አጠቃላይ ጉባኤ
በቤተሰብ ላይ ያተኮረ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል
የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


17:23

በቤተሰብ ላይ ያተኮረ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል

አስተምህሮቶቻችን እና በዘላለማዊ ቤተሰቦች ላይ ያለን እምነት ያጠነክሩናል እንዲሁም ያስተሳስሩናል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ለእኔ ብላችሁ ለፀለያችሁት ፀሎት አመሰግናችኋለው። ተሰምተውኛል

፩.

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ትምህርት በቤተሰብ ላይ ያቶክራል። ቤተሰብ ላይ ያለውን ትምህርት በተመለከተ ዋነኛ የሆነው ቤተመቅደስ ነው። እዛ ውስጥ የምንቀበላቸው ስነ ስረአቶች ወደ ሰማያዊ አባታችን መመለስ አንድንችል ይረዱናል።

በሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ፣ ፕሬዚደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የ200 ቤተመቅደሶችን ግንባታ አስተዋውቀው ነበር። በየአጠቃላይ ጉባኤው ማለቂያ ላይ አዲስ ቤተመቅደሶችን ማስተዋወቅ ይወዱ ነበር እኛም አብረናቸው ጥሩ ጊዜን እናሳልፍ ነበር። ይሁን እንጂ፣ አሁን ቀደም ያሉት ብዛት ያላቸው ቤተመቅደሶች በእቅድ እና በግንባታ ሂደቶች ገና በመጀመሪያዎቹ ሂደቶች ውስጥ እየተካሄዱ ስለሆነ፣ አዲስ ቤተመቅደሶችን ማስታወቃችንን መቀነስ ተገቢ ነው። ስለዚህ፣ በአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሽንጎ ፍቃድን፣ በዚህ ጉባኤ ላይ ምንም አይነት እዲስ ቤተመቅደሶችን አናስተዋውቅም። አሁን በቤተመቅደሱ የሚሰጡ ስነ ስርዓቶችን ለዓለም አቀፍ በሚገኙ የቤተክርስቲያን አባላት ማቅረብ እንቀጥላለን፣ ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ ቤተመቅደሶችን ግንባታ መቼ እና የት እንደሚሆን እናሳውቃለን።

እኔ አሁን ያቀረብኩት የንግግሬ ክፍል የተፃፈው የእኛ ተወዳጅ የሆኑት ፕሬዘዳንት ራሴል ኤም. ኔልሰን ካረፉ በኋላ ነው። አሁን የሚከተለው ከሳምንታት በፊት ተፅፎ ፈቃድ የተሰጠው ንግግር ቢሆንም በጌታ ምሪት የተዘጋጀ የእኔን ትምህርት ነው።

፪.

ከ30 አመት በፊት የታወጀው የቤተሰብ አዋጅ እንደሚለው፣ “ቤተሰብ ፈጣሪ ለልጆቹ ላለው ዘላለማዊ እጣ ፈንታ አላማ ዋና ክፍል ነው።” በተጨማሪም እንዲህ ያውጃል፣ “እግዚአብሔር ልጆቹን እንዲባዙ እና ምድርን እንዲሞሉ ዘንድ የሰጠው ትእዛዝ አሁንም ተግባራዊ ነው።” እንዲሁም፣ “የተቀደሰው የመዋለድ ሀይል የሚፈጸመው በህግ ተጋብተው ባል እና ሚስት በሆኑ ወንዶች እና ሴቶች መካከል ብቻ እንዲሆን እግዚአብሔር ማዘዙን ጨምረን እናውጃለን።” የዚያ ጊዜ ሽማግሌ ራስል ኤም. ኔልሰን ለብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ አድማጮች እንዳስተማሩት፣ “ቤተሰብ ለእግዚአብሔር እቅድ ወሳኝ ነው። … በእርግጥም፣ የእቅዱ አላማ ቤተሰብን ከፍ ከፍ ለማድረግ ነው።”

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዳንዴ ቤተሰብ ላይ እንደምታተኩር ቤተክርስቲያን ተደርጋ ትታወቃለች። ይህም ትክክል ነው! ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት እና የሟች ህይወታችን አላማ የሚብራሩት በቤተሰብ አንጻር ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለመንፈስ ልጆቹ ጥቅም ይሆን ዘንድ ያደረገው የሰማይ አባት እቅድ ነው። በእውነት ስለወንጌል እቅድ በመጀመሪያ የተማርነው በዘላለማዊ ቤተሰብ ሸንጎ ነው፣ በሟች ህይወት ቤተሰቦቻችን በኩል የሚተገበር ነው፣ እና የዚህ የታሰበው እጣ ፈንታ የእግዚአብሔርን ልጆች በዘላለማዊ ቤተሰብ ከፍ ለማድረግ ነው ማለት እንችላለን።

፫.

ያ የአስተምህሮ አውድ ቢሆንም፣ ተቃውሞም አለ። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በትዳር እና ልጅ በመውለድ ቅነሳ ምክንያት እየተሰቃየን ነን። ለአንድ መቶ ዓመታት ያህል ባለትዳሮች የሚመሩባቸው ቤተሰቦች ቍጥር እየቀነሰ መጥቷል፤ የወሊድ መጠንም እንዲሁ። የቤተክርስቲያናችን አባላት ጋብቻ እና የልጅ መወለድ መጠን የበለጠ አዎንታዊ ናቸው፣ ነገር ግን እነሱም በከፍተኛ ደረጃ ቀንሰዋል። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ስለ ጋብቻ ዓላማ እና ስለ ልጆች ዋጋ ያላቸውን ግንዛቤ አለማጣታቸው በጣም አስፈላጊ ነው። ይህም ወደፊት ለማግኘት የምንጥርበት ነው። ፕሬዚዳንት ኔሰን ይህንን እስተምረውናል፦ “ከፍ ከፍ መደረግ ቤተሰብን የሚመእከት ነው።” “ቤተሰቦች ከፍ ከፍ መደረግ የሚችሉት በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማዳን ስነስርዓቶች ብቻ ነው።”

በጋብቻ እና ልጅ መውለድ ላይ ያለው ሀገራዊ ውድቀቶች በታሪካዊ ምክንያቶች መረዳት ይቻላል፣ ነገር ግን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እሴቶች እና ልማዶች እነዚህን አዝማሚያዎች ማሻሻል እንጂ መከተል የለባቸውም።

ከ80 ዓመታት በፊት በልጅነቴ፣ በቀን ውስጥ የተከሰቱት ነገሮች በሙሉ በቤተሰቡ አመራር ስር በሆኑበት በአያቶቼ እርሻ ላይ እኖር ነበር። ከቤተሰብ እንቅስቃሴዎች የሚያዘናጉ እንደ ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ቴክኖሎጂዎች አልነበሩም። በአንጻሩ፣ ዛሬ ባለው የከተማ ማህበረሰብ ውስጥ ጥቂት አባላት ቋሚ ቤተሰብን ያማከለ እንቅስቃሴዎችን ያከናውናሉ። የከተማ ኑሮና ዘመናዊ ትራንስፖርት፣ የተደራጁ መዝናኛዎችና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሃሳብ ልውውጥ ወጣቶች ቤታቸውን እንደ ማረፊያ ቤት አድርገው መመልከት ቀላል እንዲሆንላቸው አድርጋል፤ እዚያም የሚተኙበትና አልፎ አልፎ የሚመገቡበት ቢሆንም ወላጆቻቸው የሚመሯቸው እንቅስቃሴዎች ግን ያን ያህል አይታዩም።

አብዛኞቹ የቤተክርስቲያኗ የአሁኑ አባላት ኑሯቸውን የሚያገኙበት መንገድም የወላጆችን ተጽዕኖን ቀንሷል። በጥንት ጊዜ፣ ቤተሰቦች አንድ ካደረጋቸው ታላላቅ ተጽእኖዎች አንዱ አንድን ግብ ለማሳካት በአንድ ላይ የመታገል ተሞክሮ ነበር—ለምሳሌ እንደ ምድረ-በዳን መግራት ወይም መተዳደሪያ ማግኘት። ቤተሰቡ የተደራጀ እና የሚመራ የኢኮኖሚ ምርት ክፍል ነበር። ዛሬ፣ አብዛኛዎቹ ቤተሰቦች ከፍተኛ የቤተሰብ አደረጃጀት እና ትብብር የማይጠይቁ የኢኮኖሚ ፍጆታ ክፍሎች ናቸው

፬.

የወላጆች ተፅዕኖ አነስተኛ እየሆነ ሲሄድ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን አሁንም ልጆቻቸውን ለቤተሰባችን የዘለአለማዊ እጣ ፈንታ እንዲዘጋጁ ከእግዚአብሔር የተሰጠ የማስተማር ሀላፊነት አላቸው (ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25 ተመልከቱ)። ብዙዎቻችን ይህን ማድረግ ያለብን ሁሉም ቤተሰቦቻችን በባህላዊ አይነት የተመሰረቱ ባልሆኑበትም ጊዜ ነው። መፋታት፣ ሞት እና መለያየት እውን ናቸው። እኔም ባደግኩበት ቤተሰብ ውስጥ ይህ አጋጥሞኛል።

የኦክስ ቤተሰብ

አባቴ የሞተው የሰባት ዓመት ልጅ ሳለሁ ነበር፤ ስለዚህ እኔና ታናሽ ወንድሜና እህቴ አንዲት መበለት እናት ነበረች ያሳደገችን። በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥም፣ እሷ ወደፊት ገፋች። እሷ ብቻኛ እና እየታገለች ነበረች፣ ነገር ግን በዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ላይ ያተኮረው ኃይለኛ ትምህርቷ እኛን መርቶናል። ልጆቿን በማሳደግ ረገድ ሰማያዊ እርዳታ ለማግኘት ምንኛ ጸለየች፤ እናም ተባርካለች! ያደግነው ሟች አባታችን ሁል ጊዜ እውን በሆነበት ደስተኛ ቤት ውስጥ ነበር። እሷም አባት እንዳለን እና ባል እንዳላት እንዲሁም በቤተመቅደስ ጋብቻቸው ምክንያት ሁሌም ቤተሰብ እንደምንሆን አስተማረችን። ጌታ አባታችንን ወደ ሌላ ሥራ ስለጠራው ለጊዜው አይገኝም ነበር።

ሌሎች ብዙ ቤተሰቦች በጣም ደስተኛ እንዳልሆኑ አውቃለሁ፣ ነገር ግን እያንዳንዷ ብቸኛ እናት ስለሰማይ አባት ፍቅር እና ስለሚመጣው የቤተመቅደስ ጋብቻ በረከቶች ማስተማር ትችላለች። እናንተም ይህን ማድረግ ትችላላችሁ! የሰማይ አባት እቅድ ይህንን ለሁሉም ሰው ያረጋግጥለታል። ሁላችንም ለቤተመቅደስ ጋብቻ እና እንደ ዘላለማዊ ቤተሰብ በመታተም ሊኖሩን ለሚችሉ በረከቶች አመስጋኞች ነን። ልክ እንደ እናቴም፣ እግዚአብሔር መከራህን ወደ ጥቅምህ ይለውጥልሃል” (2 ኔፊ 2፥2) በማለት ሌሂ ለልጁ ለያዕቆብ የገባውን ቃል ልንጠቅስ እንወዳለን። ያም ሙሉ ወይም በአሁኑ ጊዜ ያልተሟላ ለሆነው እያንዳንዱ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተሰብ የሚያመለክት ነው። እኛ የቤተሰብ ቤተክርስቲያን ነን።

ትምህርታችን እና በዘላለማዊ ቤተሰቦች ላይ ያለን እምነት ያጠነክሩናል እናም ያስተሳስሩናል። እኛ ልጆች በፔይሰን፣ ዩታ አቅራቢያ በነበረው በእርሻ ቦታው ውስጥ ስንኖር፣ የእናቴ አባት የገባውን ቃል መቼም አልረሳውም። አባቴ በሩቅ ዴንቨር፣ ኮሎራዶ መሞቱን አሳዛኝ ዜና ነገረኝ። ወደ መኝታ ክፍል ሮጬ ገባሁ እና አልጋው አጠገብ ተንበርክኬ በጣም አለቀስኩኝ። አያቴ ተከተለኝና ከአጠገቤ ተንበርክኮ “አባትህ እሆናለሁ” አለኝ። ይህ የዋህነት የተንፀባረቀበት ተስፋ አያቶች የቤተሰባቸው አባል ሲሞት ወይም ሲጠፋ የሚያጋጥማቸውን ክፍተት ለመሙላት ምን ማድረግ እንደሚችሉ የሚያሳይ ግሩም ምሳሌ ነው።

ወላጆች—ያላገቡ ወይም ያገቡ እና ሌሎች እንደ አያቶች ያሉ፣ ለልጆች ያንን ሚና የሚሞሉ—ዋና መምህሮች ናቸው። በጣም ውጤታማ የሆነው ትምህርታቸው በምሳሌ ማስተማር ነው። የቤተሰብ እቅፍ እንደ ጋብቻ እና ልጆች አስፈላጊነት፣ የሕይወት ዓላማ እና እውነተኛ የደስታ ምንጭ ያሉ ዘላለማዊ እሴቶችን ለማሳየት እና ለመማር የሚያስችል ተስማሚ ቦታ ነው። ይህም እንደ ደግነት፣ ይቅር ባይነት፣ ራስን መግዛት እንዲሁም የትምህርትንና ሐቀኛ ሥራን ጥቅም የመሳሰሉ ሌሎች ጠቃሚ የሕይወት ትምህርቶችን የምንማርበት ከሁሉ የተሻለው ቦታ ነው።

በእርግጥም ብዙ የቤተክርስቲያኗ አባላት የወንጌል እሴቶችን እና ተስፋዎችን የማይቀበሉ ተወዳጅ የቤተሰብ አባላት አሏቸው። እንደነዚህ ያሉት አባላት የእኛ ፍቅር እና ትዕግስት ያስፈልጋቸዋል። እርስ በእርሳችን በምንዛመድበት ጊዜ፣ የምንፈልገው ፍጽምና በሟችነት አስጨናቂ ሁኔታዎች ላይ ብቻ የተገደበ እንዳልሆነ ማስታወስ አለብን። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥57–59 ውስጥ ያለው ታላቅ ትምህርት ንስሐ መግባት እና መንፈሳዊ እድገት ከሞት በኋላ በሚመጣው የመንፈስ ዓለም ውስጥ ሊቀጥል እንደሚችል ያረጋግጥልናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ቤተሰቦች እርስ በርስ ለመበረታታት ሲሰባሰቡ፣ ሁላችንም በሟችነት ያጋጠሙን ኃጢአቶች እና የማይቀሩ ጕድለቶች በኢየሱስ ክርስቶስ የክብር እና የማዳን ስርየት ምክንያት ንስሐ በመግባት ይቅር ሊባሉ እንደሚችሉ ማስታወስ ይኖርብናል።

፭.

አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻ አርአያችን ነው። የእርሱን ትምህርት እና የራስን መስዋዕትነት መከተል የህይወታችን ሞዴል ካደረግን እንባረካለን። ክርስቶስን መከተል እና ራሳችንን እርስ በርስ አገልጋዮች እንድንሆን ማድረጋችን አሁን የተለመደ ለሚመስለው ራስ ወዳድነትና ግለሰባዊነት ከሁሉ የተሻለው መድኃኒት ነው።

ወላጆችም ልጆቻቸውን ከወንጌል መርሆች ውጭ ተግባራዊ እውቀትን የማስተማር ግዴታ አለባቸው። ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ትርጉም ያላቸው ነገሮች ሲያደርጉ አንድ ይሆናሉ። የቤተሰብ የአትክልት ቦታዎች የቤተሰብ ግንኙነቶችን ይገነባሉ። ደስተኛ የቤተሰብ ተሞክሮዎች የቤተሰብ ትስስርን ያጠናክራሉ። የካምፕ፣ የስፖርት እንቅስቃሴዎች እና ሌሎች መዝናኛዎች በተለይ ቤተሰቦችን ለማስተሳሰር ጠቃሚ ናቸው። ቤተሰቦች ወደ ቤተመቅደስ የሚወስዱትን ቅድመ አያቶችን ለማስታወስ የቤተሰብ ስብሰባዎችን ማዘጋጀት ይገባቸዋል።

ወላጆች በጓሮ እና በቤት ውስጥ መሥራትን ጨምሮ መሠረታዊ ስለሆነ የኑሮ ችሎታዎች ልጆችን ማስተማር አለባቸው። ቋንቋዎችን መማር ለሚስዮናዊ አገልግሎት እና ለዘመናዊ ህይወት ጠቃሚ ዝግጅት ነው። የእነዚህ የትምህርት ዓይነቶች አስተማሪዎች ወላጆች፣አያቶች ወይም የቤተሰብ አባላት ሊሆኑ ይችላሉ። ቤተሰቦች በቡድን ሆነው ሲማሩ እና ቤተሰብን እንዲሁም አባላቱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሲመካከሩ ያድጋሉ።

አንዳንዶች “ለዚያ ግን ጊዜ የለንም” ይሉ ይሆናል። በእውነት ጠቃሚ የሆነውን ለማድረግ ጊዜ ለማግኘት፣ ሁሉም ቴክኖሎጂዎቻቸውን ካጠፉ ቤተሰባቸውን ማብራት እንደሚችሉ ብዙ ወላጆች ይገነዘባሉ። እንዲሁም፣ ወላጆች እነዚያ ልጆች በእውነቱ ለእራት የሚፈልጉት ከእናንተ ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ እንደሆነ አስታውሱ።

ለበረከት ምስጋና ለማቅረብ እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመጸለይ ሌሊት እና ጠዋት ለሚንበረከኩ፣ አብረው ለሚጸልዩ ቤተሰቦች ታላቅ በረከቶች ይመጣሉ። ቤተሰቦች በቤተክርስቲያኗ አገልግሎቶች እና በሌሎች የአምልኮ ስፍራዎች አብረው ሲያመልኩ ይባረካሉ። የቤተሰብ ትስስሮችም በቤተሰብ ታሪኮች፣ የቤተሰብ ወጎች በመፍጠር እና የተቀደሱ ልምዶችን በማካፈል ይጠናከራሉ። ፕሬዚዳንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል “ከእኛ ህይወት እና ከቅድመ አያቶቻችንየሚመጡ የሚያነሳሱ ታሪኮች … ኃይለኛ የማስተማሪያ መሳሪያዎች ናቸው” ብለው እንድናስታውስ አድርገውናል። እነዚህም ብዙውን ጊዜ ለእኛ እና ለትውልዶቻችን ምርጥ የመነሳሳት ምንጮች ናቸው።

የእግዚአብሔር፣ የዘላለም አባታችን አንድያ ልጅ ስለሆነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እመሰክራለሁ። ወደ ሰማያዊ የቤተሰብ ቅልቅል የሚያመራውን የቃል ኪዳን መንገድ እንድንከተል ይጋብዘናል። በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ዳግም በተመለሱት ቁልፎች የሚመራው የክህነት የማተም ሃይሎች፣ ቤተሰቦችን ለዘለአለም አንድ ያደርጋሉ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥13–16 ተመልከቱ)። እነርሱም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ባሉት ቁጥራቸው እየጨመረ በሚሄድ የጌታ ቤተመቅደሶች ውስጥ ተግባር ላይ እየዋሉ ናቸው። ይህም እውን ነው። የዚህ አካል እንድንሆን የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጽሐፍት።

  2. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Faith and Families [እምነት እና ቤተሰቦች]” (Brigham Young University devotional, ህዳር 6፣ 2005(እ.አ.አ))፣ 3፣ speeches.byu.edu።

  3. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ሰማያትን በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ዘር ሃረግ ስራዎች ሰማያትን መክፈት፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)፣ 18።

  4. ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል፣ “Therefore I Was Taught [በመጠኑ ተማርኩ]፣” ኤንዛይን፣ ጥር 1982 (እ.አ.አ)፣ 4።