“የታላቅ ዋጋ እንቁ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“የታላቅ ዋጋ እንቁ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
ሐምሌ 1835–መጋቢት 1842 (እ.አ.አ)
የታላቅ ዋጋ ዕንቁ
ከጌታ የመጣ ተጨማሪ ቅዱስ መጽሀፍ
አንድ ቀን፣ አንድ ሰው የግብጻውያንን ቅሪተ አካል ይዞ ወደ ከርትላንድ መጣ። ከቅሪተ አካሉ ጋር የተወሰኑ ብራናዎች፣ ወይም በጣም ያረጁ የወረቀት ጥቅልሎች ነበሩ። ብራናዎቹ በላያቸው ላይ የግብጻውያን ጽሁፍ ነበራቸው። ሰውየውም እነዚህን ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አሳየው። ጆሴፍ በጽሁፎቹ በጣም ተማረከ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥219–20
አንዳንድ ጓደኞቹ ቅሪተ አካሎቹን እና ብራናዎቹን በመግዛት ጆሴፍን ረዱት። ጆሴፍ ጽሁፎቹን ባጠና ጊዜ፣ ጌታ የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢይ በነበረው በአብርሃም የተጻፉ ጥንታዊ ጽሁፎችን ገለጠለት። ኦሊቨር ካውድሪን በመሰሉ ጓደኞቹ አማካይነት፣ ጆሴፍ ጌታ ስለአብርሃም ትምህርቶች ያስተማረውን ጻፈ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥220
አብርሃም ከመወለዳችን በፊት ከሰማይ አባታችን ጋር ስለነበረን ህይወት ራዕይን አየ። እርሱም ኢየሱስ አዳኛችን ለመሆን የተመረጠ መሆኑን አየ። አብርሃም በተጨማሪ ስለ አለም አፈጣጠር ተማረ። ቅዱሳን እነዚህን ጽሁፎች ከአብርሃም በማግኘታቸው ተደስተዋል። ጌታ ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን ሊያስተምራቸው በመፈለጉ ደስተኞች ነበሩ።
አብርሃም 2፥6–11፤ 3፥–5፤ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥220
የአብርሃም ጽሁፎች የታላቅ ዋጋ እንቁ የተባለው የቅዱሳት መጽህፍት ክፍል አካል ሆነ። ይህ መጽሐፍ የሌላኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢይ የሆነው የሙሴን ጽሁፎችም እንዲሁ የያዘ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱ እውነቶችን ያስተምራል። ጌታ ሰዎች እነዚህን እውነቶች እንዲያውቁ ይፈልጋል፣ በመሆኑም እነዚህን ለጆሴፍ ስሚዝ አካፍሎታል።
የታላቅ ዋጋ ዕንቁ ደግሞም የጆሴፍ ስሚዝን ምስክርነት እና 13ቱን የእምነት አንቀጾች ይዟል። ጆሴፍ ስሚዝ የኋለኞቹ ቀናት ቅዱሳን ምን እንደሚያምኑ ለአለም ለመናገር እነዚህን ነገሮች ጽፏል። እንቁ ትንሽ እንደሆነ ሁሉ፣ የታላቅ ዋጋ እንቁ ትንሽ መጽሀፍ ነው፣ ነገር ግን በጣም ውድ ነው።