መግቢያ
አሁን ከወራት ዝግጅት በኋላ፣ በታቀደው መሰረት እና ፕሬዚዳንት ኔልሰን በመደቧቸው ተናጋሪዎች እና ሙዚቃዎች ጋር ይህን የመንፈቅ አጠቃላይ ጉባኤ እንቀጥላለን።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በተወዳጁ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ሞት እያዘንን እንሰበሰባለን። እኔ የማነጋግራችሁ እንደ አስራ ሁለቱ ቡድን ፕሬዚዳንት ነው፣ በዚህ አቋም ውስጥ በእያንዳንዱ በአጥቢያ፣ በካስማ እና በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ ላለፉት ሰባት አመታት ተኩል ድጋፍ ተሰጥቶኛል።
ከወራት ዝግጅት በኋላ፣ በታቀደው መሰረት እና ፕሬዚዳንት ኔልሰን በመደቧቸው ተናጋሪዎች እና ሙዚቃዎች ጋር ይህን የመንፈቅ አጠቃላይ ጉባኤ እንቀጥላለን። ከዝግጅቱ ተጨማሪ የሆኑት ይህ የእኔ የመግቢያ ማብራሪያ እና በፕሬዚዳንት ኔልሰን ምትክ በእሁድ ከሰአት በኋላ የመዝጊያ ክፍለ-ጊዜ ላየ የማቀርበው ንግግር ናቸው።
ከአጠቃላይ ጉባኤው ጥቂት ቀናት በፊት የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት መሞታቸው በ75 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ነው። ይህም ከጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባዎች ጋር የሚገናኘውን ወሳኝ የሆኑ የአመራር ስብሰባዎችን እና የአጠቃላይ ጉባኤ ክፍል-ጊዜዎችን እንዴት እንደምናከናወን እንድናቅድ እና በተቻለ ፍጥነት የቀብር ስነ ስርዓቱን እንድናዘጋጅ አስደርጎናል። ፕሬዚዳንት ኔልሰን በሚቀጥሉት ወራት ለቅዱሳን መመሪያ ለመስጠት የአጠቃላይ ጉባኤ ታላቅ ዋጋ እንዳለው ተረድተዋል። እኛም እርሳቸው ያቀዱትን የጉባኤ መርሃ ግብር በመከተል እርሳቸውን እናከብራለን።
በዚህ የሀዘን ወቅት፣ ከአጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባዎቻችን በፊት ለፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ክብር ለመስጠት ተሰብስበናል፣ ከዚያም ከጉባኤ በኋላ በተቻለ ፍጥነት የቀብር ስነ ስርዓታቸውን አዘጋጅተናል። ይህ ሁሉ የተደረገው በፕሬዚዳንት ኔልሰን ቤተሰብ እና በአስራ ሁለቱ ሐዋሪያር ቡድን አባላት ፈቃድ ነው።
በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ እንድንናገር የተመደብን ሁላችንም የተመደበልንን ጊዜ ለፕሬዚዳንት ኔልሰን የግል መታሰቢያን በመስጠት ለማሳለፍ ስለምንፈልግ፣ የጉባኤ ተናጋሪዎቻችን ማንኛውንም አይነት መታሰቢያ በቀነሰ ሁኔታ እንዲያቀርቡት ጠይቀናቸዋል፤ ይህንንም ያደረግነው አስቀድመን እቅድ ማውጣት በጀመርነው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የተብራራ መታሰቢያዎችን ለማቅረብ ስለሚችሉ ነው።
ለጉባኤው እና ከዚህ በፊት ያላቀረብናቸው መታሰቢያዎች ተስማሚ የሚሆን የእኔ አጭር የግል መታሰቢያ ቢኖር ይህ ነው፦ ራስል ኤም. ኔልሰንን እወዳቸው ነበር እንዲሁም ስለወንጌል እና ስለወንጌል አመራር በግል ከማውቃቸው ሌሎች ሰዎች በላይ ከፕሬዚዳንት ኔልሰን ጋረ በነበረኝ በረጅም ጊዜ ጓደኝነት እና ግንኙነት እጅግ በጣም ብዙ ተምሬአለሁ። እርሳቸው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ እና ተከታይ ስለመሆን የእኛ ምሳሌ ናቸው። ስለእነዚህ ነገሮች የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።