አጠቃላይ ጉባኤ
የምስክርነት የዘላለም ስጦታ
የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


12:17

የምስክርነት የዘላለም ስጦታ

እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ወንድ ወይም ሴት ልጆች ለራሳቸው ጥልቅ፣ ጠንካራ እና አስተማማኝ እውቀትን ማግኘት ይችላሉ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከዳግም መመለስ ሶስት ኃይለኛ እውነቶች ላይ እያሰላሰልኩ ነበር። እነዚህ እውነቶች ሕይወቴን በጥልቀት ባርከውታል። ዛሬ፣ እነዚህ እውነቶች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እርግጠኛ ምስክር ስጓዝ በጉዞዬ እንዴት እንደመሩኝ ላካፍላችሁ እወዳለሁ።

እግዚአብሔር አፍቃሪ የሰማይ አባታችን ነው።

እርሱ ሁሉን አዋቂ እና ሁሉን ቻይ ነው። በክርስቶስ ብርሃን እና በመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት፣ የእርሱ ተጽዕኖ በሁሉም ቦታ ይገኛል። እኛን መባረክ ተፈጥሮው ነው።

ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የዘላለምን እጣ ፈንታችንን ያያል። ከእርሱ ፊት ሊሰወር ሚችል ነገር የለም።

የፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ስለ ሰለስቲያል አስቡ” የሚለው ግብዣ የሰማይ አባታችንን እይታ እና ተፈጥሮ እንድንመስል ያበረታታናል።

በመለኮታዊ ባህሪያቱ የተነሳ፣ የሰማይ አባታችን በጎ ስጦታን ሁሉ፣ በዘላለማዊው አመለካከቱ እና እይታው ለሁላችን ይሰጣል።

2. ነፃ ምርጫ ለራሳችን የመምረጥ እና የመተግበር ስጦታ ነው

ይህ ደግሞም በትክክል የመምረጥ ሀላፊነት ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚያ ልዩ መብት ዋጋውን በክቡር ደሙ ከፍሏል።

አንዳንድ ጊዜ ነፃ ምርጫ ማለት የፈለግነውን ማድረግ ማለት ነው ብለን እናስብ ይሆናል። ነገር ግን ዋጋው ተከፍሏ ማለት ነፃ ምርጫ የተቀደሰ ስጦታ ነው ማለት ነው።

እኛ ወኪሎች ነን፣ እና ተወካዮች ደግሞ ለአንድ ነገር ተጠያቂዎች ናቸው። በዚህም ሁኔታ፣ ባለን እውቀት እና በተሰጠን ስጦታዎች ላይ በመመርኮዝ ለምናደርጋቸው ምርጫዎች ሁሉ ሀላፊነት አለብን። ለሚያስከትለውም መዘዝ ተጠያቂ ሳንሆን ምርጫ ማድረግ አንችልም።

ለምንድር ነው ነፃ ምርጫ ያለን?

መልካምን ለመምረጥ።

ክርስቶስን ለመምረጥ።

ደግመን ደጋግመን—የዘላለም ሕይወትን ለመምረጥ።

3. ምስክርነት መቀበል የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው

ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣ ምስክርነት፣ ከማየት የሚበልጥ ነው። እርሱ የአብ እና የወልድ ቀዳሚ ምስክር ነው። ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “በሚመጡት ቀናት ያለመንፈስ ቅዱስ መመሪያ፣ ምሪት፣ መጽናኛ እና ቋሚ ከሆነ ተጽዕኖ በመንፈሳዊነት ተቋቁመን ለመቀጠል አይቻልም” ብለዋል፡፡

ወንድሞች እና እህቶች፣ ለዚህ ነው ዛሬ እያንዳንዳችን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚያስፈልገን።

በመንፈስ ቅዱስ በኩል የሚገኝ ምስክርነት በብዙ መንገዶች ሊመጣ ይችላል። በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዳለ አምፖል፣ በአስደናቂ ሁኔታ እና በድንገት ሊመጣ ይችላል። እንደ ማለዳ ፀሐይ በቀስታ እና ከጊዜ በኋላ ሊመጣ ይችላል። እንደ ብርሃን አምድ ሆኖ፣ ቀስ በቀስ በሂደት እየደመቀ ሊገለጥ ይችላል። መንገዱ ምንም ይሁን ምን፣ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ይመጣል።

በጃማይካ ውስጥ ምስክርነት ማግኘት

ውብ በሆነች ጃማይካ ውስጥ ነበር ይደግኩት፤ ይህም አስደሳች እና ድንቅ ነበር። ነገር ግን፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስጀምር፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ለመሆን ያደረኩትን ውሳኔ ለመረዳል ያልቻሉት የክፍል ጓደኞቼ እና አብሮ አደጎቼ ነበሩ። “እንዴት ወደዚያ ቤተክርስቲያን ልትቀላቀል ቻልክ?” ብለው ይጠይቁ ነበር። የመጀመሪያውን ራዕይ አስመልክተውም—“ይህን ታሪክ እንዴት ታምናለህ?” መፅሐፈ ሞርሞንንም በመጠቆም—“ያንንስ መጽሐፍ እንዴት ታነባለህ?” “ያን ሁሉ በእውነት ታምናለህን?” እናም “ህይወትህን ለምን ታባክናለህ?”

የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ
ቅዱስ ጥሻ
መፅሐፈ ሞርሞን

ይህ በተለይም ከምቀርባቸው ሰዎች ሲመጣ፣ የሚጎዳ ነበር።

ነገር ግን እነርሱ የማያውቁት ነገር ቢኖር ይህ ነበር፦ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ልምድ ነበረኝ። ያ ምስክርነት ልቤን ሲሞላው፣ የቀኖችን ስቃይ አደነዘዘ፣ እና “ለአንዲት አጭር ጊዜ፣ የመንግሰተ ሰማይ እይታ በፊቴ [ተገለጠልኝ]።

ምናልባትም እንደእነዚህ አይነት ጥያቄዎች ተጠይቃችሁ ሊሆን ይችላል። ምናልባትም፣ አሁን እንኳን እንደ እኔ በዚህ ተጠምዳችሁ ሊሆን ይችላል።

የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እና ምስክርነቱ ለሁሉም የሚገኝ ነው።

ጃማይካ ለእኔ ማለት ፓልሚራ ለጆሴፍ ስሚዝ እንደሆነች ዓይነት ማለት ናት። ይህ የእኔ ቅዱስ ጫካ ነው። ጆሴፍ ለሸሎት የተንበረከከበት ቦታ የት እንደሆነ አላውቅም፣ ነገር ግን የእኔ ቅዱስ ጥሻ እውን በሆነበት ጊዜ የት እንደነበርኩኝ አውቃለሁ፡፡ ይህ የሆነው ፎር ግሮቭ ጎዳና፣ ማንዴቪል፣ ጃማይካ፣ መታጠቢያ ቤቴ ውስጥ ከጠዋቱ 6፡00 ላይ፣ ከተጠመቅኩ ከሶስት ዓመታት በኋላ እሮብ እለት ነበር። ይህ የተቀደሰ ልምድ የተከሰተው ከሁለት ሳምንት በፊት አንዲት የተነሳሳች እህት ሚስዮናዊ መፅሐፈ ሞርሞንን እንዳነብ ስለጋበዘችኝ ነበር። እህት ኦድሪ ክራውስ ከቤተሰቧ ጋር ዛሬ በዚህ ጉባኤ ላይ ትገኛለች፣ እንዲሁም ለዘለአለም ነው የማፈቅራት።

ጎልማሳው ሽማግሌ ብራውን ከእህት ሚስዮን ጋር

ያ ተሞክሮ ለውጦኛል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ምስክርነት ለጊዜያዊ አገልግሎት ተብሎ አይሰጥም። ከአፍቃሪው የሰማይ አባታችን የሚመጣው ስጦታ ዘለአለማዊ እንዲሆን ነው ምክኛቱም ሰጪም ዘለአለማዊ ነውና፡፡ ምስክርነት ጥቅሙ የሚያልቅበት ቀን ሊኖረው አይገባም። በሕይወቴ ውስጥ የሆነ ነገር ስለተለወጠ ወይም በዓለም ላይ የሆነ ነገር ስለተቀየረ፣ ይህም ሊዳከም ወይም ሊቀንስ አይገባውም። እየጠነከረ ሊሄድ ይገባል ምክንያቱም፣ እንደዛ የመክሊት ምሳሌው ላይ እንዳለው የአገልጋዩ መክሊት፣ የግል ምስክርነቴ የሚቀበር ሳይሆን የሚባዛ ስጦታ ነው።

በልጅነቴ ያሳለፍኳቸውን እነዚያን አስቸጋሪ የፈተና እና የስደት ቀናት ሳስበው አሁን በራሴ የማውቀው ቦታ እንድደርስ ረድቶኛል። ምንም እንኳን እነዚህ ወሳኝ የሆኑ ወደ እርግጠኛ የምስክርነት ጎዳና የሚመሩት የእምነት ክፍሎች ቢሆኑም፣ የማምን፣ ተስፋ የማደርግ ወይም እምነት ያለኝ ብቻ አይደለሁም። ጥያቄያችሁን በመጠየቅ ፣ በመማር ፣ በመጸለይ ፣ በመጾም እና በማሰላሰል የራሳችሁን መንገድ ስላቀናችሁም አመሰግናችኋለሁ። እባካችሁ አታቋርጡ። ይህንን የምሥክርነት መንገድ ለመከተል የሚቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ ተገቢ ነው። ይህን ማን ወይም ምን እንዲወስድ ትፈቅዳላችሁ? “ከዚያስ ይበልጥ ምን ያህል ምስክርነትን ከእግዚአብሔር ታገኛላችሁ?”

እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ወንድ ወይም ሴት ልጆች ለራሳቸው ጥልቅ፣ ጠንካራ እና አስተማማኝ እውቀትን ማግኘት ይችላሉ። እንደ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ተቃውሞ ቢያጋጥመውም እንኳ ምስክሩን እንዳረጋገጠው፣ እኛም በድፍረት እንዲህ ማለት እንችላለን፦ “አውቀዋለሁ፣ እናም እግዚአብሔርም እንደሚያውቀውም አውቃለሁ፣ እናም ልክደውም አልችልም፣ ደፍሬም እናኳ አላደርገውም፡፡”

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ትንሹ የምሥክር ቡቃያ እስከ ዘለአለማዊ ክብር ፍጹም እውቀት እስኪደርስ ድረስ በእናንተ ውስጥ ይሠራ።

የተጠመቃችሁ እና እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት የተረጋገጣችሁት ግን፣ “ማወቄን እርግጠኛ አይደለሁም”፣ በማለት የምትታገሉት፣ “ሁልጊዜም መንፈሱ ከእነርሱ ጋር እንዲኖር” የሚለውን የተስፋ ቃል አስታውሱ። በዚህ የተስፋ ቃል የተነሳ፣ እያንዳንዳችን ወደ ምስክርነት እና ፍጹም እውቀት የሚወስደውን መንገድ መከተል እንችላለን።

ለምስክርነታችሁ ሀላፊነትን ውሰዱ

አሁን ትልቁ እውነታ ይህ ነው፦ በማንኛውም መንገድ ምስክርነት ይሰጣል—እንደ ማለዳ ፀሀይ በቀስታ ይሁን ወይም በከበረ ራእይ ቢመጣ—ይህንን ውድ ስጦታ ለመቀበል አሁንም ምርጫን ይፈልጋል።

“ማመንን መርጫለሁ” ማለት ከእግዚአብሔር ምስክርነትን ለመቀበል ቀላል ያደርገዋል። ምስክርነታችን እየተዳከመ እንደሆነ ካወቅን፣ የመረጥናቸው ምርጫዎች የምስክርነትን ኈል የሚቀንሱ እንደሆኑ አስታውሱ። ነገር ግን ምስክርነቱ የትም አይሄድም። ከእርሱ ጋር ዳግም ለመቀራኘት መምረጥ ብቻ ነው የሚያስፈልገን።

ለማመን መምረጥ ነሻ ምርጫችንን የምንጠቀምበት ጥበባዊ እና ሀይለኛ መንገድ ነው፡፡

ምስክሬነቴን በመከላከል ረገድ ነጻ ምርጫዬን የምጠቀምበት ሌላ ከዚህ የተሻለ መንገድ የለኝም።

ፕሬዚዳንት ኔልሰን አንዲህ አስተምረዋል፦ “የምሥክርነታችሁን ኃላፊነት እንድትወስዱ እማጻናችኋልሁ። እርሱን ለማግኘት ስሩ። የራሳችሁ አድርጉት። ተንከባከቡት። ያድግም ዘንድ ተንከባከቡት። እውነትን መግቡት።”

ለእኔ፣ ቃላቱ ኃላፊነትን ይወስዳሉ፣ ይሠራሉ፣ ለሌሎች ያስባሉ፣ ባለቤት ይሆናሉ፣ ይንከባከባሉ እና ውድ እና አስፈላጊ ነገር መጋቢነት እንደተሰጠው ወኪል ይመገባሉ

በቀደመችው ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ፓርሊ ፒ. ፕራት በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ቅር ተሰሽቶ ነበር እናም እርሱን እና ቤተክርስቲያኗን ለመንቀፍ መረጠ። ፓርሊ ያስተማረው የነበረ ጆን ቴይለር የተባለ ሰው ወደ ከተማ በመጣ ጊዜ፣ ፓርሊ እርሱን ወደ ጎን ወሰደው እና ጆሴፍን እንዳይከተል አስጠነቀቀው። ጆን ቴይለር ለፓርሊ እንዲህም አለው፦

“ከካናዳ ከመውጣትህ በፊት፣ ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔር ነቢይ ስለመሆኑ ጠንካራ ምስክርነት ሰጥተሃል፣ እናም እነዚህን ነገሮች በራዕይ እና በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንደምታውቅ ተናግረሃል።”

ያኔ አንተ የተደሰትክበት ምስክርነት አሁን እኔም አለኝ። ከስድስት ወር በፊት ስራው እውነት ከሆነ ዛሬ እውነት ነው። ያኔ ጆሴፍ ስሚዝ ነቢይ ከነበረ፣ አሁን ነቢይ ነው።”

እኔ ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደነበረ እና የተቀበለው ትንቢታዊ ካባ ዛሬም እንደሚቀጥል እመሰክራለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ሥራ ይመራል።

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ወንጌሉ እርግጠኛ ምስክር ለሆነው መንገዳችሁ እንድታስቡ እጋብዛችኋለሁ። ለምስክርነታችሁ እድገት ሃላፊነት ውሰዱ፤ ነጻ ምርጫችሁን በጥበብ ተጠቀሙ እናም ለሰጪው እና ሁሉንም ክቡር ባህሪያቱን እውቅና ስጡ። ኃይሉ በእናንተ ውስጥ እንዳለ እመሰክራለሁ። ማንም ሊመርጥላችሁ አይችልም። ይህንን ስጦታ ማንም ሊወስድ አይችልም። ለማመን መምረጥ ትችላላችሁ።

ይህን ስታደርጉ፣ ምስክርነታችሁ “ወደ ዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የሕይወት ውሃ ምንጭ” እንደሚሆን ቃል እገባለሁ። ይህም መልህቅ እና ማበረታቻ ይሆናል፣ እና በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ይደግፋችኋል። መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንድታዳብሩ ያስችላችኋል። በግል የመንፈሳዊ ትምህርታችሁ ጊዜ እና አገልግሎታችሁ ይረዳችኋል። በሰይጣንና በጠላታችሁ ላይ የጦር እቃ ይሆንላችኋል። ምስክርነታችሁ በልጆቻችሁ፣ በልጅ ልጆቻችሁ፣ እና ቅድመ-የልጅ ልጆቻችሁ እና በምትወዷቸው እና በምታገለግሏቸው ላይ ሲባዛ ስታዩት ደስታ ይሆናል። ስታካፍሉት እና ለመመስከር ስትጠቀሙበት ሃያል ይሆናል።

ካወቃችሁ ታውቃላችሁ። እኔ እንደማውቅ አውቃለሁ። ይበልጥ የኢየሱስ ክርስቶስ እና የወንጌሉ እርግጠኛ ምስክሮች ያስፈልጉናል። እዛ ደረጃ ላይ ድረሱ! ፈልጉት! አስችኳይ ነው! ይህ የመጨረሻው ዘመን ነው—የዘመን ፍጻሜ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን እውነት አውጇል፦ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።”

ወንድሞች እና እህቶች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ጊዜያዊ ስጦታ እንዲሆን ታስቦ አልተደረገም። ለዚህ ማንኛውም ጊዜአዊ አይደለም፣ ሰጪውም አይደለም፣ ስጦታው ራሱ አይደለም፣ የስጦታ አድራሽም አይደለም፣ የስጦታው ርዕስ የሆነውም ጊዜያዊ አይደለም። ምስክርነታችሁም በዚሁ ተመሳሳይ መንገድ ይገለጽ። ምንም እንኳን “ሰማይና ምድር ያልፋሉ”፣ የእናንተ ምስክርነት እና የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምስክርነት በጭራሽ አያልፍም። አሁን ይህን ውድ ስጦታ አጥብቆ የመያዝ ጊዜ ነው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. እግዚአብሔር የሰማይ አባታችን ነው፣ እኛም የእርሱ ልጆች ነን። እርሱ በአምሳሉ ፈጥሮናል። እርሱ የከበረ፣ ፍጹም የሆነ “እንደ ሰው ሊዳሰስ እና ሊጨበጥ የሚችል የስጋና የአጥንት አካል” አለው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥22)።

    እግዚአብሔር በግል ያውቀናል፣ ከምንረዳውም በላይ ይወደናል። ፈተናዎቻችንን፣ ሀዘኖቻችንን እና ድክመቶቻችንን ያውቃል፣ በዚያ መሃልም ሊረዳንም ይፈልጋል። በእድገታችን ይደሰታል እንዲሁም ትክክለኛ ምርጫዎችን እንድናደርግ ይረዳናል። ከእኛ ጋር ለመነጋገር ይፈልጋል፣ እንዲሁም እኛ ከእርሱ ጋር በጸሎት መነጋገር እንችላለን” (ወንጌሌን ስበኩ፦ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የማካፈል መመሪያ [2023 (እ.አ.አ)]፣ 33)።

  2. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥46–4788፥12–13 ተመልከቱ፡፡

  3. “እግዚአብሔር አምላክ ስለሆነ ብቻ ክርስቶስ ክርስቶስ ስለሆነ ብቻ፣ በፈቃደኛነት ከመጣን በየዋህነት ልብ እና በትህትና ወደ ጸጋው ዙፋናቸው ከቀረብን፣ እኛን ከመንከባከብ እና ከመባረክ እና ከመርዳት ውጪ ሌላ ምንም አያደርጉም። እኛን እነሱ እኛን ከመባረክ ሌላ አማራጭ የላቸውም። ይህን ማድረግ አለባቸው። ይህም የእነርሱ የፍጥረት ጸባይ ነው” (ጄፍሪ አር ሆላንድን፣ “ወደ እኔ ኑ” [ብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ መንፈሳዊ ትምርት፣ መጋቢት. 2፣ 1997 (እ.አ.አ)፣ 4፣ speeches.byu.edu]።

  4. ሉቃስ 12፥2ሞሮኒ 7፥22አብርሃም 2፥8 ተመልከቱ።

  5. “ስለ ሰለስቲያል አስቡ” የሚባለውን ልምምድ እንድትከተሉ እጋብዛችኋለሁ! ስለ ሰለስቲያል አስቡ ማለት በመንፈሳዊ አስተሳሰብ መጠመድ ማለት ነው። ከመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ ከያዕቆብ እንደምንማረው ‘ስለመንፈስ ማሰብ ዘላለማዊ ህይወት ነው’ (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ))፡፡

  6. ርዕሰ እና ጥያቄዎች፣ “ነጻ ምርጫ እና ተጠያቂነት፣” የወንጌል ቤተመጻሕፍት፤ እንዲሁም 2 ኔፊ 2፥11፣ 16 ተመልከቱ።

  7. 1 ጴጥሮስ 1፥18–20አብርሃም 3፥22–28

  8. 1 ቆሮንቶስ 6፥20ን ተመልከቱ።

  9. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥78 ተመልከቱ።

  10. “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሰማይ አባት እንድንሆን የሚፈልገውን እንዴት እንደምንሆን የሚያሳየን እቅድ ነው።”

    ይህ እንከን የለሽ እና ፍጹም የሆነ ሁኔታ በተከታታይ የቃል ኪዳኖች፣ ስነ ስርዓቶች እና ድርጊቶች፣ የትክክለኛ ምርጫዎች ድምር እና ቀጣይነት ካለው ንስሃ ይመጣል። (ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “The Challenge to Become [ለመሆንን የሚገድቡ ተግዳሮቶች]፣” ሊያሆና፣ ጥር 2001 (እ.አ.አ)፣ 40፣ 41፣ አትኩሮቶች ተጨምረዋል)፤ በተጨማሪም ሙሴ 7፥33 ተመልከቱ።

  11. ሞሮኒ 10፥4–5 ተመልከቱ።

  12. “መንፈሱ በቃላት ብቻ መገደብ አያስፈልገውም፣ እርሱም ቃላቶች የሌሉት ቢሆንም በማያምታታ ቋንቋ መሰረት መንፈስን ከመንፈስ ጋር ማግባባት ይችላል። ከመንፈስ የተገኘ የንፁህ እውቀት እና የእውቀት ልውውጥ ነው፣ እናም እውቀትን ለማግኘት በእውነት ከሁሉ የተሻለው መንገድ እንደሆነ ተረድቻለሁ። ከመዳሰስ ወይም ከማየት የበለጠ ጠንካራ እና ዘላቂ ነው፤ ሥጋዊ ስሜትን ልንጠራጠር እንችላለን፣ መንፈስ ቅዱስ ግን ሲናገረን ልንጠራጠር አንችልም። በጣም አስተማማኝ ምስክር ነው። በዚህ ምክንያት፣ ይቅር የማይባለው ኃጢአት መንፈስ ቅዱስን ወይም የመንፈስ ቅዱስን ምስክርነት መካድ ነው” (ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰንን፣ “ጠንካራ የመንፈስ ግንዛቤዎች”፣ ሊያሆና፣ ሰኔ 2013 (እ.አ.አ)።)

  13. ዮሐንስ 5፥322 ኔፊ 31፥183 ኔፊ 11፥36 ተመልከቱ።

  14. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ራዕይ ለቤተክርስቲያኗ እና ራዕይ ለህይወታችን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 96። በዚያም ንግግር ውስጥ እንዲህ አሉ፦

    “የግል መገለጥን ለመቀበል አሁን ካላችሁበት መንፈሳዊ አቅም በላይ እንድትዘረጉ አሳስባችኋለሁ። …

    አቤቱ፣ የሰማይ አባታችሁ እንድታውቁት የሚፈልገው ብዙ ነገር አለ። ሽማግሌ ኔል ኤ. ማክስዌል እንዳስተማሩት፣ ‘የሚያዩ አይኖች እና የሚሰሙ ጆሮዎች ላላቸው፣ አብ እና ወልድ የአጽናፈ ሰማይን ምስጢር እየሰጡ እንደሆነ ግልጽ ነው!’ …

    በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለመደሰት እና የመንፈስን ድምጽ ይበልጥ በተደጋጋሚ እና ይበልጥ በጥራት ለመስማት አስፈላጊ የሆነውን መንፈሳዊ ስራ መስራትን ምረጡ” (95፣ 96)።

  15. ዴቪድ ኤ. ቤድናርን፣ “የራዕይ መንፈስ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 87–90፤ አሌክሳንደር ዱሽኩ፣ “ምሰሶዎች እና ጨረሮች”፣ ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ)፣ 14–16 ተመልከቱ።

  16. “ምስክርነት፣” መዝሙር፣ ቁጥር 137።

  17. ዘኁልቁ 11፥29ያዕቆብ 1፥5 ተመልከቱ።

  18. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥28ሙሴ 1፥3 ተመልከቱ።

  19. ማቴዎስ 25፥14–30 ተመልከቱ። ከመንፈስ ቅዱስ ያገኘሁት መንፈሳዊ ምስክርነት አልጠፋም። በእርግጥም እየጠነከረ መጥቷል። በወጣትነቴ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረታዊ መርሆች የተማርኳቸው ነገሮች በህይወቴ ሙሉ ጽኑ መሰረት ሆነውኛል” (ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “ሥሩን ተንከባከቡት፣ ከዚያም ቅርንጫፎቹ ያድጋሉ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2024 (እ.አ.አ)፣ 101)።

  20. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥23

  21. የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥25

  22. አልማ 32፥27፣ 30፣ 37–38፣ 41 ተመልከቱ።

  23. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77 ተመልከቱ።

  24. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥33 ተመልከቱ።

    ከዚያም፣ የሚቀጥለው ምናልባት በጣም አስፈላጊው ክፍል፣ ስጦታውን መቀበል ነው። ስጦታን በእውነት ለመቀበል፣ ዋጋ በመስጠት ለራሳችን፣ በሙሉነት በህይወታችን በመጠቀም እናም ሰጪውን በአመስጋኝነት እናስታውሳለን።

    ስጦታን መቀበል ጥረት የማያስፈልገው አይደለም ግን እና መጠቅለሊያውን ከመፍከት በላይ የሆነ ምክንያት ያለው እና ትርጉም ያለው ድርጊት ነው። መቀበል ማለት ስጦታውን እና የሰጪውን ልብ በሰጪ እና በተቀባዩ መካከል ያለውን ትስስር በሚያጠናክር መልኩ ሁለቱንም ማድነቅ እና ማገናኘት ነው” (ፓትሪክ ኪሮን፣ “ስጦታውን ተቀበሉ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2025 (እ.አ.አ)፣ 121–22)።

  25. ራስል ኤም። ኔልሰን፣ “Choices for Eternity [የዘለአለማ ምርጫዎች]” (worldwide devotional for young adults, May 15, 2022), የወንጌል ቤተመጻህፍት፡፡

  26. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 70፥3–4 ተመልከቱ።

  27. Saints: The Story of the Church of Jesus Christ in the Latter Days [ቅዱሳን፤ የኋለኛው ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ] ጥራዝ 1፣ The Standard of Truth [የእውነት መስፈርት]፣ 1815–1846 (እ.አ.አ) (2018 [እ.አ.አ)፣ 280።

  28. ሞዛያ 4፥9–12 ተመልከቱ።

  29. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥23፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል።

  30. አልማ 5፥46–48 ተመልከቱ። ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው፣ “ደህንነት ያለራዕይ ለመምጣት አይችልም፡፡ ማንም ሰው ያለዚያ ማገልገል ከንቱነት ነው፡፡ … ማንም ሰው ነቢይ መሆን ሳያስፈልገው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ መሆን ይችላል። ሰው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ምስክርስነት እና የትንቢታዊ መንፈስ ካልኖረው፣ ማንም ሰው ለክርስቶስ አገልጋይ ለመሆን አይችልም” (The Joseph Smith Papers, History, 1838–1856, volume C-1 [2 November 1838–31 July 1842] [addenda], 12, josephsmithpapers.org; spelling, capitalization, and punctuation modernized)።

  31. “በዘመናት ጫፍ ላይ ቆመን፣ በታላቁ እና ክብራዊ የታሪክ አስተያየቱ እንድደነቅለን። ይህ ባለፉት ዘመናት ሁሉ የጠቆሙት የመጨረሻው እና የዘመን ፍጻሜ ጊዜ ነው።(ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “the Summit of the Ages [በዘመናት ጫፍ]፣” ሊያሆና፣ ጥር 2000 (እ.አ.አ)፣ 90)

  32. ማቴዎስ 24፥35

  33. ሞሮኒ 10፥30ን ተመልከቱ።