አንዱን የማገልገል ኃይል
አንድን ሰው ስናገለግል፣ ወደ ክርስቶስ እንዲመጣና በጌታ ቤት እንዲያመልክ በመጋበዝ የቤዛነት ኃይሉን እንዲቀበል እንጋብዛለን።
ወንድሞችና እኅቶች፣ በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያት ውስጥ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣታ ላሳያችሁት ታማኝነት እናመሰግናለን። ግሩም ናችሁ፤ ውብ ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ። በትክክል ታታሪ የኢየሲስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ስንሆን እንዲሁም እርስ በእርስ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ስንረዳዳ የመንፈስ ቅዱስን ተጽዕኖ እንድንገነዘብ እና በጌታ ቤት ስናመልክ የእርሱ ደስታ እንዲሰማን ጸሎቴ ነው።
ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ አወጁ፤ “አሁን እኔ እና እናንተ ለጌታችንና ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት የምንዘጋጅበት ጊዜ ነው። አሁን ለደቀመዝሙርነታችን ከሁሉ የላቀ ቅድሚያ የምንሰጥበት ጊዜ ነው። ትኩረትን በወንጌል ላይ እንዳናደርግ በሚያደርጉ ነገሮች በተሞላ ዓለም ውስጥ፣ ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?”
ምላሹን እንዲህ ሰጡ፦ “በቤተ መቅደሱ ውስጥ አዘውትሮ አምልኮ ማድረጋችን ይረዳናል። በጌታ ቤት ውስጥ፣ ትኩረታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እናደርጋለን። … የበለጠ እያወቅነው እንመጣለን። … ኢየሱስ ክርስቶስን ከልብ የሚፈልግ ሁሉ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያገኘዋል።”
ታታሪ የኢየሲስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የምሆነው እንዲሁም እርስ በእርስ ደቀ መዛሙርት ለመሆን የምንረዳዳው እንዴት ነው? አንዱን እናገለግላለን። በአዳኙ መንገድ ማገልገል ርኅራኄን፣ ደግነትን ትዕግሥትን እና ያለ ፍርድ ፍቅርን ይጠይቃል። አንድን ሰው ስናገለግል ወደ ክርስቶስ እንዲመጣና በጌታ ቤት እንዲያመልክ በመጋበዝ የቤዛነት ኃይሉን እንዲቀበል እንጋብዛለን። በሌላ አነጋገር፣ ወደ ጌታ ቤት በሚወስዱ መንገዶች ሌሎችን ስናገለግል፣ ራሳችንን ለአምላክ የወሰንን ደቀ መዛሙርት እንድንሆን እርስ በርስ እንረዳዳለን።
ከኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅር እና ያለ ፍርድ ማገልገል የሚያስችለንን ኃይል እንማራለን። ከውሃ ጕድጓዱ አጠገብ የነበረችውን ሳምራዊት ሴት ታስታውሳላችሁ። ይህች ሴት ራሷን ዋጋ ቢስ፣ ብቸኛ፣ ተስፋ የቆረጠችና የማትታይ ሆኖ ተሰምቷት ሊሆን ይችላል። ያልተጋበዘች መስሏት ተሰምቷት ሊሆን ይችላል። በሕይወት ዘመኗ አምስት ባሎች የነበሯት ሲሆን አብሯት የሚኖረው ሰው ባሏ አልነበረም። ሌሎች ደግሞ የሕይወቷን ሁኔታ ሳያውቁ ፍትሃዊ ያልሆነ ፍርድ ሊሰጡ ይችላሉ። ቀኑ ውስጥ በጣም ሞቃታማ በሆነበት ወቅት ብቻዋን ወደ ውሃ ጕድጓዱ የመጣችበት አንዱ ምክንያት ይህ ሊሆን ይችላል። ይሁንና ኢየሱስ ክርስቶስ መሢሕ መሆኑን ከገለጸላቸው የመጀመሪያ ሰዎች አንዷ ነበረች። ይህች ሴት ለእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረች።
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሴቲቱ ያስተማራት፣ በእርሱ አማካኝነት አንድ ሰው ከሕያው ውኃ በመጠጣት የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንደሚችል ነው። እንዲህ ብሏል፦“እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል።”
የሰማርያዋ ሴት የአዳኙ ፍቅር ተሰማት እናም እርሱ መሢሕ መሆኑን በመንፈስ ምስክርነት ተቀበለች። ከዚህ ምስክርነት በኋላ ወደ ከተማዋ ተመልሰች እና ሌሎችም እንዲመጡና እንዲመለከቱት ጋበዘቻቸው፤ ብዙዎችም “በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድሃኒት እንደሆነ [አወቁ]።” ክርስቶስ አንደን ግለሰብ በፍቅር አገልግሏል፤ በዚህም ምክንያት ሌሎች ታማኝ ደቀ መዛሙርቱ ሆኑ።
የክርስቶስ ሐዋርያት ከሆኑት ከጴጥሮስና ከዮሐንስ ርኅራሄ በሚንጸባረቅበት መንገድ ሌሎችን የማገልገልን ኃይል እንማራለን። ከተወለደበት ጊዜ አንሥቶ ሽባ የሆነ አንድ ሰው በየዕለቱ በቤተ መቅደሱ በር ላይ ተኝቶ ገንዘብ ሲለምን ታስታውሳላችሁ። ይህ ሰው ትልቅ ቦታ እንደሌለው፣ ብቸኛ፣ ተስፋ የቆረጠና የማይታይ ሆኖ ተሰምቶት ሊሆን ይችላል። ያልተጋበዘ መስሎት ተሰምቶት ሊሆን ይችላል።
“ጴጥሮስ ግን ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።”
ጴጥሮስ ሰውየውን በቀኝ እጁ ይዞ አስነሣው እና ሰውየውም ዳነ። ወዲያው ተአምሩን ተከትሎ፣ ሰውየውም “እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ” ከጴጥሮስ እና ከዮሐንስ ጋር ወደ ቤተመቅደስ ገባ። ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ወደ ጌታ ቤት በሚወስዱ መንገዶች ለአንዱ አገልግለዋል፤ ሰውየውም የክርስቶስ ታማኝ ደቀ መዝሙር ሆነ።
ወዳጆቼ፣ በሕይወቴ ውስጥ አስፈላጊ እንዳልሆንኩ፣ ብቻዬን እንደሆንኩ፣ ተስፋ እንደቆረጥኩና እንደማልታወቅ የተሰማኝ ጊዜያት አሉ። ያልተጋበዝኩኝ መስሎኝ ተሰምቶኝ ያውቃል። በ19 ዓመቴ ተጠመቅኩኝ እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአባልነት ማረጋገጫን ተቀበልኩኝ። ከዓመት በኋላ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ ሆኜ እንዳገለግል የቀረበልኝን ግብዣ ተቀበልኩ፤ ሆኖም ስለ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገና ብዙ አላወቅሁም ነበር።
በሚስዮናዊነት አገልግሎቴ መጀመሪያ ላይ ጥቁር አፍሪካዊ ዝርያ ያላቸው ሰዎች በጌታ ቤት ውስጥ የሚያመልኩትን በረከቶች በሙሉ እንዲደሰቱ የማይፈቀድላቸው ጊዜ እንደነበረ ተማርኩ። ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ ማወቄ የቍጣ፣ የጭንቀት፣ የጥርጣሬና የፍርሃት ስሜት አሳደረብኝ። እነዚህ ስሜቶች በጣም ኃይለኛ ስለነበሩ መንፈስ ቅዱስን የመለየት ችሎታዬ ለጊዜው ጠፋ።
እንደ እድል ሆኖ፣ በፍቅር፣ በትዕግስትና በደግነት ያገለገለኝ ግሩም ሚስዮናዊ ጓደኛዬ ኬቨን ቪክ ነበረኝ። በየምሽቱ የጥርጣሬ ስሜቴን ሲመለከት ለወጣቱ ሽማግሌ ጆንሰን፣ “እወድሃለሁ” ይለኝ ነበር። ከኡለት ሳምንት በኋላ፣ የኬቭን ፍቅር እንዲሰማኝ ለራሴ ፈቀድኩኝ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ ሰማይ አባት ለመእለይ መበረታቻ አገኘሁ። እየጸለይኩ ሳለ ወደ ትምህርት እና ቃልኪዳኖች ክፍል 6 ቁጥር 21-23 ተመለከትኩ፤ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፡-
“እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ። እኔ በጨለማ ውስጥ የማበራ ብርሃን ነኝ። …
“… ስለ እነዚህ ነገሮች እውነትነት ታውቅ ዘንድ በልብህ ወደ እኔ የጮህክበትን ምሽት አስታውስ።
“ይህንን ነገር በተመለከተ ለአምሮህ ሰላምን አልተናገርኩምን? ከዚህስ የበለጠ ከእግዚአብሔር ምንስ አይነት ምስክርነትን ታገኛለህ?”
ባነበብኩበት ሰአት አስታወስኩኝ። እያነበብኩ ሳለሁ መጽሐፈ ሞርሞን የእግዚአብሔር ቃል እና ጆሴፍ ስሚዝ ዳግም የተመለስው ወንጌል ነቢይ መሆኑን ለማወቅ የጾምኩበትንና የጸለይኩበትን ቀን አስታወስኩ። በጌታ ቤት ውስጥ ያደረኩትን ቃል ኪዳኖች አስታውሳለሁ ይህም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በጣም የግል እና ቅርበት ባለው መንገድ ያገናኘኛል። የአዳኙ ፍቅር፣ ምሕረት፣ እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ የእርሱ መንግሥት እንደሆነች እና ለሁለተኛው ምጽዓቱ እኛን ለማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ የእርሱ ማረጋገጫ ተሰማኝ። ስላስታወስኩኝ መንፈስ ቅዱስን እንደገና ማወቅ ችያለሁ እናም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እና እኔ የእርሱ ደቀ መዝሙር እንደሆንኩ የበለጠ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ችያለሁ።
አንዳንድ ጊዜ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እና አስፈላጊ ያልሆኑ፣ ተስፋ የቆረጡ፣ ብቸኛ እና የማይታዩ የመሆን ስሜት ይኖረናል። ነገር ግን፣ ጓደኞቼ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ወደ ፊት መሄድ አለብን እና ቃሉን ማስታወስ አለብን፦
“በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፥ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ አለምን አሸንፌዋለሁ።”
እኔ የዚህ እውነታና የመድኃኒቱ የተስፋ በረከት ምስክር ነኝ።
ስለዚህ ለአንድ ሰው በጌታ መንገድ የምናቀርበው አገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ምን ማድረግ እንችላለን? የክርስቶስን አስተምሮትን መኖር ይረዳናል። ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንደሚገልጹት በክርስቶስ ትምህርት መኖር በህይወታችን ውስጥ መንፈሳዊ መነቃቃትን በመፍጠር እጅግ በጣም ኃይለኛ፣ በጎ ሂደትን ይፈጥራል።
የኢየሱስ ክርስቶስን የላቁ ህጎች ለመኖር ስንጥር … አዳኙ በዚህ የወደቀ ዓለም መጐተት በላይ ከፍ ያደርገናል በበለጠ የበጐ አድራጎት፣ በትሕትና፣ በልግስና፣ በደግነት፣ በራስ ተግሣጽ፣ ሰላም እና ዕረፍት ይባረከናል።”
“የክርስቶስን ትምህርት በመኖር የሚፈጠረው እንድርድሪት” ሽማግሌ ዴልጂ.ረንለንድ ሲገልጹ “መለኮታዊ ተፈጥሯችንን ወደ ዘላለማዊ እጣ ፈንታችን ለመቀየር የሚያስፈልገውን ሃይል መሥጠት ብቻ ሳይሆን፣ ተገቢ በሆነ መልኩ ሌሎችን እንድንረዳ ያበረታታናል።” ሽማግሌ ረንለንድ እንዲህ ያስታውሱናል፣ “የአዳኙ ሥራ [መፈወስ ነው] የእኛ ስራ መውደድ ነው፣ ይኸውም ሌሎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሳቡ በሚረዳ መልኩ መውደድ እና ማገልገል ማለት ነው።”
የክርስቶስን ትምህርት የመኖር አቅማችን በየቀኑ መጽሐፈ ሞርሞንን በማጥናት እና በየሳምንቱ በቅዱስ ቁርባን በመካፈል ይበለጽጋል። ፕሬዝዳንት ኔልሰን መጽሐፈ ሞርሞን “የክርስቶስን አስተምሮት ያስተምራል … እናም በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአት ስርየት ላይ በየትኛውም ቦታ ሊገኝ የሚችለውን በጣም የተሟላ እና በጣም ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ይሰጣል” ብለዋል። ይህንን መጽሐፍ እወደዋለሁ። በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን በጸሎት መካፈል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአት ክፍያና ስለ ትምህርቱ ያለንን ግንዛቤ ከፍ ያደርገዋል እንዲሁም በመንፈሳዊ ሁኔታ ያድሰናል፣ ያጽናናል እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ አምላካዊነትን ያጎናጽፈናል። “በ[ክህነት] ሥርዓቶች ውስጥ መለኰታዊ ኃይል መገለጡን አስታውሱ፣” እናም ይህ ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘው ኃይል፣ ለአንድ አምላክ የማገልገል ፍላጎታችንንና ችሎታችንን ያጠናክርልናል።
የመፅሐፈ ሞርሞን ጥናቴ እና ቅዱስ ቁርባንን መካፈሌ የተስፋ መቁረጥ ስሜትን ይቀንሳል፣ በአዳኝ መንገድ ያለውን ለማገልገል ያለኝን ቁርጠኝነት ያሳድገዋል፣ እና ደቀመዝሙርነትን ከሁሉ የላቀ ተቀዳሚ ስራዬ ለማድረግ ይረዳኛል።
ወዳጆቼ፣ የክርስቶስን አስተምሮት በመኖር ወደ ጌታ ቤት በሚወስዱ መንገዶች ለአንድ ሰው እንደምንገዛ ቃል እገባላችኋለሁ፣ መልስ በሌላቸው ጥያቄዎች እና አስፈላጊ ያልሆኑ፣ ብቸኛ፣ ተስፋ የቆረጡ እና የማይታዩ የመሆን ስሜቶች ቢኖሩም እንኳ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ወደፊት መጓዝ እንደምንችል ቃል እገባለሁ። አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጣና በጌታ ቤት እንዲሰግድ የእርሱን የመቤዥት ኃይልና ፍቅር እንዲቀበል እንጋብዛለን። በጌታ ቤት ውስጥ “[የአዳኙን] ምሕረት ይሰማናል። እጅግ አሳሳቢ ለሆኑ ጥያቄዎ[ቻችን] መልስ እናገኛለን። [እናም] የወንጌሉን ደስታ በተሻለ እንገነዘባለን።” በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።