“ዘለአለማዊ ጋብቻ እና ቤተሰቦች፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ዘለአለማዊ ጋብቻ እና ቤተሰቦች፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
1843–1846 (እ.አ.አ)
ዘለአለማዊ ጋብቻ እና ቤተሰብ
በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የታተሙ
ኤማ እና ጆሴፍ በተጋቡበት ጊዜ፣ እነርሱ ሲሞቱ ትዳራቸው እንደሚያበቃ ያምኑ ነበር። ሁሉም ጋብቻዎች እንደዚህ ነበሩ። ነገር ግን ጌታ ጋብቻ እና ቤተሰብ ለዘለአለም እንደሚኖሩ ለጆሴፍ ነገረው።
ቅዱሳን፣ 1፥413
ጌታ ስለ ዘለአለማዊ ጋብቻ ጆሴፍን አስተማረው። በክህነት ስልጣን ሃይል አማካኝነት አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን መግባት ይችላሉ። ቃል ኪዳናቸውን ከጠበቁ ጌታ ትዳራቸው ለዘለአለም እንደሚኖር ቃል ገብቷል። ይህ መታተም ተብሎ ይጠራል። ብዙም ሳይቆይ፣ ጆሴፍ እና ኤማ ለዘለአለም ታተሙ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥7፣ 19–24፤ ቅዱሳን፣ 1፥413፤ 432–33፣ 481–82፤ 492፤ 502–3
በተጨማሪም አንድ ወንድና ሴት ሲታተሙ ልጆቻቸውም ከእነሱ ጋር የታተሙ እንደሚሆኑ ጆሴፍ አወቀ። በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ምክንያት፣ ቤተሰባቸው ለዘለአለም ሊቆይ ይችላል። ጆሴፍ ስለዚህ በረከት ለቅዱሳኖች ሲነግራቸው በጣም ተደሰቱ! አብረው ለመታተም በጣም ጓጉ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፥2፤ 132:፥6–7፤ ቅዱሳን፣ 1፥492–93፣ 580
በኋላም መታተም በቤተመቅደስ ውስጥ መካሄድ እንዳለበት ጌታ አስተማረ። ቅዱሳን አብረው መታተም ይችሉ ዘንድ በናቩ የሚገኘውን ቤተመቅደስ ለመጨረስ ጠንክረው ሰሩ። ቤተመቅደሱ ተገንብቶ በተዘጋጀ ጊዜ፣ ብዙ ቤተሰቦች ታተሙ። ለሞቱት የቤተሰብ አባላትም ጭምር ታተሙ። ለዚህ በረከት አመስጋኞች ነበሩ!
ቅዱሳን፣ 1፥579–80።