አጠቃላይ ጉባኤ
በመሰዊያ መንበርከኪያ ላይ ያሉ ትሁት ነብሳት
የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:24

በመሰዊያ መንበርከኪያ ላይ ያሉ ትሁት ነብሳት

ቃል ኪዳኖቻችንን ስንገባ እና ስናከብር፣ ወደ ምህረቱ፣ ወደ ጥበቃው፣ ወደ ቅድስናው፣ ወደ ፈውሱ እና ወደ እረፍቱ የበለጠ በመቅረብ እራሳችንን ከአዳኙ ጋር እናስተሳስራለን።

መዘምራን፣ በአዲሱ መዝሙር አማካኝነት ስለሰጣችሁት ምስርነት አመሰግናለሁ።

“የህይወት ዳቦ፣ የሕይወትም ውኃ” የሚለውአዲሱ የቅዱስ ቁርባን መዝሙር ነብሴን ይሞላዋል። በመዝሙሩ ውስጥ አንድ መስመር እንዲህ ይላል፣ “አሁን የተሰበረውን ልቤን ለእርሱ በማቅረብ በመሠዊያው ፊት እቀርባለሁ።”

በ2015 (እ.አ.አ) ቤተሰባችን በዩታ ኦግደን ሚስዮን ለማገልገል ከኒውበሪ ፓርክ፣ ካሊፎርኒያ ከወጣን በኋላ ስለነዚያ ቃላት ያለኝ ግንዛቤ ይበልጥ ጨመረ። በሌይተን፣ ዩታ አቅራቢያ ያለውን የሂል አየር ሃይል ማእከል ለመጎብኘት ግብዣ ተቀብዬ ነበር። በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ገብቼ አላውቅም፣ ወይም የውትድርና ካም ውስጥ የሚያገለግል ቄስ ወይም ለአገራቸው ደኅንነትና ጥበቃ ለማድረግ የሚሠሩ ወንዶችና ሴቶች አላጋጠሙኝም ነበር።

ቄስ ሃርፕ፣ በእስር ቤቶቻችን፣ በሆስፒታሎቻችን እና በአለም ወታደራዊ ተቋማቶቻችን ውስጥ እንደሚያገለግሉት ልክ እንደ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች እና ባለሙያ ቄሶች፣ አነሳስቶኛል እንዲሁም አበረታቶኛል። በካምፕ ውስጥ በስተመጨረሻ የቆምነው በመለኮታዊ ስፍራ ነበር። ለማሰላሰል፣ ለመጸለይ፣ እና ለማምለክ ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ አገልግሎት ይሰጥ እንደሆነ ቄሱን ጠየቅሁት። ወደ ፀሎት ቤቱ የፊት ግድግዳ ሄዶ ከመጋረጃው ጀርባ መስቀል አወጣ። መስቀሉን ለፕሮቴስታንት እና ለካቶሊክ አገልግሎቶች እንደሚጠቀም ተናገረ። ለአይሁዳውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ምን እንደሚጠቀም ጠየቅሁት እና ወደ ሌላኛው ግድግዳ ፊት ሄዶ የዳዊት ኮከብን አወጣ።

እኔም “ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን አገልግሎቶችስ ምን ታደርጋለህ?” ብዬ ጠየኩት። እነዚያን ምልክቶች ገፋ በማደረግ በመቅደሱ መካከል ወዳለው ትልቅ የእንጨት መሠዊያ አመለከተ። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት በመሠዊያው ላይ ዳቦ እና ውሃ አዘጋጅተው እንደሚባርኩ ተናገረ። ትልቅ፣ ቋሚ የሚመስለው መሠዊያ ከአይሁድ፣ ሙስሊም፣ ካቶሊክ ወይም ፕሮቴስታንት ወንድሞችና እህቶች አገልግሎት በፊት እንደሚነሳ ጠየቅኩ። በእነዚህ እምነቶች መካከል ብዙዎቹ መሠዊያውን በሆነ መንገድ ስለሚጠቀሙት መሠዊያው በቦታው እንደሚሆን ተናገረ።

አብርሃም መሠዊያ ሠራ፣ ይስሐቅንም በዛ ላይ አሰረው፣ አንድያ ልጁንም ሊሠዋ ተዘጋጅቶ ነበር፣ ነገር ግን እጁ ተይዞ፣ ጌታ “እነሆኝ”! ሲል እንደ ተናገረው አርሱም እንዲሁ አለ። ስንት ጊዜ ነው ታላቁ እኔ ወይም ከነብያቱ አንዱ በፈቃደኛነት “እነሆኝ” ያለው?

በተራራው ስብከቱ ወቅት አዳኙ ወደ መሠዊያው ከመቅረባችን በፊት ከወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር እንድንታረቅ ጋብዞናል። ጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት በመሠዊያው ላይ “የተቀደ[ስን]” መሆናችንን አስተምሯል።

ነቢዩ ሌሂ “ቤቱን… እና ውድ ዕቃዎቹን ተወ።… [ከዚያም] መሠዊያ ሠራ… እናም መባ አቀረበ…እናም እግዚአብሔርን አመሰገነ።”

መጽሐፍ ቅዱስ እና መፅሐፈ ሞርሞን የእግዚአብሔርን ልጅ በመሠዊያዎች እንድናመልከው ያስተምሩናል። ለምን?

የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አዳምና ሔዋን፣ መሠዊያዎች ሠርተው ያመልኩት ነበር። ከኤደን ገነት ከተባረሩ እና “ለብዙ ቀናት” ካመለኩ በኋላ፣ አንድ መልአክ ሊጠይቃቸው ጎበኛቸው እናም እያንዳንዳቸውን ሊጠየቁ ሚገባቸውን ልብ የሚነካ ጥያቄ ጠየቀ፡- “ለምንድር ነው ለጌታ መስዋዕትን ምታቀርበው[ቢው]?”

አዳምም፣ “አላውቅም” ሲል መለሰ።

መልአኩ ለአዳም የትሁት መልስ የሰጠው ምላሽ አስደናቂ ነው፡- “ይህ ነገር የአብ አንድያ ልጅ መስዋዕት አምሳል ነው። … ስለዚህ፣ የምታደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ በወልድ ስም አድርግ፣ እና ንስሀ ግባ እና በወልድም ስም እግዚአብሔርን ለዘለአለም ጥራ።”

የቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛ እና የቤተመቅደስ መሠዊያዎች የኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕትነት እና የእርሱን ማለቂያ የሌለው የኃጢያት ክፍያ ያመለክታሉ።

ቃል ኪዳኖቻችንን ስንገባ እና ስናከብር፣ በቤተ ክርስትያን የቅዱስ ቁርባን ስርአቶችን እና ስጦታን እና ማህተምን በቤተ መቅደስ ስንቀበል፣ እራሳችንን ከአዳኙ ጋር እናስተሳስራለን፣ ወደ ምህረቱ፣ ጥበቃው፣ ቅድስናው፣ ፈውሱ እና እረፍቱ የበለጠ እንቀርባለን።

በቃልኪዳኖች አማካኝነት ምህረት እና ጥበቃ

የ15 አመት ወጣት ሆኜ፣ —በጥር ውስጥ ለአንድ እሁድ ብቻ ልዩ ለሆነ የአሜሪካ የእግር ኳስ ጨዋታ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባን አለመካፈል እችል እንደሆነ አባቴን እንደጠየኩት አስታውሳለሁ። ይህን ምርጫ ለራሴ ለማድረግ ዕድሜዬ እንደደረሰ ተናገረ እና በአንድ ምክር ላይ እንዳስብበት ጠየቀኝ። እርሱም እንዲህ አለ፣ “ቅዱስ ቁርባንን አንድ ጊዜ ላለመካፈል ከመረጥክ፣ እንደገና ላለመካፈል መምረጥ ቀላል ነው።”

አዳኙ ታላቅ አገናኝ ከሆነ፣ ተቃዋሚው ደግሞ አለያይ ነው። ሰይጣን ከተቀደሰው የአምልኮ ቦታችን እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጥበቃ እራሳችንን እንድንለይ ይፈትነናል። አዳኙን ስናመልክ፣ “የተፈጥሮ ዓለማዊ ፍሰትን እንድንቃወመው የሚያስችል ኃይልን”እናገኛለን። ከእርሱ ጋር ኅብረት ስናደርግ፣ “ከሰይጣን እንደሚያስጥለን”ቃል ተገብቶልናል። “ከዚያም በኋላ፣ ቃል ኪዳኖቻችንን ስንጠብቅ፣ በእርሱ ፈዋሽ፣ አጠንካሪ ኃይል ይባርከናል።” ኦ፣ በተቀደሱት መሠዊያዎች ላይ በቃል ኪዳኖች አማካኝነት ከአዳኙ ጋር የምናደርገውን የአንድነት ልምድ ምንኛ አከብራለሁ።

በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ እንዲሁም በሥርዓት ላይ ሥርዓትን በመፈጸም የአዳኝን ዘላለማዊ የኃጢያት ክፍያ መረዳትን መገንባት በጠላት ሽንገላ ላይ መንፈሳዊ መከላከያን ይሰጣል። ወጣት ሽማግሌ ጃጊ በሜክሲኮ ዙስተር ጃጊ በቤልጂየም እና በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች ሚስዮናውያን ጓደኞቻቸው በተገናኙ በመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ከተገኙ ጓደኞቻቸው የጥምቀትን በረከት ሲቀበሉ እና የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ሲቀበሉ የማየት እድላቸው ሰፊ ነው።

በቶንጋ ወይም በሳሞአ ውስጥ ያሉ ወጣት ጎልማሶች ከትምህርት ቤት ከተመረቁ ብዙም ሳይቆይ ቡራኬያቸውን ለመቀበል ከተዘጋጁ እና ቡራኬያቸውን ከተቀበሉ በጌታ ቤት ውስጥ የመታተም ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ቡራኬ በሚቀበሉበት ጊዜ፣ አባላት ኃይልን እና ጥበቃን የሚያመጡ አምስት ህጎችን እንዲኖሩ፣ እንዲታዘዙ እና እንዲጠብቁ ተጋብዘዋል። ከጌታ ጋር ቃል ኪዳኖችን ስንገባ፣ በምላሹ ዝምድና ይፈጠራል። ታማኝነታችንን እና ፍቅራችንን ለእርሱ እናሳያለን። የእኛ ጥንካሬ እና ሃይል በተገባው እና በሚጠበቀው በእያንዳንዱ ቃልኪዳን ይጨምራል።

ማሰላሰል እና መቀደስ

በትህትና እና በምሳሌያዊ መንገድ በጌታ መሠዊያዎች ላይ ስንንበረከክ፣ “የልባች[ንን] መመካት፣… [ራሳችንን በማዋረድ] በእግዚአብሔር ፊት” ስላለፈው ተግባራችን ወይም ስለ አንደበታችን እንድናሰላስል እድል ይሰጣል።” በወጣትነቴ፣ ከጓደኞቼ ጋር ከመውጣቴ በፊት እናቴ ብዙ ጊዜ “ማን እንደሆንክ አስታውስ፣ እንዲሁም እባክህ ቤት ስትመለስ አናግረኝ” ትለኝ ነበር። አንዳንድ ምሽት፣ ቤት በጣም ዘግይቼ በመድረሴ ምክንያት መግባቴን ማሳወቅ እረሳ ነበር። እናቴን የመጎብኘት እነዚያን አስፈላጊ እድሎች ማጣቴ ይቆጨኛል።

ዛሬ፣ ከሰማይ አባት ጋር የምገናኝበትን ጊዜ በተስፋ እጠባበቃለሁ። በዕለት ተዕለት የግል አምልኮዬ በአልጋዬ አጠገብ ወይም ከቤተሰብ ጋር ተሰብስበን በጸሎት እንበረከካለሁ፣ ከዚያም በመሠዊያው ላይ ተንበርክኬ፣ ስለ ሕይወቴ እያሰላስልኩና እየመረመርኩ እራሴን በአይነ ህሊናዬ አያለሁ። ስለእኛ ስለተሰበረው እና ስለተቆረሰው እንጀራ፣ እያንዳንዱም ምሳሌ የቤዛችን የተሰበረ ሥጋ ምልክት ስለሆነው ስለቅዱስ ቁርባን አስባለሁ። “ልክ ከእርሱ የሚካፈሉት ግለሰቦች የተለያዩ እንደሆኑት ሁሉ እያንዳንዱ ቁራጭ ዳቦም ልዩ ነው።”የሚለውን የፕሬዘዳንት ዳሊን ኤች. ኦክስን ትምህርት አስታውሳለሁ። ለፀሎት ስንበረከክ፣ ፈቃዴን እንዴት ለእግዚያብሔር እንደምሰጥ አስባለሁ።

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዳስተማሩት፥ “የቅዱስ ቁርባን ስርዓት ቅዱስ እና ከልብ ንሰሀ ለመግባት እና መንፈሳዊ እድሳት ለማድረግ በተደጋጋሚ የሚቀርብ ግብዣ ነው። ቅዱስ ቁርባንን የመካፈል ድርጊት ብቻ፣ በራሱ የሀጢያት ስርየትን አያመጣም። ነገር ግን በተሰበረ ልብ እና በተዋረደ መንፈስ በቅዱስ ቁርባን ስርዓት ላይ በጥንቃቄ ስንዘጋጅና ስንካፈል፣ ከዚያ የተሰጠን ቃልኪዳን የጌታ መንፈስ ሁሌም ከእኛ ጋር እንደሚኖር ነው። እናም የእኛ ቋሚ ጓደኛ በሆነው በሚያንጸው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በኩል፣ የሀጢያቶቻችንን ስርየት ሁሌም ማግኘት እንችላለን።”

ኤሚ እና እኔ የእኛን የህይወት ልምምዶች በቅርበት ስንመለከት፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም ፍቅር እና መስዋዕትነት ስጦታ እናከብራለን። የገሃነም ቁጣ እንዴት እንደተፈታም እናያለን። ፍርድን፣ ጭንቀትን፣ ድብርትን፣ ካንሰርን፣ የስኳር በሽታን፣ በድረ ገጾች ላይ ሚደረጉ ስድቦች፣ የማንነት ስርቆት፣ የፅንስ መቋረጦች እና ልጅ ማጣትን፣ ወንድምንና አባትን ማጣትን እንዴት ማሸነፍ እንችላለን? ምክንያቱም ኢየሱስ ከመራራው የመንቀጥቀጥ ጽዋ፣ የቁጣውን ጽዋ—ለእኔ፣ ለቤተሰቤ፣ ለሁላችንም ሲል ተካፍሏል!

አዳኝ በጌቴሴማኒ

ጌቴሴማኒ, በአዳም አብራም፣ በ altusfineart.com © 2025

በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የጠጣው “መራራ ጽዋ” እና በቀራንዮ መስቀል ላይ “እየበረታበት” የሄደው መከራው ግብዙን ፣ ጨካኙን፣ ቁጡውን፣ የተናደደውን፣ እና አንድን ሰው እንዲንቀጠቀጥ የሚያደርጉትን እኚህን ልምዶቻችንን በጌታ መሠዊያዎች ላይ እንድናስቀምጥ እና “በመንፈስ ቅዱስ በኩል ፈውስን እንድንቀበል” ያስችለናል።

እህት ፓትሪሺያ ሆላንድ እንዲህ አለች፣ “ለእናንተ እና ለራሴ ዛሬ ያለኝ ጥልቅ ጸሎት፣ የትም ብንሆን እና ምንም ብናደርግ በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል እና ሰላም በመሠዊያው ላይ እራሳችንን ሙሉ በሙሉ አሳልፈን እንድንሰጥ ነው።”

የመፈወስ እና የእረፍት ቦታ

ወደ መሠዊያው ስንመጣ፣ ሽልማት እያገኘን አይደለም፤ ስለ ስጦታ ሰጪው እየተማርን ነው። በዚያ ትምህርት እና ማስተሳሰሪያ ቃልኪዳን አማካኝነት ፈውስ ይመጣል። ኔፊ እንዲህ ብሏል፣ “ስጋዬም እስከሚነድድ ድረስ፣ በፍቅሩ ሞላኝ።” እናም ውዱ አዳኛችን፣ “እፈውሳችሁ ዘንድ ንስሃ ገብታችሁ እናም ተለውጣችሁ አሁን ወደ እኔ አትመለሱምን?”በማለት ይጋብዘናል።

ሁለቱ የመጀመሪያ ሴት ልጆቻችን ማኬንዚ እና ኤማ ገና ትንሽ ሳሉ ከሚወዷቸው ታሪኮች አንዱ የናርኒያ ዜናዎች፦አንበሳው፣ ጠንቋይዋ እና ቁም ሣጥኑየሚለው ነበር። ሁላችንም ታላቁን አንበሳ፣ አስላንን፣ ወደድነው። መጽሃፉን ስናነብ ከማይረሱ ምሽቶቻችን አንዱ ታላቁ አንበሳ ለኤድመንድ ህይወቱን የሰጠበትን ወቅት ነው። የማይረሳ የሆነበትም ምክንያት በጠንቋይዋ የአንበሳው ህይወት በድንጋይ ጠረጴዛ ላይ ሲጠፋ ወላጆች እና ሴት ልጆች እንባ ስላፈሰሱ ነበር። የማይረሳ የሆነበትም ምክንያት ምንም እንኳን አሳዛኝ ነገር ቢኖርም፣ አስደናቂው ክስተት እስኪደርስ ድረስ ተስፋ ጸንቶ ስለነበር ነው። አስላን ከሞት ሲነሳ እና፣ “ጠንቋይዋ የመስዋዕትን ትክክለኛ ትርጉም ብታውቅ ኖሮ፣ ምንም ክህደት ያልፈፀመ ተጎጂ በከሃዲ ምትክ ቢሞት፣ የድንጋይ ጠረጴዛው እንደሚሰነጠቅ እና ሞት እራሱ ማሰሪያ አቅሙን እንዲጣ ታውቃለች”ሲል በዛ ትንሽ መኝታ ክፍል ውስጥ የደስታ ጩኸቶች ተሰሙ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ቁስሎች ይፈውሳል። ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መኖር እንዲቻል ያደርጋል።

በጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ንግግራቸው፣ ፕሬዘዳንት ረሰል ኤም. ኔልሰን በቤተመቅደስ መክፈቻ ዝግጅት ወቅት ለጉብኝት ሰለመጣ ቡድን ተናግረው ነበር። አንድ ወጣት ልጅ እዛ ነበር። ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፦

“የጉብኝት ቡድኑ ወደ መንፈሳዊ ስጦታ ክፍል በገቡበት ጊዜ፣ ይህ ልጅ ሰዎች ተንበርክከው ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ወደሚገቡበት መሰዊያው አመለከተና እንዲህ አለ፣ ‘ኦ፣ ያ ደስ ይላል። ሰዎች በቤተመቅደስ ጉዞአቸው የሚያርፉበት ቦታ ይሀው ነው።’

“… እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር በቤተመቅደስ ውስጥ ቃል ኪዳን በመግባት እና ከአዳኙ አስደናቂ የተስፋ ጋር ያለውን ግንኙነት ላይ ምንም አያውቅም ይሆናል፦

“‘እናንተ ደካሞች ሸከማችሁ የከበደ ሁሉ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ

ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።

“‘ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና’ [ማቴዎስ 11፥28–30]።”

“የሰው ልጅ ራሱን የሚያስጠጋበት ቦታ የለውም፣” ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱን፣ እኔን እና እናንተን፣ በዚያ ከእርሱ ጋር እንድናርፍ ወደ ቅዱስ ቁርባን ማዕድ ጋበዘ። “ትሑት ነፍሳት በመሠዊያ ላይ ሲንበረከኩ፣” ሰላም ይበዛል። የአዳኛችን እጆች ተዘርግተዋል፤ ማዕዱ ተዘርግቷል። ኑ የእግዚአብሔርን ልጅ በቅዱስ መሰዊያዎቹ አምልኩ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. 3 ኔፊ 18፥4-9ይመልከቱ።

  2. Bread of Life, Living Water፣” መዝሙር— ለቤት እና ለቤተክርስትያን፣ ቁጥር 1008።

  3. ሞሮኒ 4፤ 5ይመልከቱ።

  4. ዘፍጥረት 22፥11

  5. ዘፍጥረት 31:1146:2ዘጸአት 3:41 ሳሙኤል 3፡4–10 ኢሳይያስ 6:8አብርሃም 3፡27

  6. ማቴዎስ 5፥23-24ይመልከቱ።

  7. ዕብራውያን 10:10-14ይመልከቱ።

  8. 1 ኔፊ 2፥4፣ 7

  9. ሙሴ 5:5፤ አርእስት መመሪያ፣“ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አይነቶች፣ በጉጉትይመልከቱ።

  10. ሙሴ 5፥5–8

  11. አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል27.2፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት ይመልከቱ።

  12. 1 ጢሞቴዎስ 5:15; 3 ኔፊ 6፡1611፡29–30ይመልከቱ።

  13. Take My Heart and Let It Be Consecrated፣” መዝሙር— ለቤት እና ለቤተ ክርስቲያን፣ ቁ. 1025.

  14. ዴል ጂ . ሬንሉድ፣ “በቃል ኪዳኖች አማካኝነት የእግዚአብሔርን ኃይል ማግኘት፣ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 37።

  15. አልማ 15፥17

  16. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “The Temple and Your Spiritual Foundation [ቤተመቅደስ እና መንፈሳዊ መሰረታችሁ]፣” ሊያሆና፣ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 94።

  17. ኢሳይያስ 28፥10፣13 ይመልከቱ።

  18. ኩዊንተን ኤል. ኩክ “አላማ እና እቅድ ማውጣት” (ለአዲስ ምስዮን ትሬዝደንቶች የተሰጠ ሴሚናር፣ ሰኔ 25፣2019 (እ.አ.አ)ይመልከቱ።

  19. አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ 27.2 ይመልከቱ።

  20. ዲ ቶድ ክርስቶፈርሰን “One in Christ,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 77–80 ይመልከቱ።

  21. ኒል ኤል አንደርሰንን፣ “መቅደሶችን፣ ምድርን የሚመለከቱ የእግዚአብሄር ቤቶች”፣ ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ) ይመልከቱ።

  22. አልማ 15፥17።

  23. 1 ቆሮንቶስ 11፥28ን ይመልከቱ።

  24. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Testimony” (ለሚስዮን ፕሬዘዳንት ሴሚናር ላይ የተሰጠ ንግግር፣ ሰኔ 25፣ 2014 (እ.አ.አ))፣ ተመልከቱ።

  25. ዴቪድ ኤ. ቤድናር ፣“Always Retain a Remission of Your Sins,” ሊያሆና ግንቦት 2016 (እ.አ.አ.), 61–62.

  26. ኢሳይያስ 51፥17, 223 ኔፊ 11:11 ይመልከቱ።

  27. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥18

  28. ራስል ኤም.ኔልሰን፣ “የቤተክርስቲያኗ ትክክለኛ መጠሪያ፣” ሊያሆና፣ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 88።

  29. 3 ኔፊ 27፥20

  30. An Eye Single: Thoughts and Teachings from Patricia T. Holland, comp. ሜሪ አሊስ ሆላንድ ማካን (2025)፣ 135።

  31. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥33 ይመልከቱ።

  32. 2 ኔፊ 4፥21

  33. 3 ኔፊ 9፥13

  34. አንበሳው፣ ጠንቋዩ እና ቁም ሣጥኑ (New York: HarperCollins, 1994), 178–79።

  35. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “አለምን ማሸነፍ እና እረፍትን ማግኘት፣,” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 95-96።

  36. ማቴዎስ 8፥20፣ አዲስ አለማቀፋዊ ትርጉም።

  37. ሉቃስ 22፥14፣ አዲስ አለማቀፋዊ ትርጉም ይመልከቱ። Recline የመጣው ከግሪክ ሲሆን anapipto፣ ነጻነትን እና እረፍትን ይጠቁማል። የተደረገው ድርጊት እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነፃ መውጣታቸውን የሚያስታውስ ነበር።

  38. እንኳን ወደ ቤት መጣችሁ፣መዝሙሮች—ለቤት እና ለቤተክርስትያን፣ ቁ. 1027።