የአጠቃላይ ባለስልጣናትን፣ የአከባቢ ሰባዎችን እና አጠቃላይ መሪዎችን መደገፍ
ወንድሞች እና እህቶች፣ አሁን፣ የድጋፍ ድምፃችሁን እንድትሰጧቸው የአጠቃላይ ባለሥልጣናትን፣ የአካባቢ ሰባዎችን እና የቤተክርስቲያኗን አጠቃላይ መሪዎችን ስም፣ ስለማቀርብ ዕድለኛ ነኝ፡፡
እባካችሁ ድጋፋችሁን በተለመደው መንገድ ግለጹ። ማንኛውንም ለድጋፍ የተጠሩ ግለሰቦችን የምትቃወሙ ካላችሁ፣ የካስማ ፕሬዝዳንታችሁን እንድታነጋግሩ እንጠይቃለን።
ስለዚህ፣ ዳለን ሀሪስ ኦክስ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ፕሬዚዳንት አድርገን እንድንደግፋቸው ይቀርባሉ።
ይህን የምትደግፉ እባካችሁን አሳውቁ።
ይህን የምትቃወሙ እንደዚሁ አሳውቁ።
የሚከተሉትን የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባላት አድርገን እንድንደግፍ ቀርቧል፦ ዳለን ኤች. ኦክስ፣ ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ ክውንተን ኤል. ኩክ፣ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ ኒል ኤል. አንድርሰን፣ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ፣ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ ዴል ጂ. ሬንላንድ፣ ጌሪት ደብልዩ ጎንግ፣ ዮልሲስ ሶሬስ እና ፓትሪክ ኪሮን።
ይህን የምትደግፉ እባካችሁ አሳውቁ።
ይህን የምትቃወሙ፣ በተመሳሳይ መልኩ አሳውቁ።
የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን አባላትን እንደ ነቢይ፣ ባለራዕዮች እና ገላጮች አድርገን እንድንደግፍቸው ቀርበዋል።
ይህን የምትደግፉ እባካችሁን አሳውቁ።
የምትቃወሙም በተመሳሳይ አይነት ምልክት አሳውቁ።
ሐሙስ ሚያዝያ 3 ቀን(እ.አ.አ) ባካሄድነው የጠቅላላ ጉባኤ የአመራር ስብሰባ ሁለት አዳዲስ የአካባቢ ሰባዎች እንደተጠሩ እና በቤተክርስቲያኗ ድረ-ገፅ ይፋ እንደተደረጉ እናሳስባለን። እነዚህን ወንድሞች በአዲሱ ምድባቸው እንድትደግፏቸው እንጋብዛችኋለን።
ይህን የምትደግፉ እባካችሁ አሳውቁ።
የምትቃወሙም በተመሳሳይ ምልክት አሳውቁ።
ሌሎች አጠቃላይ ባለስልጣናት፣ የአካባቢ ሰባዎች እና አጠቃላይ መሪዎች አሁን እንደተመሰረቱት እንድንደግፍ ቀርበዋል።
ይህንን የምትደግፉ ማሳወቅ ትችላላችሁ።
ይህን የምትቃወሙ ካላችሁም እንደዚሁ አሳውቁ።
ወንድሞች እና እህቶች፣ ለቤተክርስቲያኗ አመራር ስላሳያችሁት ድጋፍ እናመሰግናችኋለን።
በአካባቢ ሰባዎች የሚደረጉ ለውጦች
የሚቀጥሉት የአካባቢ ሰባዎች የአጠቃላይ ጉባኤ ክፍል በሆነው የመሪዎች ክፍለ ጊዜ ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል፦
ባኑ ኬ.ሂራናንዳኒ እና ፌርናንዶ ቢባስ