አጠቃላይ ጉባኤ
የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው
የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


13:16

የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው

ማስተራረቅ የሚጀምረው እጅግ በጣም መሰረታዊ በሆነው ቦታ—እንዲሁም በልባችን ውስጥ ነው። ከዚያም በቤታችን እና በቤተሰቦቻችን ውስጥ።

እንኳን ወደ አጠቃላይ ጉባኤ በደህና መጣችሁ በዚህ ስለተሰበሰብን እንዴት አመስጋኝ ነኝ።

እነዚህን የጉባኤ ሂደቶች በመጠባበቅ ላይ ሳለን፣ ወደ እዚያ ይመሩ የነበሩትን ሳምንታት ላይ የተከሰቱትን በከፍተኛ ደረጃ እናውቃለን። ልባችን በሀዘን ላይ መሆኑን እንገነዘባለን እናም አንዳንዶች በአለም ላይ በሚከሰቱ ሁከት ወይም አሳዛኝ ክስተቶች እርግጠኛ አለመሆን ይሰማቸዋል። በሚሽጋን የሚገኘውን የተቀደሰውን የጸሎት ቤትን ጨምሮ በተቀደሱ ቦታዎች የተሰበሰቡ ሀይማኖታዊ ሰዎች እንኳን ህይወታቸውን ወይም የሚወዷቸውን አጥተዋል። ካለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ወዲህ እናንተ፣ ቤተሰቦቻችሁ፣ እና ዓለማችን ባሳለፋችኋቸው ነገሮች ምክንያት የብዙዎቻችሁ ልብ ከብዶ እንደነበር ስናገር ከልቤ ነው።

ቅፍርናሆም በገሊላ

በኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ወቅት፣ በገሊላ ባህር አጠገብ እንዳላችሁ ታዳጊ ወጣት እንደነበራችሁ አድርጋቹ በአዕሮዓችሁ ተመልከቱ። መልዕክቶቹ ብዙዎችን የሳበ፣ የአንድ አይሁድ መምህር ቃላት ተሰራጭተዋል። ጎረቤችም እርሱን ለመስማት ከባህር ማዶ ወዳለ ተራራ ለመጓዝ አቅደዋል።

በአቧራማዎቹ የገሊላ ጎዳናዎች ላይ ከሚሄዱት ጋር ተቀላቅላችኋል። በደረሳችሁም ጊዜ፣ ይህን ኢየሱስን ለመስማት የተሰበሰበው ታላቅ ህዝብ አስገርሟችኋል። አንዳንዶች በዝግታ ‘’መሲሁ’’ በማለት ያንሾካሹካሉ።

ይህንን ታዳምጣላችሁ። ቃላቶቹ ልባችሁን ይነካሉ። ወደ ቤታችሁ በመመለስ ላይ ባላችሁበት ረዥም ጉዞ ላይ፣ ከመናገር ይልቅ ጸጥታን መርጣችኋል።

አስደናቂ ነገሮችን ታሰላስላላችሁ—ከሙሴ ህግ ይልቅ የላቁ ነገሮችን። ሌላኛውን ጉንጫችሁን ስለመስጠት እና ጠላቶቻችሁን ስለመውደድ ተናግሯል። “የሚያስተራርቁ ብፁአን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና” በማለት ተስፋን ሰጠ።

በእናንተ እውነታ፣ አስቸጋሪ ቀናት ክብደታቸው በተሰማችሁ ጊዜ--ያለመረጋጋት እና ፍርሃት--ሰላም የራቃችሁ መስሎ ይሰማችኋል።

ፍጥነታችሁ በቅጽበት ይጨምራል፣ ትንፋሽ እያጠራችሁ ወደቤት ትደርሳላችሁ። ቤተሰባችሁ ተሰብስቧል፣ አባታችሁም፣ “ምን እንደሰማችሁ እና እንደተሰማችሁ ንገሩን” በማለት ይጠይቃችኋል።

ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ሁሉ እንዲበራ፣ ስደት በደረሰባችሁ ጊዜም እንኳ ቢሆን ጽድቅን እንድትፈልጉ ጋብዟችሁ እንደነበር ታካፍላላችሁ። “የሚያስተራርቁ ብፁአን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና” ያለውን በደገማችሁ ጊዜ ድምጻችሁ ይተናነቃችኋል።

እንዲህ በማለት ትጠይቃላችሁ፣ “ዓለም በሁከት ባለበት ጊዜ፣ ልቤ በፍርሃት በተሞላ ጊዜ፣ እና ሰላም እጅግ የራቀ መስሎ በሚታይ ጊዜ በእውነት እኔ አስተራራቂ መሆን እችላለሁን?”

አባታችሁ እናታችሁን አየት በማድረግ እና በርጋታ፣ “አዎን። እኛ የምንጀምረው እጅግ በጥአም መሰረታዊ በሆነው ቦታ—በልባችን ነው። ከዚያም በቤታችን እና በቤተሰቦቻችን። በዚያም ልምምድን ባደረግን ጊዜ፣ ማስተራረቅ ወደ መንገዶቻችን እና ወደ መንደሮቻችን ሊሰራጭ ይችላል።”

ወደ ፊት 2000 ዓመታትን ሂዱ

ወደ ፊት 2000 ዓመታትን ሂዱ። ይህን በምናባችን ማሰብ አይጠበቅብንም—ይህ የእኛ እውነታ ነው። ምንም እንኳ ዛሬ እየተነሳ ያለው ትውልድ የሚሰማው ጫና ጥንት በገሊላ የነበረው ታዳጊ ወጣት ይሰማው ከነበረው የተለየ ቢሆንም—ጽንፈኝነት፣ ዓለማዊነት፣ በቀል፣ የጎዳና ነውጥ፣ የጭካኔ ስራ፣ እና የመህበራዊ ሚዲያ ቁልል—ሁለቱም ትውልዶች የቅራኔን እና የመወጠር ልምዶችን ይጋፈጣሉ።

በሚያስመሰግን ሁኔታ፣ ወጣት ወንዶቻችን እና ሴቶቻችን በተመሳሳይ መልኩ ወደራሳቸው የተራራው ስብከት ጊዜ—ወደ ሴሚናሪ፣ወደ ለወጣቶች ጥንካሬ፣ እና ወደ ኑ ተከተሉኝ ተስበዋል። እዚህ፤ ብርሃናቸውን በሌሎች ፊት ለማብራት፣ በስደት ውስጥ እንኳ በመሆን ጽድቅን ለመፈለግ፣ እና ጠላቶቻቸውን ለመውደድ ከጌታ ተመሳሳይ የጽናት ግብዣን ይቀበላሉ።

በተጨማሪ ከዳግም መመለሱ ሃያው ነቢያት አበረታች ቃላትን ይቀበላሉ፦ “የሚያስተራርቁ ያስፈልጋሉ።” ደስ የማይል ባልሆነ ሁኔታ ያለመስማማት። ክርክርን እና ትእቢትን በይቅርታ እና ፍቅር ተኩ። አግባብ የሌለው የጥላቻን ወይም የመከፋፈል ግድግዳን ሳይሆን፣ የትብብርን እና የመረዳትን ግድግዳ ገንቡ። እንዲሁም ተመሳሳይ የተስፋ ቃል፦ “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።”

ዛሬ እየተነሳ ያለው ትውልድ ልብ በኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት እና በወደፊት ተስፋ የተሞላ ነው። እነርሱም እንዲህ በማለት ይጠይቃሉ፣ “ዓለም በሁከት ባለበት ጊዜ፣ ልቤ በፍርሃት በተሞላ ጊዜ፣ እና ሰላም እጅግ የራቀ መስሎ በሚታይ ጊዜ በእውነት እኔ አስተራራቂ መሆን እችላለሁን?’”

የሚያስተጋባው ምላሽ አንዴ በድጋሚ አዎን ነው! አዳኙ የተናገራቸውን እነዚህን ቃላት በደስታ እንቀበላለን፤ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ … ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።”

ዛሬ፣ ማስተራረቅ የሚጀምረው እጅግ በጣም መሰረታዊ በሆነው ቦታ—እንዲሁም በልባችን ውስጥ ነው። ከዚያም በቤታችን እና በቤተሰቦቻችን ውስጥ። በዚያም ልምምድን ባደረግን ጊዜ፣ ማስተራረቅ ወደ ጎረቤቶቻችን እና ወደ ማህበረሰባችን ሊሰራጭ ይችላል።

የዘመኑ የኋለኛው ቀን ቅዱስ የሚያስታራርቅባቸውን እነዚህን ሶስት ስፍራዎች በተጨማሪ እናስብ።

በልባችን ውስጥ ማስተራረቅ

የመጀመሪያው በልባችን ውስጥ ነው። የክርስቶስ አገልግሎት ጥርት ያለው ክፍል ልጆች ወደ እርሱ እንዴት እንደመጡ ይገልጻል። በዚያም ውስጥ ፍንጭ አለ። የአንድን ልጅ ንጹህ እና የዋህ የሚያስተራርቅ ልብ መመልከት ለእኛ ልቦች መነሳሳት ሊሆን ይችላል። የመጀመሪያ ክፍል እድሜ ውስጥ ያሉ አያሌ ልጆች “አስተራራቂ መሆን ማለት ምን ይመስላል?“ ለሚመለው ጥያቄ እንዲህ መልሰው ነበር።

በቀጥጣ በልባቸው ያለውን መልስ አካፍላችኋለሁ! ሉክ እንዲህ አለ፣ “ዘወትር ሌሎችን እርዱ።” ምንም እንኳ ትክክል ባይመስልም፣ እርስ በርስ ይቅር መባባል ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ግሬስ አካፈለች። አና እንዲህ አለች፣ “ከእርሷ ጋር ማንም የሚጫወት ሰው ያልነበራትን አንዲት ሴት አየሁ፣ በመሆኑም ከእርስዋ ጋር ለመጫወት ሄድኩ።” ሊንዲ አስተራራቂ መሆን ማለት ሌሎችን መርዳት እንደሆነ አንጸባረቀች። “ከዚያም ታስተላልፉታላችሁ። በእንደዚህ መልኩ ይቀጥላል።” ሊየም እንዲህ አለ፣ “ለእናንተ ክፉ እንኳን ቢሆኑ፣ ለሰዎች ክፉ አትሁኑ።” ሎንደንም አስተጋባ፣ “አንድ ሰው ቢሳለቅባችሁ ወይም ክፉ ቢሆንባችሁ፣ ’እባክህ አቁም’ በሉት”። ትሬቨር በማስተዋል እንዲህ አለ፣ “አንድ ለውዝ የሚተርፍ እንኳ ቢሆን እና ያንንም የምትፈልጉት ቢሆን፣ ከሌላው ጋር ተካፈሉ።”

የእነዚህ ልጆች መልስ ሁላችንም ከመለኮታዊ ዝንባሌ ጋር እና ከርህራሄ ጋር የተወለድን መሆናችንን የሚያረጋግጥ ነው። ማስተራረቅን፣ በዚህ ህይወትም ሆነ በሚቀጥለው ህይወት በረከትን በማምጣት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እነዚህን መለኮታዊ ባህርያት ከልባችን ጋር የሚያያይዝ ነው።

በቤት ውስጥ ማስተራረቅ

ሁለተኛ፣ በማሳመን፣ በትእግስት፣ በእርጋታ፣ በደግነት፣ በትህትና፣ እና በማያቋርጥ ፍቅር እርስ በርሳችን ተጽዕኖን ለመፍጠር የጌታን ንድፍ በመጠቀም በቤታችን ውስጥ ማስተራረቅን ማዳበር።

እነዚህን መሰረተ ሃሳቦች በተግባር በመጠቀም፣ አንድ ቤተሰብ ማስተራረቅን እንዴት የቤተሰብ ጉዳይ እንዳደረገ የሚያሳይ አንድ የሚያነሳሳ ታሪክ እነሆ።

ልጆች በዚህ ቤተሰብ ውስጥ በአብዛኛው ቁጡ፣ ራሱን ዝቅ በሚያደርግ፣ እና ድርቅ ያለ ባህሪ ካለው ጎልማሳ ግለሰብ ጋር መልካም ባልሆነ ግንኙነት እየተቸገሩ ነበር። ልጆቹም በጉዳት እና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በመሆን፣ ምናልባትም ያንን ተመሳሳይ ክፉ ባህርይ ማጉላት ብቸኛ መንገድ እንደሆነ ማሰብ ጀመሩ።

በአንድ ምሽት፣ ቤተሰቡ ጉዳዩ ስለፈጠረው አለመረጋጋት እና ጉዳት አብረው መነጋገር ጀመሩ። ከዚያም አንድ ሃሳብ መነጨ—መፍትሄ ሳይሆን፣ ነገር ግን ሙከራ ነበር።

በዝምታ ወይም በበቀል ምልሽ ከመስጠት ይልቅ፣ ልጆቹ አንድ ያልተጠበቀን ነገር ለማድረግ ወሰኑ፤ ለጉዳዩ በደግነት ምላሽ መስጠት። ትህትና ያለበትን ጥብቅ ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ምንም እንኳ ያገኙት ምላሽ መጥፎ ቢሆንም የታሰበበትን፣ ከልብ የመነጩ ደግ ቃላትን እና መልካም ተግባራትን ለማድረግ ነበር። ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ያንን ለመሞከር፣ ከሙከራውም በኋላ ዳግም ሊሰባሰቡ እና ሊመክሩበት ተስማሙ።

ምንም እንኳ አንዳንዶች በመጀመሪያ ያመነቱ ቢሆንም፣ በእውነተኛ ልብ ለእቅዱ ቁርጠኛ ሆነው ነበር።

ከዚያ ቀጥሎ የተከሰተው ነገር አስገራሚም ነበር።

ቀዝቃዛው የቃላት ልውውጥ መሟሟት ጀመረ። ፈገግታ ግንባር መቋጠርን ተክቷል። በአንድ ወቅት ሩቅ እና መጥፎ የነበረው ጎልማሳ መቀየር ጀመረ። በፍቅር በመምራት ምርጫቸው ተሞልተው የነበሩት ልጆች በለውጡ ሃሴትን አገኙ። ለውጡ እጅግ ሃያል ከመሆኑ የተነሳ የክትትል ስብሰባ እቅዱ አስፈላጊ አልነበረም። ደግነት በጸጥታ ስራዋን ሰርታለች።

በጊዜ ሂደት፣ እያንዳንዱን ከፍ በማድረግ እውነተኛ የጓደኝነት ሰንሰለት ተፈጥሯል። አስተራራቂ ለመሆን፣ ሌሎችን ይቅር እንላለን እናም ወደታች ከመጎተት ይልቅ ሌሎችን አስበንበት እንገነባቸዋለን።

በማህበረሰባችን ውስጥ ማስተራረቅ

ሶስተኛ፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ማስተራረቅ በሁለተኛው አስጨናቂ የዓለም ጦርነት ወቅት፣ ሽማግሌ ጆን ኤ. ውድሶ እንዳስተማሩት፦ “የሰላም ማህበረሰብን ለመገንባት ብቸኛው መንገድ ሰላም ወዳድ እና ሰላምን አምጪ የሆኑ ወንዶችን እና ሴቶችን መገንባት ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ፣ በዚያ የክርስቶስ ትምህርት … የዓለምን ሰላም በመዳፉ ይይዛል።”

የሚከተለው ታሪክ ያንን መርህ ውብ በሆነ ሁኔታ የሚገልጽ ነው።

ከአያሌ ዓመታት በፊት ሁለት ወንዶች—ከናይጄሪያ የመጡ አንድ የሙስሊም ኢማም እና አንድ የክርስቲያን ፓስተር—በአንድ ህመም በተሞላበት የሃይማኖት ክፍፍል የማይስማማ አስተያየት ነበራቸው። እያንዳንዳቸው በጠለቀ ሁኔታ ተሰቃይተዋል። ሆኖም ግን፣ በይቅርታ የፈውስ ሃይል አማካይነት፣ መንገዱን በአንድነት ለመጓዝ መረጡ።

ፓስተር ጄምስ ዉዬ እና ኢማም ሙሃመድ አሻፋ

ኢማም ሙሃመድ አሻፋ እና ፓስተር ጄምስ ዉዬ የሰላም ባልደረቦች የማይመስሉት ጓደኛሞች ሊሆኑ ቻሉ። በአንድነት፣ የእምነትን የስምምነት ማእከል መስርተዋል። አሁን ሌሎችን ጥላቻን በተስፋ እንዲተኩ ያስተምራሉ። የሁለት ጊዜ የኖቤል ሽልማት እጩ በመሆን፣ በቅርቡ የኮመን ዌልዝ ሰላም ተሸላሚ በመሆን ተሰይመዋል።

እነዚህ ቀድሞ ጠላት የነበሩ በአሁን ወቅት ተሰብሮ የነበረውን በመጠገን ጎን ለጎን የሄዱ፣ አስተራራቂ የመሆን የጌታ ግብዣ የሚቻል ብቻ ሳይሆን—ሃያል መሆኑ ያሳዩ ህያው ምስክሮች ናቸው።

የእግዚአብሔርን ክብር ስናውቅ፣ “እርስ በእርስ ለመቆሳሰል አናስብም፣ ነገር ግን በሰላም መኖርን እንጂ።” በጉባኤያችን እና በማህበረሰባችን፣ አንዳችን አንዳችንን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለማየት እንምርጥ።

የአንድ ሳምንት የአስተራራቂ እቅድ

በማጠቃለል፣ አንድን ግብዣ አቀርባለሁ። ማስተራረቅ ተግባርን ይጠይቃል—ከነገ ጀምሮ ያ ለእያንዳንዳችን ምን ሊሆን ይችላል? ባለሶስት ደረጃ ያለው የማስተራረቅ የአንድ ሳምንት እቅድን ልታስቡ ትችላላችሁን?

  1. ከክርክር የጸዳ ቤት፦ ክርክር ሲነሳ፣ አብርዱት እና ወደ ደግነት ቃላት እና ምግባር ቀይሩት።

  2. የበይነመረብ ድልድይ ግንባታ፦ ከመለጠፋችሁ በፊት፣ ወይም በአየር ሃሳባችሁን ከማዋላችሁ በፊት፣ “ይህ ድልድይን ይገነባልን?” በማለት ጠይቁ። ካልሆነም፣ አቁሙ። አትላኩት። ከዚያ ይልቅ መልካምነትን አካፍሉ። በጥላቻ ቦታ ሰላምን አትሙ።

  3. ጠግኑ እና ተዋሃዱ፦ እያንዳንዱ ቤተሰብ የተወጠረን ግንኙነት ይቅር ለማለት፣ ለማገልገል፣ ለመጠገን፣ እና ዳግም ለመዋሃድ መፈለግ ይችላል።

ማጠቃለያ

“የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው” ወደሚለው መልእክት ያካሄደኝ ስሜት ካገኘሁ ጥቂት ወራት ሆነውኛል። በማጠቃለል፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ልቤን በመንካት የመሰጠኝን ላካፍል እወዳለሁ።

ማስተራረቅ የክርስቶስ ዓይነት ባሕርይ ነው። የሚያስተራርቁ አንዳንድ ጊዜ ገራገር ወይም ደካማ ተደርገው ይቆጠራሉ—በሁሉም መልኩ። ዳሩ ግን የሚያስተራርቅ መሆን ማለት ደካማ መሆን አይደለም፣ ነገር ግን ዓለም በማይረዳው መልኩ ጠንካራ መሆን ማለት ነው። ማስተራረቅ ብርታትን እና መስማማትን ይጠይቃል ነገር ግን የመርህ መስዋእትነትን የሚጠይቅ አይደለም። ማስተራረቅ ማለት በተዘጋ አዕምሮ ሳይሆን በተከፈተ ልብ መምራት ማለት ነው። ማስተራረቅ በተጨበጠ ቡጢ ሳይሆን በተዘረጋ እጅ እርስ በርስ መቀራረብ ነው። ማስተራረቅ አደስ ነገር፣ በህትመት ደረጃ አዲስ የሆነ ነገር አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ እና በመፅሐፈ ሞርሞን ለነበሩት በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት የተሰጠበት ነው። ማስተራረቅ ጥንት ቤተክርስቲያኗ ዳግም ከተመለሰችበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ በኋለኛው ቀን ነቢያት ትምህርት የተሰጠበት ጉዳይ ነው።

አስተራራቂ ለመሆን በጣርን ጊዜ አፍቃሪ የሰማይ አባት እንደሆኑ ልጆች መለኮታዊ ሚናችንን እናሳካለን። የሰላም አለቃ፣ የህያው እግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምስክርነቴን እሰጣለሁ፣ አሜን።