አጠቃላይ ጉባኤ
የምትጠሩበት ስም
የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:1

የምትጠሩበት ስም

በኢየሱስ ስም መጠራት ምን ማለት ነው?

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ ጌታ በቀጥታ የሚናገረን ከሆነ፣ እኛ እንድንረዳው የሚያደርገው የመጀመሪያው ነገር ስለ እውነተኛው ማንነታችን ነው፦ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች፣ የቃል ኪዳን ልጆች እና የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነን። ሌላ ማንኛውም ዓይነት ስያሜ በመጨረሻ ልንመካበት አንችልም።

ለእራሴ ይህንን የተማርኩት ትልቁ ልጄ የመጀመሪያውን ሞባይል ስልኩን ሲያገኝ ነበር። በታላቅ ደስታ የቤተሰቦቹን እና የጓደኞቹን ስም ወደ እውቂያዎቹ እየመዘገበ ማስገባት ጀመረ። አንድ ቀን፣ እናቱ ስትደውልለት አየሁ። በስክሪኑ ላይ “እናት” የሚል ስም ታየ። ያ የማስተዋል እና የክብር መልክ ያለው ምርጫ ነበር—እናም በቤታችን ውስጥ ካሉት ወላጆች ለተሻለችው አክብሮት እንዳለን የሚያሳይ መሆኑን አምናለሁ። በፍጥረት መሰረትም፣ የማወቅ ጉጉት ተሰማኝ። ምን አይነት ስም ለእኔ ሰጥቶኛል?

ዌንዲ “እናት” ተብላ ከተሰየመች እኔ ደግሞ “አባት” መሆን አለብኝ ብዬ በማሰብ የእርሱን ስም አድራሻዎች በስልኩ ውስጥ ማሰስ ጀመርኩ። አልተገኘም። “አባ” የሚል ካለም ፈልኩኝ። አሁንም አልተገኘም። የማወቅ ጉጉቴ ወደ መጠነኛ ጭንቀት ተለወጠ። “ኮሪ” ብሎ ይሆን የሚጠራኝ? በፍፁም። በመጨረሻም ጥረት፣ “እኛ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ነን—ምናልባትም ‘ፔሌ’ ብሎ ይጠራኛል” ብዬ አሰብኩ። የምኞታዊ አስተሳሰብ። በመጨረሻም፣ የራሴን ስልክ ቁጥር ደወልኩ፣ እና ሁለት ቃላት በስክሪኑ ላይ ብቅ አሉ፦ “እናት ያልሆነው”!

ወንድሞች እና እህቶች፣ እናንተ በምን ዓይነት ስም ነው የተጠራችሁት?

ኢየሱስ ተከታዮቹን በብዙ ዓይነት ስሞች ጠርቷቸዋል፦ ቀደመዛሙርት። ወንዶች እና ሴቶች ልጆች። የነቢያት ልጆች። በጎች። ወዳጆች። የአለም ብርሀን። ቅዱሳን። እያንዳንዱም ዘላለማዊ ጠቀሜታዎችን ይዘዋል እናም ከአዳኝ ጋር ያለውን ግላዊ ግንኙነት ያጎላሉታል።

ነገር ግን ከእነዚህ ስሞች መካከል አንዱ ከሌሎቹ ሁሉ በላይነት ይነሳል—እናም ያም የክርስቶስ ስም ነው። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ ንጉስ ቢንያም በአጽኖት እንዲህ አስተምሯል፦

“ደህንነት ሊመጣበት የሚችል ሌላ ስም የለም፤ ስለዚህ የክርስቶስን ስም እንድትወስዱ እፈልጋለሁ። …

“እናም እንዲህ ይሆናል፣ ማንም ይህንን ያደረገ በእግዚአብሔር ቀኝ ይገኛል፣ የሚታወቅበትን ስም ያውቃልና፤ በክርስቶስ ስም ይጠራልና።”

የክርስቶስን ስም በራሳቸው ላይ የወሰዱት የእርሱ ደቀ መዛሙርት እና ምስክሮች ይሆናሉ። በሐዋርያት ሥራ ውስጥ፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በኋላ፣ ማንም በኢየሱስ የሚያምን፣ የሚጠመቅ እና መንፈስ ቅዱስን የሚቀበል ሁሉ የኃጢያት ስርየትን እንደሚቀበል በእግዚአብሔር የተመረጡ ምስክሮች እንዲሰብኩ እና እንዲመሰክሩ እንደታዘዙ እናነባለን። እነዚህን ቅዱስ ስነ ስርዓቶች የተቀበሉት ከቤተክርስቲያኗ ጋር ተሰብስበው ደቀ መዛሙርት ሆኑ እና ክርስቲያንኖችም ተባሉ። መፅሐፈ ሞርሞንም የክርስቶስን አማኞች እና የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባል የሆኑትን እንደ ክርስቲያኖች እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የገቡትን “የክርስቶስ ልጆች፣ ወንዶች እና ሴት ልጆቹ” ብሎ ይገልፃቸዋል።

በኢየሱስ ስም መጠራት ምን ማለት ነው? ቃል ኪዳኖችን መግባት እና መጠበቅ ፣ ሁልጊዜ እርሱን ማስታወስ፣ ትእዛዛቱን ማክበር፣ እና “በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ነገር … የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነው ለመቆም ዘንድ … ፈቃደኛች” መሆን ማለት ነው። የክርስቶስን መልእክት ከትምህርቱ፣ ከቃል ኪዳኖቹ እና ከስርአቶቹ ጋር በአለም ዙሪያ ሲያደርሱ ከነቢያት እና ከሐዋርያት ጋር መቆም ማለት ነው። እንዲሁም መከራን ለማስታገስ እና ብርሃን ለመሆን እና ለሰው ሁሉ በክርስቶስ ተስፋን ለማምጣት ሌሎችን ማገልገል ማለት ነው። በእርግጥም፣ ይህ የዕድሜ ልክ ሂደት ነው። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው “ይህ ማንም ሰው በአንድ አፍታ ሊደርስበት የማይችል ደረጃ ነው።”

ምክንያቱም የደቀ መዝሙርነት ጉዞ ጊዜን እና ጥረትን ስለሚጠይቅ “በሥርዓት ላይ ሥርዓትን፣ በትእዛዝም ላይም ትእዛዝ “ ተደርጎ የሚገነባ ሲሆን፣ በዓለማዊ የማዕረግ ስሞች መጠመድ ቀላል ነው። እነዚህ ጊዜያዊን ዋጋን ብቻ ይሰጣሉ እናም በጭራሽ ግን በራሳቸው በቂ አይደሉም። ቤዛ እና ዘላለማዊ የሆኑት ነገሮች “በቅዱሱ መሲህ እና በእርሱ አማካይነት” ብቻ ይመጣል። ስለዚህ፣ በተለይም ብዙ የሚፎካከሩ ድምፆች እና ተፅዕኖዎች ባሉበት ዘመን፣ ደቀ መዝሙርነትን ቅድሚያ እንድንሰጥ የሚያደርጉትን ትንቢታዊ ምክሮችን መከተል በወቅቱ አስፈልጊ እና ጥበብም ነው። የንጉሥ ቢንያም ምክር ዋና መልእክት ይህ ነበረ፣ “የምትጠሩበትን ድምፅ፣ እናም ደግሞ በእርሱ የምትጠሩበትን ስም እንድታዳምጡና እንድታውቁ፣ … በልባችሁ የተፃፈውን [የክርስቶስን] ስም ሁልጊዜ እንድትጠብቁ እፈልጋለሁ።”

ማርቲን ጋስነር

ይህንን በራሴ ቤተሰብ ውስጥ አይቻለሁ። ቅድመ አያቴ ማርቲን ጋስነር ለዘለአለም ተለውጧል ምክንያቱም ትሁት የቅርንጫፍ ፕሬዘዳንት የአዳኝን ጥሪ በመመለሱ የተነሳ። በ1909 (እ.አ.አ) በጀርመን ውስጥ፣ ጊዜታዎቹ የከፉ ነበሩ፣ እናም ገንዘብ ማግኘት ከባድ ነበር። ማርቲን በቧንቧ ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ የብየዳ ሰራተኛ ሆኖ ይሠራ ነበር። በራሱ ፈቃድ፣ አብዛኛውን የክፍያ ቀናት በመጠጥ፣ በማጨስ እና ለሌሎች መጠጥ በመግዛት አብቅቷል። በመጨረሻም ሚስቱ ከዚህ ድርጊቱ ካልተቆጠበ ጥላው እንደምትሄድ አስጠነቀቀችው።

አንድ ቀን፣ የማርቲን የስራ ባልደረባው የተጨማደደ የሀይማኖት ወረቀት በእጁ ይዞ ወደ መጠጥ ቤቱ ሲሄድ አገኙት። በመንገድ ላይ አግኝቶት ነበር እናም ዋይስሰን ሲ ቮን ደን ሞርሞንን? ወይም ስለ ሞርሞኖች ምን የምታውቀው ነገር አለ? የሚለውን በራሪ ጽሁፍ ካነበበ በኋላ የተለየ ነገር እንደተሰማው ለማርቲን ነገረው። ያም ርዕር እንደተቀየረ እርግጠኛ ነኝ።

ጀርባው ላይም ማህተም የተደረገበት አድራሻ ቤተክርስቲያኗ የት እንዳለች ለመረዳት ትንሽ በቂ ነበር። ይህም በብዙ ርቀት ላይ ትገኝ ነበር፣ ነገር ግን ባነበቡት ነገር ውስጣቸው ስለተነካ በዚያው እሁድ በባቡር ተሳፍረው ይህን ለመፈተሽ ወሰኑ። እንደደረሱም አድራሻው የጠበቁት ቤተክርስቲያን ሳይሆን የቀብር ቤት ሆኖ አገኙት። ማርቲን ተጠራጠረ—ምክንያቱም በእውነቱ፣ በቀብር ቤት ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን የሰጠችው ተስፋ በጣም ትንሽ ስለነበር።

ነገር ግን ፎቅ ላይ፣ በሚከራይ አዳራሽ ውስጥ፣ ጥቂት የቅዱሳን ቡድን አገኙ። አንድ ሰውም ወደ ምስክርነት ስብሰባ እንዲመጡ ጋበዛቸው። ማርቲን በመንፈስ ተነክቶ ነበር እናም በቀላል፣ እና በጠነከሩ ምስክርነቶችም በጣም ተደንቆ፣ እርሱም የራሱንም ምስክርነት ተካፈለ። እናም በዚያ ቦታ ነበር፣ ይገኝበት በማይመስል ስፍራ ውስጥ፣ እውነት መሆን እዳለበት አስቀድሜ አውቃለሁ ያለው።

ከዚያም በኋላ፣ ሰውየው እራሱን እንደ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት አስተዋወቀ እናም ተመልሰው እንደሚመጡ ጠየቃቸው። ማርቲን በጣም ሩቅ ቦታ እንደሚኖር እና በየእሁዱ ለመጓዝ አቅም እንደሌለው ገለጸ። የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ በቀላሉ “ተከተሉኝ” አለው።

የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ ጓደኛ ወደሚሠራበት በአቅራቢያው ወደሚገኝ ፋብሪካ ጥቂት መንገዶችን አብረው ተጓዙ። ከአጭር ጊዜ ውይይት በኋላ ማርቲን እና ጓደኛው ለሁለቱም የሥራ እድል ቀረበላቸው። ከዚያም፣ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱም ወደ አንድ የመኖሪያ ሕንፃ መራቸውና ለቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ቤት አዘጋጁላቸው።

ይህ ሁሉ የሆነው በሁለት ሰዓታት ውስጥ ነበር። ማርቲን እና ቤተሰቡ በሚቀጥለው ሳምንት ተዛወሩ። ከስድስት ወራት በኋላ፣ ተጠመቁ። በአንድ ወቅት ተስፋ ቢስ ሰካራ ተብሎ የሚታወቀው ሰው፣ ለአዲሱ እምነቱ ቀናተኛ በመሆኑ—በዚህ ጊዜ የከተማው ሰዎች “ቄሱ” ብለው ይጠሩት ጀመር፣ ምናልባትም የአሽሙር ስሜት ሳይኖረው አይቀርም።

የቅርንጫፉን ፕሬዚዳንት በተመለከተ፣ ስሙን ልነግራችሁ አልችልም—ማንነቱ ለጊዜው ጠፍቶኛል። እኔ ግን ደቀ መዝሙር፣ አምባሳደር፣ ክርስቲያን፣ ደጉ ሳምራዊ፣ እና ወዳጅ ብዬ እጠራዋለሁ። የእርሱ ተጽዕኖ አሁንም ድረስ ከ116 ዓመታት በኋላም ይሰማል፣ እናም እኔም በደቀ መዝሙርነቱ ጫንቃ ላይ ቆሜያለሁ።

ጋስነር በቤተመቅደስ አጠገብ

በፖም ፍሬ ውስጥ ያሉትን ዘሮችን መቁጠር ትችላለህ፣ ነገር ግን ከአንድ ዘር የሚመጡትን የፖም ፍሬዎች መቁጠር አትችልም የሚል አንድ አባባል አለ። በቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ የተዘራው ዘር ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፍሬዎችን አፍርቷል። ከ48 ዓመታት በኋላ በመጋረጃው በሁለቱም በኩል፣ በርካታ የማርቲን ቤተሰብ ትውልዶች በበርን ስዊዘርላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ሊታተሙ እንደሚዘጋጁ አስቀድሞ አያውቅም ነበር።

ምናልባትም ከሁሉ የሚበልጡት ስብከቶች የማንሰማቸው ነገር ግን በጸጥታ ውስጥ የምናያቸው ኢየሱስን ለመምሰል በሚጥሩ፣ የተራ ሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚስተዋሉ ትሁት ድርጊቶች እና ተግባራት ናቸው። እኚህ ደግ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ያደረጉት ነገር ለወረት ሚደረግ የተግባር ዝርዝር አልነበረም። በአልማ መጽሐፍ እንደተገለጸው ወንጌልን እየኖረበት ነበር፦ “የተራቡትን፣ ወይም የተጠሙት፣ የታመሙትን … ማንንም አላባረሩም፤ … ለሁሉም፣ ለወጣቶችም ሆነ ለሽማግሌዎች፣ … ለወንድም ሆነ ለሴት … ደግ ነበሩ።” ልንዘነጋው የማይገባን ነጥብ ደግሞ ቢኖር፣ “ከቤተክርስቲያን ለሆኑም ሆነ ላልሆኑት” የትኛዎቹንም አላሰናበቱም።

ጆሴፍ ስሚዝ እንዳለው፣ በራሳቸው ላይ የክርስቶስን ስም የሚወስዱት “በእግዚአብሔር ፍቅር የተሞላ ሰው፣ ቤተሰቡን ብቻ በመባረክ አይረካም፣ ነገር ግን መላውን የሰው ዘር ለመባረክ በመጨነቅ መላውን አለም ይዘልቃል።”

ኢየሱስ የኖረው በዚህ መንገድ ነበር። እንዲያውም፣ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉንም መጻፍ እስኪያቅታቸው ድረስ ብዙ ነገሮችን አድርጓል። ሐዋርያው ዮሀስ እንደመዘገበው፣ “ኢየሱስ ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፣ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለየጻፉት መጻህፍት አለም ራሱ ባልበቃቸው ይመስለኛል።”

ከሌሎች ጋር በተገናኘን ቁጥር የእግዚአብሔርን ፍቅር እና የመንፈስ ቅዱስን የማረጋገጫ ሀይል እንዲሰማቸው መልካም በማድረግ እና ደቀ መዝሙርነትን የህይወት ዘመን ቅድሚያ በመስጠት የክርስቶስን ምሳሌ ለመከተል እንትጋ። ከዚያም ከአያቴ እንዲሁም ከሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች ልክ እንደ ደቀ መዝሙሩ እንድርያስ፣ “መሲሑን አግኝተናል” ብለው ካወጁት ጋር ልንቀላቀል እንችላለን።

በመጨረሻ፣ ማንነታችን በአለም ነገር ሊገለጽ አይችልም። ነገር ግን የእኛ ደቀ መዝሙርነት በምንቀበላቸው ስርዓቶች፣ በምንጠብቃቸው ቃል ኪዳኖች እና በመልካም ተግባራችን ለእግዚአብሔር እና ለባልንጀራችን በምናሳየው ፍቅር ይገለጻል። ፕሬዚዳንድ ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ እኛ በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጆች፣ የቃአል ኪዳን ልጆች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ነን።

ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው እንደሆነ እና እኛን እንዳዳነን እመሰክራለሁ። “በስም ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ” ያለው እርሱ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም.ኔልሰን፣ “Choices for Eternity [ለዘለአለም የሚሆኑ ምርጫዎች]” (worldwide devotional for young adults፣ ግንቦት 15፣ 2022 (እ.አ.አ)፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት ተመልከቱ።

  2. ዮሐንስ 8፥3113፥35 ተመልከቱ።

  3. 2 ቆሮንጦስ 6፥18ሞዛያ 27፥25 ተመልከቱ።

  4. 3 ኔፊ 20፥25 ተመልከቱ።

  5. ዮሐንስ 10፥27 ተመልከቱ።

  6. ዮሐንስ 15፥14–15 ተመልከቱ።

  7. ማቴዎስ 5፥14–163 ኔፊ12:14–16 ተመልከቱ።

  8. ሮሜ 1፥6–7ኤፌሶን 2፥19; 3 ኔፊ 23፥9 ተመልከቱ።

  9. ሞዛያ 5፥8–9

  10. የሐዋርያት ስራ 2፥3810፥39–48 ተመልከቱ።

  11. የሐዋሪያት ስራ 11፥26 ተመልከቱ።

  12. አልማ 46፥15፤ እንዲሁም ሞዛያ 6፥4–6 ተመልከቱ፡፡

  13. ሞዛያ 5፥7

  14. ሞሮኒ 6፥3 ተመልከቱ።

  15. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79 ተመልከቱ።

  16. ዮሐንስ 14፥15 ተመልከቱ።

  17. ሞዛያ 18፥9

  18. ሞዛያ 2፥17 ተመልከቱ።

  19. 3 ኔፊ 15፥12 ተመልከቱ።

  20. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ] [2007 (እ.አ.አ)]፣ 211።

  21. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥12፤ ደግሞም ኢሳይያስ 28፥10 ተመልከቱ።

  22. 2 ኔፊ 2፥6

  23. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2024 (እ.አ.አ)፣ 121።

  24. ሞዛያ 5፥12፤ ደግሞም ሞዛያ 5፥14–15 ተመልከቱ።

  25. 2 ቆሮንጦስ 5፥20 ተመልከቱ።

  26. ሉቃስ 10፥30–37 ተመልከቱ

  27. ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2020 (እ.አ.አ)፣ 76።

  28. የሐዋርያት ስራ 10፥38 ተመልከቱ።

  29. አልማ 1፥30

  30. Teachings: Joseph Smith [ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ]፣ 426።

  31. ዮሐንስ 21፥25፤ ደግሞም 3 ኔፊ 26፥6 ተመልከቱ።

  32. ዮሀንስ 1፥41

  33. ራስል ኤም. ኔልሰን “Choices for Eternity [ለዘለዓልመ ያለ ምርጫ]።”

  34. ኢሳይያስ 43፥1