ልባችሁን አታጠጥሩ
በቅንነት ንስሀ ከገባን፣ እራሳችንን ትሁት ካደረግን፣ እና በጌታ ከታመንን እና ከተመካን፣ ልባችን ይለሰልሳል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም መመለስ የጀመረው፣ እግዚአብሔር አብ እና ውድ ልጁ ለወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ ትሁት ጸሎቱን ለመመለስ በመጡበት ጊዜ ነበር። እንደ ዳግም መመለስ ክፍል፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የጥንት ሰነዶችን በእግዚአብሔር ስጦታና ሀይል ተረጎመ። ሰነዱም “እግዚአብሔር በጥንት በአሜሪካ ከኖሩት ህዝቦች ጋር ያደረጋቸው ነገሮች መዝገብ ነው፣ እናም ዘለዓለማዊ የሆነውን የወንጌል ሙላት የያዘ ነው።”
ወጣት ልጅ ሳለሁ መጽሐፈ ሞርሞንን ሳነብ ላማን እና ልሙኤል የተሰጣቸውን እውነት ለምን አላመኑም ፣የጌታ መልአክ ተገልጦ በቀጥታ ሲያነጋግራቸው እንኳ ብዬ ብዙ ጊዜ አስብ ነበር ። ላማን እና ልሙኤል ለምንድር ነው የአባታቸውን የሌሂን፣ እና የታናሽ ወንድማቸው ኔፊን ትምህርቶች ትሁት እና ታዛዥ ሆነው መቀበል ያልቻሉት?
ለዚህ ጥያቄ አንዱን መልስ በ 1 ኔፊ ውስጥ አገኘሁት፣ ይህም ፣ ኔፊ “በልባቸው ጠጣርነት የተነሳ [አዘነ] እንደሚለው ነው።” ኔፊ ታላቅ ወንድሞቹን “እንዴት በልባችሁ ጠጣርነት፣ በአዕምሮአችሁ እውር ሆናችሁ?“ ብሎ ጠየቀ።
ጠጣር ልብ አለው ማለት ምን ማለት ነው?
“የጠጣርነ“ በበመፅሐፈ ሞርሞን የኮሪያ ቋንቋ ትርጉም ውስጥ 완악 (Wan-Aak [ዋን-አክ]፦ 頑惡) ነው፡፡ ሀረጉም “ግትር“ የሚል ትርጉም ያለውን “Wan [ዋን]” (頑) ፊደል፣ እንዲሁም “ክፉ” የሚል ትርጉም ያለውን “Aak [አካ]” (惡) የቻይንኛ ፊደል ይጠቀማል። ልባችንን ስናጠጥር፣ እንታወራለን፣ እንዲሁም መልካም ነገሮች ወደ ልባችን እና አዕምሮአችን መግባት አይችሉም። ግትር እንሆናለን እናም፣ ለእግዚአብሔር ነገሮች ልባችንን በመዝጋት፣ በምድራዊ ፍላጎቶች ላይ ተጨማሪ ትኩረት እንሰጣለን። የሌሎችን ሀሳቦች እና መመሪያዎች ችላ በማለት፣ በእራሳችን ሀሳቦች ላይ ብቻ ማተኮርንም እንመርጣለን። ለአለማዊ እና ለጠላት ነገሮች ተጽዕኖ እንጂ ለእግዚአብሔር ነገሮች ልባችንን ላለመክፈት እንመርጣለን። ልባችን ሲጠጠሩ፣ የመንፈስ ቅዱስን ተጽዕኖን እንቃወማለን። እኛም “እግዚአብሄርን ለማስታወስ [የምንዘገይ] እና ከጊዜም በኋላ “ቃሉ [ሊሰማን የማይቻል] እንሆናለን።
አልማ በአሞኒሀ ምድር ለነበሩት ሰዎች እንዳስተማረው፣ አንዳንዶች “በልባቸው ጠጣርነትና በአዕምሮአቸው መታወር የእግዚአብሔርን መንፈስ አይቀበሉ[ም]።“ በተጨማሪም እንዲህ አስተምሯል፣ “እናም ልባቸውን የሚያጠጥሩ ሚስጥሩን በተመለከተ ምንም እስከማያውቁ ድረስ የቃሉ ትንሽ ክፍል ይሰጣቸዋል።” ከጊዜ በኋላም፣ መንፈስ ይወጣል፣ እናም ልክ እንደ ላማን እና ልሙኤል ልባቸውን ካጠጠሩት ጌታም “ቃላቱን ይወስዳል።“ ላማን እና ልሙኤል የመንፈስ ቅዱስ ስሜቶችን በመቃወም፣ ልባቸን በማጠጠር በመቀጠላቸው፣ እና የአባታቸው ሌሂን ቃላት እና አስተምህሮዎች ላለመቀበል በመምረጣቸው፣ እነርሱም በመጨረሻ የእግዚአብሔርን ዘለአለማዊ እውነት አልተቀበሉም።
ከላማነና ልሙኤም በሚነጻጸር ሁኔታ፣ ኔፊ፣ ከጌታ መንፈስ መመሪያ በመሻት፣ ራሱን ሁልጊዜ ትሁት አደረገ። መልሶም፣ ጌታ የኔፊን ልብ አለሳለሰው። ኔፊም እንዲህ ብሏል፣ “ወደ ጌታ ጮህኩ፤ እናም እነሆ እርሱ ጎበኘን፣ እኔም አባቴ የተናገራቸውን ቃላት ሁሉ እንዳምን ዘንድ ልቤንም አባባው።“ ጌታ ኔፊ የእግዚአብሔርን ሚስጥሮች በሙሉ እና ቃላቱን እንዲቀበል፣ እንዲገነዘብ፣ እና እንዲያምን ረዳው። ኔፊ የመንፈስ ቅዱስ ቀጣይ ጓደኝነትን ለማግኘት ችሏል።
ልባችንን ላለማጠጠር ምን ማድረግ እንችላለን?
መጀመሪያ፣ የዕለት ተዕለት ንስሀን እንለማመዳለን።
አዳኛችን እንዳስተማረው፣ “ንሰሃ የሚገባን እናም እንደህፃን ልጅ ወደ እኔ የሚመጣንም እቀበለዋለሁ።“ ውዱ ነቢያችን ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፦
“ንስሃ የእድገት ቁልፉ ነው። ንጹህ እምነት በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ወደፊት እንድንጓዝ ያደርገናል።
“እባካችሁን ንስሃ መግባት አትፍሩ ወይም ንስሃችሁን አታዘግዩት። ሰይጣን በሃዘናችሁ ይደሰታል። … ተፈጥሯዊውን ሰው በማውለቅ የሚገኘውን ደስታ ዛሬውኑ ጀምሩ። አዳኙ ሁል ጊዜ ይወደናል ነገር ግን በተለይ ንስሃ ስንገባ።“
ልባችንን በማለስለስ እና ወደ ጌታ መመምጣት ደስታን ስናገኝ፣ እኛም “የዋህ፣ ትሁትና ትዕግስተኛ፣ በፍቅር የተሞላ፣ ልጅ አባቱ የሰጠዉን እንደሚቀበለዉ ሁሉንም ነገሮች ጌታ የሚሰጠውን ለመቀበል ፈቃደኛ” እንሆናለን።
ሁለተኛ፣ ትሁትነትን ለመለማመድ እንችላለን።
የዕለት ተዕለት ንስሀ ለልባችን ትህትናን ያመጣል። ልክ ሕጻን ልጅ ለአባቱ እንደሚታዘዝ ሁሉ፣ እኛም በጌታ ፊት ትሑት መሆን እንፈልጋለን። ከዚያም ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ይገኛል፣ እንዲሁም ልባችንም ይለሰልሳል።
ባለቤቴ፣ ሱ፣ እና እኔ ላለፉት አራት አመታት የምናውቃቸው አስገራሚ የሆኑ ጥንዶችን አሉ። ከእነርሱ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገናኝ፣ ባሏ የቤተክርስቲያኗ አዲስ አባል ነበር፣ እናም ሚስቱም ከሚስዮኖች ጋር እየተገናኘች ወንጌልን ታጠና ነበር። ብዙ ሚስዮኖች እርሷን ወደ ክርስቶስ እንድትመጣ ለመርዳይ ተገናኝተዋት ነበር። ለወንጌሉ የማይናወጥ ምስክርነት እንዳላት እና ቤተክርስቲያኗ እውነት እንደሆነች ታውቅ ነበር። በአብዛኛው ጉብኝታችን ጊዜ መንፈሱ ይሰማት ነበር እናም በስብሰባዎች ሁሉ ተሳታፊ ነበረች። ከአጥቢያው አስደናቂ አባላት ጋር መገናኘትም ትወድ ነበር። ቢሆንም ግን፣ ወደ ጥምቀት ውሀ ለመግባት ለመወሰን አስቸጋሪ ሆኖ አገኘችው። አንድ ቀን እርሷ ሞሮኒ 7፥43–44 አነበበች፣ ይህም እንዲህ ይላል፦
“እናም በድጋሚ፣ እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ፣ የዋህ እና በልቡ የሚራራ ካልሆነ በስተቀር እምነት እና ተስፋ ሊኖረው አይችልም።
ከሆነ ግን [እምነታችሁ] እና [ተስፋችሁ] ከንቱ ነው፤ ምክንያቱም በልቡ የሚራራ እናም የዋህ ካልሆነ በጌታ ፊት ተቀባይነት አይኖረውምና።“
እነዚህን ቁጥሮች ካነበበች በኋላ፣ ምን ማድረግ እንዳለባት ተገነዘበች። በልብ የራራ እናም የዋህ ስለመሆን ትርጉሙ ምን እንደሆነ አውቃለሁ ብላ አስባ ነበር። ነገር ግን፣ ግንዛቤዋ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለማክበር ብቁ የሆነ እምነት እና ተስፋ አልነበረውም። ግትርነቷን እና የራሷን ጥበብ መተው ነበረባት። ንስሀ በመግባት ራሷን ትሁት ለማድረግ ጀመረች። ትህትናን ከእግዚአብሔር እይታ አንጻር መረዳት ጀመረች። በሰማይ አባቷ ላይ በመተማመን ልቧን እንዲያራራላት ጸለየች። በእነዚህ ጸሎቶች በኩል፣ የሰማይ አባት እንድትጠመቅ እንደሚፈልግ ከመንፈስ ምስክርነትን ተቀበለች።
ሁለቱም ባልና ሚስት ይበልጥ ትሁት በሆኑ ቁጥር፣ የእግዚአብሔርን ቃላት በይበልጥ መረዳት ጀመሩ ፣ እናም የአዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስን አስተምህሮት ለመከተል ልባቸውን አለሳለሱ።
ሶስተኛ፣ አዳኝን ማመን እና በእርሱ መመካት እንችላለን።
ኔፊ ጌታን በመታመን ልቡ እንዲራራለት በመፍቀድ ዙሪያ ታላቅ ምሳሌ ነበር። እንዲህም አስተምሯል፣ “በአንተ ታምኛለሁ፣ እንዲሁም ለዘለዓለም በአንተ እታመናለሁ። እምነቴን በስጋ ክንድ ላይ አላደርግም።” በተመሳሳይ፣ ለነቢዩ በተሰጠው ራዕይ ውስጥ፣ ጌታ እንዳለው፣ “ወደ መልካም፣ አዎን፣ በትክክል ለመስራት፣ በትህትና ለመራመድ፣ በጽድቅ ለመፍረድ፣ በሚመራው መንፈስ ላይ እምነትህን አድርግ።“ እምነታችንን በጌታ ላይ እንጥላለን እናም በእርሱ ላይ እንመካለን፣ እርሱም ልባችንን ያለሰልሰዋል፣ እናም በፈተናዎቻችን፣ በችግሮቻችን፣ እና በስቃያችንም እርዳታ እናገኛለን።“
በቅንነት ንስሀ ከገባን፣ እራሳችንን ትሁት ካደረግን፣ እና በጌታ ከታመንን እና ከተመካን፣ ልባችን ይለሰልሳል። መንፈሱን ያፈስልናል እናም የሰማይ ሚስጥሮችን ያሳየናል። ያስተማራቸውን ቃላቶች በሙሉ እናምናለን፣ እንዲሁም ግንዛቤአችን የዘለቀ ይሆናል።
አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ የየዋህነት የመጨረሻው ምሳሌ ነው። በ2 ኔፊ 31፥7 ውስጥ እንደምናነበው፣ “ነገር ግን ቅዱስም እንኳን ቢሆን፣ በስጋ መሰረት ለሰው ልጆች በአብ ፊት እራሱን እንዳዋረደ አሳይቷል፣ እናም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ለእርሱ ታዛዥ መሆኑን ለአባቱ መስክሯል።“ ምንም እንኳን እርሱ ቅዱስ እና ፍጹም ቢሆንም፣ በአባቱ ፊት ራሱን የዋህ አደረገ እናም በመጠመቅ ለእርሱ ታዛዥ ነበር።
በሟች ህይወቱ መጨረሻ ላይ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መራራ ጽዋን በመቀበል፣ ፈቃዱን ለአባቱ አሳልፎ ሰጠ። ይህም ስቃይ እርሱ “የሁሉም ታላቅ [የሆነው እርሱ] እግዚአብሔርን፣ ከስቃዩ የተነሳ እን[ዲ]ንቀጠቀጥ እናም ከእያንዳንዱ ቀዳዳ እን[ዲ]ደማ እናም በአካል እና በመንፈስ እን[ዲ]ሰቃይ አደረገው። አዳኝም “መራራውን ጽዋ እንዳ[ይ]ጠጣ … እና እን[ዲ]ሸማቀቅ“ ጠየቀ። ሆኖም፣ “ለአብ ክብር ይሁን፣ እናም ጠጥ[ቶታል] እናም ለሰዎች ልጆችም ዝግጅ[ቱ]ን ጨርሷል።“
ወንድሞች እና እህቶች፣ የስነምግባር ነጻ ምርጫ ተሰጥቶናል። ልባችንን ለማጠጠር መምረጥ እንችላለን፣ ወይም ልባችንን ለማሰላሰል መምረጥ እንችላለን። በየዕለቱ ህይወታችን ውስጥ፣ የጌታን መንፈስ በልባችን እንዲመጣ እና እንዲገባ ለመጋበዝ መምረጥ እንችላለን። በእነዚህ ምርጫዎች ፣ ሰላም እና ደስታ እንዳሉ አውቃለሁ።
የአባቱን ፈቃድ የተከተለውን፣ የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ እንከተል። ይህን ስናደርግ፣ ጌታ እንዲህ ቃል ገብቶልናል፣ “ልባቸውን የማያደነድኑ ከሆኑ፣ ዶሮ ጫቹቶቿን በክንፎቿ እንደምትሰበስብ እንዲሁ እኔም እሰበስባቸዋለሁ።” በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።