ፈገግ ያሉ ፊቶች እና አመስጋኝ ልቦች
የህይወት ፈተናዎችን እና እያደገች ያለችውን ቤተ ክርስትያን ፍላጎቶች ሲጋፈጡ፣ የኛ ቅዱሳን አፍሪካ ውስጥ ያላቸው ታላቅነት ይበልጥ የሚታይ ይሆናል።
ከጥቂት አመት በፊት፣ በዚህ በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ በተደረገ የለውጥ ማስታወቂያ፣ ከሰባዎቹ ቡድን ከፕሬዝዳንትነት ምደባዬ ተነስቼ ነበር። ስሜ ጡረታ ከወጡት ከአጠቃላይ ባለ ሥልጣናት ስም አቅራቢያ ስለሚነበብ ብዙዎች እኔ የአገልግሎት ጊዜዬን እየጨረስኩ እንደሆነ ገምተው ነበር። ከጉባኤውም በኋላ፣ ለቀጣይ የህይወቴ ምዕራፍ ብዙ የምስጋና እና የመልካም ምኞት መልእክቶች ደርሰውኛል። አንዳንዶችም በሰሜን ሶልት ሌክ የሚገኘውን ቤቴን ለመግዛት ጥሪ አቅርበዋል። እንደምናፈቅ ማየት እንዲሁም ስጨርስ ቤታችንን ለመሸጥ እንደማልቸገር ማወቁ ደስ የሚያሰኝ ነበር። ነገር ግን እስካሁን እዚያ አልደረስኩም።
አዲሱ ምድቤ እኔን እና ሞኒካን ቤተክርስቲያኑ በማበብ ላይ ወዳለች ወደ ውቢቷ አፍሪካ ወሰደን። በአፍሪካ በደቡባዊ አካባቢ ባሉ ታማኝ ቅዱሳን መካከል ሆኖ ማገልገል እና ጌታ ለእነርሱ ያለውን ፍቅር መመስከር መታደል ነው። ብዙ የተሳካላቸውን እና በደንብ የተማሩ የቤተክርስትያን አባላት ጨምሮ ሌሎችን ለማገልገል ጊዜያቸውን እና ተሰጥኦቸውን ሲገብሩ በሁሉም አስተዳደግ ያሉ የትውልድ ቤተሰቦችን ማየት የሚያበረታታ ነው።
በተመሳሳይ ጊዜም፣ ከክልሉ ህዝብ ፅፍ አንጻር፣ ብዙ ትሁት የሆኑ ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን እየተቀላቀሉ እና በታማኝነት የአስራት በረከቶች እና በቤተ ክርስቲያን በሚሰጡ የትምህርት እድሎች ህይወታቸው እየለወጡ ነው። እንደ ስኬት በትምህርት ቤት፣ ኢንግሊዝኛ ክህሎት ማዳበር (EnglishConnect)፣ BYU–Pathway እና የቋሚ ትምህርት እርዳታ፣ ያሉ ፕሮግራሞች የብዙዎችን በተለይም በማደግ ላይ ያለውን ትውልድ ህይወት ይባርካሉ።
ፕሬዘደንት ጀምስ ኢ. ፋውስት በአንድ ወቅት፣ “ይህች ቤተ ክርስቲያን የግድ ታላላቅ ሰዎችን አትስብም ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተራ ሰዎችን ታላቅ ታደርጋለች” ብለዋል።
የህይወት ፈተናዎችን እና እያደገች ያለችውን ቤተ ክርስትያን ፍላጎቶች ሲጋፈጡ፣ የኛ ቅዱሳን አፍሪካ ውስጥ ያላቸው ታላቅነት ይበልጥ የሚታይ ይሆናል። ሁልጊዜ በአዎንታዊ አመለካከት ይቀርባሉ። የፕሬዘዳንት ራሰል ኤም. ኔልሰንን ትምህርት የሆነውን ታዋቂ ትምህርት ያካትታሉ፤
“የሚሰማን ደስታ ካሉን የህይወታችን ሁኔታዎች ጋር ግንኘነት አነስተኛ ነው እናም በህይወታችን ትኩረት ከምንሰጠው ነገር ጋር ያላቸው ተዛምዶ ታላቅ ነው።
“የህይወታችን ትኩረት በእግዚአብሔር የደህንነት እቅድ … እና በኢየሱስ ክርስቶስና በወንጌሉ ላይ ሲሆን፣ በህይወታችን ከተከሰተው ወይም—ካልተከሰተውም—ሁኔታ ባሻገር ደስታ ሊሰማን ይችላል።”
ተግዳሮቶች ቢኖሩም እንኳ ደስታን ያገኛሉ። ከአዳኙ ጋር ያለን ግንኙነት ችግሮችን በፈገግ ባሉ ፊቶች እና በአመስጋኝ ልቦች ለመቅረብ እንደሚያስችለን ተምረዋል።
ከሞዛምቢክ በመጀመር፣ ይህንን መርህ ምሳሌ ከሚሆኑን ታማኝ ቅዱሳን ጋር አንዳንድ ልምዶቼን ላካፍል።
ሞዛምቢክ
ከጥቂት ወራት በፊት፣ ቀድሞ 10 ክፍሎች ለነበረው የአንድ አመት እድሜ በነበረው የካስማ ኮንፈረንስ ላይ በበላይነት መርቼ ነበር። ከ2,000 የሚበልጡ ሰዎች ትንሿን አዳራሽ እና ሦስት ድንኳኖችን ሞልተው ነበር። የካስማው ፕሬዝዳንት 31 አመቱ ነበር፣ ባለቤታቸው 26 አመቷ ነበር፣ ሁለት ትናንሽ ልጆችም አሏቸው። እሱ ይህን እያደገ እና ፈታኝ እየሆነ ያለን ካስማን ፈገግ ባለ ፊት እና አመስጋኝ ልብ ብቻ ያለምንም ቅሬታ ይመራል።
ከፓትርያርኩ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፣ ባለቤቱ በጠና መታመሟን እና ለእርሷ እንክብካቤ ለማድረግ እደተቸገረ ሰማሁ። ጉዳዩን ከካስማ ፕሬዘዳንት ጋር ከተነጋገርን በኋላ፣ የክህነት ቡራኬን ሰጠናት። ፓትርያርኩ በአማካይ ስንት የፓትርያሪካዊ በረከቶች እንደሚሰጡ ጠየኳቸው።
“ከስምንት እስከ አስር” ብለው መለሱ።
“በወር?”፣ ብዬ ጠየኳቸው።
እነርሱም፣ “በሳምንት!” ብለው መለሱ። በየሳምንቱ መጨረሻ ያን ያህል ማድረግ ብልህነት እንዳልሆነ መከርኳቸው።
“ሽማግሌ ጎዶይ”፣ አሉ፣ “አዳዲስ አባላትን እና ብዙ ወጣቶችን ጨምሮ በየሳምንቱ ይመጣሉ”። በድጋሚ፣ ያለምን ሰበብ—ፈገግ ባለ ፊት እና አመስጋኝ በሆነ ልብ ብቻ።
ከቅዳሜ ምሽት የካስማ ጉባኤ ክፍለ ጊዜ በኋላ፣ ወደ ሆቴሉ እየሄድኩ ሳለ፣ ሰዎች በመንገድ ዳር ምግብ ሲገዙ አየሁ። ሾፌሬን ቀን ሳይሆን እጅግ ጨለማ በሆነበት ጊዜ ለምን እንደሚያደርጉት ጠየኩት። አሱም ቀኑን ሙሉ ስራ ላይ ስለሚሆኑ ገንዘቡን ማግኘት እና መግዛት የሚችሉት በኋላ ላይ መሆኑን ነገረኝ።
“አሃ፣ ነገ ላይ ለመብላት ዛሬ እየሰሩ ነዋ” አልኩት።
እሱ ግን፡ “አይ ዛሬ ማታ ለመብላት ቀን እየሰሩ ነበር” ሲል አረመኝ። አባሎቻችን የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተስፋ አድርጌ ነበር፣ ነገር ግን በዚያች የአገሪቱ ክፍል ብዙዎች ተመሳሳይ ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸው አረጋገጠ። በማግስቱ ማለዳ፣ በእሁድ ክፍለ ጊዜአችን እና ሁኔታቸውን በቅርቡ በተረዳወበት ወቅት እንኳ፣ ፈገግ ባሉ ፊቶች እና በአመስጋኝ ልቦች የበለጠ ተነካሁ።
ዛምቢያ
ወደ ሰንበት ስብሰባ እየሄድኩኝ ሳለ፣ የካስማ ፕሬዘዳንቱ እና እኔ አንድ ባልና ሚስት ከአንድ ሕፃን እና ሁለት ትናንሽ ልጆች ጋር በመንገድ ላይ ሲሄዱ አየን። እንድንሸኛቸው ልንጠይቃቸው ቆምን። በጣም ተደንቁ፣ ደስም አላቸው። ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለመሄድ ምን ያህል ጊዜ እንዲሚወስድባቸው ስጠይቃቸው አባትየው እንደ ልጆቹ ፍጥነት ከ45 ደቂቃ እስከ አንድ ሰአት ሊወስድ እንደሚችል መለሰልኝ። ያለምንም ቅሬታ—ፈገግ ባሉ ፊቶች እና አመስጋኝ ልቦች፣ ይህን ጉዞ በየእሁዱ ይደጋግሙ ነበር።
ማላዊ
አንድ እሑድ ከካስማ ጉባኤ ቀደም ብሎ፣ የሕዝብ ትምህርት ቤቶችን እንደ መሰብሰቢያ ቤቶች የሚጠቀሙ ሁለት ቅርንጫፎችን ጎበኘሁ። አንዳንድ መሠረታዊ ነገሮች እንኳን ሳይኖራቸው የሕንፃዎቹ ደሳሳነት እና የቦታው አነስተኛ ሁኔታ አስደንግጦኝ ነበር። በእዚያም ጥቂት አባላትን እዳገኘው፣ ለስብሰባ ቤታቸው በቂ ያልሆነ ሁኔታ አለመኖሩ ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከተለመደው ረጅም የእግር ጉዞ በመራቅ በአቅራቢያቸው የሚሰበሰቡበት ቦታ በማግኘታቸው ደስተኞች ነበሩ። በድጋሚ፣ ምንም ቅሬታዎች አልነበሩም—ፈገግ ያሉ ፊቶች እና አመስጋኝ ልቦች ብቻ ነበሩ።
ዝምባቡዌ
ከቅዳሜው የአመራር ስልጠና በኋላ፣ የካስማ ፕሬዝዳንቱ በተከራየው ቤት ውስጥ ወደሚደረግበት የእሁድ አገልግሎት ወሰዱኝ። 240 ሰዎች ተገኝተው ነበር። ከዚያም ኤጲስ ቆጶሱ በዚያ ሳምንት የተጠመቁ 10 አዳዲስ አባላትን አስተዋወቁ። ጉባኤው በሁለት ትንንሽ ክፍሎች ተከፍሎ፣ አንዳንድ አባላትም ከህንጻው ውጭ ተቀምጠው ስብሰባውን በመስኮትና በሮች ይመለከቱ ነበር። ምንም ቅሬታዎች አልነበሩም—ፈገግ ያሉ ፊቶች እና አመስጋኝ ልቦች ብቻ ነበር።
ሌሴቶ
ይህችን “የተራራማው መንግስት” በመባልም የምትጠራውን ትንሽዬ ውብ አገር ጎበኘሁ፣ የቤተ ክርስትያን አውራጃ ካስማ ለመሆንም ስትዘጋጅ አየሁ። ከቅዳሜ ስብሰባዎች በኋላ፣ በተከራዩበት ቤት ውስጥ ከሚገኙት ቅርንጫፍዎቻቸው በአንዱ የእሁድ አገልግሎቶችን ተሳተፍኩ። የቅዱስ ቁርባን ክፍል ሞልቶ ነበር፣ ሰዎች ለመሳተፍ ከበሩ ውጭም ቆመው ነበር። ለቅርንጫፍ ፕሬዘዳንቱ ትልቅ ህንጻ እንደሚያስፈልገው ነገርኩት። ይህ የእርሱ አባላት ግማሹ ቁጥር ብቻ እንደሆነ ሲነግረኝ በጣም ተገረምኩ። ሌላኛው ግማሹ ደግሞ ከቀጣይ ግማሽ ሰዓት በኋላ በሁለተኛው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ይሳተፋል። በድጋሚ፣ ምንም ቅሬታዎች አልነበሩም—ፈገግ ያሉ ፊቶች እና አመስጋኝ ልቦች ብቻ ነበር።
ቀደም ሲል በሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን በተጠቀሰው፣ በርካታ ወጣቶቻች ላይ በደረሰ አስከፊ የትራፊክ አደጋ ምክንያት ወደ ሌሶቶ ተመለስኩ። ቤተሰቦቹን እና መሪዎችን ስጎበኝ፣ የሃዘን ድባብ ጠብቄ ነበር። በምትኩ፣ ሁኔታውን በሚያበረታታ እና በሚያነቃቃ መንገድ የሚቋቋሙትን ጠንካራ እና ጽኑ የሆኑ ቅዱሳን አገኘሁ።
በዚህ ምስል ላይ የምትታየው ከአደጋ በሕይወት የተረፈችው የ14 ዓመቷ ኤምፎ አኒሲያ ንኩ ”በኢየሱስ ታመኑ፣ ሁልጊዜም ወደ እርሱ ተመልከቱ፣ በእርሱ ሰላም ታገኛላችሁና፣ በፈውስም ሂደት ውስጥ ይረዳችኋል” በማለት በራሷ ቃል ተናግራለች።
እነዚህ ሕይወታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላይ ያተኮሩ በመሆናቸው አዎንታዊ አመለካከታቸውን የምናይባቸው ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። እርዳታ እና ተስፋ የት ማኘት እንዳለባቸው ያውቃሉ።
የአዳኙ የፈውስ ኃይል
ለምንድነው አዳኙ እነርሱን እና እኛን በህይወታችን በማንኛውም ሁኔታ ሊረዳ የቻለው? መልሱ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ይገኛል፦
“እናም በመከራና በሁሉም ዓይነት ህመምና ፈተናዎች በመሰቃየት ይሄዳል። …
“… አንጀቱ በምሕረት እንዲሞላ፣ … ሕዝቡን እንደ ድክመታቸው እንዴት መርዳት እንዳለበት ያውቅ ዘንድ፣ ደዌአቸውን በእርሱ ላይ ይወስዳል።”
ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዳስተማሩት፣ እኛ ይምናልፍበት ግን አዳኙ የማያውቀው ምንም አይነት አካላዊ ህመም፣ ጭንቀት ወይም ድካም የለም። “እኔ እና አናንተ በድካም ጊዜ “ማንም ሰው ‘[የሚያጋጥመኝን ነገር አይረዳም] …’ ምናልባትም ማንም ሰው አያቅም፣ ብለን እንጮኽ ይሆናል። የእግዚአብሔር ልጅ ግን በሚገባ ያውቃል እናም ይረዳል።” እና ለምን? ምክንያቱ “ከእኛ በፊት ሸክማችንን ስለተሰማው እና ስለተሸከመ ነው።”
በማቴዎስ ላይ በሚገኘው የክርስቶስ ቃል ምስክርነቴን እቋጫለው ማቴዎስ 11፡-
“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
“ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
ልክ በአፍሪካ እንዳሉት ቅዱሳን ይህ የተስፋ ቃል እውነት መሆኑን አውቃለሁ። እዚያ እውነት ነው፣ እንዲሁም በሁሉም ቦታም እውነት ነው። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።