በክርስቶስ በኩል ያሉ ትናንሽ እና ቀላል ነገሮች
የክርስቶስን ትምህርት ቀለል ባለ እና በሚያተኩር መንገድ መጠቀም በየእለቱ ህይወታችን ደስታ እንድናገኝ ይረዳናል።
1. መግቢያ
ከሰላሳ ሶስት አመት በፊት፣ በዩታ ኦግደን ሚሲዮን ውስጥ ለማገልገ የሚሲዮን ጥሪ ደብዳቤዮን ተቀበልኩኝ። እርግጥ ነው፣ ከአውሮፓ በመምጣቴ ምክንያት፣ እንደ “አረንጓዴ ጄል-ኦ ከካሮት ጋር” እና “የቀብር ድንች” ያሉ አንዳንድ የአካባቢ የዩታ ወጎች ለእኔ ትንሽ ለየት ያሉ ነበሩ!
ይሁን እንጂ፣ በአብዛኛዎቹ ቅዱሳን ታታሪነት እና ደቀመዝሙርትነት፣ የቤተክርስቲያናን ስብሰባ በሚካፈሉት የሰዎች ቁጥር መብዛት እና ሙሉ በሙሉ በእንቅስቃሴ ላይ ባሉ የቤተክርስቲያኗ ፕሮግራሞች በጥልቁ ተገርሜ ነበር። የሚሲዮን አገልግሎቴ ሲያበቃ፣ የተሰማኝ ደስታ እና ያየሁት መንፈሳዊ ኃይል እና እድገት ለወደፊቱ ቤተሰቤ እንዲገኝ ማረጋገጥ ፈለኩኝ። በአስቸካይ ሒወቴን “ዘላለማዊ በሆኑት ኮረብታዎች ጥላ ስር” ለመኖር ቆርጬ ነበር።
ይሁን እንጂ፣ ጌታ የተለዩ እቅዶች ነበሩት። እቤት በተመለስኩበት የመጀመሪያው እሁድ ላይ፣ ጠቢብ የሆነው ኤጲስ ቆጶሴ በአጥቢያችን ውስጥ እንደ የወጣት ወንዶች ፕሬዘዳንት ሆኜ እዳገለግል ጠራኝ። እነዚን አስደናቂ የሆኑ የወጣት ወንዶችን ቡድንን በማገልገሌ ምክኒያት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር በመሆን የሚመጣው ደስታ ከቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ብዛት ወይም ደግሞ ከፕሮግራሙ ደረጃ ጋር ያለው ተዛምዶ ትንሽ እንደሆነ በፍጥነት ተረዳው።
ስለዚህ ቆንጆ የሆነችውን ሚስቴን ማርግሬትን ሳገባ፣ በደስታ አውሮፓ ውስጥ ለመቆየት እና እዛ የትውልድ አገራችን በሆነችው ጀርመን ውስጥ ቤተሰባችንን ለማሳደግ ወሰንን። በጋራ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ከብዙ አመታት በፊት እንዲ በማለት ያስተማሩትን ማየት ችለናል፦ “የሚሰማን ደስታ ከህይወታችን ሁኔታዎች ጋር ያለው ግንኙነት አነስተኛ ነው ነገር ግን በህይወታችን ውስጥ ትኩረት ከምንሰጣቸው ነገሮች ጋር ያለው ተዛምዶ ታላቅ ነው።” የህይወታችን ትኩረት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ መልእክት ላይ ሲሆን፣ የትም እንኑር የት ደቀመዝሙር በመሆን የሚገኘውን ሙሉ በረከት ልናገኝ እንችላለን።
2. በክርስቶስ በኩል ያሉ ትናንሽ እና ቀላል ነገሮች
ይሁን እንጂ፣ አለማዊነት፣ ውዝግብነት እና ግራ መጋባት እየጨመረ በመጣበት አለም እንዲሁም በተለያዩ እና አብዛኛውን ጊዜ በሚያጋጩ መልዕክቶች እና ፍላጎቶች በተሞላ አለም ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ባሉት ብዙ እና ውድ የሆኑ ነገሮች ላይ ቱክረታችን እንዳለ ሆኖ እንዲቆይ አይኖቻችን የታወሩ እና ልባችን የደነደነ እንዳይሆን መከላከል የምንችለው እንዴት ነው? ግራ በሚያጋባ ወቅት፣ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለየቆሮንጦስ ቅዱሳን “በክርስቶስ በኩል ባሉት ትናንሽ እና ቀላል ነገሮች” ላይ እንዲያተኩሩ በማስታወስ ትልቅ ምክርን ሰጠ።
የክርስቶስ አስተምህሮቶች እና የወንጌል ህግጋት ትናንሽ ልጆች ሊረዳቸው እስኪችሉ ድረስ እንኳን በጣም ቀላል ናቸው። በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነትን በመለማመድ፣ ንሰሐን በመግባት፣ በመጠመቅ፣ በመንፈስ ቅዱስ በኩል በመቀደስ እና እሰከጨረሻው በመጽናት የኢየሱስ ክርስቶስን የመቤዘት ሃይል ማግኘት እና የሰማይ አባታችን ያዘጋጀልንን ሁሉንም መንፈሳዊ በረከቶች መቀበል እንችላለን። ፕሬዘደንት ኔልሰን ይህንን ጉዞ “የቃልኪዳኑ መንገድ” እንዲሁም “የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ደቀመዝሙር የመሆን ሒደት” በማለት ቆንጆ በሆነ መልኩ ገልጸው ነበር።
ይህ መልዕክት በጣም ቀላል ከሆነ፣ አብዛኛውን ጊዜ የክርስቶስን ህግ ለመኖር እና ምሳሌዎቹን ለመከተል ከባድ እንደሆነ የሚሰማን ለምንድን ነው? ይህ ሊሆን የሚችለው ምንአልባት እኛ ትናንሽ የሆኑ ነገሮችን ካለጥረት ወይም ካለትጋት ለማከናወን እጅግ ቀላል እንደሆኑ አድርገን በተሳሳተ መንገድ ስለምንተረጉመው ይሆናል። ክርስቶስን መከተል ተከታታይነት ያለው ትጋት እና ለውጥን ይጠይቃል። “ተፈጥሮአዊ ሰውነትን በመቀየር እና ልክ እንደ ህጻን ልጅ መሆን አለብን።” ይህ “እምነታችንን በጌታ ላይ ማድረግን” እና ልክ ትናናሽ ልጆች እንደሚያደርጉት ውስብስብ የሆኑ ነገሮችን መተውን ያካትታል። የክርስቶስን ወንጌል ቀላል በሆነ እና አትክሮት በተሰጠው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ በእለት ተእለት ህወታችን ደስታን እና በአገልግሎታችን ሚሪትን ማግኘት እንድንችል እንዲሁም በሂወት ውስጥ ላሉ አንዳድን በጣም አስቸጋሪ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስን እንድናገኝ እና ትልቁን መከራችችን መጋፈጥ እንድንችል ጥንካሬን ይሰጡናል።
ነገር ግን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን በሕይወታችን ሙሉ ጉዞ ውስጥ ይህን ቀላልነት በተግባር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን? አዳኝን ለመከተል በምንፈልግበት ጊዜ ፕሬዘደንት ኔልሰን “በንጹሕ እውነት፣ በንፁህ ትምህርት እና በንፁህ መገለጥ” ላይ እንድናተኩር አሳስበውን ነበር። “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንዳደርግ ይፈልግብኛል?” በማለት አዘውትረው መጠየቅ፣ ጥልቅ አቅጣጫ ያሳያል። የእሱን ምሳሌ መከተል እርግጠኛ ባልሆነ መንገድ አስተማማኝ መንገድን እና አፍቃሪ እና ቀን ወደ ቀን ለመያዝ የሚቻል የሚመራ እጅን ይሰጣል። እርሱ የሰላም አለቃና መልካም እረኛ ነው። እርሱ አጽናኛችን እና አዳኛችን ነው። እርሱ ዓለታችንና መጠጊያችን ነው። እሱ ጓደኛ ነው—ጓደኛህ እና ጓደኛዬ! ሁላችንም እግዚአብሔርን እንድንወድ፣ ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ እና ባልንጀራችንን እንድንወድ ይጋብዘናል።
የእርሱን ምሳሌ ለመከተል እና በክርስቶስ ላይ ባለ እምነት ወደፊት ስንገፋ፣ የኃጢያት ክፍያውን ሃይል ስንቀበል፣ እና ከእርሱ ጋር የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ለማስታወስ ስንመርጥ፣ በፍቅር ልባችንን ይሞላል፣ ተስፋ እና ፈውስ መንፈሳችንን ያነሳሳል እናም ደግሞ መራራነትና ሀዘን በምስጋና እና ቃል ለተገቡ በረከቶች ለመጠበቅ ባለ ትግስት ይተካል። አንዳንድ ጊዜ፣ እራሳችንን ጤናማ ካልሆኑ ግንኙነቶች ማራቅ ወይም የባለሙያ እርዳታን ማግኘት ሊያስፈልገን ይችላል። ነገር ግን በሁሉ ሁኔታ፣ ቀላል የሆኑ የወንጌል መርሆችን ተግባራዊ ማድረግ በህይወት ተድጋሮቶች በጌታ መንገድ ማለፍ እንድንችል ይረዳናል።
እንደ ጸሎትን፣ ጾምን፣ የቅዱሳን መጽሐፍት ጥናትን፣ በየእለቱ ንሰሃ መግባትን፣ ቅዱስ ቁርባንን በየሳምንቱ መውሰድን እና ተከታታይነት ያለው በጌታ ቤት ውስጥ አምልኮ ማድረግን የመሳሰሉ የነዚህ ቀላል ተግባሮች አቅምን ዝቅ እናደርጋለን። ነገር ግን “አንዳንድ ትላላቅ ነገሮችን” ማድረግ እንደሌለብን አስተውለን ቀላል እና ንጹ የሆኑ አስተምህሮቶች መጠቀምን ለእራሳችን ማእከል ስናደርግ፣ ወንጌሉ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን እንዴት “በልዩ ሁኔታ እንደሚሰራ” ማየት እንጀምራለን። ከባድ ሐዘን ገጥሞን ቢሆን እንኳን ጥንካሬን እና “እግዚአብሔር ፊት ልበ ሙሉነትን” ማግኘት እንችላለን። ሽማግሌ ኤም ራስል ባላርድ ብዙ ጊዜ፦ “እኛ ሰላምን፣ ደስታን እና ሐሴትን የምናገኘው በነዚያ ትናንሽ እና ቀላል በሆኑ ነገሮች ውስጥ እንደሆነ አስታውሰውናል።”
በክርስቶስ በኩል የሚገኙትን ቀላል እና ግልጽ የሆኑ ነገሮችን ተግባራዊ ማድረግ ሰዎችን ከክንውኖች በላይ ማድረግ እና ዘላለማዊ ግንኙነቶችን ከአጭር ጊዜ ባሕሪዎች ማስበለጥ እንድንችል ያደርገናል። በእግዚአብሔር የደህንነት እና ከፍ ከፍ የመደረግ ስራ ላይ፣ የቤት ለቤት ጥየቃ አገልግሎታችንን ከማደራጀት ይልቅ “ይበልጥ ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ላይ እናተኩራለን።” ማድረግ ባቃተን ነገሮች ላይ ከመጨነቅ ይልቅ ማድረግ ለምንችላቸው ነገሮች ቅድሚያ ለመስጠት እራሳችንን ነጻ እናደርጋለን። ጌታ ይህንን አስታውሶናል ፦ “ስለዚህ፣ መልካም ሥራን ትሰሩ ዘንድ አትታክቱ፣ የታላቅ ስራን መሰረት እየገነባችሁ ነውና። እናም ከትትንሽ ነገሮች ታላላቅ ነገሮች ይወጣሉና።” ሁኔታዎቻችን ምንም ይሁኑ ምን ትናናሽ ነገሮችን ለመስራት እና በትህትና ለመተግበር የሚያነሳሳ ምን የመሰለ ሃያል ማነቃቂያ ነው።
3. ኦማ ሲዝላ
ሴት አያቴ ማርታ ሲዝላ ትላልቅ ነገሮችን ለማምጣት “ትናንሽ እና ቀላል ነገሮችን” በመስራት ግሩም ምሳሌ ነበረች። በፍቅር ኦማ ሲዝላ ብለን በፍቅር እንጠራት ነበር። ኦማ፣ ሴልቦንጄል በተባለች በምዕራብ ፕረሻ በኩል በምትገኝ ትንሽዬ መንደር ውስጥ ከቅድመ አያቴ ጋር በመሆን ግንቦት 30፣ በ1926 (እ.አ.አ) የኢየሱስ ክርስቶስን ወጌል ተቀበለች።
ማርታ ሲዝላ (ከቀኝ) በጥምቀቷ ቀን።
ጌታን እና ወንጌሉን ትወድ ነበር እንዲሁም የገባቻቸውን ቃልኪዳኖች በመጠበቅ ቆራጥ ነበረች። በ1930 (እ.አ.አ) በሰአቱ የቤተክርስቲያኗ አባል ያልነበረውን አያቴን አገባች። ከዚ ጊዜ ጀምሮ ለኦማ ወደ ቤተክርስቲያን ስብሰባዎች መሄድ የማይቻል ሆነ ምክኒያቱም የወንድ አያቴ እርሻ በአቅራቢያው ከሚገኘው መሰብሰቢያ ርቀት ነበረው። ነገር ግን ማድረግ የምትችለው ነገር ላይ አቶከረች። ኦማ መጸለይን፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ማንበብን እና የጺዮንን መዝሙሮች መዘመርን ቀጠለች።
አንዳንድ ሰዎች በነበራት እምነት ላይ ንቁ ያልሆነች መስሎአቸው ሊሆን ይችላል ነገር ግን ይህ ከእውነት የራቀ ነበር። አክስቴ እና አባቴ ሲወለዱ ቤት ውስጥ የክህነት ስልጣን ተሸካሚ እና በአቅራቢያ ያሉ የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ወይም ስነ ስርአቶችን ማግኘት በማይቻልበት ጊዜ እሷ በድጋሚ የተቻላችን አደረገች እንዲሁም ልጆቿ “እንዲጸልዩ እና በጌታ ፊት በጥንቃቄ እንደራመዱ” በማስተማር ላይ አተኮረች። ከቅዱስ መጽሃፍት ታነብላቸው፣ የጺዮንን መዝሙሮች አብራቸው ትዘምር እንዲሁም በየቀኑ አብራቸው ትጸልይ ነበር። 100 ፐርሰንት ቤትን ያማከለ የቤተክርስቲያን አገልግሎት።
በ1945 (እ.አ.አ)፣ ወንዱ አያቴ ከቤት ርቆ ባለው ጦርነት ውስጥ እየተሳተፈ ነበር። ጠላቶች ወደ እርሻቸው ሲመጡ፣ ኦማ ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ መጠለያን ለማግኘት የሚወዱትን እርሻ ትታ ሁለት ትንንሽ ልጆቿን ይዛ ሄደች። ከባድ እና ለሂወት አስጊ ከሆነ ጉዞ በሃላ፣ በስተመጨረሻም በ1945 በሰሜናዊ ጀርመን መጠለያ አገኙ። ሰውነታቸው ላይ ከለበሱት ልብስ በስተቀር የቀራቸው አንድም ነገር አልነበረም። ነገር ግን ኦማ ማድረግ የምትችለውን ነገር በማድረግ ቀጠለች፦ ከልጆቿ ጋር በየቀኑ ጸለየች። በልቧ የሸመደደችውን የጺዮንን መዝሙሮች አብራቸው በየቀኑ ዘመረች።
ህይወት በጣም ከባድ ነበር፣ እናም ለብዙ አመታት አትኩሮቷ በጠርጴዛው ላይ የሚበላ ምግብ መኖሩን ማረጋገጥ ላይ ብቻ ነበር። ነገር ግን በ1955 (እ.አ.አ) አባቴ 17 አመቱ ሳለ፣ በሬንስበርግ ከተማ ወደ ንግድ ትምህርት ቤት እየሄደ ነበር። አንድ ህንጻ አልፎ ሲሄድ [“Kirche Jesu Christi der Heiligen der Letzten Tage”] “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን” የሚልን ጽሁፍ አነበበ።” ይህንንም አሰበ፦ “ይህ የሚገርም ነው፣ ይህ እኮ የእናቴ ቤተክርስቲያን ነው።” ስለዚህ፣ ወደቤት ሲመጣ፣ ለኦማ ቤተክርስቲያኗን እንዳገኘ ነገራት።
25 አመታት ሙሉ ከቤተክርስቲያኗ ጋር ምንም ግኑኝነት ሳይኖራት ከቆየች በኋላ ምን ተሰምቷት እንደሆነ ልታስቡ ትችላላችሁ። ቀጣዩን እሁድ ለመሳተፍ ቆርጣ ነበር እንዲሁም አባቴ ከእሷ ጋር እንዲሄድ አሳምናው ነበር። ሬንድስበርግ እነሱ ይኖሩበት ከነበረው ስፍራ ከ20 ማይሎች (32 ኪሎ ሜትር) በላይ ነበር። ይህ ግን ኦማ ከቤተክርስቲያን ሊያስቀራት አይችልም ነበር። በቀጣዩ እሁድ፣ አንድ ላይ ከአባቴ ጋር ብስክሌቷን ይዛ እየነዱ ወደ ቤተክርስቲያን ሄዱ።
የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ሲጀምር፣ አባቴ ፕሮግራሙ በቅርብ እንዲያበቃ ተስፋ እያደረገ የመጨረሻ ወንበሮቹ ላይ ቁጭ አለ። ይህ የኦማ ቤተክርስቲያን እንጂ የእርሱ አልነበረም። ያየው ነገር እጅግ በጣም የሚያበረታታ አልነበረም፣ የተመለከተው የሚሳተፉት እድሜያቸው የገፉ ጥቂት ሴቶች እና በስብሰባው ውስጥ ሁሉንም ነገር በጉብዝና ይመሩ የነበሩ ሁለት ሚሲዮናዊያንን ነበር። ነገር ግን ከዛ በኋላ አባቴ ትንሽ ልጅ ከነበረ ጀምሮ ይሰማውን የነበረውን የጺዮንን መዝሙሮች መዘመር ጀመሩ፦ “Come, Come, Ye Saints,” “O My Father,” “Praise to the Man.” ይህች ትንሽ መንጋ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ የሚያውቀውን የጺዮን መዝሙሮች ሲዘምሩ መስማቱ ልቡን ነካው፣ እናም ወዲያውኑ እና ያለ ምንም ጥርጥር ቤተክርስቲያኗ እውነት እንደሆነች አወቀ።
አያቴ ከ25 ዓመታት በኋላ የተሳተፈችው የመጀመሪያው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ አባቴ ዳግም ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነተኛነት የግል ማረጋገጫን ያገኘበት ስብሰባ ነበር። ከሶስት ሳምንታት በኋላ መስከረም 25፣ በ1955 (እ.አ.አ) ከአያቴ እና ከአክስቴ ጋር ተጠመቀ።
በሬንድስበርግ ያ ትንሽ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ከተደረገ ከ70 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። ስለ ኦማ ብዙ ጊዜ አስባለሁ፣ በእነዚያ በብቸኝነት ምሽቶች፣ ማድረግ የምትችለውን ትንሽ እና ቀላል ነገር፣ ለምሳሌ ስትጸለይ፣ ስታነብ እና ስትዘምር ምን ተሰምቷት እንደሚችል አስባለሁ። ዛሬ እዚህ በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ ቆሜ ስለ ኦማ ስናገር፣ ፈተናዎቿ እንዳሉ ሆነው፣ ቃል ኪዳኖቿን ለመጠበቅ እና በጌታ ለመታመን ባሳየችው ቁርጠኝነት እንዲሁም ለእሷ ብቻ ሳይሆን፣ ምናልባት አሁን ትንሽ ለውጥ እያዩ ነገር ግን ወደፊት ትላላልቅ ነገሮች እንደሚሆኑ በማመን በአስቸጋሪ ሁኔታቸው ውስጥ ሆነው በክርስቶስ በኩል ያሉ ትናንሽ እና ቀላል ነገሮች ላይ ትኩረትን ለሚያደርጉ በአለም ዙሪያ ላሉት ለብዙዎቹ ድንቅ ቅዱሳኖች ጭምር ልቤ በትህትና እና በአመስጋኝነት ይሞላል።
4. ትናንሽ እና ቀላል ነገሮች
የወንጌሉ ትናንሽ እና ቀላል ነገሮች እንዲሁም በታማኝነት በክርስቶስ ላይ ማተኮር ወደ እውነተኛ ደስታ እንደሚመሩን፣ ድንቅ ተአምራትን እንደሚያመጡ እና ሁሉም ቃል የተገቡ በረከቶች እንደሚፈጸሙ በራስ መተማመን እንደሚሰጡን በራሴ ተሞክሮ ተምሬአለሁ። ይህ ለእኔ እውነት እንደሆነ ሁሉ ለእናንተም እውነት ነው። ሽማግሌ ጀፍሪ አር ሆላንድ እንዳሉት፣ “አንዳንድ በረከቶች በቶሎ ይመጣሉ፣ አንዳንዶች ዘግይተው ይመጣሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ መንግስተ ሰማያት እስክንገባ ድረስ አይመጡም፣ ነገር ግን የኢየሱስ ከርስቶስን ወንጌል ለሚቀበሉ በረከቶቹ ይመጣሉ።” ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።