አጠቃላይ ጉባኤ
ጌታ ስራውን እያፋጠነ ነው
የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


14:55

ጌታ ስራውን እያፋጠነ ነው

ጌታ ስራውን በሚያፋጥንበት ጊዜ፣ ወንጌሉን የሚቀበሉትን መውደድ መንከባከብ፣ እና ማገልገል ይገባናል።

ቻርለስ ዲከንስ የሁለት ከተማዎች ታሪክ የተሰኘውን አንጋፋውን ልብ ወለድ መጽሐፉን “የዘመኑ ምርጥ ጊዜ ነበር፤ የዘመኑ አስከፊ ጊዜም ነበር” በማለት በታዋቂነት ጀምሯል። ይህም በእርግጥ በእኛም ጊዜ እውነት ነው።

“ምድር ሁሉም በሁከት ውስጥ [እንዳለች]” በሚመስል በተበጠበጠ ጊዜ እየኖርን ነን። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች አስታራቂዎች እንድንሆን ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን የሰጡት ማሳሰቢያ ዛሬ ጠዋት በሽማግሌ ጋሪ ኢ. ስቲቨንሰን አጽንዖት ተሰጥቶታል። ይህ አንድነትን፣ ሰላምን እና “ለአስከፊው ጊዜ” መፈወስን የሚያፈራ አስፈላጊ አካል ነው።

እኛ ደግሞም፣ እኔ እንደማተኩርበት፣ “በዘመኑ ምርጥ ጊዜ” ውስጥን እየኖርን ነን። ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 1 ላይ እንደ መቅድም እንደዳወጀው፣ የወንጌል ሙላት “እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ [ይታወጃል]”። ጌታ በእውነት ስራውን በእኛ ጊዜ እያፋጠነ ነው። እነዚህ ፈታኝ ጊዜዎች ቢኖሩም እንኳ በፍጥነት የሆነ እና እየሆነም ላለው ለዚህ ፈጣን ስራ ከልብ ማመስገን አለብን። እየኖርን ያለነው የጌታ ተከታዮች ድምጹን ለመስማት እና ክፍት በሆነ ልብና አዕምሮ ምላሽን ለመስጠት እድለኞች በሆኑበት ጊዜ ነው። ለአዳኝ እና ለትእዛዛቱ ቆራጥ የሆኑ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት፣ አላማን እና ጥልቅ የሆነ የግል ሰላም እያገኙ ናቸው።

በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት፣ ወደ ቃል ኪዳኑ ጎዳና የገቡት ሰዎች ብዛት በከፍተኛ ጨምረውታይተዋል። ከእነዚህም መካከል አንዱ በ1837 (እ.አ.አ) እና 1850 (እ.አ.አ) መካከል ተከስቷል። ዳግም በተመለሰችው የጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት መካከል አንዳንዶቹ በእንግሊዝ አገር በሚስዮናዊነት አገልግለዋል። እነዚህ ተልእኮዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተክርስቲያኗን እንዲቀላቀሉ አስችለዋል፣ እንዲሁም በ1850 (እ.አ.አ) ከዩናይትድ ስቴትስ ይልቅ በእንግሊዝ አገር የሚኖሩ ብዙ የቤተክርስቲያኗ አባላት ነበሩ። በዚያን ጊዜ፣ ጌታ እነዚህን ቅዱሳን ወደ ዩታ እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው። የብዙ ህዝብ ስደት ተከስቷል፣ አንዳንዶቹም Perpetual Emigrating Fund [በዘላቂ የስደተኞች ገንዝብ በብድር] የተደገፉ ነበሩ።

በ1852 (እ.አ.አ) ከእንግሊዝ እና ከዌልስ የተለወጡ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ የመድረሳቸውን ታሪክ እወደዋለሁ። ቡድኑም በሻምበል ፒት የሙዚቃ ብድን ታጅበው ከነበሩትን ከቀዳሚ አመራር ጋር በኢምግሬሽን ካንየን አፍ ላይ ተገናኙ። Deseret News [ዴዘረት ዜና] እነርሱን “እህቶችና ልጆችን ጨምሮ በእግር የሚጓዙት የሀይማኖት ተሰዳጆች፣ በፀሀይ የተቃጠሉ እና ቆዳቸው ሻካራ የሆኑ ቢሆኑም፣ ግን ተስፋ ያልቆረጡ፣ ልባቸው ደስተኛ እና ተነሳሽ የሆነ ነበሩ፣ ይህም በደስታ እና በሀሴት ፊታቸው በግልጽ ይገለጣል” በማለት ገልጿቸዋል።

እነርሱም “የቤተመቅደሱን ክፍል ሲያልፉ፣ በዘጠኝ ዙር የጦር መሳሪያ ሰላምታ ተሰጣቸው፣ … በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች፣ ከተለያዩ የከተማው ክፍሎች ተሰባስበው፣ በክብር እና በደስታ አቀባበል ላይ አንድ ሆነው ነበር።” ፕሬዚዳንት ብሪገም ያንግ እንዲህ ብለው ተናገሩ፡- “ጌታ የእስራኤል አምላክ ይባርካችሁ። … እኛ ያለማቋረጥ ስለ እናንተ ጸለይን፤ እስራኤልን እንድንሰበስብ ያዘዘንን፣ የሰውን ልጆች ወንጌልን በመስበክ እና ለመሲሑም መምጣት እንዲዘጋጁ በማድረግ እርሱ እንድናድናቸው ወዳዘዘን፣ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ጸሎቶች ቀርበዋል።”

በዚያ አስደሳች መንፈሳዊ አጋጣሚ፣ አዲስ ለተለወጡት እና ወደ ጌታ ቤተክርስቲያን ለሚመለሱ ሁሉ በድጋሚ ላረጋግጥላቸው፦ እንወዳችኋለን፤ አናንተን እንፈልጋችኋለን፤ ጌታ ይፈልጋችኋል። ነገር ግን በሰለስቲያል መንግሥት ወደ እግዚአብሔር አብ እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያመራው የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለመራመድ የምታደርጉትን ጥረት የሰማይ በረከቶች እንዲረዷችሁ እንጸልያለን።

በዘመናችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለው እምነት እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ ግልጽ ማስረጃ አለ። በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ወደ ቤተክርስቲያኗ በመለወጥ በሚገቡት ላይ አስደናቂ እድገት ታይቷል። ባለፉት 36 ወራት ወደ 900,000 የሚጠጉ አማኞች ቤተክርስቲያኗን ተቀላቅለዋል። እነዚህ የተለወጡ ሰዎች ከጠቅላላው የቤተክርስቲያኗ አባላት 5 በመቶ ያህሉ ናቸው። አዲስ አባላትን ክፍት በሆነ እጆች እና ለመረጣችሁትም መንገድ በጥልቅ አድናቆት እንቀበላቸዋለን።

እነዚህ ባለፉት 36 ወራት ውስጥ ወደ ቤተክርስቲያኗ የተቀላቀሉ 900,000 ሰዎች፣ በ1940 (እ.አ.አ) ቤተክርስቲያኗ ከተመሰረተችበት 110ኛ ዓመት የምስረታ በአል ጊዜ ከነበሩት የ860,000 የቤተክርስቲያኗ አባላት ቁጥር በላይ ይበልጣል። ይህም ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ፣ ሽማግሌ ዲዬተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እና እኔ የተወለድንበት ዓመት ነበር።

እነዚህ አስደናቂ አዲስ የቤተክርስቲያኗ ተቀላቃዮች ከሁሉም የዓለም ክፍል የመጡ ናቸው። በዚህ ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ፣ በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በእስያ፣ በፓሲፊክ እና በላቲን አሜሪካ ውስጥ የነበሩት ቤተክርስቲያኗን የመቀላቀል ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ፣ ከ20 በመቶ በላይ ጨምሯል። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የ17 በመቶ ጭማሪ አይተናል። የጌታ ስራ በሀይለኛ መንገዶች ወደፊት መሄዱን ቀጥሏል። እነዚህ እየጨመሩ የሚሄዱት ቁጥሮች፣ ወንጌል ልብን እንደሚነካ እና በሁሉም ቦታ ህይወትን እንደሚቀይር የሚያሳይ ግልጽ ምስክር ነው።

በዘመናችን እነዚህ ውድ ቤተክርስቲያኗን ተቀላቃዮች አማካኝ በሆነ ቦታ ላይ አይሰበሰቡም። በቤተክርስቲያኗ አባላት እምነት እና ቅዱስ ስጦታ የተነሳ፣ በመላው አለም መሰብሰቢያ ቤተክርስቲያናትን እና ቤተመቅደሶችን በመገንባት ምዕመናንን ለመደገፍ ግብዓቶች አሉን። አስፈላጊ በሆኑ የክህነት ቁልፎች እና በተሰጡት ግብአቶች፣ የማዳን ስነ ስርዓቶች አሁን በአብዛኛዎቹ የአለም ክፍሎች ይገኛሉ።

የምንኖርበት ቦታ ምንም ይሁን ምን፣ ከመጀመሪያ ታሪካችን ለገለፅኳቸው እንግሊዛዊ እና ዌልስ ቅዱሳን እንዳደረግን፣ የአሁኑ አባላት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ አባላትን መቀበል አለባቸው። በዚህ ክፍለ-ጊዜ ማንም ሰው በስሜትም ሆነ በመንፈሳዊ ብቻውን መቀመጥ እንደሌለበት ያስተማረን የሽማግሌ ጌሪት ደብሊው. ጎንግ ንግግርን እወደዋለሁ።

ቅዱስ የሆነው ሀላፊነታችን አዲስ እን የሚመለሱ አባላትን መቀበል እና ተቀባይነት እንዲሰማቸው ማድረግ ነው። ጌታ ስራውን ሲያፋጥን፣ ወንጌሉን የሚቀበሉትን ማፍቀር፣ መንከባከብ፣ እና ማገልገል ይገባናል። “[እኛ] አንድ ልብ እና አንድ አእምሮ [ኖሮን]፣ እና በጽድቅም [በመኖር]” የፅዮንን ሕዝብ ባለንበት ለመገንባት መርዳት እንችላለን። ከጌታ ጋር አንድ ለመሆን፣ በጌታ ፊት እኛም አንድ መሆን አለብን። የጥምቀት ቀን ምንም ይሁን ምን፣ ሁሉም አባላት ሌሎችን የመቀበልን ሃላፊነት ይጋራሉ።

ለቤተክርስቲያኗ አባላት የምመክረው፣ እነዚህ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የተቀበሉ ውድ የተመረጡ ሰዎችን እንድናቅፋቸው ነው።

ፕሬዚዳንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ እንዳስተማሩን፣ አዲስ የቤተክርስቲያኗ ተቀላቃይ “ጓደኛ፣ ሀላፊነት፣ እና ‘በእግዚአብሔር መልካም ቃል’ (ሞሮኒ 6፥4) መመገብ” ያስፈልጋቸውል። እኛም እነዚህ አዲስ ተቀላቃዮች እንግዶች ብቻ እንዳልሆኑ ከሚያረጋግጡ ጓደኞች መካከል መሆን እንችላለን። ሌሎችን ማገልገል የሚችሉ እና የማገልገል ጥሪዎችን የሚቀበሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆናቸውን እንዲረዱ ልንረዳቸው እንችላለን። በቤተክርስቲያኗ የተቀላቀሉ ወጣቶች የሙሉ ጊዜ ተልዕኮን ለማገልገል ማሰብ አለባቸው። ሁሉም እንደ ክርስቶስ ዓይነት ህይወት ለመኖር በመጣር ቁርጥ ያለ ውሳኔ ማድረግ አለባቸው።

ብዙዎች በታላቅ የግል መስዋዕትነት ቤተክርስቲያኗን ይቀላቀላሉ እናም የቅዱሳን ጓደኞቻቸውን ፍቅር እና ድጋፍ በጣም ይፈልጋሉ።

አዲስ ለሆናችሁ ወይም ወደ እምነት ለምትመለሱ ለእናንተ፣ ሊያጋጥሟችሁ የሚችሉ ተግዳሮቶች ይኖራሉ። በራሳችሁ ትእግስተኛ ሁኑ። ሚስዮናውያኑ አስፈላጊ የሆነውን ትምህርት አስተምረዋችኋል እናም በቅዱሳት መጻሕፍት እና ወንጌሌን ስበኩ የሚገኙትን የመንግስቱን ቃል ኪዳኖች እና ስነ ስርዓቶች ለእናንተ ተገልጸዋል።

ስርአቶችን እና ቃል ኪዳኖችን መቀበል እና ትእዛዛትን መኖር አስፈላጊ ናቸው። ከፍ ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ በሆኑት ቃል ኪዳኖች ላይ አተኩር። ወንጌል ከፍ ከፍ ማድረግን የሚቻል ያደርገዋል፣ ይህም ከእግዚአብሔር ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ማድረግ እና መጠበቅን ይጠይቃል። ከጥምቀት፣ መረጋገጥ እና የመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን ለወንዶች ከመሰጠት በቀር፣ የምንገባቸው ቃል ኪዳኖች የሚከናወኑት በቤተመቅደስ ውስጥ ነው። ለሙታን፣ እያንዳንዳቸው እነዚህ የማዳን ስነ ስርዓቶች የሚከናወኑት በቤተመቅደስ ውስጥ ብቻ ነው። በዚህም መሰረት፣ ራሳችሁን ለቤተመቅደስ ማዘጋጀት የአሁኑ ግባቹ መሆን ይገባዋል።

አንዳንድ ጊዜ ለምታውቁት ነገር በቂ እንዳልሆናችሁ ይሰማችኋል። የወንጌል እውቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ታላቅ በረከት ነው፣ ነገር ግን የማዳን ስርዓት አይደለም። ወንጌል የእውቀት ፈተና አይደለም። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን የተስፋ ቃል እንደሰጡን፣ “መፅሐፈ ሞርሞንን በጥሞና በየቀኑስታጠኑ፣ በየቀኑ የተሻሉ ውሳኔዎችን ትወስናላችሁ—በየቀኑ። … በምታጠኑት ነገር ላይ ስታሰላስሉ፣ የሰማይ መስኮቶች እንደሚከፈቱ፣ እንዲሁም ለራሳችሁ ጥያቄዎች መልስ እና ለግል ህይወታችሁ መመሪያ ትቀበላላችሁ።”

በተጨማሪም፣ በእሁድ ስብሰባዎች የሚከናወነው፣ በየአመቱ የሚቀያረው የቤተክርስቲያኗ ትምህርት ብሉይ ኪዳንን፣ አዲስ ኪዳንን፣ መጽሐፈ ሞርሞንን፣ እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን ያጠቃልላል። ከጊዜ በኋላ የወንጌል እውቀታችሁ ሲያድግ የበለጠ በራስ መተማመን ይሰማችኋል። ቅዱሳት መጻህፍትን አዘውትሮ ማጥናት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መለወጣችሁን በማጠናከር ህይወታችሁን ይባርካል እና ያበለጽጋል።

የኢየሱስ ክርስቶስን ንፁህ ትምህርት መማር የህይወት ዘመን መሻት ነው፣ ትምህርትን በመረዳትም ሆነ ክርስቶስን በመምሰል መኖር። አስፈላጊ ቃል ኪዳኖች የቃል ኪዳን መንገድ ብለን የገለፅነውን ማዕቀፍ ያቀርባሉ። እነዚህ መርሆዎች በፕሬዚዳንት ኔልሰን በኃይል ተሰጥተዋል። ሁሉም አባላት፣ በተለይም አዲስ እና ተመላሾች፣ ስለ ቃል ኪዳኖች እና ስለ ቃልኪዳን መንገድ የሰጡትን የእርሳቸውን ትንቢታዊ መልእክቶች በማጥናትና በመቀበል መባረክ ይችላሉ።

ከፍ ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ የሆነውን እያንዳንዱን ቃል ኪዳን በአግባብ የመቀበል ግብ ካወጣችሁ፣ ወደ ሰለስቲያል መንግስት በሚወስደው መንገድ ላይ ትሆናላችሁ። በቤተመቅደሱ እና በቤተመቅደስ ስርዓቶች ላይ ትኩረታችን ማድረግ አለባቸው። አብዛኛዎቹ ቃል ኪዳኖች ለእያንዳንዱ ግለሰብ ይገኛሉ። ዘላለማዊ ጋብቻ የሆነው አንዱ ቃል ኪዳን፣ ጥረታችሁን ከጓደኛ ጋር አንድ ማድረግን ያካትታል። ግባችን ያንን ዘላለማዊ ጓደኛ ማግኘት መሆን አለበት።

ሆኖም በዚህ ጊዜ ዘላለማዊ ጋብቻ የማይቻል ከሆነ ተስፋ አትቁረጥ። ትእዛዛትን ከሚጠብቁ ታማኝ አባላት ምንም በረከት እንደማይከለከል ነቢያት አስተምረዋል። አንድ የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ፣ ንጉስ ቢንያም፣ በሚያምር ሁኔታ ብሎታል፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ… በሁሉም ነገሮች … የተባረኩ ናቸው፣… እስከ መጨረሻው በታማኝነት ከዘለቁ፣… ለዘለአለም በማያልቀው ደስታ ከእግዚአብሔር ጋር [ይኖራሉ]።”

አሁን ያላገኛችሁት ከሆነ በኋላ እንደምታገኙት፣ አባላት ፍጹም አይደሉም። እዚህ ምድር ላይ በምንኖርበት ጊዜ ስህተት እንደምንሰራ የተገለጠው አስተምህሮ ግልጽ አድርጎታል። የምንኖረው ፍጽምና በጎደለው እና በወደቀ ዓለም ውስጥ እንጂ፣ በሰለስቲያል ዓለም ውስጥ አይደለም። ይህ ህይወት፣ ንስሐ ለመግባት እና ራሳችንን ለማረጋገጥ የማያቋርጥ እድሎች ያሉትበት፣ የፈተና ጊዜ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምሰል ስንጥር፣ ሁላችንም ብቁ እንዳልሆንን ይሰማናል። የኃጢያት ክፍያው ስንወድቅ በየቀኑ ንስሃ እንድንገባ ያስችለናል። ሌላው የመፅሐፈ ሞሮን ነቢይ፣ ኔፊ እንዳለው፦ “ስለሆነም ፍጹም የሆነ የተስፋ ብርሃን፣ እናም የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር እየኖ[ረን] በክርስቶስ ባ[ለን] ፅኑነት መቀጠል አለ[ብን]። ስለሆነም፣ የክርስቶስን ቃል በመመገብ፣ እናም እስከመጨረሻው በመፅናት የምትቀጥሉ ከሆነ፣ እነሆ አብ እንዲህ ይላል፦ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል።”

የዘመናችንን ተግዳሮቶች ስናሰላስል፣ አዳኝ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት፣ በሁከትና በዓመፅ ጊዜም እንደኖረ ማስታወስ አለብን። ትኩረቱ በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ፈተና ላይ አልነበረም፤ በቅዱሳን ፍጹምነት ላይ ነበር።

ያለማቋረጥ ግርግር ባለበት አለም አዳኝን እና ትምህርቱን እና አስተምህሮቱን ለመከተል ቀላል ሆኖ አያውቅም። አዳኝ በሟች ቆይታው በተለዋዋጭ አለም ውስጥ የነበረው ህይወት ቀላል አልነበረም፣ እና ለመጀመሪያው መሪዎቻችን እና አባላትም ቀላል አልነበረም፣ እንዲሁም ለእኛ ቀላል አይደለም። እንደ እድል ሆኖ፣ በህይወት ያሉ ነቢያት ለዘመናችን የምንፈልገውን መመሪያ ይሰጡናል። ፕሬዘደንት ዳለን ኤች. ኦክስ ያንን መንፈሳዊ ሃይለኛ ውርስ ይቀጥላሉ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ዘላለማዊ እና እውነት መሆኑን እመሰክራለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው እንደሆነ፣ እንዲሁም በኃጢያት ክፍያው ምክንያት፣ በእርሱ አንድ መሆን እንደምንችል ጥርጣሬ የሌለውን እና እርግጠኛ የሆነውን ምስክርነቴንአቀርባለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ቻርልስ ዲክንስ፣ የሁለት ከተማዎች ታሪክ [1859 (እ.አ.አ)]፣ 1።

  2. ከዲከንስ ጭብጦች አንዱ በማህበራዊ አለመረጋጋት ወቅት ያለው የግለሰብ ለውጥ ሀሳብ ነው።

  3. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥26

  4. ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2025 (እ.አ.አ)፣ 6-9 ተመልከቱ።

  5. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥23

  6. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥73 ተመልከቱ።

  7. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥23፤ በተጨማሪም ዮሃንስ 14፥27 ተመልከቱ።

  8. የሐዋሪያት ስራ 2፥41 ተመልከቱ።

  9. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112 ተመልከቱ። ይህ ራዕይ የተሰጠው በሐምሌ 23 ቀን 1837 (እ.አ.አ) ነበር፣ ይህም ወንጌሉ በእንግሊዝ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰበከበት ቀን ነበር። ስለእነዚህ ተልዕኮዎች ተጨማሪ ለማግኘት፣ ጄምስ ቢ አለን፣ ሮናልድ ኬ. ኤስፕሊን እና ዴቪድ ጄ. ዊትከር፣ Men with a Mission: The Quorum of the Twelve Apostles in the British Isles [ተልእኮ ያላቸው ሰዎች፦ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን በእንግሊዝ ደሴቶች ውስጥ]፣1837–1841 (እ.አ.አ) [1992 (እ.አ.አ)] ተመልከቱ።

  10. አብዛኛዎቹ እነዚህ የቤተክርስቲያኗ ተቀላቃዮች ከሰራተኞች የህብረተሰብ ክፍል የመጡ ነበሩ። ቻርለስ ዲከንስ አንዳንዶቹን በአማዞን መርከብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ ሲዘጋጁ ተመልክቷቸዋል። በግምገማው ውስጥ መልካም አስተያየት ነበረው። እርሱም፣ “በዲግሪያቸው የእንግሊዝ ምርጫ እና አበባ” በማለት ገልጿቸዋል (“The Uncommercial Traveler,” All the Year Round, July 4, 1863, 446)። በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 1፥26–28 ተመልከቱ።

  11. “Arrival from England, by the ‘Perpetual Emigrating Fund’ [ከእንግሊዝ ወደዚህ መድረስ፣ በዘላቂ የስደተኞች ገንዘብ]፣” Deseret News፣ መስከረም 18፣ 1852 (እ.አ.አ)፣ 90 ተመልከቱ።

  12. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥62፣ 70፤ እንዲሁም 1 ቆሮንቶስ 15፥40–42 ተመልከቱ።

  13. በአባላት እና በስታቲስቲክስ መዝገቦች እና በሚስዮናውያን ክፍል የቀረበ መረጃ።

  14. በአባላት እና በስታቲስቲክስ መዝገቦች እና በሚስዮናውያን ክፍል የቀረበ መረጃ።

  15. መረጃው የተዘጋጀው በየአባልነት እና የስታቲስቲክስ መዛግብቶች ነው።

  16. በአባላት እና በስታቲስቲክስ መዝገቦች እና በሚስዮናውያን ክፍል የቀረበ መረጃ።

  17. በ1890 (እ.አ.አ) አካባቢ፣ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች አባላት ወደ ዩታ ከመሰብሰብ ይልቅ በአገራቸው እንዲቆዩ ማበረታታት ጀመሩ። ከኢንተር ማውንተን ዌስት ውጭ ያሉት የመጀመሪያዎቹ ካስማዎች የተደራጁት በ1920 (እ.አ.አ) አካባቢ ሲሆን፣ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳ ውጭ ያለው የመጀመሪያው ካስማ በኒውዚላንድ ነበር የተደራጀው። (ብራንደን ኤስ. ፕሊው፣ እትም፣ Mapping Mormonism: An Atlas of Latter-day Saint History [ሞርሞንነትን በካርታ ስራ መዘርዘር፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ታሪክ አትላስ] (2012) (እ.አ.አ) ፣ 184–85 ተመልከቱ።

  18. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥11–16ን ተመልከቱ።

  19. ጌረት ደብሊው. ጎንግ፣ “ማንም ሰው ብቻውን አይቀመጥም፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2025 (እ.አ.አ)፣ 40–43 ተመልከቱ።

  20. ሙሴ 7፥18

  21. ዮሐንስ 17፥20–211 ቆሮንቶስ 12፥11–31 ተመልከቱ።

  22. ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “Converts and Young Men [ተቀያሪዎች እና ወጣቶች]፣” ኤንዛይን፣ ግንቦት 1997 (እ.አ.አ)፣ 47።

  23. ያዕቆብ 2፥5፤ ደግሞም ማቴዎስ 19፥29ሮሜ 2፥11ኤፌሶን 2፥19ሞዛያ 18፥8–9 ተመልከቱ።

  24. ወንጌሌን ስበኩ፦ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የማካፈል መመሪያ [2023 (እ.አ.አ)]፣ 17።

  25. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥7 ተመልከቱ።

  26. Russell M. Nelson, “መፅሐፈ ሞርሞን ያለ እሱ ህይወታችሁ ምን ትመስል ነበር?)፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 62–63፤ ደግሞም ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል፦ “መለኮታዊ ጆሮ የማይሰማ በሚመስል ጊዜ እና ምንም መለኮታዊ ድምጽ የማይናገር በሚመስል ጊዜ፣ … [እራሳችንን] በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካስገባን ርቀቱ እየጠበበ፣ መንፈሳዊነቱ ይመለሳል።” (Teachings of Presidents of the Church: Spencer W. Kimball [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል] [2006 (እ.አ.አ)]፣ 67) ተመልከቱ።)

  27. ዮሀንስ 5፥39 ተመልከቱ።

  28. ለምሳሌ፣ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “እግዚአብሔር ያሸንፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር0 2020 (እ.አ.አ)፣ 92–95፤ “የመንፈሳዊ ፍጥነት ሃይል፣” ሊያሆና፣ ግንቦር 2022 (እ.አ.አ)፣ 97–100፤ “አለምን ማሸነፍ እና እረፍትን ማግኘት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 95–98 ተመልከቱ።

  29. ሞዛያ 2፥41

  30. አልማ 34፥32 ተመልከቱ።

  31. 2 ኔፊ 31፥20

  32. ኤፌሶን 4፥11–15 ተመልከቱ።

  33. ዮሀንስ 17፥20–22 ተመልከቱ።