አጠቃላይ ጉባኤ
ኢየሱስ ክርስቶስ እና አዲሱ ጅማሬያችሁ
የጥቅምት 2025 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


14:20

ኢየሱስ ክርስቶስ እና አዲሱ ጅማሬያችሁ

ሁላችንም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እና ምክንያት አዲስ ጅማሬ ሊኖረን ይችላል። እናንተም እንዲሁ።

የቅዱሳን መጻህፍት አገላለጽ፤ ኢየሱስ መልካም በማድረግ ሄደ

ኢየሱስ “መልካምን እያደረገ ዞረ።” ያንን ቀላል ገለጻ በሀዋርያት ስራ ላይ እናነበዋለን። እንዴት ያለ ታላቅ አገላለጽ ነው! በርግጥም ኢየሱስ መልካምን እያደረገ ሄደ! እርሱ የደስታ—የመልካምነት—ሁሉ ምንጭ ነው! መላውን ምድራዊ ህይወቱን መልካምን በማድረግ አሳልፏል። እርሱ “መሃሪ እና ደግ፣ ታጋሽ፣ እና በመልካምነት እና በእውነት ቸር፣” በመልካምነት እና በምህረት ዘለአለማዊ ነው።

የእርሱን ቸርነት እና ምህረቱን ለመግለጽም ሆነ ለማጠቃለል የሚደረግ ሙከራ ይህን ማቃለል ይሆናል! በእውነት፣ ሐዋርያው ዮሐንስ ለመግለጽ እንደሞከረው ምናልባት እያንዳንዱን የአዳኙን መልካምነት መገለጥ ለመዘገብ ብንሞክር፣ “ሊጻፉ የሚችሉትን መጻህፍት ዓለም ራሱ የሚችለው አይሆንም።”

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን አዲስ ጅማሬን አጎናጽፎናል።

በህያውነት በቅዱሳት መጻህፍት ከተቀመጡት ውስጥ ኢየሱስ “መልካምን እያደረገ” ዞረ የሚሉት ጥቂት ምሳሌዎች ጥልቅ መገረም እና መደነቅ የሚፈጥሩ ሲሆን በተለይም የእርሱን ተዓምራት ለመታዘብ፣ ትምህርቶቹን ለመቀበል፣ እና ፈውሱን ለመለማመድ በዚያ እርሱ በነበረበት የመሆን አጋጣሚው ቢኖረን እና ይህንንም ብናስብ ይበልጥ ያስደንቀናል። እርሱ ከማህበረሰቡ ተገልለው ከነበሩት ጋር ተነጋግሯል፣ ደዌ የነበረባቸውን እና ያልነጹትን ዳስሷል፣ ለዛሉትም መጽናናትን አምጥቷል፣ ነጻ አውጪ የሆነን እውነት አስተምሯል፣ እንዲሁም ሃጢያተኞችን ወደ ንሰሃ ጠርቷል። ለእያንዳንዱ ለምጻም፣ አይነ ስውር፣ እና አመንዛራ ሴት፤ ለሽባው፣ ለደንቆሮው፣ እና ለማይናገረው፤ ለእያንዳንዷ ላዘነች እናት፣ በጭንቀት ላለ አባት፣ ላዘነች መበለት፤ ለተኮነኑት፣ ላፈሩት፣ ለሚሰቃዩት፤ በአካል ወይም በመንፈስ ሙት ለነበሩት ያደረገው አዲስ ጅማሬን መስጠት ነበር። አዎን፣ ሌላ አስደናቂ አገላለጽ!

እያንዳንዱ የተናገራቸው ነገሮች ለፈወሳቸው፣ ለባረካቸው፣ ላስተማራቸው እና ከሃጢያት ላሳረፋቸው ለእያንዳንዳቸው አዲስ ጅማሬን አጎናጽፏል። ከእነርሱ አልተለየም፣ እና በርግጥም ከእናንተ አይለይም። በዚህ ወቅት ህይወት ሰጪ የሆኑትን እነዚህን ቃላት ከእርሱ መስማትን አስቡ፤

“ልጄ ሆይ፣ ሃጢያትህ ተሰረየችልህ።”

“አንቺ ሴት፣ እልሻለሁ፣ ተነሺ።”

“ትነጻ ዘንድ እወዳለሁ።”

“እኔም አልፈርድብሽም፤ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ሀጢአትን አትስሪ።”

“ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ።”

ለእነዚህ ግለሰቦች የተነገረው የአዳኙ ቃላት አጭር ነበሩ፣ ነገር ግን እርሱ በዚያ ውስጥ አዲስ ታላቅ የይቅርታ፣ የፈውስ፣ የመታደስ፣ የሰላም፣ እና የዘለዓለም ህይወትን አድማስ ስሎላቸዋል። የከበረው ዜና ደግሞ ለእኔ እና ለእናንተ ተመሳሳይ አዲስ ጅማሬን የሰጠ መሆኑ ነው። ሁላችንም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እና ምክንያት አዲስ ጅማሬ ሊኖረን ይችላል። እናንተም እንዲሁ። አዲስ ጅማሬ አብ ለልጆቹ ባለው እቅድ ውስጥ ዋነኛው ነው። ይህች የአዲስ ጅማሬ ቤተክርስቲያን ናት! ይህች የትኩስ ጅማሬ ቤተክርስቲያን ናት!

ይህች የአዲስ ጅማሬ ቤተክርስቲያን ናት

በውሃ እና በመንፈስ ጥምቀት፣ “ዳግም እንወለዳለን” እናም “በአዲስ ማንነት እንጓዛለን።” ያ አዲስ ጅማሬ በሃጢያት ሸክም ውስጥ ሲታገል ለቆየው ወይም በአስቸጋሪ ህይወት ተጽእኖ ውስጥ እና ባልተሳካ ግንኙነት ሲሰቃይ ለነበረ ምን ያህል ተስፋን ያመጣል? ኢየሱስ የሃጢያት ይቅርታም ሆነ በህይወት አዲስ ጅማሬ አላስፈለገውም፣ ሆኖም እርሱ ራሱ ተጠምቋል፣ ይህም ለእያንዳንዳችን ባዘጋጀልን የአዲስ ጅማሬ መንገድ በታላቅ እረፍት እንጓዝ ዘንድ ነው።

የእኛ አዲስ ጅማሬ በአንድ ጊዜ የሚከሰት አይደለም። ጥምቀታችን በአዲሱ ጅማሬ አንዱ ክስተት መሆኑን እናስባለን። አይደለም። አንድ እድል ብቻ አይደለም ያለን። እነዚህ አዲስ ጅማሬዎች በየቀኑ ሊከሰቱ ይችላሉ! በርግጥም በሚያስፈልገን ጊዜ ሁሉ አያሌ አዲስ የሆኑ ጅማሬዎችን ሊሰጠን ለዚህ ዓላማ የሞተውን ፍጹም የሆነውን የአዳኛችንን ስጦታ ለማሰብ በየሳምንቱ ጥቂት ቁራሽ ዳቦ እና ጥቂት የኩባያ ውሃን በተቋደስን ጊዜ ነው! ኢየሱስ የሚያስፈልገንን ያህል አዲስ ጅማሬዎችን ይሰጠናል።

በመደሰት እና በቁርጠኝነት በክርስቶስ ወደ አዲስ ህይወት በምናደርገው ቁርጠኝነት፣ “አዲስ ፍጥረት” መሆን እንችላለን፣ ይህም አሮጌው ነገር ሁሉ ያለፈበት እና ሁሉም ነገር አዲስ የሆነበት ነው። ምንም እንኳ ህያዋን በወደቀው ዓለም ውስጥ የሚጣጣሩ ቢሆንም፣ በአዳኙ የመፈወስ እና የመታደስ ሃይል ተከታታይ እምነትን በማሳየት ያ ዳግም እድል ምን ያህል እየጣረች ላለች ነፍስ እረፍትን ይሰጥ ይሆን? እጅግ እንዲሰቃይ ባደረገው ህመም ውስጥ እንኳን ሆኖ፣ ከእያንዳንዱ የሰውነቱ ቀዳዳ የደም ጠብታ፣ በአካል እና በመንፈስ ሲሰቃይ፣ እና መራራው ጽዋ ከእርሱ እንዲወሰድ ቢጸልይም፣ አዳኙ የአባቱን ፈቃድ ከመፈጸም እና መለኮታዊውን ተልዕኮ ከማሳካት ወደ ኋላ አላለም። እንደገናም፣ በእግዚአብሔር በታማኝነት መፅናት ምን እንደሚመስል አሳይቶናል።

በምናደርገው በእያንዳንዱ ቃልኪዳን እና ያንንም ለመጠበቅ በምናደርገው በእያንዳንዱ ጥረት፣ “አዲስ ልብን” እና ሙሉ የሆነ “አዲስ መንፈስን” ልንቀበል እንችላለን። ቀስ በቀስ፣ የእርሱን መልካምነት ወደ ልባችን በጋበዝን ቁጥር እና በአእምሮአችን ያለውን በራስ የመሸነፍ ድምጽ ባስወገድን ጊዜ፣ የእርሱ ህዝቦች እንሆናለን ምክንያቱም እርሱን አምላካችን ስለምናደርገው ነው። ኢየሱስ ንጉሳችን እና እረኛችን፣ እንዲሁም የሰላም አለቃችን የመሆን ጽኑ ፍላጎት አለው በመሆኑም በልባችንም ሆነ በአዕምሮአችን ይህንኑ ለማድረግ መምረጥ እንችላለን።

ንሰሃን የምናይበት አዲስ ጅማሬ

ንሰሃ ለአዲስ ጅማሬያችን፣ ትኩስ ጅምር፣ እና ለዳግም እድል በር ከፋች ነው። የውድ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ትምህርቶች ስለመለኮታዊው የንሰሃ ስጦታ ያለን የተዛባ አመለካከትን የሚያጠራ ነው፣ እናም በመጨረሻ ልንይዘው የጀመርን ይመስለኛል።

ወጣቶቻችን ንሰሃ ለእነርሱ ምን ማለት እንደሆነ ሲገልጹ መስማት አስደሳች ነገር ነው። ፈገግታ በተሞላ ፊት፣ በቅርቡ አንዲት ወጣት ሴት ይህን ስትናገር ሰማሁ፣ “ስለንሰሃ፣ ስለየቀኑ ንስሀ፣ ሳስብ የማይታመን ሃሴት እና ተስፋ ይሰማኛል። ለሰማይ አባቴ እና ለአዳኜ ፍቅር እና ደስታ ይሰማኛል። ወደ ሰማዩ አባቴ በጸሎት ለመምጣት እና እየተቸገርኩ ባለሁበት በማንኛውም ነገር እርዳታውን ለመጠየቅ አልፈራም። መጥፎ የሆነን ነገር ሳደርግ እኔን ለመያዝ የሚሞክሩ እንዳልሆኑ አውቃለሁ። ክንዶቻቸው በሰፊው ተዘርግተዋል። ይህ ለእኔ ንሰሃ ነው!’’ አለች። ይህች ወጣት ሴት ያንን ተረድታለች ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት አዲስ ጅምር ሊኖራት ይችላል!

አዲስ ጅማሬ ለእያንዳንዱ ሰው፣ በሁሉም ጊዜ

አዲስ ጅማሬ ያስፈልጋችኋልን? እናንተስ፣ ትኩስ ጅምርን ማድረግ ትችላላችሁን? ጌታ ያገለገላቸውን—ያስተማራቸውን፣ የፈወሳቸውን፣ ከሞት ያስነሳቸውን፣ ይቅር ያላቸውን እና ወደ ነበሩበት የመለሳቸውን ሰዎች አስቡ። ከተወሰነ የኢኮኖሚ ክፍል ወይም መደብ የመረጣቸው ናቸውን? እርሱ በጻድቁ እና በሃጢያተኛው መካከል እየለየ ነበርን? ምክንያቱም ይበልጥ የሚያስፈልጉ ወይም የሚወደዱ ስለነበሩ ሰዎችን ለይቶ ያወጣ ነበርን? በፍፁም።

ደም ይፈሳት እንደነበረችው ሴት፣ ሎሌው ሊሞተበት እንደነበረው እንደ ሮማዊው የመቶ አለቃ፣ እንደ ለምጻሙ፣ እንደ ኢያኢሮስ፣ እና እንደ አይነ ስውሩ በርጤሜዎስ ያሉት አንዳንዶቹ የመፈወስ ኃይል እንዳለው በማመን በታላቅ እምነት ወደ እርሱ መጡ ። የናዝሬቱ መምህር መልካምነት እና ሃይል ህይወታቸውን እና እድላቸውን ይቀይራል በሚል ተስፋ፣ እያንዳንዳቸው እምነታቸውን በመስመሩ ላይ አድርገዋል። እናም አደረገው። ፈውሱ እንዲፈስ አድርጓል።

ነገር ግን ልጁ እንደ ታመመበት እየጮኸ የነበረ አባት፣ ምናልባትም እንደናንተው ሁሉ፣ “ጌታ ሆይ፣ ያለማመኔን እርዳው፣ አምናለሁ” ብሎ ላለው ኢየሱስ የሚናወጥ እምነት የነበራቸውንም እንዲሁ ባርኳል፣ ለአመንዝራይቱ ሴት፣ ፣ ለናይኗ መበለት፣ በቤተሳይዳ መጠመቂያ ለነበረው ሽባ ሰው፣ እና አይነ ስውር ሆኖ ለተወለደው ሰው ላሉ ላልፈለጉት ሁሉ እንኳን ርህራሄን አሳይቷል። እየፈለጋችሁት ወይም እየተከተላችሁት ሳይሆን እንኳን በህይወታችሁ መልካምን እያደረገ እንደሆነ ተሰምቷችሁ ያውቃልን?

ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸው የቅዱሳን መጻህፍት ሰዎች፣ ለሚሰሙት እና ምላሽ ለሚሰጡት ሁሉ የሃጢያት ይቅርታን ያገኘ አዲስ ህይወትም ይሁን ወይም ከህመም የተፈወሰ አዲስ ህይወት ወይም ከሞት የተነሳ አዲስ ህይወት አዲስ ጅምርን ሰጥቷል።

ይህ ለእኔ እና ለእናንተ ምን ማለት ነው? የእርሱ መልካምነት እና ምህረት እናም የፍቅር ደግነት ድንበርን አያውቅም። አዲስ ጅማሬዎች አብ ለልጆቹ ባለው እቅድ መሃል ላይ ያሉ ናቸው። ትኩስ ጅምር የወልድ ተልዕኮ ነው! አዲስ ጎህ፣ አዲስ ምዕራፍ፣ እና አዲስ እድሎች የወንጌል የምስራች መሰረታዊ ነገሮች ናቸው!

በመሆኑም አዲስ ጅማሬን ለመቀበል ከቃልኪዳናችሁ ለረዥም ጊዜ ርቃችሁ ቆይታችኋልን? አይደለም። ሌላ እድል እንዲሰጣችሁ ብዙ ጊዜ ይህን ወይም ያንን አድርጋችኋልን? አይደለም። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አዲስ ታሪክን ለመጻፍ እንዲረዳችሁ ከክርስቶስ ብዙ ርቃችሁ ሄዳችኋልን? አይደለም። ከመስጠማችሁ ሃሳብ ሊያተርፍ የሚሻ ብቸኛው ባላጋራችን ዲያብሎስ ብቻ ነው። ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡

እናም አዲስ ጅማሬዎች ለሃጠያታችን እና ለስህተታችን ከሆነው በላይ ነው። በአዳኙ መልካምነት እና ጸጋ አማካይነት፣ በአሮጌው አስተሳሰብ ላይ፣ በመጥፎ ልሞድ ላይ፣ በአስከፊ ወዳጅነት ላይ፣ በእኩይ አመለካከት ላይ፣ ሃይል በማጣት ስሜት ላይ፣ ሌሎችን በመፈረጅ ዝንባሌ ላይ እና የግል ሃላፊነትን በመሸሽ ላይ ሊሰለጥን የሚችል አዲስ ጅማሬ ሊኖረን ይችላል። ለዓመታት ሲያታክቷችሁ የነበሩትን ስለራሳችሁ ያላችሁን ነገር ልትቀይሩ ትችላላችሁ። በመምህሩ ጥንካሬ አዲስ ጅማሬ አማካይነት ዳግም ልትጀምሩ ትችላላችሁ። እርሱ አዲስ ጅማሬዎችን ለእኛ ለመስጠት በፍጹም አይታክትም።

በተመሳሳይ ሃጢያት ወይም በሚደጋገም አታካች ትግል ውስጥ ላሉት ለእነዚያ፣ መሄዳችሁን ቀጥሉ። እርሱ በፊት ለፊታችሁ መሰናክልን አላደረገም። እርሱ በሁለተኛ እድላችሁ ላይ ውስንነትን አላደረገም። ወደ ፊት ግፉ። ጥረታችሁን ቀጥሉ። በዙሪያችሁ ካሉት እርዳታን ፈልጉ። እናም በቅን ልቦና ወደ አባታችሁ በተመለሳችሁ ቁጥር ለእናንተ ባለው አዲስ ጅምር ታምናላችሁ። ሆን ተብሎ የሚደረግን ሃጢያት፣ ግድ የለሽ ድግግሞችን፣ እና ትእቢት የተሞላበትን አመጽ እዚያው ባሉበት ተዉት። የግድ ቀድሞ በነበራችሁበት ማንነት ልትሆኑ አያስፈልጋችሁም። አዲስ ጅምራችሁን፣ ሁለተኛውንም ሆነ ሶስተኛውን ወይም አራተኛውን--ወይም መቶኛውን--በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስርየት ያገኛችሁትን እድል አክብሩት።

ለተሰጠኝ እና ገና ለሚሰጠኝ አዲስ ጅማሬ ሊገለፅ ከሚችለው በላይ አመስጋኝ ነኝ።

ማጠቃለያ

አዳኛችን ዛሬ ያለእርሱ ሃሴት ልናደርግበት የማንችልበትን አንድ የመጨረሻ ንግግሩን ተናግሯል። ከጌቴሴማኒ ከባድ ስቃይ በኋላ እና ከአሰቃቂው የመስቀል ስቃይ ማብቂያ ላይ፣ “ተፈጸመ” ብሏል። የመሲሃዊ ትንቢት ተፈጽሟል፣ እናም የሰብዓዓዊ ፍጡር ሃጢያት እና ስቃይ ሙሉ ክፍያ ተከፍሏል። “ተፈጸመ” በማለት ፍጹም እና ዘለዓለማዊ መስዋእትነቱን ገልጿል። በሶስተኛው ቀን እርሱ ራሱ አዲስ ህይወትን እስከጀመረበት ቀን፣ የከበረ በመሆን በአዲስ ጅማሬ፣ በአብ ሃይል በትንሳኤ እስከተነሳበት ቀን ድረስ የሃጢያት ክፍያው የተሟላ ሊሆን ባልቻለ ነበር።

እርሱ ዘወትር አባቱን የሚያስደስት ስራ በመስራቱ ምክንያት፣ እና “በሁሉም ነገሮች የአባቱን ፈቃድ በመፈጸሙ፣” እኔና እናንተ አዲስ ጅማሬ ሊኖረን ይችላል። ዛሬም ቢሆን፣ አሁኑኑ አዲስ ጅማሬያችሁን ተቀበሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ከኛ ጋር ቁጥር ሥፍር የሌላቸውን አዲስ ምእራፎች በመጻፍ የእምነታችን ጀማሪ እና ፈጻሚ ነው። እርሱ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ነው—የሃፍረታችን እና የስቃያችን ማብቂያ ነው፣ እንዲሁም በእርሱ የሚገኝ የአዲስ ህይወት ጅማሬ ነው፣ የኋላውን እየተውን በፈለግነው ልክ በአዲስ ጅማሬ በአዲስ ጎህ ዳግም ጸጋውን እንቀበል። በርግጥ “የእርሱ መልካምነት እና ምህረት በህይወታችን ዘመን ሁሉ ይከተሉናል።” በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. የሃዋርያት ስራ 10፥38፣ በተጨማሪ “ህያው ክርስቶስ፤ የሃዋርያት ምስክርነት፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  2. ሞሮኒ 7፥12–13 ተመልከቱ።

  3. ዘጸአት 34፥5–7 ተመልከቱ።

  4. ዮሀንስ 21፥25 ተመልከቱ።

  5. ማርቆስ 2፥5

  6. ማርቆስ 5:41

  7. ማቴዎስ 8፥3

  8. ዮሀንስ 8፥11

  9. ሉቃስ 8፥48

  10. ሻይን ኤም. ቦወን፣ “Because I Live, Ye Shall Live Also፣ሊያሆና፣ ህዳር 2012 (እ.አ.አ)፣ 15 ተመልከቱ።

  11. ዮሐንስ 3:3; ሞዛያ 27:25

  12. ሮሜ 6:4

  13. ሞሮኒ 6፥8

  14. 2 ቆሮንቶስ 5፥17

  15. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥16–19

  16. ሕዝቀኤል 36፥26–28 ተመልከቱ።

  17. ለክርስቶስ ያለን እምነት እና ለእርሱ ያለን ፍቅር ወደ ንስሀ መግባት፣ ወይም ከእርሱ ፍላጎት ጋር የማይስማሙትን ሀሳቦቻችንን እምነቶቻችንን፣ እና ጸባዮቻችንን ወደመቀየር ይመራናል። ንስሀ መግባትም እግዚአብሔርን፣ እራሳችንን፣ እና አለምን በአዲስ አመለካከት ማየትን ያካትታል” (ወንጌሌን ስበኩ፦ የሚስዮናዊ አገልግሎት መመሪያ [2018 (እ.አ.አ)]፣ 62)።

    “የንስሐ ትምህርት ከመዝገበ-ቃላት ፍቺ ይልቅ በጣም የሰፋ ነው። ኢየሱስ ‘ንስሐ ግቡ’ ሲል ደቀ መዛሙርቱ ያንን ትዕዛዝ በግሪክ ቋንቋ metanoeo[ሜታኖእ] በሚለው ግስ ዘግበውታል። ይህ ኃይለኛ ቃል ትልቅ ትርጉም አለው። በዚህ ቃል፣ ቅድመ ቅጥያ meta [ሜታ] ማለት ‘ለውጥ’ ማለት ነው። ቅጥያው ከአራት አስፈላጊ የግሪክ ቃላት ጋር ይዛመዳል፦ nous [ኑስ]፣ ትርጉሙ ‘አእምሮ’፤ gnosis [ግኖሲስ]፣ ትርጉሙ ‘እውቀት’፤ pneuma [ፒኖማ], ‘መንፈስ’ ማለት ነው፤ እና pnoe [ፒኖ]፣ ትርጉሙም ‘እስትንፋስ’” (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Repentance and Conversion [ንስሀ እና መቀየር]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2007 (እ.አ.አ) 103)።

    ከዘወትር እና በየቀኑ ንስሃ ላይ ትኩረት ከማድረግ ይበልጥ ነጻ የሚያወጣ፣ ይበልጥ ከፍ ወዳለ ክብር የሚያደርስ እና በግለሰብ ደረጃ ለምናደርገው እድገት ጠቃሚ የሆነ ነገር የለም። ንስሃ አንድ ጊዜ የሚደረግ ክስተት ሳይሆን ሂደት ነው። ለደስታ እና ለአእምሮ ሰላም ዋናው ቁልፍ ነው። ከእምነት ጋር ሲጣመር ንስሃ የእየሱስ ክርስቶስን የሃጥያት ክፍያ ሃይል እንድናገኝ በሩን ይከፍትልናል፡፡

    “በየቀኑ ትንሽ ሻል ያለ ነገር የማድረግን እና የመሆንን—በየቀኑ የሚደረግ ንስሃ ያለውን የማበርታት ሃይል ተለማመዱ።

    ንስሃ ለመግባት ስንመርጥ መለወጥን እንመርጣለን! አዳኛችን ልንሆን ወደምንችለው ምርጥ እኛነታችን እንዲለውጠን እንፈቅድለታለን፡፡ በመንፈስ ለማደግ እና ደስታን ለመቀበል እንመርጣለን—በእርሱ ነጻ የመውጣት ደስታ፡፡ ንስሃ ለመግባት በምንመርጥበት ጊዜ ይበልጥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆንን እንመርጣለን!“ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የተሻለ ማድረግ እንዲሁም የተሻልን መሆን እንችላለን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 67።

    በየቀኑ በንስሃ ደስታን አግኙ።

    ንስሃ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? አልማ “ንስሃን እና በጌታ ላይ እምነትን ካልሆነ በቀር ምንም እንዳ[ንሰብክ]” [ሞዛያ 18፥20] አስተምሯል። “እያንዳንዱ ተጠያቂነት ያለበት እና ዘለአለማዊ ክብርን የሚፈልግ ሠው ንስሃ ያስፈልገዋል። ልዩ ሁኔታዎች የሉም። …

    “በቃል ኪዳኑ መንገድ መሄድ፣ ከእለት ተዕለት ንስሃ ጋር ተዳምሮ፣ አወንታዊ መንፈሳዊ ፍጥነትን ያቀጣጥላል።” (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የመንፈሳዊ ፍጥነት ሃይል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ) 98።).

  18. ማርቆስ 5፥25–34 ይመልከቱ።

  19. ማቴዎስ 8፥5-13 ይመልከቱ።

  20. ማቴዎስ 8፥1-4 ይመልከቱ።

  21. ማርቆስ 5፥22-43 ተመልከቱ።

  22. ማርቆስ 10፥46-52 ተመልከቱ።

  23. ማርቆስ 9፥17-27 ተመልከቱ።

  24. ዮሐንስ 8፥3-11 ተመልከቱ።

  25. ሉቃስ 7፥12-15 ተመልከቱ።

  26. ዮሐንስ 5፥1-9 ተመልከቱ።

  27. ዮሐንስ 9፥1–7 ተመልከቱ።

  28. ዮሀንስ 19፥30 ተመልከቱ።

  29. አልማ 34፥14–16 ተመልከቱ።

    “አዳኝ፣ ‘ተፈጸመ፣’ ሲል፣ የሟች ህይወቱን ጠቅሷል፣ ምክንያቱም ስቅለቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በሚሄደው ኃይሉ ላይ ምልክት ነው” (ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል፣ in Conference Report፣ ሚያዝያ 1946 (እ.አ.አ፣ 49)።

    “አዳኙ በመስቀሉ ላይ በተፈጸመ ጊዜ፣ ‘ተፈጸመ‘ ብሎ ሲጮኽ ስራውን አልጨረሰም። እርሱ፣ እነዚያን ቃላት ሲጠቀም፣ የደረሰበትን መከራ ብቻ እንጂ በምድር ላይ ስላደረገው ታላቅ ተልእኮ ምንም አልተናገረም።” (ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ፣ Gospel Doctrine፣ 5ኛ እትም [1939 (እ.አ.አ)] 449–50)።

  30. ዮሀንስ 8፥29 ተመልከቱ።

  31. 3 ኔፊ 11፥11

  32. መዝሙር 23፥6