የሁሉም ነገሮች መመለሻ ጊዜ
(የሐዋሪያት ስራ 3፥21)
በጣም አስፈላጊው እና የከበረው “የምስራች፣” ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌሉን እና ቤተክርስቲያኑን በኋለኛው ቀናት በዳግም እንደመለሰ የሚናገረው መልእክት ነው።
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በዛሬ ሚያዚያ 6 ቀን፣ 1830 (እ.አ.አ) ከ195 አመታት በፊት ነበር።
የተወሰኑ አማኞች እና ጓደኞች ለዚህ ወሳኝ እና አስደሳች ወቅት ተሰበሰቡ። የቅዱስ ቁርባን ስነ-ስርዓት ሲደረግ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ሲሰጥ፣ የክህነት ስነ-ስርዓት ሲደረግ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነት ሲሰበክ በስብሰባው ላይ የተገኙት ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ተባርከዋል።።
ቤተክርስቲያኑን በዳግም በመመስረት፣ ጌታ በራዕይ አማካኝነት የ24 አመት ጆሴፍ ስሚዝን እንደ ቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ መሪ ሾመው፦ “ባለራዕይ፣ ተርጓሚ፣ ነቢይ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ፣ በእግዚአብሔር አብ ፈቃድ እና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌ [አደረገው]።”
በዓለም ታሪክ ውስጥ የዚህ ልዩ ክስተት አስፈላጊነት እና ቀጣይነት ያለው ተጽዕኖን ስንመለከት የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ እናገኝ ዘንድ አጥብቄ እጸልያለሁ።
የመጀመሪያው ራዕይ
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መደበኛ አደረጃጀት ተከታታይ ተዓምራዊ ተሞክሮዎች ውጤት ነበር። ከእነዚህ ልምዶች አደኛው ከ10 አመታት በፊት በኒው ዮርክ ግዛት ሰሜናዊ ክፍል ውስጥ ተከሰተ።
በጸደይ 1820 (እ.አ.አ) ጆሴፍ ስሚዝ የሚባል አንድ ወጣት ለመጸለይ በቤቱ አቅራቢያ ወደሚገኝ ጫካ ውስጥ ገባ። ስለነፍሱ መዳን ጥያዎች ነበሩት እናም “[ከቤተክርስቲያኖቹ] ሁሉ የየትኛው ትክክለኛ እንደሆነ እና የትኛውን መቀላቀል እንዳለበት ለማውቅ” ጓጓ። እግዚአብሔር ጸሎቱን እንደሚመልስ እና እንደሚመራው ጆሴፍ አመነ።
እባካችሁን ጆሴፍ የቱ እውነት እንደሆነ ለማወቅ ብቻ እንዳልጸለየ እወቁ። ይልቁንስ፣ እውነትን ይተገብር ዘንድ ምን እውነት እንደሆነ ለማወቅ ጸለየ። ጆሴፍ በእምነት ጠየቀ እናም በሚቀበለው መልስ አማካኝነት ለመተግበር ወሰነ።
“ለእርሱ ከልብ የመነጨ ጸሎት ምላሽ፣ እግዚአብሔር አብ እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለጆሴፍ እንደተገለጡ እና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተነገረው መሠረት ‘ሁሉ ነገር ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንዲመለስ’ አድርገዋል።(የሃዋሪያት ስራ 3፥21) በዚህ ራእይ ውስጥም፣ የቀደሙት ሐዋርያት ሞት ተከትሎ፣ የክርስቶስ የአዲስ ኪዳኗ ቤተክርስቲያን ከምድር እንደጠፋች ተማረ።” ጆሴፍ ስሚዝ ትምህርትን፣ ስልጣንን እና ቃል ኪዳናትን እና ስነ-ስርዓትን በድጋሚ ለመመለስ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ጆሴፍ እንዲህ ብሏል፦ “ብርሀናቸውና ክብራቸው የሚገለጽበት ሁሉ ብቁ ያልሆነ ሁለት ሰዎች በአየር ከእኔ በላይ ቆመው አየሁ። አንዱም ስሜን በመጥራት እና ወደ ሌላው በመጠቆም አናገረኝ--የምወደው ልጄ ይህ ነው። እርሱን ስማው!”
በዚህ ራዕይ እና በተከታታይ መንፈሳዊ ልምዶች እርሱ እግዚአብሔር እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንደግለሰብ እንዳወቁት፣ ለዘላለማዊ ደህንነቱ እንደተጨነቁ እና እሱ የሚያከናውነው ተልዕኮ እንዳላቸው ጆሴፍ ስሚዝ መረዳት ቻለ። ስለ ስላሴ መለኮት ባህሪያት፣ ጸባይ እና ፍጹምነት—አብ እና ወልድ የተለያዩ አካል ስለመሆናቸው ጠቃሚ ትምህርትንም ተማረ። ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ እና በስጋ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የስጋ አካል ያላቸው እንደሆኑ ጆሴፍ ስሚዝ አወጀ። እንዲህ አለ፣ “አብ እንደ ሰው ሊዳሰስ እና ሊጨበጥ የሚችል የስጋ እና አጥንት አካል አለው፤ ወልድም ደግሞ እንዲሁ ነው፣ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የስጋ እና አጥንት አካል የለውም፣ ነገር ግን የመንፈስ አካል አለው።”
አብ እና የወልድ ጆሴፍ ስሚዝን ጉብኝት በታላቁ “አለም ከመጀመሩ አንስቶ በሁሉም ቅዱስ ነቢያት አንደበት ስለተነገረው የሁሉም ነገሮች መመለስ” ውስጥ አነሳሽ ክስተት እንደነበረ እመሰክራለው።
መፅሐፈ ሞርሞን
በአዳኙ የተመለሰች ቤተክርስቲያን መደበኛ አደረጃጀት እንዲመሠረት ያደረጉ ተዓምራዊ ተሞክሮዎች ተከታታይነት ውስጥ ሁለተኛው የመጽሐፈ ሞርሞን መተርጎምና መውጣት ነበር።
“ዮሴፍ ስሚዝ የጥንት መዝገብ የሆነውን መፅሐፈ ሞርሞን፤ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርን ለመተርጎም የእግዚአብሔር ስጦታ እና ሀይል እንደተሰጠው በተጨማሪ እንመሰክራለን። … ይህ ቅዱስ ጽሑፍ ከትንሳኤው በኋላ ብዙም ሳይቆይ በምእራባዊ ክፍለ አለም በሰዎች መካከል የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ የግል አገልግሎት ታሪክ ይገኙበታል። መጽሐፈ ሞርሞን የሕይወትን ዓላማ ያስተምራል እንዲሁም ለዚያ ዓላማ መሠረታዊ የሆነውን የክርስቶስን ትምህርት ያብራራል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ እንደ ተጓዳኝ ቅዱስ ቃል፣ መፅሀፈ ሞርሞን የሰው ልጆች በሙሉ የሰማይ አፍቃሪ አባት ወንድ እና ሴት ልጆች እንደሆኑ፣ እርሱ ለህይወታችን መለኮታዊ እቅድ እንዳለው እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስም ዛሬ እንደ ጥንቶቹ ቀናት እንደሚናገር ይመሰክራል።”
እንደ የአዳኙ መልሶ የተቋቋመ ቤተክርስቲያን አባልነት፣ “በትክክል እስከተተረጎመ ድረስ፣ መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን፤ ደግሞም መፅሐፈ ሞርሞንም የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን።” መፅሐፈ ሞርሞን ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ነው፣ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነታ ያረጋግጣል እናም ከመጽሐፍ ቅዱስ የጠፉ ግልጽ እና ውድ እውነታዎችን ይመልሳል።
የክህነት ስልጣን መመለስ
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በመለኮታዊ ስልጣን እና በቃል ኪዳኖች እና በስነ-ስርዓቶች በአዳኙ የተመሰረተችው የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ከምድር እንደጠፋች ያስተምራል። በኋለኛው ቀን ወስጥ የሁሉም ነገሮች መመለስ እንደተተነበየው፣ የጥንት ነቢያት እና ሐዋርያት ለጆሴፍ ስሚዝ የክህነት ስልጣንን በአካል ሰጡት እናም የክህነት ቁልፎችን አበረከቱለት። የአዳኙን የተመለሰውን ቤተክርስቲያን መደበኛ ምስረታ የመራው በታምራዊው ተከታታይ ልምዶች ውስጥ ይህ ሶስተኛው ነበር።
የክህነት ስልጣን የእግዚአብሔር አገልጋዮች “[እርሱን] እንዲወክሉት እና በእርሱ ስም እንዲተገብሩ” ይፈቅድላቸዋል። “የክህነት ቁልፎች በእግዚአብሔር ልጆች ምትክ የክህነት አጠቃቀምን ለመምራት የሚያስችል ስልጣን ነው።”
በአብ እና በወልድ ምሪት መሰረት ለኃጢያት ስርየት ሙሉ በሙሉ በመጥለቅ ለማጥመቅ ከሞት የተነሳው መጥምቁ ዮሐንስ የጥምቀት ስልጣንን በ1829 (እ.አ.አ) መልሷል። በዛ ተመሳሳይ አመት ውስጥ፣ ከመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ሐዋሪያት ሦስቱ፣ ማለትም ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የክህነት ስልጣን ሀላፊነቶችን እና ተጨማሪ ቁልፎችን እንደገና መልሰዋል።
ቤተክርስቲያኗ በመደበኛ ከተመሰረተች ከስድስት አመት በኋላ፣ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ወስጥ፣ ሙሴ፣ ኤሊያስ እና ኤልሳዕ የእግዚአብሔርን ስራ በኋለኛው ቀናት ውስጥ ለማከናወን ለጆሴፍ ተጨምሪ ስልጣንን ሰጡት።
ኤሊያስ የአብርሃምን የወንጌል ዘመን እንዲሁም የአብርሃምን ቃል ኪዳን ጨምሮ አስረከበ።
በምድር ላይ የሚደርጉ ስነ-ስርዓቶች ለዘላለም የታሰሩ እንዲሆኑ የሚፈቅዱ ስልጣንን በመስጠት ለምሳሌ ቤተሰቦችን ሞትን በሚያልፍ በዘላለማዊ ግንኙነት ማጣመርን ኤሊያስ የህትመትን ሃይል ቁልፎች ሰጠ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተመሰረተ
ጆሴፍ ስሚዝ መጽሐፈ ሞርሞንን ሲተረጉም የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተመልሶ እንደሚቋቋም የሚጠቁሙ ራዕዮችን ተቀበለ። ነገር ግን ጌታ ቤተክርስቲያኑን ወዲያውኑ እንዳያቋቁም ጆሴፍን አዘዘው። ይልቁንስ፣ “በትንቢት እና ራዕይ መንፈስ” ጌታ ለጆሴፍ “መቼ የእርሱን ቤተክርስቲያን ዳግም በምድር ላይ እንደሚያቋቁም” ገለጸለት።
ከክህነት መመለስ እና ከመጽሐፈ ሞርሞን እትመት በኋላ ቤተክርስቲያኗ የተመሰረተችው በተገቢ ቅደም ተከተል ነበር። የመጽሐፈ ሞርሞን የመጀመሪያዎቹ ቅጂዎች በመጋቢት 26፣ 1830 (እ.አ.አ) ዝግጁ ሆኑ እናም ቤተክርስቲያኗ በሚያዚያ 6 በመደበኛነት ተቋቋመች።
“የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን … እንደገና የተመለሰችው የክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ናት። ይህች ቤተክርስቲያን በዋነኛው የማዕዘን ራስዋ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ህይወት እና መጨረሻ በሌለው የኃጢያት ክፍያው እና በእውኑ ትንሳኤው ላይ ተተክላለች። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና ሐዋርያትን ጠርቶ የክህነት ስልጣን ሰቷቸዋል። መንፈስ ቅዱስን፣ የደህንነትን ስነስርዓቶችን ለመቀበል እና ዘላቂ ደስታን ለማግኘት ሁላችንም ወደ እርሱ እና ወደ ቤተክርስቲያኑ እንድንመጣ ይጋብዘናል።”
የዘመን ሙላት ጊዜያቶች
የአብ እና የወልድ ለጆሴፍ ስሚዝ መገለጥ፣ የመጽሐፈ ሞርሞን መተርጎም እና መምጣት እና የክህነት ስልጣን እና ቁልፎች መመለስ ከ195 አመታት በፊት ለጌታ ቤተክርስቲያን መመለስ አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎች ነበሩ።
በብሉይ ኪዳን ነቢዩ ዳንኤል ካለምንም እጅ ከተራራ ላይ ተቆርሶ መላውን ምድር ስለሚሞላ ድንጋይ ህልም ተረጎመ። ቤተክርስቲያኗ ከተመሰረተች ከአንድ አመት በኋላ፣ ጌታ የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፎች “በምድርም ለሰው [እንደተሰጡ]” እናም “ከዚህም [የኢየሱስ ክርስቶስ] ወንጌል፣ እጅም ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ምድርን እስከሚሞላ ድረስ እንደሚንከባለለውም ድንጋይ” እንደሚሆን ለጆሴፍ ስሚዝ መመሪያ ሰጠው።
እመሰክራለው፦ ጌታ ቃል ኪዳኑን እየፈጸመ ነው። የአዳኙ መልሳ የተቋቋመችው ቤተክርስቲያን በመላው አለም እየተቋቋመች ነው እናም እግዚአብሔር “በዘመን ፍጻሜ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ [የሚጠቅልልበት]” መሳሪያ ነች።
የጌታ ያኋለኛው ቀን ስራ “በየዘመናቱ የእግዚአብሔር ህዝብን ፍላጎት ያነሳሳ ጉዳይ ነው፤ ይህ ነቢይ፣ ቀሳውስት እና ነገሥታት ልዩ በሆነ አስደሳችነት የኖሩበት መሪ ሃሳብ ነው፤ እኛ የምንኖርበትን ቀን በጉጉት እየተጠባበቁ ነበር፤ እናም በሰማያዊ እና በደስታ ሙሉ ጥበቃ ተሞልተው ስለዚህ ቀናችን ዘምረዋል እናም ተንብየዋል።”
በዚህ በታላቁ እና በመጨረሻው የመላው ወንጌል ዘመናት “ሙላት እና የተፈጸመ እና ፍጹም አንድነት፣ እና ከአዳም ቀናት እስከ አሁን የተገለጡት የዘመናት፣ ቁልፎች፣ እና ሀይላት፣ እና ክብሮች መተሳሰራቸው አስፈላጊ ነው። እና ይህም ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ከዚህ ምድር መመስረት ጀምሮ ያልተገለጡት … ይገለጣሉ …በዚህ በዘመን ፍጻሜ ውስጥ።
ነቢዩ ጆሴፍ በተጨምራዊ እንዲህ ገለጠ፣ “በማንኛውም ዘመን ውስጥ በሁሉን ቻይ ምሪት እና ትዕዛዝ መሰረት በክህነት ተጠይቀው የሚያውቁት ሁሉም ሰነ-ስርዓቶች እና ሃላፊነቶች በመጨረሻው ዘመን ይሰጣሉ … በሁሉም ቅዱስ ነቢያት አንደበት ተነግሮ የነበረውን መልሶ መቋቋምን ያሳካሉ።”
የተስፋ ቃሎች እና ምስክርነት
በማንኛውም አለም ውስጥ ማንኛውም ሰው ሊቀበለው የሚችለውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌሉን እና ቤተክርስቲያኑን በኋለኛው ቀናት ውስጥ የመለሰበትን መልዕክት “መልካም ዜናን” በጣም አስፈላጊ እና የከበሩ መሰረታዊ ነገሮችን ለማጠቃለል ሞክሬአለው።
ሁሉም ይህንን መልዕክት እንዲያጠኑ እና እንዲያረጋግጡ እጋብዛለው። “የዳግም መመለስ መልዕክትን በጸሎት የሚያጠኑ እና በእምነት የሚተገብሩ ሰዎች ስለመለኮታዊነቱ እና ለአለም ተስፋ ለተገባው ለጌታችን እና ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ለማዘጋጀት ስላለው እቅድ የራሳቸውን ምስክርነት በማግኘት እንደሚባረኩ [በመንፈስ ቅዱስ ሃይል አማካኝነት]” ቃል እገባለሁ። ልክ እንደ ጆሴፍ ስሚዝ ከእግዚአብሔር የሚመጣን መልስ ለመቀበል እና ለመተግበር በቅንነት ስትጸልዩ ያንን መለኮታዊ ምስክርነት ለመገንዘብ እና ምላሽ ለመስጠት ያላችሁ አቅም ይጨምራል።
ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር አባታችን እንደሆነ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ አንድያ እና ውድ ልጅ እንደሆነ እመሰክራለሁ። አዳኛችን እና ቤዛችን ነው።
እናም አብ እና ወልድ ለወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ እንደተገለጡለት ያም በኋለኛው ቀናት የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ዳግም መመለሰ እንዳስጀመረ በደስታ እመሰክራለሁ። መፅሐፈ ሞርሞን ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ነው እናም የእግዚአብሔርን ቃል ይዟል። አዳኝን የመወከል እና በስሙ የመተግበር የክህነት ስልጣን በድጋሚ በምድር ላይ ይገኛል። እናም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደገና የተመለሰችው የክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ናት። እነዚህ ነገሮች እውነት እንደሆኑ ምስክርነቴን የምሰጠው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።