አጠቃላይ ጉባኤ
እንደ ትንሽ ልጅ
የሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


15:10

እንደ ትንሽ ልጅ

ህጻናት እና ልጆች እና ወጣቶች ከሙሉ ጥንካሬው እና ከውበቱ ጋር በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር መንግስት የሚበለፅጉ ምስሎች መሆናቸውን እመሰክራለሁ።

ኢየሱስ የምድራዊ ሕይወቱን የመጨረሻ ዓመት የጀመረው የሐዋርያቱን ሥልጠና በማጠናከር ነበር። የእርሱ መልዕክት እና ቤተክርስቲያኑ ከእርሱ በኋላ የሚቀጥሉ ቢሆን ኖሮ፣ እርሱን ለ24 ወራት ብቻ በሚያውቁት በ12 በጣም ተራ ሰዎች ልብ ውስጥ ብዙ እውቀት እና ብዙ መርሆች በተሞሉ ነበር።

አንድ ቀን ኢየሱስ ከእነርሱ መካከል ሲከራከሩ አይቶ በኋላም፣ “እርስ በርሳችሁ ስለምን ትከራከራላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም በተነጋገሩት ንግግር ስላፈሩ “ዝም አሉ” በማለት ታሪኩ ይገልጻል። ነገር ግን ከመምህራን ሁሉ የሚበልጠው ይህ የልባቸውን አሳብ ተረድቶ በዚያ የመጀመሪያውን ግላዊ የኩራት ግርዶሽ አስተዋለ። ስለዚህ እርሱ “ህጻንንም [ጠራ] …

እንዲህም አለ፣ “እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።

“እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፣ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሡ ነው። ”

ክርስቶስ ከመወለዱ በፊትም እንኳ የንጉሥ ቢንያም የስንብት ስብከት ስለ ሕፃን ትሕትና የሚናገረውን ይህን ጥልቅ አስተያየት እንደያዘ ሊስተዋል ይገባዋል። እንዲህም ይነበባል፦ “ተፈጥሮአዊው.ሠው ከአዳም ውድቀት ጀምሮ ለእግዚአብሄር ጠላት ነው፣ እናም እርሡም ለመንፈሥ ቅዱስ ግብዣ ፈቃደኛ ካልሆነና፣ ተፈጥሮአዊው ሠውነቱን ካልቀየረ እናም በጌታ በክርስቶስ ያሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ቅዱስ ካልሆነና፣ … ልጅ ከአባቱ ተቀባይ እንደሚሆን … ካልሆነ [እስከመጨረሻው የእግዚአብሄር ጠላት ይሆናል]።”

አሁን፣ እኛ የማናበረታታቸው አንዳንድ የሕፃናት ዝንባሌዎች እንዳሉ ግልጽ ነው። ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት፣ የዚያን ጊዜ የሶስት ዓመቱ የነበረው የልጅ ልጄ የአምስት ዓመቷን እህቱን እጇ ላይ ነከሳት። አማች በዚያ ምሽት ልጆቹን በመንከባከብ ለልጁ የሚያስቡትን የይቅርታ ትምህርቶችን በሙሉ በንዴት አስተምሯታል፣ ታናሽ ወንድሟ ምናልባት በእጁ ላይ ያለው ንክሻ ምን እንደሚሰማው እንኳን አያውቅም ነበር በማለት ደምድሟል። የልጅ ልጄ፣ “አሁን አውቋል” ብላ በልጆች የመኝታ ክፍል መስኮት በሚያንቀጠቅጥ ድምፅ ጩኸት እስክታሠማ ድረስ ያ የአባትነት ጥረት ለአንድ ደቂቃ፣ ምናልባት ለአንድ ደቂቃ ተኩል፣ ለሚሆን ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ሠርቶ ነበር።

ስለዚህ በህይወት ልምድ በሌላቸው ልጆች በጎነት ውስጥ ማየት የሚኖርብን ምንድን ነው? ከመላው መፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ እጅግ በጣም ጥልቅ በሆነ የፍቅር ሥሜት በተሞላው ትዕይንት ውስጥ ክርስቶስ ራሱን እንዲያለቅስ ያደረገው ምንድን ነው? ኢየሱስ ልክ በእሳት መካከል እንደሆነ ከሠማይ ጠባቂ መላእክት እነዚያን ልጆች እንዲከቡ አድርጎ አዋቂዎች “ህፃናቶቻቸውን እንዲመለከቱ” ባዘዘ ጊዜ ምን እያስተማረ ነበር?

ያን ሁሉ ነገር ያነሳሳው ምን እንደሆነ አናውቅም፣ ነገር ግን ከንጽህናቸው እና ከየዋህነታቸው፣ ከውስጣዊ ትህትናቸው እና በህይወታችን ላይ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ማሰብ አለብኝ።

ለምንድነው በአንድ ነቢይ የተስፋ መቁረጥ ጊዜ “የከንቱ ከንቱ ነው” የተባለው? እንዴት ነው “ከከንቱ አስተሳሰብ እና የሰው ልጆች ትዕቢት” በሌሂ ራዕይ በመንፈሳዊ የሞተውን ታላቁን እና ሰፊውን ሕንፃ የሚያመለክቱት?። ራሳቸውን በማገልገል የፀለዩት የዞራማውያን ቡድንስ? አልማ ስለእነርሡ እንዲህ ብሏል፣ “እነሆ፣ አምላክ ሆይ፣ በዓለም ከንቱ ነገሮች እስከ ማበጥ ድረስ ሲኩራሩ በአንደበታቸው ግን ወደአንተ ይጮሃሉ።”

በተቃራኒው ከልጆች ጸሎት የበለጠ አስደሳች፣ የበለጠ ንጹህ፣ ወይም የበለጠ ትሁት ነገር አለን? ይህም ሠማይ በክፍሉ እንደሚገኝ አይነት ነው። እግዚአብሔር እና ክርስቶስ እውነተኛ ናቸው፣ ነገር ግን ለሌሎች በሂደት አጋጣሚው እንደነገሩ ሊሆን ይችላል።

ሽማግሌ ሪቻርድ ኤል. ኢቫንስ ከ60 አመት በፊት እንደጠቀሰው፡- “ብዙዎቻችን ክርስቲያን መሆናችንን እንናገራለን፣ እኛ ግን … እርሱን በቁም ነገር አንመለከተውም። … እርሱን እናከብራለን፣ ነገር ግን እርሱን አንከተልም። … የእርሱን ንግግሮች እንጠቅሳለን፣ ነገር ግን በእነሱ አንኖርም።’’ “በእርሱ እንደነቃለን፣ ነገር ግን አናመልከውም።”

ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ ኢየሱስን ከርኩሰት የስድብ መስመር በላይ ከፍ አድርጎ ቢመለከተው ኖሮ ሕይወት ምን ያህል የተለየ ሊሆን በቻለ ነበር።

ነገር ግን ልጆች በእውነት እርሱን ይወዱታል፣ እናም ያ ፍቅር በህይወት መጫወቻ ሜዳ ውስጥ ወደ ሌሎች ግንኙነቶቻቸው ሊሸጋገር ይችላል። እንደ ደንብ፣ በትናንሽ አመታት ውስጥ፣ ልጆች በቀላሉ ይወዳሉ፣ በቀላሉ ይቅር ይላሉ፣ እና በጣም በሚያስደስት ሁኔታ ይስቃሉ፣ በጣም ቀዝቃዛ፣ በጣም ከባድ የሆነው ልብ እንኳን ሊቀልጥ ይችላል።

ጥሩ፣ ዝርዝሩ ይቀጥላል። ንፅህናስ? ማመን? ብርታት? ባህርይ?

በአንድ ወጣት ጓደኛዬ የታየውን በእግዚአብሔር ፊት ያለውን ትህትና ለማየት ከእኔ ጋር ና።

ኢስተን ዳሪን ጆሊ

ጥር 5፣ 2025 (እ.ኤ.አ)፣—ከ 91 ቀናት በፊት—ኢስተን ዳርሪን ጆሊ የአሮናዊ ክህነት ሥልጣን ተሰጠው እንዲሁም በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ዲያቆን ተሹሞ ነበር።

ኢስተን እስከሚያስታውሰው ድረስ የጌታን እራት፣ ቅዱስ ቁርባንን ማሣለፍ ይፈልግ ነበር። ነገር ግን ይህ የተቀደሰ ዕድል አይሣካልኝም፣ እወድቃለሁ፣ መሣቂያ እሆናለሁ ወይም ራሴን እና ቤተሰቤን አሣፍራለሁ በሚል አንጀት በሚያላውስ ፍርሃት የታጀበ ነበር።

ኢስተን ያልተለመደ እና በጣም የሚያጎሣቁል ህመም አለበት።

አያችሁ፣ ኢስተን ኡልሪች ኮንጀኒታል መስኩላር ዳያስትሮፊ [Ullrich congenital muscular dystrophy] የተሠኘ ያልተለመደ እና በጣም የሚያጎሣቁል ህመም አለበት። የወደፊት ምኞቱን እና ተስፋውን በማሟጠጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ የወጣትነት ህይወቱን በሚያስፈሩ ፈተናዎች እየሞላው ነበር። በቅርቡ በቋሚነት በተንቀሳቃሽ ወንበር የሚንቀሣቀስ ይሆናል። ቤተሰቡ ከዚያ በኋላ ስለሚጠብቀው ነገር አይናገሩም።

ሹመት ከተሠጠው በኋላ ባለው ቀጣይ እሑድ ቀን ኢስተን ቅዱስ ቁርባንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሣልፋል። በድብቅ ይዞት የነበረው ፍላጎት እራሱን እና እነዚህን ቅዱስ ምልክቶች የአጥቢያው ኤጲስ ቆጶስ ለሆነው አባቱ ማቅረብ ይችል ዘንድ ነበር። ሲለምን እና ሲማፀን የነበረውን ያንን ሥራ ሲጠብቅ፣ ማንም፣ ማንም፣ ሊረዳው እንደማይሞክር ዋስትና ለማግኘት አለቀሰ እንዲሁም ለመነ። በብዙ ምክንያቶች ይህንን ብቻውን ያለማንም እርዳታ ማድረግ ፈልጎ ነበር።

ካህኑ —የተቆረሰውን የክርስቶስ አካል የሚወክል አርማ የሆነውን—ዳቦውን ከቆረሠ እና ከባረከ በኋላ ኢስተን፣ በችግር እና በቁርጠኝነት በተሰበረው ሰውነቱ ወደ ላይ ወጣ። ይሁን እንጂ ከስብሰባ አዳራሹ ወለል ከፍ እስካለው መድረክ ድረስ ሦስት ትልቅ መጠን ያላቸው ደረጃዎች ነበሩ። ስለዚህም ትሪውን ከተቀበለ በኋላ የቻለውን ያህል ወደ ላይ ተንጠራራና ከእጅ መደገፊያው በላይ ባለው ቦታ ላይ አስቀመጠው። ከዚያም ከፍ ካሉት ደረጃዎች በአንዱ ላይ ተቀምጦ በሁለቱም እጆቹ የቀኝ እግሩን ወደ መጀመሪያው ደረጃ ጎተተው። ከዚያም የግራ እግሩን ወደዚያው ደረጃ ጎተተ፣ የግሉን ባለ ሶስት ደረጃ የኤቨረስት ተራራ ጫፍ ላይ እስኪደርስ ድረስ በብዙ ጥረትና ሃይል ወደ ላይ ቀጠለ።

ከዚያም እንዲቆም ወዳስቻለው ወደ ምሰሶው ራሱን አንቀሣቀሠ። ወደ ትሪው ተመለሰ። ጥቂት ተጨማሪ እርምጃዎችን ከወሰደ በኋላ ዓይኖቹ እንባ እያመነጩና በፊቱ ላይ እየወረዱ ይህንን ፍጹም ደፋር እና ታማኝ ልጁን ከማቀፍ እራሱን መግታት በነበረበት፣ አባቱ፣ በኤጲስ ቆጶሱ ፊት ቆመ። ከዚያም ኢስተን ፊቱ ላይ በጥልቅ ፈገግ እንዲል ባደረገው እፎይታ፣ “[እኔ ላደርገው [የሰጠኝን] ስራ ፈፅሜ በምድር [አባቴን] አከበርኩ[ት]” ብሎ ሊሆን ይችላል።”

እምነት፣ ታማኝነት፣ ንጽህና፣ መታመን፣ ክብር እና በመጨረሻም እንደዚያ ሊያስደስተው ለፈለገው አባት ያለው ፍቅር። እነዚህ እና ሌሎች ባህርያት እኛም “እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፣ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሡ ነው” እንድንል ያስችለናል።

እህቶች እና አባቶች እናም ጓደኞች፣ እኔ እጅግ በጣም ቆንጆ እንደሆኑ በማውቃቸው ምስሎች ዝርዝር አናት ላይ የሚገኙት ህጻናት እና ልጆች እንዲሁም ልክ ዛሬ እንደጠቀስነው ዓይነት ህሊና ያላቸው እና በዋጋ ሊተመኑ የማይችሉ ወጣቶች እንደሆኑ እመሰክራለሁ። ከሙሉ ጥንካሬው እና ከውበቱ ጋር በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር መንግስት የሚበለጽጉ ምስሎች መሆናቸውን እመሰክራለሁ።

በዚያም አይነት የምስክርነት መንፈስ፣ በወጣትነቱ ጆሴፍ ስሚዝ አይቻለሁ ያለውን እንዳየና፣ ተቀብያለሁ ያለውን እንደተቀበለ እመሰክራለሁ። ትሁት እና ንጹህ የሆኑት ራስል ኤም. ኔልሰን በእግዚአብሔር የተሾሙ እና ተሰጥኦ ያላቸው ነቢይ እንዲሁም ባለ ራዕይ እንደሆኑ እመሰክራለሁ። ከቋሚ የንባብ የህይወት ዘመን ስመጣ፣ መፅሐፈ ሞርሞን ካነበብኳቸው ሁሉ በጣም የሚክስ መጽሐፍ እንደሆነ እና በብዙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የትንሿ መኖሪያዬ ቁልፍ ድንጋይ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ክህነት እና ጸሎት—የክርስቶስ ክህነት እና የእናንተ ጸሎት—ህይወቴን በዳግም እያደሱ እንደሆኑ እመሰክራለሁ። ይህ ሁሉ እውነት እንደሆነ አውቃለሁ እንዲሁም ይህንንም የምመሰክረው ታዛዥ ከሆኑት ልጆች ሁሉ እጅግ ታላቅ ታዛዥ በሆነው፣ አልፋ እና ኦሜጋ በሆነው፣ ታላቁ በሆነው፣ በተሰቀለው፣ በታመነውም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ማርቆስ 9፥33

  2. ማርቆስ 9፥34

  3. ሉቃስ 9፥47 ይመልከቱ።

  4. ማቴዎስ 18፥2–4

  5. ሞዛያ 3፥19

  6. 3 ኔፊ 4፥17፤ እንዲሁም ቁጥሮች 11–24 ይመልከቱ።

  7. መክብብ 1፥2

  8. 1 ኔፊ 12፥18

  9. አልማ 31፧27

  10. ጄምስ ደብሊው. ክላርክ፣ በሪቻርድ ኤል ኢቫንስ፣ በኮንፈረንስ ሪፖርት፣ ሚያዝያ 1965 (እ.አ.አ)፣ 136 ላይ የተጠቀሰው። ሽማግሌ ኢቫንስ ይህ ጥቅስ የመጣው በዶክተር ጄምስ ደብሊው. ክላርክ እንደመጣ አሳውቀዋል፣ እሱም በዊልያም ኤች. ዳንፎርዝ የተጠቀሰው ነበር።

  11. ክላርክ፣ በሪቻርድ ኤል. ኢቫንስ፣ በኮንፈረንስ ሪፖርት፣ ሚያዝያ 1965 (እ.ኤ.አ)፣ 136።

  12. ዮሀንስ 17፥4። በብራየን እና ቻሪሳ ጆሌ ለጀፍሪ አር. ሆላንድ የተካፈ፤እ የግል ታሪክ፣ ጥር 2025 (እ.አ.አ)።

  13. ማቴዎስ 18፥4

  14. ራዕይ 1፥5 ተመልከቱ።