አጠቃላይ ጉባኤ
የቤተሰብ አዋጅ—ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጡ ቃላት
የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


13:58

የቤተሰብ አዋጅ—ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጡ ቃላት

የአዋጁ ምንጭ መለኮታዊ ነው፣ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ቃል በሚገባው ትልቅ አክብሮት ልንይዘው ይገባል።

ይህ የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ “ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” የተዋወቀበት 30ኛ አመትን የምናከብርበት ነው። ይህ አዋጅ በመለኮታዊ ንድፍ በራዕይ ቃላት የተፈጠረው “ቤቤተሰብ የማህብረሰብ ዋና መሰረታዊ ክፍል እንዲሆን እና እንዲጠናከር” ነው።

እናትም ሆናችሁ አባት፣ ሴት ልጅ፣ ወንድ ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ አያት፣ አክስት፣ አጎት፣ ወንድም፣ እህት፣ ወይም የአጎት ልጅ ሁሉም ሰው ቤተሰብ አለው። ከሁሉም በላይ፣ እያንዳንዳችን “በሰማይ ወላጆች የተወደድን የመንፈስ ሴት እና ወንድ ልጆች [ነን] … [እያንዳንዱዳችን] መለኮታዊ ተፈጥሮ እና ፍጻሜ [እንዳለን]” [እንደሆንን]አዋጁ ይናገራል።

በ2015 ወደ ቅዱስ ሐዋርያነት በተጠራሁ ጊዜ እንደሚከተለው ምክር ተሰጥቶኝ ነበር፣ “ይህ አዋጅ አሁን ያንተ ነው። ስምህ [በርዕሱ ላይ ባለው ‘የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ሸንጎ’ በሚለው ቃል ላይ በመጠቆም] እዚህ አለ። ይሰማህ እንዲሁም ያንተ የሆነ ያህል አድርገህ አስተምረው።”

የቤተሰብ አዋጁን እወደዋለሁ። ከአፍሪካ እስከ አውስትራሊያ እና በዚያ መካከል በአለም ዙሪያ ባለው በሁሉም ቦታ ቤተሰብ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ ውስጥ ስላለው ሚና መስክሬያለሁ። የአዋጁ ምንጭ መለኮታዊ ነው፣ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ቃል በሚገባው ትልቅ አክብሮት ልንይዘው ይገባል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ከዚህ መድረክ ላይ ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ፣ “ቃላት ተፅእኖ ያሳድራሉ”ስልየተናገርኩትንአስታውሱ።

አዋጁን የምናምንበት ዋና መልእክት ስለመሆኑ ጥቂት የኋላ ታሪኩን ልስጣችሁ።

በ1994 (እ.አ.አ) ፣ አዋጁ ከመቅረቡ ከአንድ አመት በፊት፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን፣ ማህበረሰቡ እና መንግስታት እግዚአብሔር ለቤተሰብ፣ ለጋብቻ እና ለጾታ ካወጣቸው ህግጋት እንዴት እየወጡ እንዳሉ ተወያዩ። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን በኋላ ላይ እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል “ያየነው ነገር በዚህ አላበቃም” ። የተለያዩ ማህበረሰቦች በጾታዊ ድርጊቶች ላይ ያሉትን ሁሉንም መስፈርቶች እና ገደቦች ለማስወገድ የሚያደርጓቸውን ጥረቶች ማየት ችለናል። የፆታ ግራ መጋባትን አይተናል። ሁሉም ሲመጣ አይተናል።”

አስራ ሁለቱ፣ ቤተክርስቲያኗ በቤተሰብ ላይ ያላትን አቋም የሚያጠቃልል ይፋዊ አዋጅ የሆነ ሰነድ ለማዘጋጀት ወሰኑ። በዚያ ዓመትም፣ በእግዚአብሔር የተጠሩት እነዚህ ነቢያት ስለቤተሰብ የሚናገር አዋጅ አዘጋጁ። ፕሬዚዳንት ዳለን ኤች ኦክስ፣ እነርሱ “ምን [እንደሚናገሩ] እና [እንዴት እንደሚናገሩ]” ለማወቅ በጸሎት ወደ ጌታ መቅረባቸውን አስታውሰዋል። ፕሬዚዳንት ሃዋርድ ደብሊው ሀንተርን፣ ፕሬዚዳንት ጎርደን ቢ.ሂንክሊን፣ እና ፕሬዚዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰንንለሚያካትተውለቀዳሚ አመራር አቀረቡት።

ከወራት በኋላ መጋቢት 1995 (እ.አ.አ)፣ ፕሬዚዳንት ሃንተር ከዚህ አለም በሞት ተለዩ እና ፕሬዚዳንት ሂንክሊ 15ኛው የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ሆኑ። አሁን አዋጁ በእጃቸው ሆኖ ነበር። ይህንን አዋጅ ለቤተክርስቲያኗ ለመስጠት ትክክለኛው ጊዜ መቼ ይመጣል? ያ ጊዜ ከስድስት ወራት በኋላ መጣ።

ከአጠቃላይ ጉባኤ ቀደም ብሎ የሚካሄደው የመሰከረም 23 የሴቶች አጠቃላይ ጉባኤ ከመካሄዱ ከቀናት በፊት፣ ፕሬዚዳንት ሂንክሊ እና አማካሪዎቻቸው ከሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት ጋር ለመመካከር ተገናኙ። እህቶችም፣ ልክ እንደ ሐዋርያቱም፣ በሴቶች እና በቤተሰቦች ላይ ያሉትን ስጋቶችን እየመዘኑ ነበር። መጪው ስብሰባ በቤተሰብ ላይ እንዲያተኩር አድርገው ነበር።

ፕሬዚዳንት ሂንክሊ በስብሰባው ላይ ለሴቶች ንግግር እንዲያደርጉ ቀጠሮ ተይዞላቸው ነበር። በሚያቀርቡት ንግግር አቅጣጫ ላይ ሲያሰላስሉ ቆዩ። ውይይቱ እየገፋ ሲሄድ፣ አዲስ የተፈጠረውን ነገር ግን ገና ለሕዝብ ያልተዋወቀውን “ቤተሰብ፦ ለዓለም የተላለፈ አዋጅ” ሲሉ በስም ጠቀሱ። ይህ የሴቶች ስብሰባ ስለቤተሰብ ወሳኝ የሆነ አዋጅ ለማቅረብ ትክክለኛው ጊዜና ቦታ ነበር?

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዚዳንት ኢሌን ጃክ በኋላ እንዲህ ብለው አብራርተዋል፦ “በወቅቱ አዋጁ ስለቤተሰብ ምን እንደሚል አናውቅም ነበር። ከርዕሱ ስለምን እንደሆነ ልንገነዘብ ችለን ነበር፣ ነገር ግን ስለቤተሰብ … የሚቀርብ ማንኛውም ነገር አዎንታዊ እንደሚሆን ተሰማን። … ራዕይ የሚቀበሉ የአስራ ሁለቱ ቡድን አባላት እንዳሉን ጥልቅ አዎንታዊ ስሜት ተሰማኝ።

በዚያ ቅዳሜ ዕለት የተደረገው የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ታሪካዊ ነበር። ፕሬዘደንት ሂንክሊ የቤተሰብ አዋጁን በእነዚህ አስፈላጊ ቃላት አስተዋወቁ፦“እውነት መስለው የሚቀርቡ ብዙ ውስብስብ የሆኑ፣ ስለ መስፈርቶች እና ስለ ሴቶች ብዙ የሚያስቱ፣ ቀስ በቀስ በአለም መንገዶች የሚያበላሹን ብዙ የሚያታልሉ እና የሚያባብሉ ነገሮች አሉ። በዚህም ምክንያት የዚህች ቤተክርስቲያን ነቢያት፣ ባለ ራእዮች እና ገላጮች እነዚህን እውነቶች በታሪኳ ውስጥ ደጋግመው እንዳስተማሩት ሁሉ ከቤተሰብ ጋር ስለተያያዙ መስፈርቶች፣ ትምህርቶች እና ልማዶች አስቀድመን ማስጠንቀቅ እንዳለብን ተሰምቶናል።”

ከዚያም አዋጁን ሙሉ በሙሉ አነበቡት። ጌታ እንዳለው፣ “በእኔም ድምፅ ሆነ ወይም በአገልጋዮቼ ድምፅ፣ አንድ ነው።”

አዋጁ “ቤተሰብ በእግዚአብሔር የተቋቋመ” ነው ይላል። የዚያን አረፍተ ነገር ግልጽነት እወደዋለሁ። አዋጁ በውስጣችን ያለውን መለኮታዊነት እና በፊታችን ያለውን ዘላለማዊ የወደፊት ሕይወት በማሰብ ምድራዊ ሕይወትን እንድንኖር የቀረበ ጥሪ ነው። ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ ብለው ገፀልው ነበር፣ “እናንተ እውነተኛ የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች ናችሁ። … አትሳሳቱ፣ አቅማችሁ መለኮታዊ ነው። ተግታችሁ ስትሹ፣ እግዚአብሔር ማን መሆን እንደምትችሉ ያሳያችኋል።”

አዋጁ ሲተዋወቅ ከብዙ የዓለም ሰዎች አመለካከት ጋር የሚጣጣም አልነበረም። ያን ጊዜም አልነበረም። አሁንም አይደለም። አዋጁ በቤተሰብ፣ በጋብቻ እና በጾታ ላይ በሚናገረው የማይስማሙ አሉ። አንዳንዶች ቤተክርስቲያኗ በዚያ እንዳትቀጥል፣ እንድትከልሰው ወይም አዋጁን ወደ ጎን እንድትለው ሃሳብ ያቀርባሉ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ፕሬዚዳንት ሂንክሊ እንዳሉት ይህ የቤተሰብ አዋጅ መለኮታዊ ትምህርት ነው። መርሆቹ ከመስመር የወጡ አይደሉም ነገር ግን ከጌታ እና ከእርሱ የቃል ኪዳን መንገድ ጋር ፍጹም አብረው የሚሄዱ ናቸው። የአዋጁ አስተምህሮ ያን ጊዜ እና አሁን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ተገልጧል። ይህቺ የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት፤ እርሱም የምንኖርባቸውን እውነቶች አዘጋጅቷል።

አንዳንዶቻችሁ በአዋጁ ላይ አሰላስላችሁ፣ እንዲህ ትሉ ይሆናል፣ “ይህ ለእኔ አይሰራም”። “ለሌሎች ስሜት ግድ የሚሠጠው አይመስልም።” “ቤተሰቤ ይህን አይመስልም።” “ከእኔ ሁኔታ ጋር የሚስማማ አይደለም።”

አሳሳቢ የሚሆንባችሁ ሰዎች፣ የሰማይ ወላጆች ልጅ፣ የሰማይ አባታችሁ ቤተሰብ አካል እንደሆናችሁ እወቁ። ከእርሱ በላይ ማንም የሚያውቃችሁ ወይም ስለእናንተ በጥልቅ የሚያስብ የለም። ወደ እርሱ ተመለሱ፣ ልባችሁን ለእርሱ አፍስሱ፣ በእርሱ እና በተስፋ ቃሉ እመኑ። በሚወዳችሁ አዳኛችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰብ አላችሁ። እርሱ ወደ ምድር የመጣው የኃጢአት ክፍያ ሊከፍልልን እንዲሁም የስህተቶቻችንን እና በጣም መጥፎ የሆኑ ቀናትን ሸክም ሊሸከምልን ነው። የሚገጥማችሁን እና የሚሰማችሁን ይረዳል። ወደ እርሱ ተመለሱ፣ ከእናንተ ጋር እንዲሆን፣ ከፍ እንዲያደርጋችሁ እና እንዲያበረታታችሁ መንፈስ ቅዱስንእንደሚልከው እመኑ። “በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ሁሉ ራሱን በስፋት የሚያፈስ፣ ከሁሉ ነገሮች በላይ አስፈላጊ እና ለነፍስ በጣም ደስ የሚያሰኝ” ፍቅራቸው ይሰማችሁ።

ሁሉም የጌታ ሐዋርያት በጣም ይወዷችኋል። ስለእናንተ እንለምናለን እንዲሁም የጌታን መመሪያ እንፈልጋለን። ከእኛ ጋር ሁኑ። የምትኖሩት ጠላታችሁ የራሱ ያደርጋችሁ በሚፈልግበት አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ነው። አትኮብልሉ። ከኮበለላችሁም ተመለሱ። የሚወዷችሁ ሌሎቹ ሰዎች እንደሚዘረጉት እጆቻችን ወደ እናንተ ተዘርግተዋል።

አዋጁ “ወላጆች ልጆቻቸውን በፍቅር እና በጽድቅ የማሳደግ የተቀደሰ ሀላፊነት አላቸው” በማለት ይገልፃል። መፅሐፈ ሞርሞን ስለዚህ እውነት ሁለተኛ ምሥክርነት ይሰጣል። በመጀሪያው ምእራፍ የመክፈቻ ቁጥር ላይ እንደተናገረው፣ “እኔ ኔፊ ከመልካም ወላጆች ተወለድኩ” የሚልን እናነባለን። መፅሐፈ ሞርሞንን ደግመን እና ደጋግመን የጀመርነው በሂደቱም ደግሞ እነዚህን ቃላት የምናስታውሰውስንቶቻችን ነን? በልባችሁ ያዟቸው።

በአዋጁ ውስጥ በጣም ከምወዳቸ አረፍተ ነገሮች አንዱ ይህ ነው፦ “በቤተሰብ ህይወት ደስታ የሚገኘው ቤተሰብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ላይ ሲገነባ ነው።”

ደስተኛ መሆን የማይፈልግ ማነው?

የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ምን ምን ናቸው? አሁንም ከአዋጁ ውስጥ፣ “እምነት፣ ጸሎት፣ ንስሀ መግባት፣ ምህረት፣ ክብር፣ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ ስራ እና ጤናማ የሆኑ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች።”

እነዚህን ቁልፍ መርሆዎች በመተግበር ህይወቱ የማይሻሻል ማነው? ማናችንም ብንሆን ፍጹም በሆነ መንገድ ልናደርግ አንችልም ሆኖም “ልታደርጉ ከምችሉት በጣም የተሻለውን አድርጉ” የሚሉትን የፕሬዚዳንት ሂንክሊን ጥበብ ያዘሉ ቃላት ልንከተል እንችላለን።

በአዋጁ ውስጥ፣ “አባቶች በፍቅር እና በፅድቅ ያስተዳድሩ፣ “ እንዲሁም “እናቶች በቀደምትነት ልጆቻቸውን የመንከባከብ ሀላፊነት አለባቸው” የሚል እናነባለን። ማስተዳደር ማለት የበላይነት እንዲሁም መንከባከብ ማለት ሁለተኛ ደረጃ ሚና ያለው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር፣ ለወንዶችና ለሴቶች የተለያዩ ሆኖም አንዳቸው ሌላውን የሚያሟሉ እኩል እና አስፈላጊ የሆኑ ሚናዎችን ሰጥቷቸዋል።

የግል ታሪክን ላካፍል።

አንድ ቀን እሷን ሳላማክር ቁልፍ ውሳኔ ከወሰንኩበት ጊዜ በኋላ እኔና ባለቤቴ እኩል አጋር በመሆን በተሻለ መንገድ መሥራትን ተማርን። የወሰድኩት እርምጃ አስገረማት፣ ባልጠበቀችው በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አስገባት። በኋላም፣ እጇን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ፣ “ሮን፣ እባክህ ዳግመኛ እንደዚያ እንዳታደርግብኝ” ስትል አጥብቃ ተናገረች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በደንብ እንግባባለን።

በቤተሰብ አዋጁ ውስጥ “አባቶች እና እናቶች በእኩል አጋርነታቸው የመረዳዳት ሀላፊነት አለባችው” የሚል እናገኛለን።

የሚጠቅመው እኩል የሚለው ቃል ነው። አዋጁ “ቅዱስ ኃላፊነቶቻችን” በማለት በገለጸው በዚህ ሥራ ላይ አብረን በመስራታችን እኔና እህት ራዝባንድ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በእኩልነት የተጣመረ ትዳር መሥርተናል። ሁሉም ልጆቻችን ትዳር ስለመሰረቱ፣ እኔና እህት ራዝባንድ እነሱ እና የትዳር ጓደኞቻቸው እንዴት እኩል አጋር መሆን እንደሚችሉ ምክር መስጠታችንን ቀጥለናል።

ቱኩረታችንን በእግዚአብሔር ክብር ላይ አድርገን ስንኖር እርስ በርሳችን እንከባበራለን እንዲሁም እርስ በርስ እንደጋገፋለን። እነዚያ መለኮታዊ የጽድቅ መንገዶች የግልን ፣ የቤተሰብን እና የኅብረተሰብን ሕይወት ወደ መረጋጋት ይመራሉ።

የሰማይ አባታችን ወደ እርሱ ቤት እንድንመራ፣ እንድንማር እና በፍቅር፣ በጥንካሬ፣ በዓላማ እና በዘላለማዊ መረዳት እንድንሞላ ሊረዳን የቤተሰብ አዋጁን ሰጥቶናል። ወደ እርሱ እና ወደ ውድ ልጁ ቀርባችሁ እንድትኖሩ በሙሉ ነፍሴ እማፀናችኋለሁ። ይህን በምታደርጉበት ጊዜ፣ መንፈሱ እንደሚያነሳሳችሁ፣ እንደሚመራችሁ እንዲሁም በልባችሁ ውስጥ ቃል የገቡላችሁን “አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ” ሰላም እንዲሰማችሁ እንደሚረዳችሁ ቃል እገባላችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጽሐፍት።

  2. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጽሐፍት።

  3. ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ፣ “ቃላት ዋጋ አላቸው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ)፣ 70፣ 75–76 ተመልከቱ።

  4. ሼሪ ዱው፣ Insights from a Prophet’s Life: Russell M. Nelson [2019 (እ.አ.አ)]፣ 208።

  5. ይህ የቤተ ክርስቲያኗ የመጀመሪያ ይፋዊ አዋጅ አልነበረም። በ1995 (እ.አ.አ) ከታወጀው “የቤተሰብ፦ ለአለም የተሰጠ አዋጅ” በፊት በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ በ1841 (እ.አ.አ)፣ 1845 (እ.አ.አ)፣ 1865 (እ.አ.አ) እና 1980 (እ.አ.አ) የታወጁ አዋጆች ነበሩ። የመጨረሻው አዋጅ የተሰጠው በ2020 (እ.አ.አ) ነበር፦ “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት በዳግም መመለስ፦ የሁለት መቶኛ አመት መታሰቢያ ለአለም የተላለፈ አዋጅ”። (See Emma Benson, “What We Learn from the Proclamations of the Restoration” [digital-only article], Liahona, Dec. 2021, Gospel Library.)

  6. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “The Plan and the Proclamation” [ዕቅዱ እና አዋጁ]ኢንዛይን፣ ፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 30።

  7. See Dew, Insights from a Prophet’s Life, 209–10.

  8. See Barbara Morgan Gardner and Olivia Osguthorpe,፣ “Delivering the Family Proclamation: Insights from Former Relief Society President Elaine L. Jack,” Religious Educator, vol. 24, no. 2 (2023), 164

  9. See Gardner and Osguthorpe, “Delivering the Family Proclamation,” 162–65; see also Elaine L. Jack, “Relief Society: A Balm in Gilead,” Ensign, Nov. 1995, 92. በንግግሯ ውስጥ፣ ፕሬዚዳንት ጃክ እንዳስተማሩት፦ “ቤተሰቦች ታላቅ ደስታችንን እና አንዳንዴም በጣም የሚያሳዝን ልባችንን ያመጣሉን። ቤተሰቦች የመማሪያ አካባቢን፣ እኛ ፈጽሞ ያልተመረቅን ግን ሁልጊዜ የምንማርበት የትምህርት ክፍል ይሰጣሉ። በቤተሰባችን ውስጥ የበጎ አድራጎት፣ የትእግስትናነት መርሆዎች፣ ታማኝነትን፣ ደግነትን፣ ልግስናን፣ ራስን መግዛትን እና አገልግሎትን ማካፈል በመተግበር የሚገኘውን መንፈሳዊ ሰላም ማድነቅን እንማራለን። እነዚህ እህቶች, የቤተሰብ እሴቶች በላይ ናቸው፤ እነዚህ የጌታ የሕይወት መንገድ ናቸው።”

    በወቅቱ የክህነት ሥራ አስፈፃሚ ሸንጎ ሊቀመንበር የነበሩት ሽማግሌ ዳለን ኤች. ኦክስም በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል (see Gardner and Osguthorpe, “Delivering the Family Proclamation,” 167)።

  10. See Gardner and Osguthorpe, “Delivering the Family Proclamation,” 165.

  11. “ቤተሰብ፦ ለዓለም የተላለፈ አዋጅ” ከሚያዝያ 6 ቀን 1980 (እ.አ.አ) ጀምሮ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያኗ ይፋዊ አዋጅ ይሆናል። እስከዚያ ጊዜ ድረስ ቤተክርስቲያኗ አራት ይፋዊ አዋጆችን ብቻ አውጥታ ነበር፣ እነዚህም ስለ ትምህርት፣ ስለ እምነት፣ ስለ ታሪክ፣ ስለ ማስጠንቀቂያዎች፣ ስለ ግብዣዎች እና ስለ ቤተክርስቲያኗ እድገት እና ወደፊት ግፋት መግለጫዎችን ያነሱ ናቸው (see Encyclopedia of Mormonism [1992], “Proclamations of the First Presidency and the Quorum of the Twelve Apostles,” 3:1151–57)።

  12. Elaine L. Jack, in Gardner and Osguthorpe, “Delivering the Family Proclamation,” 166.

  13. ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “Stand Strong Against the Wiles of the World [የዓለምን ሽንገላዎች በጽናት ተቋቋሙ]፣” ኤንዛይን፣ ህዳር 1995 (እ.አ.አ)፣ 100። በጥቅምት 1976 (እ.አ.አ) በተደረገው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል “በታሪክ ዘመናት ሁሉ አገሮች የተለያዩ በሽታዎችን፣ ወረራዎችን፣ ረሃብን፣ የመሬት መንቀጥቀጥን፣ ወረርሽኞችን፣ የመንፈስ ጭንቀቶችን መቋቋም ችለዋል፣ ነገር ግን የቤተሰብን መበታተን መትረፍ አልቻሉም” በማለት የተናገሩትን አንድ አሜሪካዊ ደራሲ ጠቅሰዋል (in “A Report and a Challenge,” Ensign, Nov. 1976, 7–8)።

  14. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥38

  15. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጽሐፍት

  16. ራስል ኤም። ኔልሰን፣ “Choices for Eternity [የዘለአለማ ምርጫዎች]” (worldwide devotional for young adults, May 15, 2022)፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት፡፡

  17. ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “Stand Strong Against the Wiles of the World [የዓለምን ሽንገላዎች በጽናት ተቋቋሙ]፣” 100 ተመልከቱ።

  18. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍትን ተመልከቱ።

  19. 1 ኔፊ 11፥22–23

  20. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  21. 1 ኔፊ 1፥1

  22. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  23. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  24. ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “Women of the Church [የቤተክርስቲያኗ ሴቶች]ኤንዛይን፣ ህዳር 1996 (እ.አ.አ)፣ 69።

  25. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት። “በቤት ውስጥ ባል ወይም አባት ከሌለ እናትየው ቤተሰቡን በበላይነት ትመራለች።” (አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል2.1.3)።

  26. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  27. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  28. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  29. በጥቅምት 1991 አጠቃላይ ጉባኤ ላይ፣ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ እንዳስተማሩት፣ አዳምና ሔዋን “በአትክልቱ ስፍራ ጎን ለጎን ቆሙ። አብረው ከአትክልቱ ስፍራ ተባረሩ እና በላባቸው ላብ እንጀራቸውን ለማግኘት ጎን ለጎን አብረው ሰሩ” (“Our Solemn Responsibilities [መለኮታዊ ሀላፊነቶቻችን]፣” ኤንዛይን፣ ህዳር 1991 (እ.አ.አ)፣ 51)።

  30. ፊልጵስዮስ 4፥7