በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
በጋና የነበረ ‘’እገዳ’’


‘’በጋና የነበረ ‘እገዳ’፣ ’’ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“በጋና የነበረ ‘እገዳ’፣፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ሰኔ 1989–ህዳር 1990 (እ.አ.አ)

በጋና የነበረ ‘’እገዳ’’

ቅዱሳን መሰባሰብ ባልቻሉበት ሁኔታ በታማኝነት መቆየት

አሊስ ጆንሰን እና ሄቲ ብሪማ በኮፎሪዱዋ፣ ጋና ውስጥ ወንጌልን ሲያካፍሉ።

አሊስ ጆንሰን በሃገሯ ጋና ውስጥ ስታገለግል የነበረች ሚስዮናዊ ነበረች። እርሷ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መመስከር እና የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለማሳደግ መርዳትን ትወድ ነበር።

ቅዱሳን4፥416–17

አሊስ እና ሄቲ ወንጌልን ዳግም ማካፈል እንደማይችሉ ተረድተዋል።

አንድ ቀን፣ አሊስ አንድ የሚያናድድ ዜና ደረሳት። የጋና መንግስት ከዚህ በኋላ የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ሊካሄዱ አይቻሉም አለ። ሚስዮናውያን ከዚህ በኋላ ማስተማር አልቻሉም።

ቅዱሳን4፥417

የፖሊስ መኮንኖች ከተዘጋው የቤተክርስቲያን ህንጻ ውጪ።

የፖሊስ መኮንኖች ሚስዮናውያንን መኖሪያቸውን ትተው እንዲሄዱ አደረጓቸው እንዲሁም ቢስክሌቶቻቸውንም ወስዱባቸው። አንዳንድ አባላትም በእስር ቤት ተጥለው ነበር። ወታደሮች የቤተክርስቲያኗን ህንጻዎች ቆለፉ እናም ማንኛውንም ሰው አያስገቡም ነበር። ሰዎች ይህንን ‘’እገዳ’’ በማለት ጠርተውታል።

ቅዱሳን4፥417–18

አሊስ ከአንድ ከጓደኛዋ ጋር ለመኖር ሄደች።

ሚስዮናውያን ወደ ቤት መሄድ ነበረባቸው። አሊስ በሌላ ከተማ ከጓደኛዋ ጋር ለመኖር ሄደች። እርሷ ፈጽሞ ሚስዮኗን ለመጨረስ እንደማትችል በማወቋ ተጨነቀች።

ቅዱሳን4፥418

በጋና ስጥ ያሉ ቅዱሳን ።

በጋና የነበሩ ቅዱሳን ግራ ተጋብተው፣ አዝነው፣ እናም ፈርተው ነበር። እነርሱ ምን መጥፎ ነገር እንዳደረጉ ባለማወቃቸው ግራ ተጋብተው ነበር። ዳግም እንደገና ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ይችሉ ይሆን?

ቅዱሳን4፥418

ቅዱሳን በቤታቸው የቅዱስ ቁርባንን ሲወስዱ።

ምንም እንኳ በየቅርንጫፎቻቸው መሰባሰብ ባይችሉም፣ ቅዱሳን አሁንም ጌታን ይወዱ እና ሊያመልኩት ይፈልጉ ነበር። እነርሱ በየቤቶቻቸው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎችን ያደርጉ ነበር። ክህነት የነበራቸው የቤተሰብ አባላት ዳቦውን እና ውሃውን ይባርኩ እናም ለቀሩት የቤተሰብ አባላት ያካፍሉ ነበር።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥32ቅዱሳን4፥419

ቅዱሳን በቤት ውስጥ አብረው ወንጌልን ሲያካፍሉ።

ከወር እስከ ወር፣ እገዳው ቀጠለ። ቅዱሳን መዝሙሮችን ዘመሩ እናም በየቤታቸው ወንጌልን አንዳቸው ለአንዳቸው አስተማሩ። እምነታቸው ጸንቶ እንዲቆይ አንዳቸው አንዳቸውን ጎበኙ። ወደቤተክርስቲያን ተመልሰው በሚሄዱበት ወቅት ለመክፈል አስራታቸውን ለይተው አስቀመጡ። እገዳው እንዲያበቃም ጸለዩ እናም ጾሙ።

ቅዱሳን4፥436–37

አሊስ ዳግም ሚስዮንን እንድታገለግል ግብዣ እየቀረበላት።

በመጨረሻም፣ ከ18 ወራት በኋላ፣ መንግስት ቤተክርስቲያኗ እንደገና ስብሰባዎችን እንድታደርግ ወሰነ። በአሁኑ ጊዜ የኮሌጅ ተማሪ የነበረችውን አሊስን ለማናገር አዲሱ የሚስዮን ፕሬዚዳንት ጠየቀ። ‘’ከትምህርትሽ በኋላ ትመለሻለሽን እናም ሚስዮንን ታገለግያለሽን?’’ በማለት ጠየቀ። “አይ፣” በማለት መለሰች። ‘’እኔ አሁን ማገልገል ነው የምሻው!’’

ቅዱሳን4፥437–39

በጋና ያሉ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን ስብሰባ ላይ።

አሊስ እና ሌሎች ቅዱሳን ዳግም ወደቤተክርስቲያን ለመሄድ በመቻላቸው በጣም ተደስተዋል! ከእገዳው በኋላ በነበረው በመጀመሪያው እሁድ፣ አያሌ ሰዎች ምስክርነታቸውን መስጠት በመፈለጋቸው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባው ለሁለት ሰአታት በሚሆን ያህል ተራዘመ። ጌታ እንዴት እንደባረካቸው እና እምነታቸው ጸንቶ እንዲቆይ እንደረዳቸው ተነጋገሩ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥75ቅዱሳን4፥438