናችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም ከምንጊዜውም በበለጠ መጠን ድንቅ የሆነውን ግንዛቤ እንድትቀበሉ እጋብዛችኋለሁ። የስጦታ ማሰሪያውን በመፍታት፣ መጠቅለያ ወረቀቱን በመቅደድ፣ ማሸጊያ ሳጥኑን በመክፈት፣ እና ለዚህ መሰረታዊ እውነት፣ ንጹህ ግንዛቤን በአመስጋኝ ትህትና በመጣር መቀበል አለባችሁ። መንፈስ ቅዱስ እናንተ የልዑል አምላክ ልጅ እንደሆናችሁ ለልባችሁ ምስክርነት ይሰጣል።

ይህን ግርማ ሞገስ ያለው እውነታ ወደ ነፍሳችሁ ስትቀበሉ እና ምቾት እና ደስታ ሲሰማችሁ አጠቃላይ ሁኔታችሁ ይለወጣል! በህይወታችሁ ምንም ቢከሰትም ባይከሰትም ፍቅሩን ሊሰማችሁ፣ ድምፁን መሥማት እና እጁን ማወቅ ትችላላችሁ። ራሣችሁን እና ሌሎችን የምታዩበትን መንገድ መቀየር ትችላላችሁ። ከአዳኛችሁ ጋር ያላችሁ የቃል ኪዳን ትስስር ይበልጥ እየጠነከረ ይሄዳል፣ እናም በዚህ ጣፋጭ ስጦታ መነጽር ህይወት አዲስ ብሩህነት፣ ውበት እና ተስፋ ትይዛለች።

እባካችሁ፣ ይህንን የለውጥ እውቀት በነፍሳችሁ ውስጥ በጥልቅ እየተቀበላችሁ መሆኑን ለመረዳት ትፀልያላችሁን? እባካችሁ ስጦታውን ትቀበላላችሁን? ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በጥልቀት፣ በነጻነት፣ በብዛት ይህንን ታደርጋላችሁ—እንዲሁም ይህንን በማድረግ ከዚህ ጋር ተከትለው በሚመጡ ሌሎች ስጦታዎች ሁሉ መትረፍረፍን ትቀበላላችሁን?

ይህን የዘለአለም እውነት ስጦታን ተቀበሉ

“ይህን ስጦታ ከእግዚአብሔር ለመቀበል ምን ማድረግ አለብኝ?” ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። በእርግጥ፣ ምንም አይደለም። ከሰጪው የሚመጣ ስጦታ ነው። ይህም እውነት ነው። በመቀበል አስገቡት። እናንተ የእርሱ ልጆች ናችሁ። ለእርሱም ተወዳጅ ናችሁ። አታወሳስቡት። ባልሆነ መንገድ እኔ ይህ አይገባኝም በሚል አስተሳሰብ ይህንን ስጦታ ለመቀበል አታግዱ። እውነታው ግን፣ ማናችንም ብንሆን “የተገባን” አይደለንም—ሁሉንም የአብ ስጦታዎች የምንቀበለው በቅዱስ መሲህ መልካምነት፣ ምህረት እና ጸጋዎች ብቻ ነው፣ ነገር ግን እርሱ እያንዳንዱ ልጆቹ እንዲቀበሏቸው ምን ያህል ይፈልጋል። ከዚያም፣ አዲሱ እና የሚታደሰው ግንዛቤአችሁሲመጣላችሁ፣ የዚህን ስጦታ ሰጪን በማመስገን ተደሰቱ።

በ20ዎቹ አጋማሽ ላይ እምነቴን ካገኘሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ እኔ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ መሆኔን ለማወቅ ነቃሁ። ይህንን ስጦታ የበለጠ በተሟላ መልኩ ባደረግሁ መጠን፣ ማን እንደ ሆንኩ እና ምን ያህል ሙሉ በሙሉ እንደምወደድ በይበልጥ አውቃለሁ። በማስተዋል እንዳድግ የረዱኝ አንዳንድ ነገሮች የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላቶች፣ የአባቴ በረከቶች፣ የቤተመቅደስ አምልኮ፣ ሌሎችን ማገልገል፣ ምስጋናን ለመስጠት እና ከአባቴ ጋር የማደርገው የተቀደሰ ጸሎት ናቸው። ይህን ውብ እውነት ባውቅ ኖሮ በህይወቴ ውስጥ የነበሩኝ የቀድሞ ሀዘን፣ ህመም እና ለቅሶዬ እንዴት ልዩ እንደሚመስሉ፣ ማስታገሻ እንደሚያገኙ፣ እና አብዛኛዎቹ እንደሚሸነፉ ሳስተውል እደነቃለሁ።

ወደ ክርስቶስ ኑ እና ተቀበሉ

ሞሮኒ “የእግዚአብሔርን ስጦታዎች እንዳንክድ” ነገር ግን “ወደ ክርስቶስ እንድንመጣ እና መልካም ስጦታን ሁሉ እንድንይዝ” አጥብቆ ይመክረናል። በፍቅሩ ደግነት በመተማመን እና ሁሉንም የደስታ፣ የሰላም፣ የተስፋ፣ የብርሃን፣ የእውነት፣ የመገለጥ፣ የእውቀት እና የጥበብ ስጦታዎችን —ጭንቅላታችሁን ወደ ላይ ከፍ አድርጋችሁ፣ እጆቻችሁን ዘርግታችሁ፣ እና ለመቀበል ዝግጁ በመሆን ወደ ክርስቶስ መምጣት ትችላላችሁ እነዚህን ስጦታዎች መቀበል ትችላላችሁ፣ ምክንያቱም ውድ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ እና ውድ የእግዚአብሔር ወንድ ልጅ እንደሆናችሁ ባላችሁ እውቀት አስተማማኝ እና መሰረት ያላችሁ ስለሆናችሁ እና እንዲበዣችሁ፣ እንዲያጸድቃችሁ እና እንዲቀድሳችሁ ፍጹም ቅዱስ ልጁን ስለሰጣችሁ ነው።

እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ናችሁ። ይህ የምንዘምረው አስደሳች መዝሙር ብቻ አይደለም። እባካችሁ ይህን የእውቀት እና የግንዛቤ ስጦታ ከእርሱ ትቀበሉታላችሁ፣ ትከፍቱታላችሁ እና ትወስዳላችሁ? ይህንንም ውድ ሀብት አቅርባችሁ ትይዙታላችሁን? ይህን ስጦታ እንደገና ተቀበሉ ወይም ምናልባት በእውነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀበሉት እና ሁሉንም የሕይወታችሁን ገጽታ እንዲለውጥ አድርጉ። እግዚአብሔር በልጁ ስጦታ ያዘጋጀላችሁ ከሁሉ የላቀው መንገድ ይህ ነው። እናንተ ያላችሁት ደስታ እንዲኖራችሁ ነው! በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።